ግጥም ብቻ 📘
63.7K subscribers
1.57K photos
31 videos
61 files
179 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እንዳትመለሺ ፣ መምጪያ መንገድሽ ላይ
እሾህ ብዘራበት ...

ልቤ ሳቅ ታየበት ...

የጨለመው ዓይኔ – ብርሃን ዘነበበት

ኃጢያትም አንዳንዴ – የእግዜር እጅ አለበት

By Thomas Atsede

@getem
@getem
@paappii
43😁21👎8🔥8😱6
ይቅር በላቸው[ፀሎት]

የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች
ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሀብቶች...
_  _  _
ሸንበቆ ድግፍ እፍኝ ትምክህቶች
መውደቂያ ያጡ ድፍን ተምኔቶች!

ይቅር በላቸው...

የተጣደፉ ፈራጅ ከንፈሮች
ያልተማከሩ ልብና አፎች!
ያልደነገጡ ድንድን ስሜቶች
ያልተረጋጉ ሰንካላ እምነቶች!

ይቅር በላቸው!

ይበልጥም...
የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች!
ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሃብቶች!

_  _  _
ያስመከቱኝን ውዥቅ ቀለማት
ያስፎከሩኝን ግንጥል ድምቀታት!

ይቅር በላቸው!

አልደበቁኝም ልሽሽው ካልኩት
አላስጣሉኝም ከተሯሯጥኩት
አላወጡኝም ከሰው ትከሻ
ወይ አልሰጡኝም ዝና ሙገሳ፨

ይቅር በላቸው!

ማራቸው ያለህ ልቤ አስታኮ፧
አብረህ አስበኝ ሊልህ ነው እኮ፧፧

By @alem3_b [ዓለም]
@getem
@getem
@getem
47🔥11👍3😱2
ለፀሐይ ፍካት ማን ይፈግጋል?
ለሰማይ ንጣት ማን ይደግሳል?
ማን ግድ ብሎት ማን ስሜት ሰጥቶት?
ከምድር አልፎ ሰማዩን አይቶት?¡

ዘልቋል ከውስጥኽ?ገብቶሃል ቅኔው?
ምን ብትነጠፍ ሰማይ ብትሆነው
የያዘው እክል እስካልለቀቀው፧
ከኑሮ አሻግሮ ግትር አንገቱን እስካላዞረው፧
መቼም አያይህ ያልቀናለት ሰው!


By @alem3_b[ዓለም]
@getem
@getem
@getem
21🔥8
ድሮ አንቺን ለማየት
ሰፈርሽ ስመጣ
አንዲት ዝርግ ድንጋይ
አየሁ ተቀምጣ ፤
ቁጭ አልኩኝ በድንገት
እንዲህ እንደ ዘበት…
ያፈቀረሸ ልቤ ፣ ሳሉ ሲነሳበት
ማስታገሻ ነበር ፣ ሰፈርሽ መገኘት።

ዛሬስ አትይኝም?

እዛው ተቀምጬ
አትመጣም ወይ? እያልሁ
አንቺ ብትቀሪ…
:
ዲግሪ ጭኖ መጣ
ሀይስኩል ተማሪ።

እዛው ትናንትና
እዛው አንቺ ሰፈር
ከጠፍጣፉ ድንጋይ
ሳልነሳ ቀንቶኝ…
:
ያምና ብላቴና
ያልፈኛል ገላምጦኝ።

አትገረሚም ወይ?

ሳልነሳ ከዛ
ቤተ መቅደስ ታዛ
ከስር የማይጠፋ
የወንጌል ሰባኪ
ቅስናውን ገድፎ
በየመሸታ ቤት
ሲያወርድ ያድራል ውስኪ።

እዛው ትናንትና
አንቺን ከማይበት
ከጠፍጣፉ ድንጋይ
ተቀምጬ እያለሁ
አንዱ አብሮ አደጌ
በመኺና ባየው-
እጆቼን ዘረጋሁ
ለናፍቆት ሰላምታ
መስታወቱን ሳበ
በእንዴት ነህ? ፈንታ

ያን ጊዜ ተከፋሁ
ውስጤን ቦረቦረኝ-
ምናል እንደ ድሮው
አቅፎ ሰላም ቢለኝ?

(ጎስቁያለሁ በቃ?🤔)

አትገረሚም ወይ?

