ግጥም ብቻ 📘
63.7K subscribers
1.57K photos
31 videos
61 files
179 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የራስ ገድል!
^^   ^^   ^^   ^^  ^^   ^^   ^^   ^^  ^^
ደፈጣ ነው ውጊያ ብቻ፥
መገዳደር  ያለ መርቻ፣

ላለመርገፍ ተቀርጥፎ፥
ላለመውደቅ ተዝለፍልፎ!

የማልጣል ተንጠልጥዬ፥
የማልወድቀው ተፈንቅዬ፥
ይሄው  ምርኮ ከ'ግሬ በታች፣
በረሃዬን በእምባ ሸማች።!

ቀራንዮ በኮረብታ፣
የብቻዬን ጎለጎታ፣  ...  ...  ..
ችንካር አለው ደግሞ ስቅል፣...
የራስ ምርኮ የራስ ገድል።፨!

@alem3_b [ዓለም]

@getem
@getem
@getem
45🔥6👎5👍2
የውድቀቴን መንገድ
ሸርሽራ በመውደድ
ያቀናችኝ ንግስት ... የሰጠችኝ ክብር
አቤት አቤት ሲያምር

{ልክ እንዳንቺ ማርያም}

መኖር እንድጠላ መንፈሴን አድክሞ
ማጣት አንቆኝ ሲዞር ክንዱን አፈርጥሞ
የምሆነው ጠፍቶኝ
ተንበርክኬ ሳዝን ሳትለኝ ደካማ
ቀና አረገችኝ ቀንበሬን ተሸክማ!

እምቅ የእንባ ጠል
ጉንጬን ሲንጠለጠል
ኅዘን በደቆሰው ልስልስ ስስ አንጀቷ
ዕንባዬን ያበሰው
አቤት ሲያምር ጣቷ

{ልክ እንዳንቺ ማርያም}

እኔነት እስካጣ ፍቅር ሸሽቶኝ በሮ
ብቸኝነት ሚስማር ሲያደማኝ ቸንክሮ
የማረገው ጠፍቶኝ
ሞቴን እየናፈቅኩ ሳዘጋጅ መስቀሌን
ትንፋሽ ለገሰችኝ ዳብሳ ሰንበር ቁስሌን

የጅራፍ ሹል ትርትራት
የልቤ ስውር ስብራት
አድቅቆ ሲጥለኝ ... እንዲሆን ለነፍሷ
ስሞ ሳቅ ያሳየኝ
አቤት ሲያምር ጥርሷ

{ልክ እንዳንቺ ማርያም}

ስትችልበት ማዘን
ስታውቅበት ማቀፍ
ብሶት አስዘርግፎ
በሰላም ማሳረፍ

{ልክ እንዳንቺ ማርያም}

ስትችልበት ጸሎት
ስታውቅበት ማውራት
ጨለማን ገርስሶ
በፈገግታ ማብራት

{ልክ እንዳንቺ ማርያም}

ስትችልበት ማከም
ስታውቅበት ማዳን
ፍቅር በልብ ሰጥቶ
መለገስ ማር ኪዳን

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@paappii
52🔥7👍1👎1
ለምን አይባልም
-------------------

አንዱ

ዘመኑን በሙሉ ፤
ያለምንም እረፍት ተግቶ ያስቀድሳል

ሌላው....

"ባንድ ቀን ንሰሀ ፤
ከፃድቁ እኩል፥ ገነትን ይወርሳል ።

ይህንን እያየ ...

ልባችን አስካክቶ ጥያቄ ቢጥልም
እግዜር አዋቂ ነው ለምን? አይባልም።

By kirubel

@getem
@getem
@paappii
251🔥44👍8🤩1
ሀሜት የት ነበረ??

በፊት....

