Forwarded from Amanuel Y.
📢 የሰላም ድምፆች | Voices for Peace
የግጥም ስብስብ (Anthology) — የሕትመት ጥሪ
ዓለም አቀፉ የፀሐፊያን ማኅበር PEN International አባል የሆነው PEN Eritrea፣ ‘የሰላም ድምፆች’ በሚል ርዕስ ለኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ገጣሚያን የሚሆን ድንቅ የጋራ መድብል የሕትመት ዕድል አዘጋጅቷል።
📌 መሥፈርቶች
✍️ ከዚህ ቀደም ያልታተሙ እስከ 3 ግጥሞች (በአጠቃላይ ከ5 ገጽ ያልበለጠ)
🕊️ ጭብጥ፦ ሰላም፣ ግጭት፣ ተስፋ፣ ስደት፣ መትረፍ (Survival) ወይም ተያያዥ ማኅበራዊ ጉዳዮች
🌍 በየትኛውም ቋንቋ የተጻፉ ግጥሞችን ማቅረብ ይቻላል
🎁 የተመረጡ ግጥሞች፦
📖 በጋራ መድበል ተሰብስበው ይታተማሉ
✍️ ከገጣሚያኑ ጋር በመመካከርና ባለቤትነታቸው ተጠብቆ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ይተረጎማሉ
👉🏾 የተመረጡ ገጣሚያን የ $200 ዶላር (ሁለት መቶ ዶላር) ክፍያ ያገኛሉ።
📅 ማብቂያ ቀን፦ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. (June 29, 2026)
🔗 ዝርዝር መረጃና ማመልከቻ ሊንክ፦
አማርኛ፦ https://peneritrea.com/blog/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%8b%b5%e1%88%9d%e1%8d%86%e1%89%bd-voices-for-peace-%e1%8b%a8%e1%8c%8d%e1%8c%a5%e1%88%9d-%e1%88%b5%e1%89%a5%e1%88%b5%e1%89%a5
English: https://peneritrea.com/blog/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d
የግጥም ስብስብ (Anthology) — የሕትመት ጥሪ
ዓለም አቀፉ የፀሐፊያን ማኅበር PEN International አባል የሆነው PEN Eritrea፣ ‘የሰላም ድምፆች’ በሚል ርዕስ ለኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ገጣሚያን የሚሆን ድንቅ የጋራ መድብል የሕትመት ዕድል አዘጋጅቷል።
📌 መሥፈርቶች
✍️ ከዚህ ቀደም ያልታተሙ እስከ 3 ግጥሞች (በአጠቃላይ ከ5 ገጽ ያልበለጠ)
🕊️ ጭብጥ፦ ሰላም፣ ግጭት፣ ተስፋ፣ ስደት፣ መትረፍ (Survival) ወይም ተያያዥ ማኅበራዊ ጉዳዮች
🌍 በየትኛውም ቋንቋ የተጻፉ ግጥሞችን ማቅረብ ይቻላል
🎁 የተመረጡ ግጥሞች፦
📖 በጋራ መድበል ተሰብስበው ይታተማሉ
✍️ ከገጣሚያኑ ጋር በመመካከርና ባለቤትነታቸው ተጠብቆ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ይተረጎማሉ
👉🏾 የተመረጡ ገጣሚያን የ $200 ዶላር (ሁለት መቶ ዶላር) ክፍያ ያገኛሉ።
📅 ማብቂያ ቀን፦ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. (June 29, 2026)
🔗 ዝርዝር መረጃና ማመልከቻ ሊንክ፦
አማርኛ፦ https://peneritrea.com/blog/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%8b%b5%e1%88%9d%e1%8d%86%e1%89%bd-voices-for-peace-%e1%8b%a8%e1%8c%8d%e1%8c%a5%e1%88%9d-%e1%88%b5%e1%89%a5%e1%88%b5%e1%89%a5
English: https://peneritrea.com/blog/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d
Pen Eritrea
‘የሰላም ድምፆች’ (Voices for Peace) የግጥም ስብስብ – ሕትመት ጥሪ - Pen Eritrea
Voices for Peace: Poetry Anthology – Call for Subordination
❤24👍4
ላ'ባቴ
ሰው ብቻ አይደለህም፣
ካፈር ወጥተህ ላፈር
መላክ ነህ ሉሲፈር...