ሰዎች አሉኝ ከንቱ
መንገድ ቀየሩብኝ
ቀፍፎ ፣ ጎርብጧቸው
ዘባተሎ ጨርቄ…
ያካሌ ቡትቱ።

(ጎስቁያለሁ ለካ !)

እዛው ቁጭ ብዬ
ተዓምር ደረሰ
ሰፈሩ ተዳሰ
ቅጥሩ ፈራረሰ

የግቢያችሁ በሩ
ይከብድ የነበረው
በአባትሽ ትከሻ…
:
የማንም ወመኔ
አጨሰበት ሺሻ።

እዛችው ከትናንት
ከግቢያችሁ ማዶ
እስክሰማ ድረስ
ቀጭን ክፉ መርዶ
:
እየጫኑ ዲግሪ፣
እየናቀኝ ውሪ፣
ሰክሮ እየሳተ…
የ’ግዜአብሔር አዳሪ
እብድ ነው እያሉኝ
እነ ቲቲ ፣ ሜሪ

እየተቃመበት
የአባትሽ ገዳም
እየተጨሰበት
የእናትሽ በዓት
ትዝታችን ሲናድ
በከተማ ልማት ፤

አንዱም ድል ሳይመታኝ
ስንቱን ዘመን ሽሬ
እልፍ ዘመን ኖሬ

ሁሉን እየረታሁ …
ሁሉን እየነሳሁ…
“አግብታለች” ቢሉኝ
በድንገት ተነሳሁ።

(ታስታውሽኝ ይሆን?)
አታውቂኝም ለካ🥹

ሚካኤል .አ

@getem
@getem
@paappii
67🔥23😢19👍3
እውነትም ሰገነት!

ውሸት አልነበረም ያ ሁሉ ሙገሳ፥
ሰማይ ታህል ነበር ጨረቃ አንችን ለብሳ።
አድማስና ማማ ማጋነን ቢመስል፥
ወንዝ እንኳ ሚረጋው ሲቃኝ ባንቺ ምስል፤

እውነት? ያባይ ጅረት ሳቅሽን ይበልጣል?
የጢሱ ርግብታ? ከርጋታሽ ይሰክናል?
እስቲ ጽጌሬዳ?ይመ--ስልሻል ወይ፣
ይቅርና በበጋ እርሙንስ በጸደይ?!

ንግግርሽ ሃገር አርምሞሽ አሃጉር
አንቺ ላይ ከረመ ውበት ሲያንጎራጉር!።

ሃሳብሽ ገራገር መርኅሽ ዝምታ፣፨
                    .
                    .
                    .
እውነትም ሰገነትእውነትም ከፍታ!።🙌🏿

By @alem3_b [ዓለም]
@getem
@getem
@getem
49👎3🤩1
እንዳትረሺኝ  ብዬሽ፤
አትርሳኝ ብለሽኝ ፤

በቃል ክር አስሬሽ፤
በቃል ክር አስረሽኝ፤

በደልሽኝ በደልኩሽ፤
በደልኩሽ በደልሽኝ ፤

ቃልሽን አከበርሽ
ቃሌን አከበርኩኝ ፤

ይሄ በደላችን...
እንኳን  በ'ዚህ ሕይወት
በመቃብርም ውስጥ ችሎ አያረሳሳም፤
ደግሞ እንደምታውቂው
የወዳጅ ፍቅሩ እንጅ በደሉ አይረሳም ።

By Tewodros kassa

@topazionnn
@topazionnn
60🔥7
~  ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~ ~  ~
°
ብሸፍተም ሰው ስገድል..
ስትጠራኝ ሳትሸነግል..
ቀስቴን ጥዬ ተሸነፍኩኝ
አንተን ሳይህ 'ረገፍኩኝ፨

ድንገት ራደ ሰዉነቴ፣
ተፈታልኝ ሰንሰለቴ፨
°
ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትለውጥ
ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትጠራ፣
ጨካኙን ልብ ደግ ያልሰራ፣
ታኖራለህ ስታራራ፨፨
°
ለካ እንዲ ነህ ስታንኳኳ፣
ጻዲቅ ሆነ ገዳዩ እንኳ፨!

By @alem3_b[ዓለም]
@getem
@getem
@getem
56🔥10👍7😢6
አገር ንቆ..ሰው አይጸድቅም!

@myPoems396
@getem
@getem
@getem
12🔥4
ደህና......

እንዴት አደርክ?
    (ደህና!)

እንዴት ዋልክ?
   (ደህና!)