የጎረቤቴ በር በቀን አይዘጋም
እኛም ለመፋቀር መሽቶልን አይነጋም
'አቡሽ' ቡና ጥራ...ሲሉን ደስ እያለን
አዋቂው ሲታደም  ጓዳ ግባ ሁላ መቼ እናውቃለን??
   ልክ እንደ ቡና ቁርስ መሀል ቁልጭ ቁልጭ
  ሲያዝኑ እያዘንን ሲስቁም መብለጭለጭ
   ውሉን ባንረዳው የጨዋታቸውን
   እናውቅ ግን ነበር አንጀት ሆዳቸውን፤
  እንከን በየዘመን፣ጥልም በየጊዜው ነበረ አይካድም፣
ግን በኛ ልጅነት እዛው እርቅ ይወርዳል ወዴትም አይሄድም፤

አሁን...
ባህል የለሽ ወጉ እኛን አርቆናል
በዘመን መዘመን ስራ አቀለለ እንጂ እኛን አቅልሎናል፤
   ንግግር በግጥም ወዝ ቸፍ ቢልበት
   ለአንዳንዱ ይከብደዋል ለአንዳንዱ ቀሎበት
   ከእውነታው አልርቅም መቅረቡ ይጥመኛል
   ከማስመሰል በላይ መምሰሉ ከብዶኛል፤
በቀን ሰው ፈርተናል የጨለመው ጥሞን
ውሸት ሰፍቶብናል ቀናው መንገድ ጠቦን!
እሺ....
ይሄ መፈራራት ፣ይሄ መተማማት ኢትዮጵያን ካስቀረ፣
ያኔ ልጅ እያለን 'ሀሜት' የት ነበረ????

@Weyblann ያቡ

@getem
@getem
44🔥10🎉4👎1
እድሜ ለጊዜ!

ዘመን ደግ ነው...
ጊዜ ደግ ነው አይደለም ክፉ
ይኸው ተረስቷል አለንጋ ግፉ!

መራቅ ደግ ነው አመት መንጎዱ
እኛናእኛችን እንዲዋደዱ
[እኛናእኛችን እንዲላመዱ]

በጊዜ ፍጥነት...
በቀኑ ክንፈት...

ያ ሁሉ 'እዬ'ታ፣
ሆነ ትዝታ!
[እድሜ ለጊዜ]

ሲያልፍ ሲተካ ልብም ቀዝቅዟል፣
እንጂማ ባይሆን....
ያ ሁሉ እሮሮ በምን ይረሳል?!
[ያ ሁሉ እምባ በምን ይደርቃል]

@alem3_b[ዓለም]

@getem
@getem
@getem
👍2722🔥7👎2
ጥሞና ግሮሰሪ

ተከሳሽ እገሌ፣  በቀደመው ወር ጥር
አራት ሳት' ገደማ፣ ላምስት' ሲቆጥር
ከላዩ ደርቦ የቻይና፣ ሌዘር ኮት
ተሸፋፍኖ ከሰው፣ ጥሶ ከመለኮት
እየተገላበጠ ተራምዶ በእንክብል
ጥቁር ተከናንቦ አርጎ የፊት ጭምብል
(የማይታይ መስሎት!)
ግራጫ ቀለም፣ አርጎ የክት ሱሪ
ደርድሮ ሲጠጣ፣ ገነት ግሮሰሪ
ባይን አማኝ ምስክር
በባዶ ክርክር
ከዛሬ ጀምሮ፣ ከመቅደስ ተባሯል
ለጥሞና ጊዜ፣ ለስድስት ወር ታስሯል።
*
(ተከሳሽ መልስ አለህ?)
:
እርግጥ ነው
አልክድም ክሳቹን፣ ቅዳሜ አመሻሽ ለውስኪ ስገባ
የኔ ጥያቄ ግን፣
ታማኙ ምዕመን ፣ ያይን ምስክሩ ምን ሊሰራ ገባ?
:
:
(ከስድስት ወር በኋላ)
:
:
የመሰከረበት ያ ታማኝ አገልጋይ
ጥሞና ተብሎ ከታሰረው ታጋይ
የነደደ እሳት፣ በስካር ቆስቁሰው
ከሸንጎ ቆመዋል፣ ክፉኛ ተቧቅሰው
*
ሸንጎ ተጀምሮ ክሱ ሲዘረዘር
*
ለካ!
ለጥሞና ጊዜ፣ የታሰረው ወጣት
ገነት ግሮሰሪን፣ ለልማት ስላጣት
ሆዱና አድማሱን፣ እስከ ጥግ አስፍቷል
በጥሞና ጊዜው፣ ግሮሰሪ ከፍቷል።
(ጥሞና ግሮሰሪ)