ክብርህ ማንነትህ፣ ባመፅ የሚታፈር
የማትንበረከክ የማትርመጠመጥ፣
ከባለጌ ዙፋን በርጩማ የምትመርጥ።
ያለ ባህር ሰርጓጅ ያለ ሙሴ በትር፣
በመታገስ ብቻ ባህር የምትመትር።
ካዘልከኝ ጀምሮ በእንኮኮ ጫንቃህ ላይ፣
ከፍታውን እንጂ፣ ዝቅታውን ሳላይ።
እንደ ንሥር መጠቅሁ፣ እንደ ኮከብ በራሁ፣
የገዛ ክንፎቼን እንደ ዳንቴል ሰራሁ።
በርግጥ ደሀ ነበርክ...
ከሰላምታ በቀር የማታበረክት፣
ነጠላህ መናኛ፣ ሰውነትህ የክት።
በርግጥ ደሀ ነበርክ፣ የነጣህ የጠራህ፣
ከጦር ሜዳ ይልቅ፣ ገበያ ሚያስፈራህ።
ቤሳ ባታወርሰኝ፣ አወረስከኝ ትግል፣
የትም እንዳይጥለኝ ህይወት እንደ ፈንግል።
አባዬ ብርሃን አባ የምስራቅ በር፣
ገመና ሸሻጊ እንደ ካባ ገበር፣
አባቴ ባትሆን፣ ምን ይውጠኝ ነበር።
By ብዕውቀቱ ስዩም
@getem
@getem
@paappii
ሰው ብቻ አይደለህም፣
ካፈር ወጥተህ ላፈር
መላክ ነህ ሉሲፈር...
ክብርህ ማንነትህ፣ ባመፅ የሚታፈር
የማትንበረከክ የማትርመጠመጥ፣
ከባለጌ ዙፋን በርጩማ የምትመርጥ።
ያለ ባህር ሰርጓጅ ያለ ሙሴ በትር፣
በመታገስ ብቻ ባህር የምትመትር።
ካዘልከኝ ጀምሮ በእንኮኮ ጫንቃህ ላይ፣
ከፍታውን እንጂ፣ ዝቅታውን ሳላይ።
እንደ ንሥር መጠቅሁ፣ እንደ ኮከብ በራሁ፣
የገዛ ክንፎቼን እንደ ዳንቴል ሰራሁ።
በርግጥ ደሀ ነበርክ...
ከሰላምታ በቀር የማታበረክት፣
ነጠላህ መናኛ፣ ሰውነትህ የክት።
በርግጥ ደሀ ነበርክ፣ የነጣህ የጠራህ፣
ከጦር ሜዳ ይልቅ፣ ገበያ ሚያስፈራህ።
ቤሳ ባታወርሰኝ፣ አወረስከኝ ትግል፣
የትም እንዳይጥለኝ ህይወት እንደ ፈንግል።
አባዬ ብርሃን አባ የምስራቅ በር፣
ገመና ሸሻጊ እንደ ካባ ገበር፣
አባቴ ባትሆን፣ ምን ይውጠኝ ነበር።
By ብዕውቀቱ ስዩም
@getem
@getem
@paappii
❤109👍21👎13🔥8😁4😢1
ይቅናት
.
.
ልጂት ተላላ አይኗም ቀልቃላ
በሺ ሰው ትኩረት ልቧ ማይሞላ
ሁሉንም መያዝ ሁሉንም ማግኘት
ሰላሳ ነገር ባንዴ መመኘት
የማያደክማት እረፍት የማታውቅ
ገና ጅምር ናት ተፈጥራ ማታልቅ
ደሞ ታምራለች እግዚኦ መልኳ
አይደርስባትም ሉሲፈርንኳ
አይኗም እንደ ልጅ አንጀት ያባባል
ጉድፍ ገብቶበት ውበት ያነባል
ልኬት የላትም ማነፃፀሪያ
ንጉስ ቢጠጋት ይመስላል ባሪያ
ኧረ'ዲያ....!
እኔ ግን ልቤን ልኬን ስለማውቅ
ቅዠት ህልሜ ላይ ከምደባልቅ
ምንም ብወዳት ምንም ብታምርም
መ'ላክ ጠልፌ ከቤቴ አላስርም
የራሴን ቀብር በጄ አልቆፍርም
ትሂድ ትንሳፈፍ ክንፏን ታማታ
እድል የቀናው የማታ ማታ
ላባዋ ሲረግፍ ዳዴ ስትጀምር
ያግኛትና መንገዷን ያስምር...