እንዴት አመሸክ?
   ( ደህና!)፤

ደህና ሚለው ቃሌን
    ከጅምሩ አውቀው
በሁሌ ሰላምታ
     ጠየቁኝ አጥብቀው፤
ህ!
ሰላምታው ቢበዛ
  አንድም ላይሰጥ ተስፋ
(አሁን ግን ደህና ነህ?)
    የሚል እንዴት ይጥፋ!???

@Weyblann
@getem
@getem
28😢19👍10
"ግልፅ ጠላ"

ከግልፅ ቃል ምነው ፣ ስውር ቅኔ ቀናን
ከተቀበረ አካል ፣ ትንሳኤ ሕይወት አደራን
ከቀና ጎዳና ፣ ከሀምራዊም ፈትል
ልባችን አማረው ፣ የተጠላለፈ ቅል
ምነው መመንጨሩ ፣ ምነው መጎልጎሉ
ሰውነት ነው ወይ ፣ ማይረጋው አጉሉ
ምንድነው የሆነው ፣ ምንስ ተበጀነው
ድብቁን...
ይቀናናል ማረስ ፣ ፍልሰታ አበጀነው
ምነው ተብከነከን ፣ በአሮጌ አቁማዳ
ተሯሯጥን ደርሰን ፣ ሊላትመን ከዕዳ

መፈለግ ማውጠንጠን ፣ ማወቅን አስቃዠን
መጎልጎል መመርመር ፣ መመንጨር ጎመዠን
አበሳጨንሳ ፣ ራሱ በቀጥታ
ሲጠማዘዝብን ፣ ቀኛችን በረታ
ሲጠላለፍብን ፣ ቅሉ ሲያታክት
ከዝርው ዘር ይልቅ ፣ ወደድን የክት

ሰው የሆነ ሰው ፣ ወደደ በኩሉን
ያለ አዲስ ነገር ፣ አባከነ አቅሉን
አዕምሮው ናወዘ ፣ ወረደ ትከሻው
የልቡን የልቡን ፣ በልቦናው ሲሻው
በዕውቀቱ ቅል ፣ ቁጥር ሲያማታ
አለማወቅ አውቆ ፣ በሕይወት ሲያመነታ
ግርታ ደምኖ ፣ ጭጋግን ሲፈጥር
የልቡ ሥጋ ፣ ድንጋይ ሆኖ ሲሻክር
በጭጋግ በፅልመት ፣ መኖሩ ስትመር
ያለ አዲስ ነገር ፣ አዲስ መንገድ ሲፈጥር
አጓጓዝ ያስተምራል ፣ መድረሻ ተረስቶ
መሄድ መሄድ ይላል ፣ መጨረሻውን ስቶ
በምናቡ ደክርቶ ፣ በመንገዱ ዋትቶ
አረማመድ ሲያምረው ፣ አቋቋሙን ትቶ
አሯሯጥ ይሄዳል ፣ ዛሬውን ዘንግቶ
አሁንን ለማን ፣ መዳኑ ዘግይቶ?
ዛሬን ለማን?
መኖርን ለማን?
እኮ ለማን ትቶ?

By Natnael Abebe

@getem
@getem
@getem
15
ሂድ!

አትጠራጠሩ እውነት ነው ነገሩ
አትደናበሩ ተስማምቷል አገሩ

ተረት ተተርቶ በምግባር ተፈትቶ መፅሐፍም ተፅፏል
ወደፊት ነውንጂ ወደኋላ ያየ ባምላክ ይቀፀፋል!

By @Lawyerly1

@getem
@getem
@getem
19🔥2
#ደብዝዞ_መወደድ

በልክ መሸፈን በልክ መገኘት፡
በልክ ጮሌነት  በልክ   መሞኘት፤
አቤት ስትችይበት!

በልክ ማወደስ  በልክ  መፎገር፡
መስመር  ያልዘለለ  ጨዋታና ነገር፤

በ ል ክ መቀበል በልክ መሸኘት፡
እ ኩ ል ሕብርና እኩል ብቸኝነት፤
አቤት ስትችይበት!
ኑሮና ቀለምሽ ወይነ~ደጋ መንደር፣
ለሰው አታሳዪ ካንድ ስምሽ በቀር።

ሳይሽቀረቀሩ ሳይሉ ወጣ ወረድ፣
ይገርማል ግን እኮ ደብዝዞ መወደድ!
አልተገኘሽም ስታሽካኪበት በየ በዓሉ
እንዲህም ሆነሽ~ታምሪያለሽ አሉ!
እቴ..