አይን አማኙም ከዚሁ፣  ሰባት ጠጥቶ
ሳይከፍል በጉራ፣ ጥሶ ሄዷል ወጥቶ።
ይልቅ በቢሉ ውስጥ እንዲህ ፅፎለታል
ክርስቶስ እዳዬን፣ ጠቅልሎ ከፍሎታል።


በጥሞና ጊዜ
ከምዕመን ለማሸሽ፣ ልክ አግባብ ቢኖርምኀ
በግ ከበግ ጋር እንጂ፣ ተኩላ ጋር አይኖርም።
ለስድስት ወር ባለም'፣ የከረመች ነፍስ
ወደ ውጭ እንጂ፣ ወደቤቱ አትነፍስ።

ፀሀፊ ሰምረ የሽዋስ

@getem
@getem
@getem
42🔥9👍4😱4
ሴት እና ኑሮ

በሌት አትምጪ እንደ ዘራፊ፤
እስኪነጋልን ልረፍ እረፊ፤

ቀኑን እንዳሻሽ ከቻልሽ ምጪ፤
ከኑሮ በላይ ለጆሮ ልቀሽ ብትደመጪ!

By @Lawyerly1

@getem
@getem
@paappii
38🤩10
( ስንትና ስንት ዓመት )
================

ከከፍታዬ ላይ ከፍቅሬ ሳልወርድ
ሌላ እቅፍ ሳያምረኝ
ሌላ አካል ሳል''ለምድ ...

ጨዋታሽን ሳልጠግብ
ሳቅሽ ሳይሰለቸኝ
ከአንቺ በቀር ያለው
ዓለም ሳይመቸኝ ....

ፍቅርን ከጀመርነው
እንዲያ እንደ ዘበት
ይኸው ተቆጠረ
ስንትና ስንት ዓመት !

አንቺ ውብ ጸሐዬ ...

" ወረት ይዞህ እንጂ
በጠዋቷ ሙቀት
ከርማ ስታቃጥል
አትደርስም ከቤቷ .. "
:
ሲሉ ያደከሙኝን
ምላሶች ታግሼ
በልቤ ዙፋን ላይ
አንቺን ብቻ አንግሼ ....

እጆችሽን ሳልለቅ
ከሰመረ ህይወት
ይኸው እንደዋዛ
ስንትና ስንት ዓመት !

@Kiyorna

@getem
@getem
@getem
41😁2🤩2
አለመምረጥን መምረጥ ፣ …ቢቻል
-----------------------------------------


ከጠዋት ጣይና ፥ ከጨረቃ ብርሃን?
በፊያሜታና ፥ ከሸገሯ ሮማን?
እንዲህ ያለው ምርጫ ፥
ጽድቅ ነው እርግማን?

በረሃብ አይደለም ፥ በሲኦል አይደለም

ፈጣሪ 'ሚቀጣህ ፥

ምርጫ እየሰጠ ነው ፥ ደስታ የሚያሳጣህ።

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@paappii
😁9657👍8🔥3👎2
በለጋ አዕምሯችን፣
‎የገባንን ፅፈን፤
‎ልክ ነው በማለት፣
‎ልክነትን አልፈን፤
‎ወራዜነት ቀጥፈን፤
‎እኛነትን ጥለን፣
‎እኔነትን ታቅፈን፤

‎በተናጠል ኖረን፤
‎አይገርምም?
‎ዛሬም ትክክል ነን፤

‎ወዶ አይተርቱ
‎"ሆድ ከሀገር ይሰፋል"
‎ለሆዱ ያደረም፣
‎ትውልድን ያጠፋል፤

‎ማንነት ለማወቅ፣
‎"ጠይቁ" የሚሉን፤
‎በኛ ሊከብሩ ነው፣
‎የሚነጣጥሉን፤

‎እነሱ
‎ሁሉም በፊናቸው፣
‎የሚሰብኩን እውነት፤

‎(ያው እውነት ከተባለ!)