እያልኩ ለሰው ቸር እመኛለሁ
አልችላትማ... ምን አደርጋለሁ?
By Tadios Alemayehu
@getem
@getem
@paappii
.
.
ልጂት ተላላ አይኗም ቀልቃላ
በሺ ሰው ትኩረት ልቧ ማይሞላ
ሁሉንም መያዝ ሁሉንም ማግኘት
ሰላሳ ነገር ባንዴ መመኘት
የማያደክማት እረፍት የማታውቅ
ገና ጅምር ናት ተፈጥራ ማታልቅ
ደሞ ታምራለች እግዚኦ መልኳ
አይደርስባትም ሉሲፈርንኳ
አይኗም እንደ ልጅ አንጀት ያባባል
ጉድፍ ገብቶበት ውበት ያነባል
ልኬት የላትም ማነፃፀሪያ
ንጉስ ቢጠጋት ይመስላል ባሪያ
ኧረ'ዲያ....!
እኔ ግን ልቤን ልኬን ስለማውቅ
ቅዠት ህልሜ ላይ ከምደባልቅ
ምንም ብወዳት ምንም ብታምርም
መ'ላክ ጠልፌ ከቤቴ አላስርም
የራሴን ቀብር በጄ አልቆፍርም
ትሂድ ትንሳፈፍ ክንፏን ታማታ
እድል የቀናው የማታ ማታ
ላባዋ ሲረግፍ ዳዴ ስትጀምር
ያግኛትና መንገዷን ያስምር...
እያልኩ ለሰው ቸር እመኛለሁ
አልችላትማ... ምን አደርጋለሁ?
By Tadios Alemayehu
@getem
@getem
@paappii
❤99🔥23🤩11👍6😁6😱2🎉1
¹
አለሽ የሆነ ነገር......
አለሽ የሆነ መስህብ ....
አለሽ የሆነ ግርማ.......
(እንዲያ ባይሆንማ.....)
ወደ ላይ.... ወደ ላይ......
(ወደ ጥጥ ደመና) ሽቅብ መንጠራራት (መኩራራት) ሳያንሰው ፣
ዝቅ ሊል ወዳንቺ —···
ዋርካን እንደ ሐረግ ምን አልፈሰፈሰው?
ያልለመደበትን (ያ'ላፈጣጠሩ) ስለምን ይቸገር?
አለሽ የሆነ ነገር....!
²
(እኔማ በእኔ ቤት......)
ከሆዱ በልጦበት....
ገበሬ ለውበት —···· እርሻውን አይለቅም ፣
ወፍ ያለ አይመስለኝም....
ዝማሬ የማያውቅ —··· ስንጥር የማይለቅም ፣
ሰው ገላ ላይ ሆኖም —···መንደፍ የጠፋበት — ንብ አይቼ አላውቅም ።
እንዲህ ያለ ጥበብ — እንዲህ ያለ መላ ፣
ባንቺ አየሁ ፡ ባንቺ አየሁ — የታለ በሌላ?!
³
አለሽ የሆነ ነገር....
አለሽ....!
ከጥንት መንፈስ የተዋረሰሽ ....
እንደ ደሊላ — የጀግናውን ልብ ያስበረገገ
(ሳምሶንን ድኩም ያረገ ) ።
እሷስ በአንዲት መቀስ — በፀጉር መላጫ ፤
ይበልጣል ያንቺ ሳቅ — የጥሜ መቁረጫ ።
⁴
አለሽ የሆነ ነገር.....
ያቺ “ሔለን” ሚሏት የግሪክ ሀገር ውብ
የትሮይ ምርኮኛ ፤
የጠፋች እንደሆን እሷን ለማስመለስ......
በሺህ መርከብ ፈረስ — ዘምቶ አየን ጦረኛ ።
ሰውማ አመሉ ነው ይዋጋል ይሞታል ፤
አይበቃም ላንቺ ግን ባህሩም ይዘምታል።
⁵
አለሽ የሆነ ነገር.....
አዳም የጥንቱ — ቀልብ የሳተበት
ሕግ የሻረበት (የሔዋን ፍቅር)
የተቀጣበት ።
(የእሱን አየን....)
ገነት ሲቀር (ሞት ሲመጣ)
በአንዲት ፍሬ — ትንሽ በለስ ፣
እኔስ ባንቺ የገባሁት —···
ሃጢያቴ በምን ይመለስ?
አለሽ የሆነ ነገር....