ሳትሽቀረቀሪ ሳትይ ክርትት ሰደድ፣
ማነው ያስተማረሽ?
                             ደብዝዞ     
                                     መወደድ!

አቤት ስትችይበት!

@myPoems396
@getem
@getem
@getem
13🤩3🔥2
🦋ማያዬ🦋

በጨቅላ ቡረቃ
‎ፈንድቄ ምውለው፤
‎ስላንቺ ሳስብ ነው
‎ፈገግ የምለው፤

‎እፀ በለስ ወይን
‎የምሽት አዝመራ፤
‎የመለኮት እቅፍ
‎የፍቅር ደመራ፤

‎የጠዋት መዝሙሬ
‎ማለዳ ብስራቴ፤
‎ተጠግኗል ባንቺ
‎ደዌ ስብራቴ፤

‎ሀኪሜ ወዳጅሽ
‎ናፍቆሻል በጠና፤
‎ነይ መጥተሽ ደባብሽው
‎ይፈወሳልና፤

‎ብሌኔ ማያዬ
‎ስስት ቁንጅናዬ፤
‎ድብቋ ጀነቴ
‎ግልጧ መፅናኛዬ፤

‎ለውለታሽ ምላሽ
‎አሰናዳው ማጀት፤
‎ዝግጁ ነኝ ሁሌም
‎ካንቺ ጋር ለማርጀት፤

‎ፊደል ግምጃው ጠርቶኝ
‎ለክብሩ እጁን ስሜ፤
‎የሚመጥንሽን
‎አሰሳ ታድሜ፤

‎ድርሻዬን ዘግኜ
‎ድርሻሽን ለቅሜ፤
‎ይኼን ነው የምልሽ
‎እቺ ናት አቅሜ፤

‎የነፍስ ወይራ ነሽ
‎እጣን እና ከርቤ፤
‎ከፃፍኩልሽ በላይ
‎ይወድሻል ልቤ።

By @Abstruse12

@getem
@getem
@paappii
7🔥1
እግዜር የኔው ይቆይ አስቀድማቸው..
.
.
መቼም እስከኖሩ
ሰው እንደ ፊቱ
መከራው ልዬ ነው
መቼም እስካሉ
እንደ አይን መጠኑ
ሰው ዕዳው ብዙ ነው

የኔ ስቃይ ባያንስ
ባይበልጥም አቋሙ
የኔው ስኬት ይቆይ
ሌሎቹ ይቅደሙ

በየ ቤተስኪያኑ
የሚፈሱ ዕንባዎች
ተራ ሲጠብቁ
ያለቀሱት ብዙ
አመታት በተስፋ
እየጠባበቁ

አስቀድማቸው
ለምን..?
ዕንባቸው ደርቋል
ከአይናቸው
ተስፋ ስላጣ
ፊታቸው

የኔው ይደርሳል
ተራዬ ይቆየኝ
አድርግላቸው
ችግር የለውም
እኔኑ ባታዬኝ

ልቤ ስለሚያዝን
ለመከረኛ ሰው
አልፎልኝ ካልደረስኩ
ይለፍብኝ በማልቅሰው

' በማለቅሰው ዕንባ
በተስፋዬ ካፊያ
ሰውን ካላኖርኩት
ምን ያደርጋል ጥድፊያ

እግዜር...የኔው ይቆይ
እናቶች ይቅደሙ
አባቶች ይቅደሙ
በልጅ ፊት አንሰው
ባለማኖር ውስጥ
ስለሚታመሙ

አባት አንሶ አይታይ
ግርማው አይጠውልግ
በልመናው ቃል
ተራው አስቀድመው
እንዲያደገድግ

ተራዬ ደርሶኝ
ስኬቴ ሁሉ ለሰው ካልደረሰ
ለሰው ኗሪው ይቅደም
መጨረሻ ልሁን
ዕንባን ካላበሰ

@geez_mulat

ይነበብ

ይህ ግጥም ፍፁም ከልቤ ያለውን ሀሳብ ያለምንም የቃላት ምርጫ የፃፍኩት ስራዬ ነው እስከ ሂዎት መጨረሻዬ የምወደው ስራዬ ነው  መታወሻ ይሁነኝ

@getem
@getem
@getem
26👍5🔥2😢2