‎የኔ ጥያቄ ግን፣
‎ምንድነው ማንነት?

‎እህት፣ ወንድምህ ላይ፣
‎መቀሰር ጣትህን?

‎(እንደዛ ከሆነ)

‎የዛሬ ስላቅህ
‎ነገ ተመልሶ፣
‎ይነካል ቤትህን፤

‎ሕመሜ ካስደሳ፣
‎ከበሮ ካስነሳ፣
‎ጎሽ፣ እሰይ፣ ለማለት፤

‎ከደጅህ ካራቀኝ፣
‎ክንድህ ካልጠበቀኝ፣
‎የቱ ጋር ነው እውነት?

‎ምንድነው ነው ልክነት?

‎የልጅነታችን፤
‎በሙሉ ልባችን፤

‎አድጎብን ማመኑ፣
‎ትተን መመርመሩን፤
‎ዛሬም ትክክል ነው፣
‎ሌሎች የሚነግሩን።

🖋ON

@getem
@getem
@getem
28
"ይድነቅሽ ድንቄ"

ይለቀማል ጥጥ ፣ ይለቀማል ወርቁ
ግዮን መፍሰሻሽስ ፣ እግዚያር ነው ስንቁ
ላለማለቁ!
እንደወንዝሽ ያለ ፣ ሌላ ወንዝ አውቄ
ጅረቱ ከእሳት ፣ መፍሰሱ ለጽድቄ
ገረመኝ ደነቀኝ ፣ ይድነቅሽ ድንቄ
ጠጥቼው መጣሁ ፣ ልነግርሽ ፈልጌ
ከምንጩ ስጠጣ ፣ታወቀኝ መፍለቄ
እስከመጨረሻ ፣ ላይጠማኝ መጽደቄ

By Natnael Abeba

@getem
@getem
@getem
28👍1
ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ
ሳስታውሳት ስትረሳኝ

ኢትዬጵያ ወባ ሆናብኝ
ራሴ...ለአንገት ከብዳብኝ

ሀገር ጀርባዋን ስታሳየኝ
ስተን እንደ ሽታ
ወገን ሚባል ጠፋኝ ረግፎ በበሽታ

ሀገርማ
ጫንቃዋማ
ቆስሏል እንደ ንፍሮ
ሀገርማ ፊቷማ
ተቀባብቷል በፊልትሮ
ህዝብ ሚሉት እየሰመጠ
ጉድጓድ ደርሷል የግል ኑሮ

ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ
ሳስታውሳት ስትረሳኝ

እያደርኩ እየሞትኩኝ
ጥንብ አንሳ ላያነሳኝ
ሰው መሆንጥሎኝ 
አውሬ ነው የሚያነሳኝ

ብቻ ጭዱ ያለቦታዋ
እኔን ማቀፍ ለምን ሻተች
ሀገር ታጥባ ወታ
በእኔ እቅፍ እየሸተተች

ለመሽተቴ አትፍረዱ
እንባዬ ነው የሚያወዛኝ
ሳቅ ባክህ አይባልም
ሀገር ሞቶበት ላለ ሀዛኝ

ሀገር ወባ ሆና
ስታንቀጠቅጠኝ በትኩሳት
መቼም ህመሜ ናት

አንዳንዴ አይነግሩትም
ህመምን ጠልተው አይጠሉትም

እያንቀጠቀጠችኝ
እያብረከረከችኝድ
በጭድ ቤቷ እየኮሰኮሰችኝ
ወባ ሆና እያመመችኝ
ትታ የማተወኝ
ትቼ የማልተዋት
ሀገር አለችኝ

By @geez_mulat

@getem
@getem
@getem
39👍5🔥2
"ቃል ያለ ቃል"