__
By Bekalu shumye
Inspired by Cole Porter's: “You've got that thing ”
@getem
@getem
@paappii
አለሽ የሆነ ነገር......
አለሽ የሆነ መስህብ ....
አለሽ የሆነ ግርማ.......
(እንዲያ ባይሆንማ.....)
ወደ ላይ.... ወደ ላይ......
(ወደ ጥጥ ደመና) ሽቅብ መንጠራራት (መኩራራት) ሳያንሰው ፣
ዝቅ ሊል ወዳንቺ —···
ዋርካን እንደ ሐረግ ምን አልፈሰፈሰው?
ያልለመደበትን (ያ'ላፈጣጠሩ) ስለምን ይቸገር?
አለሽ የሆነ ነገር....!
²
(እኔማ በእኔ ቤት......)
ከሆዱ በልጦበት....
ገበሬ ለውበት —···· እርሻውን አይለቅም ፣
ወፍ ያለ አይመስለኝም....
ዝማሬ የማያውቅ —··· ስንጥር የማይለቅም ፣
ሰው ገላ ላይ ሆኖም —···መንደፍ የጠፋበት — ንብ አይቼ አላውቅም ።
እንዲህ ያለ ጥበብ — እንዲህ ያለ መላ ፣
ባንቺ አየሁ ፡ ባንቺ አየሁ — የታለ በሌላ?!
³
አለሽ የሆነ ነገር....
አለሽ....!
ከጥንት መንፈስ የተዋረሰሽ ....
እንደ ደሊላ — የጀግናውን ልብ ያስበረገገ
(ሳምሶንን ድኩም ያረገ ) ።
እሷስ በአንዲት መቀስ — በፀጉር መላጫ ፤
ይበልጣል ያንቺ ሳቅ — የጥሜ መቁረጫ ።
⁴
አለሽ የሆነ ነገር.....
ያቺ “ሔለን” ሚሏት የግሪክ ሀገር ውብ
የትሮይ ምርኮኛ ፤
የጠፋች እንደሆን እሷን ለማስመለስ......
በሺህ መርከብ ፈረስ — ዘምቶ አየን ጦረኛ ።
ሰውማ አመሉ ነው ይዋጋል ይሞታል ፤
አይበቃም ላንቺ ግን ባህሩም ይዘምታል።
⁵
አለሽ የሆነ ነገር.....
አዳም የጥንቱ — ቀልብ የሳተበት
ሕግ የሻረበት (የሔዋን ፍቅር)
የተቀጣበት ።
(የእሱን አየን....)
ገነት ሲቀር (ሞት ሲመጣ)
በአንዲት ፍሬ — ትንሽ በለስ ፣
እኔስ ባንቺ የገባሁት —···
ሃጢያቴ በምን ይመለስ?
አለሽ የሆነ ነገር....
__
By Bekalu shumye
Inspired by Cole Porter's: “You've got that thing ”
@getem
@getem
@paappii
❤53🔥14
የውድቀቴን መንገድ
ሸርሽራ በመውደድ
ያቀናችኝ ንግስት ... የሰጠችኝ ክብር
አቤት አቤት ሲያምር
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
መኖር እንድጠላ መንፈሴን አድክሞ
ማጣት አንቆኝ ሲዞር ክንዱን አፈርጥሞ
የምሆነው ጠፍቶኝ
ተንበርክኬ ሳዝን ሳትለኝ ደካማ
ቀና አረገችኝ ቀንበሬን ተሸክማ!
እምቅ የእንባ ጠል
ጉንጬን ሲንጠለጠል
ኅዘን በደቆሰው ልስልስ ስስ አንጀቷ
ዕንባዬን ያበሰው
አቤት ሲያምር ጣቷ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
እኔነት እስካጣ ፍቅር ሸሽቶኝ በሮ
ብቸኝነት ሚስማር ሲያደማኝ ቸንክሮ
የማረገው ጠፍቶኝ
ሞቴን እየናፈቅኩ ሳዘጋጅ መስቀሌን
ትንፋሽ ለገሰችኝ ዳብሳ ሰንበር ቁስሌን
የጅራፍ ሹል ትርትራት
የልቤ ስውር ስብራት
አድቅቆ ሲጥለኝ ... እንዲሆን ለነፍሷ
ስሞ ሳቅ ያሳየኝ
አቤት ሲያምር ጥርሷ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
ስትችልበት ማዘን
ስታውቅበት ማቀፍ
ብሶት አስዘርግፎ
በሰላም ማሳረፍ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
ስትችልበት ጸሎት
ስታውቅበት ማውራት
ጨለማን ገርስሶ
በፈገግታ ማብራት
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
ስትችልበት ማከም
ስታውቅበት ማዳን
ፍቅር በልብ ሰጥቶ
መለገስ ማር ኪዳን
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@paappii
ሸርሽራ በመውደድ
ያቀናችኝ ንግስት ... የሰጠችኝ ክብር
አቤት አቤት ሲያምር
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
መኖር እንድጠላ መንፈሴን አድክሞ
ማጣት አንቆኝ ሲዞር ክንዱን አፈርጥሞ
የምሆነው ጠፍቶኝ
ተንበርክኬ ሳዝን ሳትለኝ ደካማ
ቀና አረገችኝ ቀንበሬን ተሸክማ!