ስንን ያለ ኮሳሳ
ባለ ማወቅ የከሳ
ስልል ያለ ስናና
ተካድኖት ኦና

ይቆማል አይቆምም
ይገጥማል አይገጥምም
ይጠራል አይጠራም
ይጮኻል አይሰማም

እንዲህ ነው...
ቃል ያለ ቃል
ነፍስ ያደርቃል።

በአጀባ ያንቃል
በሁካታ ይደቃል
ለሞት ያነቃል
ኮታ ይነጥቃል።

ቃል ያለ ቃል
ነፍስ ያደርቃል።

By Natnael Abebe

@getem
@getem
@paappii
21🔥5
የሰካራሙ ፍልስፍና ✍️

እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል
እንደዚህ ይለዋል በሰካራም ድምጡ
በደልና መፅድቅ  እንዲለዋወጡ...

እንዲህ ተናገረ...
" ሰማያት ያለኸው፣ እግዚያር ሆይ ጌታዬ
  ሃሳብ  ቢጤ ላንተ፣ በፊትህ ከታዬ
  ምን መሰለህ እግዚያር...  
  በዚህኛው አለም በምንኖርባት፣
                     ሰዎች በተቃርኖ መርህ ይኖራሉ
  ተው!...ስትል ጥሰው፣
                 አድርግ ያልካቸውን መቼ ያደርጋሉ?
እኔንም ተመልከት...
አትስከር ያልከውን፣ ትዛዝህን ልጥስ
ዘውትር እየጠጣው፣ ዘውትር ለምን ላልቅስ?
ስለዚህ እግዝያር
ለዚህ ተቃርኖ ዛር
አንድ መፍትሔ አለኝ...
አታድርግን ጓግተን ከምንላወሰው
ህግጋት ቀልብሰህ ብትቃረን ከሰው
እጥር ምጥን ያለች፣ ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?...
(ቤተ መቅደስ እንዳትመጡ
የወይን ጠጅ ሂዱ ጠጡ
ቅድስናን እንዳትኖሩ
በደል ብቻ ሂዱ ዝሩ)...
በዛች ትንሽ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?
እኔንም ተመልከት...
እዚህኛው ዓለም ላይ፣ ሰው ተቃርኖን ተግቶ ይከውናል
እንዳትመጡ ስላልክ
ፍቃድህን ልጥስ፣ ምናልባት መቅደስህ እመጣ ይሆናል።"
"
እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል።
ፈጥረህ ትንሽ ድግስ
አድርግን አታደርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ

በደል አቅፎ እየኖረ፣ እንዲያ ያመካኛል
ሐጥያት መፅደቅ ቢሆን፣ እያለ ይመኛል።
ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
እንዲያ ብታደርግስ።

By ሰምረ የሽዋስ

@getem
@getem
@getem
23🔥13👍2🤩1
የቁም ፍቅር


ስደክም ብውል አዳር ብለፋም፤
አስታውሳለሁ ከውስጤ አይጠፋም፤
የዛ ቀን ግለት የዛች ቀኑ ፍም፤

ያገኘሁሽ ቀን በዛች ካፌ ፍክት ብለሽ፣
ያየሁሽ ለታ እዚያ ጥግ ላይ ስልክሽን ይዘሽ፤

'ሰው አለው' ብዬ ወንበሩን ልስብ፣
ገና ሳልለው እንዲሁ ባሳብ፤

ሳወጣ ሳወርድ ቃላት ስመርጥ፣
አይንሽን ስቃኝ ከንፈሬን ስመጥ፤

እንዲሁ ቆሜ እንዲሁ እንዳለሁ፤
ለካ ሳላውቀው እረዥም ሰአት ተገትሬያለሁ፤

አሁን ስመለስ ራሴን ሳገኘው፤
ዙሪያ ገባውን ባይኔ ብቃኘው፤

አልለማ አልሰማ አልጠፋ አልበራ፤
እንዲሁ ብቻ ግትር ብዬ እንደጅብራ፤

'እብድ ነው?' በሚል አስተያየትሽ ብትገረምሚኝ፤
አቅፌው ሄድኩኝ ያንድ ደቂቃ ፍቅሬን ሳትሰሚኝ፤

By @Lawyerly1

@getem
@getem
@getem
40🔥7
እንዳትመለሺ ፣ መምጪያ መንገድሽ ላይ
እሾህ ብዘራበት ...