እምቅ የእንባ ጠል
ጉንጬን ሲንጠለጠል
ኅዘን በደቆሰው ልስልስ ስስ አንጀቷ
ዕንባዬን ያበሰው
አቤት ሲያምር ጣቷ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
እኔነት እስካጣ ፍቅር ሸሽቶኝ በሮ
ብቸኝነት ሚስማር ሲያደማኝ ቸንክሮ
የማረገው ጠፍቶኝ
ሞቴን እየናፈቅኩ ሳዘጋጅ መስቀሌን
ትንፋሽ ለገሰችኝ ዳብሳ ሰንበር ቁስሌን
የጅራፍ ሹል ትርትራት
የልቤ ስውር ስብራት
አድቅቆ ሲጥለኝ ... እንዲሆን ለነፍሷ
ስሞ ሳቅ ያሳየኝ
አቤት ሲያምር ጥርሷ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
ስትችልበት ማዘን
ስታውቅበት ማቀፍ
ብሶት አስዘርግፎ
በሰላም ማሳረፍ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
ስትችልበት ጸሎት
ስታውቅበት ማውራት
ጨለማን ገርስሶ
በፈገግታ ማብራት
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
ስትችልበት ማከም
ስታውቅበት ማዳን
ፍቅር በልብ ሰጥቶ
መለገስ ማር ኪዳን
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@paappii
❤53🔥7👍1👎1
ሀሜት የት ነበረ??
በፊት....
የጎረቤቴ በር በቀን አይዘጋም
እኛም ለመፋቀር መሽቶልን አይነጋም
'አቡሽ' ቡና ጥራ...ሲሉን ደስ እያለን
አዋቂው ሲታደም ጓዳ ግባ ሁላ መቼ እናውቃለን??
ልክ እንደ ቡና ቁርስ መሀል ቁልጭ ቁልጭ
ሲያዝኑ እያዘንን ሲስቁም መብለጭለጭ
ውሉን ባንረዳው የጨዋታቸውን
እናውቅ ግን ነበር አንጀት ሆዳቸውን፤
እንከን በየዘመን፣ጥልም በየጊዜው ነበረ አይካድም፣
ግን በኛ ልጅነት እዛው እርቅ ይወርዳል ወዴትም አይሄድም፤
አሁን...
ባህል የለሽ ወጉ እኛን አርቆናል
በዘመን መዘመን ስራ አቀለለ እንጂ እኛን አቅልሎናል፤
ንግግር በግጥም ወዝ ቸፍ ቢልበት
ለአንዳንዱ ይከብደዋል ለአንዳንዱ ቀሎበት
ከእውነታው አልርቅም መቅረቡ ይጥመኛል
ከማስመሰል በላይ መምሰሉ ከብዶኛል፤
በቀን ሰው ፈርተናል የጨለመው ጥሞን
ውሸት ሰፍቶብናል ቀናው መንገድ ጠቦን!
እሺ....
ይሄ መፈራራት ፣ይሄ መተማማት ኢትዮጵያን ካስቀረ፣
ያኔ ልጅ እያለን 'ሀሜት' የት ነበረ????
@Weyblann ያቡ
@getem
@getem
በፊት....
የጎረቤቴ በር በቀን አይዘጋም
እኛም ለመፋቀር መሽቶልን አይነጋም
'አቡሽ' ቡና ጥራ...ሲሉን ደስ እያለን
አዋቂው ሲታደም ጓዳ ግባ ሁላ መቼ እናውቃለን??