ልቤ ሳቅ ታየበት ...

የጨለመው ዓይኔ – ብርሃን ዘነበበት

ኃጢያትም አንዳንዴ – የእግዜር እጅ አለበት

By Thomas Atsede

@getem
@getem
@paappii
43😁21👎8🔥8😱6
ይቅር በላቸው[ፀሎት]

የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች
ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሀብቶች...
_  _  _
ሸንበቆ ድግፍ እፍኝ ትምክህቶች
መውደቂያ ያጡ ድፍን ተምኔቶች!

ይቅር በላቸው...

የተጣደፉ ፈራጅ ከንፈሮች
ያልተማከሩ ልብና አፎች!
ያልደነገጡ ድንድን ስሜቶች
ያልተረጋጉ ሰንካላ እምነቶች!

ይቅር በላቸው!

ይበልጥም...
የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች!
ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሃብቶች!

_  _  _
ያስመከቱኝን ውዥቅ ቀለማት
ያስፎከሩኝን ግንጥል ድምቀታት!

ይቅር በላቸው!

አልደበቁኝም ልሽሽው ካልኩት
አላስጣሉኝም ከተሯሯጥኩት
አላወጡኝም ከሰው ትከሻ
ወይ አልሰጡኝም ዝና ሙገሳ፨

ይቅር በላቸው!

ማራቸው ያለህ ልቤ አስታኮ፧
አብረህ አስበኝ ሊልህ ነው እኮ፧፧

By @alem3_b [ዓለም]
@getem
@getem
@getem
47🔥11👍3😱2
ለፀሐይ ፍካት ማን ይፈግጋል?
ለሰማይ ንጣት ማን ይደግሳል?
ማን ግድ ብሎት ማን ስሜት ሰጥቶት?
ከምድር አልፎ ሰማዩን አይቶት?¡

ዘልቋል ከውስጥኽ?ገብቶሃል ቅኔው?
ምን ብትነጠፍ ሰማይ ብትሆነው
የያዘው እክል እስካልለቀቀው፧
ከኑሮ አሻግሮ ግትር አንገቱን እስካላዞረው፧
መቼም አያይህ ያልቀናለት ሰው!


By @alem3_b[ዓለም]
@getem
@getem
@getem
21🔥8
ድሮ አንቺን ለማየት
ሰፈርሽ ስመጣ
አንዲት ዝርግ ድንጋይ
አየሁ ተቀምጣ ፤
ቁጭ አልኩኝ በድንገት
እንዲህ እንደ ዘበት…
ያፈቀረሸ ልቤ ፣ ሳሉ ሲነሳበት
ማስታገሻ ነበር ፣ ሰፈርሽ መገኘት።

ዛሬስ አትይኝም?

እዛው ተቀምጬ
አትመጣም ወይ? እያልሁ
አንቺ ብትቀሪ…
:
ዲግሪ ጭኖ መጣ
ሀይስኩል ተማሪ።

እዛው ትናንትና
እዛው አንቺ ሰፈር
ከጠፍጣፉ ድንጋይ
ሳልነሳ ቀንቶኝ…
:
ያምና ብላቴና
ያልፈኛል ገላምጦኝ።

አትገረሚም ወይ?