ልክ እንደ ቡና ቁርስ መሀል ቁልጭ ቁልጭ
ሲያዝኑ እያዘንን ሲስቁም መብለጭለጭ
ውሉን ባንረዳው የጨዋታቸውን
እናውቅ ግን ነበር አንጀት ሆዳቸውን፤
እንከን በየዘመን፣ጥልም በየጊዜው ነበረ አይካድም፣
ግን በኛ ልጅነት እዛው እርቅ ይወርዳል ወዴትም አይሄድም፤
አሁን...
ባህል የለሽ ወጉ እኛን አርቆናል
በዘመን መዘመን ስራ አቀለለ እንጂ እኛን አቅልሎናል፤
ንግግር በግጥም ወዝ ቸፍ ቢልበት
ለአንዳንዱ ይከብደዋል ለአንዳንዱ ቀሎበት
ከእውነታው አልርቅም መቅረቡ ይጥመኛል
ከማስመሰል በላይ መምሰሉ ከብዶኛል፤
በቀን ሰው ፈርተናል የጨለመው ጥሞን
ውሸት ሰፍቶብናል ቀናው መንገድ ጠቦን!
እሺ....
ይሄ መፈራራት ፣ይሄ መተማማት ኢትዮጵያን ካስቀረ፣
ያኔ ልጅ እያለን 'ሀሜት' የት ነበረ????
@Weyblann ያቡ
@getem
@getem
❤44🔥10🎉4👎1
ጥሞና ግሮሰሪ
ተከሳሽ እገሌ፣ በቀደመው ወር ጥር
አራት ሳት' ገደማ፣ ላምስት' ሲቆጥር
ከላዩ ደርቦ የቻይና፣ ሌዘር ኮት
ተሸፋፍኖ ከሰው፣ ጥሶ ከመለኮት
እየተገላበጠ ተራምዶ በእንክብል
ጥቁር ተከናንቦ አርጎ የፊት ጭምብል
(የማይታይ መስሎት!)
ግራጫ ቀለም፣ አርጎ የክት ሱሪ
ደርድሮ ሲጠጣ፣ ገነት ግሮሰሪ
ባይን አማኝ ምስክር
በባዶ ክርክር
ከዛሬ ጀምሮ፣ ከመቅደስ ተባሯል
ለጥሞና ጊዜ፣ ለስድስት ወር ታስሯል።
*
(ተከሳሽ መልስ አለህ?)
:
እርግጥ ነው
አልክድም ክሳቹን፣ ቅዳሜ አመሻሽ ለውስኪ ስገባ
የኔ ጥያቄ ግን፣
ታማኙ ምዕመን ፣ ያይን ምስክሩ ምን ሊሰራ ገባ?
:
:
(ከስድስት ወር በኋላ)
:
:
የመሰከረበት ያ ታማኝ አገልጋይ
ጥሞና ተብሎ ከታሰረው ታጋይ
የነደደ እሳት፣ በስካር ቆስቁሰው
ከሸንጎ ቆመዋል፣ ክፉኛ ተቧቅሰው
*
ሸንጎ ተጀምሮ ክሱ ሲዘረዘር
*
ለካ!
ለጥሞና ጊዜ፣ የታሰረው ወጣት
ገነት ግሮሰሪን፣ ለልማት ስላጣት
ሆዱና አድማሱን፣ እስከ ጥግ አስፍቷል
በጥሞና ጊዜው፣ ግሮሰሪ ከፍቷል።
(ጥሞና ግሮሰሪ)
አይን አማኙም ከዚሁ፣ ሰባት ጠጥቶ
ሳይከፍል በጉራ፣ ጥሶ ሄዷል ወጥቶ።
ይልቅ በቢሉ ውስጥ እንዲህ ፅፎለታል
ክርስቶስ እዳዬን፣ ጠቅልሎ ከፍሎታል።
¶
¶
በጥሞና ጊዜ
ከምዕመን ለማሸሽ፣ ልክ አግባብ ቢኖርምኀ
በግ ከበግ ጋር እንጂ፣ ተኩላ ጋር አይኖርም።
ለስድስት ወር ባለም'፣ የከረመች ነፍስ
ወደ ውጭ እንጂ፣ ወደቤቱ አትነፍስ።
ፀሀፊ ሰምረ የሽዋስ
@getem
@getem
@getem
ተከሳሽ እገሌ፣ በቀደመው ወር ጥር
አራት ሳት' ገደማ፣ ላምስት' ሲቆጥር
ከላዩ ደርቦ የቻይና፣ ሌዘር ኮት
ተሸፋፍኖ ከሰው፣ ጥሶ ከመለኮት
እየተገላበጠ ተራምዶ በእንክብል
ጥቁር ተከናንቦ አርጎ የፊት ጭምብል
(የማይታይ መስሎት!)