ሳልነሳ ከዛ
ቤተ መቅደስ ታዛ
ከስር የማይጠፋ
የወንጌል ሰባኪ
ቅስናውን ገድፎ
በየመሸታ ቤት
ሲያወርድ ያድራል ውስኪ።

እዛው ትናንትና
አንቺን ከማይበት
ከጠፍጣፉ ድንጋይ
ተቀምጬ እያለሁ
አንዱ አብሮ አደጌ
በመኺና ባየው-
እጆቼን ዘረጋሁ
ለናፍቆት ሰላምታ
መስታወቱን ሳበ
በእንዴት ነህ? ፈንታ

ያን ጊዜ ተከፋሁ
ውስጤን ቦረቦረኝ-
ምናል እንደ ድሮው
አቅፎ ሰላም ቢለኝ?

(ጎስቁያለሁ በቃ?🤔)

አትገረሚም ወይ?

ሰዎች አሉኝ ከንቱ
መንገድ ቀየሩብኝ
ቀፍፎ ፣ ጎርብጧቸው
ዘባተሎ ጨርቄ…
ያካሌ ቡትቱ።

(ጎስቁያለሁ ለካ !)

እዛው ቁጭ ብዬ
ተዓምር ደረሰ
ሰፈሩ ተዳሰ
ቅጥሩ ፈራረሰ

የግቢያችሁ በሩ
ይከብድ የነበረው
በአባትሽ ትከሻ…
:
የማንም ወመኔ
አጨሰበት ሺሻ።

እዛችው ከትናንት
ከግቢያችሁ ማዶ
እስክሰማ ድረስ
ቀጭን ክፉ መርዶ
:
እየጫኑ ዲግሪ፣
እየናቀኝ ውሪ፣
ሰክሮ እየሳተ…
የ’ግዜአብሔር አዳሪ
እብድ ነው እያሉኝ
እነ ቲቲ ፣ ሜሪ

እየተቃመበት
የአባትሽ ገዳም
እየተጨሰበት
የእናትሽ በዓት
ትዝታችን ሲናድ
በከተማ ልማት ፤

አንዱም ድል ሳይመታኝ
ስንቱን ዘመን ሽሬ
እልፍ ዘመን ኖሬ

ሁሉን እየረታሁ …
ሁሉን እየነሳሁ…
“አግብታለች” ቢሉኝ
በድንገት ተነሳሁ።

(ታስታውሽኝ ይሆን?)
አታውቂኝም ለካ🥹

ሚካኤል .አ

@getem
@getem
@paappii
68🔥23😢19👍3
እውነትም ሰገነት!

ውሸት አልነበረም ያ ሁሉ ሙገሳ፥
ሰማይ ታህል ነበር ጨረቃ አንችን ለብሳ።
አድማስና ማማ ማጋነን ቢመስል፥
ወንዝ እንኳ ሚረጋው ሲቃኝ ባንቺ ምስል፤

እውነት? ያባይ ጅረት ሳቅሽን ይበልጣል?
የጢሱ ርግብታ? ከርጋታሽ ይሰክናል?
እስቲ ጽጌሬዳ?ይመ--ስልሻል ወይ፣
ይቅርና በበጋ እርሙንስ በጸደይ?!

ንግግርሽ ሃገር አርምሞሽ አሃጉር
አንቺ ላይ ከረመ ውበት ሲያንጎራጉር!።

ሃሳብሽ ገራገር መርኅሽ ዝምታ፣፨
                    .
                    .
                    .
እውነትም ሰገነትእውነትም ከፍታ!።🙌🏿

By @alem3_b [ዓለም]
@getem
@getem
@getem
49👎3🤩1
እንዳትረሺኝ  ብዬሽ፤
አትርሳኝ ብለሽኝ ፤

በቃል ክር አስሬሽ፤
በቃል ክር አስረሽኝ፤

በደልሽኝ በደልኩሽ፤
በደልኩሽ በደልሽኝ ፤

ቃልሽን አከበርሽ
ቃሌን አከበርኩኝ ፤

ይሄ በደላችን...
እንኳን  በ'ዚህ ሕይወት
በመቃብርም ውስጥ ችሎ አያረሳሳም፤
ደግሞ እንደምታውቂው
የወዳጅ ፍቅሩ እንጅ በደሉ አይረሳም ።

By Tewodros kassa

@topazionnn
@topazionnn
60🔥7