ግራጫ ቀለም፣ አርጎ የክት ሱሪ
ደርድሮ ሲጠጣ፣ ገነት ግሮሰሪ
ባይን አማኝ ምስክር
በባዶ ክርክር
ከዛሬ ጀምሮ፣ ከመቅደስ ተባሯል
ለጥሞና ጊዜ፣ ለስድስት ወር ታስሯል።
*
(ተከሳሽ መልስ አለህ?)
:
እርግጥ ነው
አልክድም ክሳቹን፣ ቅዳሜ አመሻሽ ለውስኪ ስገባ
የኔ ጥያቄ ግን፣
ታማኙ ምዕመን ፣ ያይን ምስክሩ ምን ሊሰራ ገባ?
:
:
(ከስድስት ወር በኋላ)
:
:
የመሰከረበት ያ ታማኝ አገልጋይ
ጥሞና ተብሎ ከታሰረው ታጋይ
የነደደ እሳት፣ በስካር ቆስቁሰው
ከሸንጎ ቆመዋል፣ ክፉኛ ተቧቅሰው
*
ሸንጎ ተጀምሮ ክሱ ሲዘረዘር
*
ለካ!
ለጥሞና ጊዜ፣ የታሰረው ወጣት
ገነት ግሮሰሪን፣ ለልማት ስላጣት
ሆዱና አድማሱን፣ እስከ ጥግ አስፍቷል
በጥሞና ጊዜው፣ ግሮሰሪ ከፍቷል።
(ጥሞና ግሮሰሪ)
አይን አማኙም ከዚሁ፣ ሰባት ጠጥቶ
ሳይከፍል በጉራ፣ ጥሶ ሄዷል ወጥቶ።
ይልቅ በቢሉ ውስጥ እንዲህ ፅፎለታል
ክርስቶስ እዳዬን፣ ጠቅልሎ ከፍሎታል።
¶
¶
በጥሞና ጊዜ
ከምዕመን ለማሸሽ፣ ልክ አግባብ ቢኖርምኀ
በግ ከበግ ጋር እንጂ፣ ተኩላ ጋር አይኖርም።
ለስድስት ወር ባለም'፣ የከረመች ነፍስ
ወደ ውጭ እንጂ፣ ወደቤቱ አትነፍስ።
ፀሀፊ ሰምረ የሽዋስ
@getem
@getem
@getem
❤42🔥9👍4😱4
ሴት እና ኑሮ
በሌት አትምጪ እንደ ዘራፊ፤
እስኪነጋልን ልረፍ እረፊ፤
ቀኑን እንዳሻሽ ከቻልሽ ምጪ፤
ከኑሮ በላይ ለጆሮ ልቀሽ ብትደመጪ!
By @Lawyerly1
@getem
@getem
@paappii
በሌት አትምጪ እንደ ዘራፊ፤
እስኪነጋልን ልረፍ እረፊ፤
ቀኑን እንዳሻሽ ከቻልሽ ምጪ፤
ከኑሮ በላይ ለጆሮ ልቀሽ ብትደመጪ!
By @Lawyerly1
@getem
@getem
@paappii
❤38🤩10
( ስንትና ስንት ዓመት )
================
ከከፍታዬ ላይ ከፍቅሬ ሳልወርድ
ሌላ እቅፍ ሳያምረኝ
ሌላ አካል ሳል''ለምድ ...
ጨዋታሽን ሳልጠግብ
ሳቅሽ ሳይሰለቸኝ
ከአንቺ በቀር ያለው
ዓለም ሳይመቸኝ ....
ፍቅርን ከጀመርነው
እንዲያ እንደ ዘበት
ይኸው ተቆጠረ
ስንትና ስንት ዓመት !
አንቺ ውብ ጸሐዬ ...
" ወረት ይዞህ እንጂ
በጠዋቷ ሙቀት
ከርማ ስታቃጥል
አትደርስም ከቤቷ .. "
:
ሲሉ ያደከሙኝን
ምላሶች ታግሼ
በልቤ ዙፋን ላይ
አንቺን ብቻ አንግሼ ....
እጆችሽን ሳልለቅ
ከሰመረ ህይወት
ይኸው እንደዋዛ
ስንትና ስንት ዓመት !
@Kiyorna
@getem
@getem
@getem
================
ከከፍታዬ ላይ ከፍቅሬ ሳልወርድ
ሌላ እቅፍ ሳያምረኝ
ሌላ አካል ሳል''ለምድ ...
ጨዋታሽን ሳልጠግብ
ሳቅሽ ሳይሰለቸኝ
ከአንቺ በቀር ያለው
ዓለም ሳይመቸኝ ....
ፍቅርን ከጀመርነው
እንዲያ እንደ ዘበት
ይኸው ተቆጠረ
ስንትና ስንት ዓመት !
አንቺ ውብ ጸሐዬ ...
" ወረት ይዞህ እንጂ
በጠዋቷ ሙቀት
ከርማ ስታቃጥል
አትደርስም ከቤቷ .. "
:
ሲሉ ያደከሙኝን
ምላሶች ታግሼ
በልቤ ዙፋን ላይ
አንቺን ብቻ አንግሼ ....
እጆችሽን ሳልለቅ
ከሰመረ ህይወት
ይኸው እንደዋዛ
ስንትና ስንት ዓመት !
@Kiyorna
@getem
@getem
@getem
❤41😁2🤩2
በለጋ አዕምሯችን፣
የገባንን ፅፈን፤
ልክ ነው በማለት፣
ልክነትን አልፈን፤
ወራዜነት ቀጥፈን፤
እኛነትን ጥለን፣
እኔነትን ታቅፈን፤
በተናጠል ኖረን፤
አይገርምም?
ዛሬም ትክክል ነን፤
ወዶ አይተርቱ
"ሆድ ከሀገር ይሰፋል"
ለሆዱ ያደረም፣
ትውልድን ያጠፋል፤
ማንነት ለማወቅ፣
"ጠይቁ" የሚሉን፤
በኛ ሊከብሩ ነው፣
የሚነጣጥሉን፤
እነሱ
ሁሉም በፊናቸው፣
የሚሰብኩን እውነት፤
(ያው እውነት ከተባለ!)
የኔ ጥያቄ ግን፣
ምንድነው ማንነት?
እህት፣ ወንድምህ ላይ፣
መቀሰር ጣትህን?
(እንደዛ ከሆነ)
የዛሬ ስላቅህ
ነገ ተመልሶ፣
ይነካል ቤትህን፤
ሕመሜ ካስደሳ፣
ከበሮ ካስነሳ፣
ጎሽ፣ እሰይ፣ ለማለት፤
ከደጅህ ካራቀኝ፣
ክንድህ ካልጠበቀኝ፣
የቱ ጋር ነው እውነት?
ምንድነው ነው ልክነት?
የልጅነታችን፤
በሙሉ ልባችን፤
አድጎብን ማመኑ፣
ትተን መመርመሩን፤
ዛሬም ትክክል ነው፣
ሌሎች የሚነግሩን።
🖋ON
@getem
@getem
@getem
የገባንን ፅፈን፤
ልክ ነው በማለት፣
ልክነትን አልፈን፤
ወራዜነት ቀጥፈን፤
እኛነትን ጥለን፣
እኔነትን ታቅፈን፤
በተናጠል ኖረን፤
አይገርምም?
ዛሬም ትክክል ነን፤
ወዶ አይተርቱ
"ሆድ ከሀገር ይሰፋል"
ለሆዱ ያደረም፣
ትውልድን ያጠፋል፤
ማንነት ለማወቅ፣
"ጠይቁ" የሚሉን፤
በኛ ሊከብሩ ነው፣
የሚነጣጥሉን፤
እነሱ
ሁሉም በፊናቸው፣
የሚሰብኩን እውነት፤
(ያው እውነት ከተባለ!)
የኔ ጥያቄ ግን፣
ምንድነው ማንነት?
እህት፣ ወንድምህ ላይ፣
መቀሰር ጣትህን?
(እንደዛ ከሆነ)
የዛሬ ስላቅህ
ነገ ተመልሶ፣
ይነካል ቤትህን፤
ሕመሜ ካስደሳ፣
ከበሮ ካስነሳ፣
ጎሽ፣ እሰይ፣ ለማለት፤
ከደጅህ ካራቀኝ፣
ክንድህ ካልጠበቀኝ፣
የቱ ጋር ነው እውነት?
ምንድነው ነው ልክነት?
የልጅነታችን፤
በሙሉ ልባችን፤
አድጎብን ማመኑ፣
ትተን መመርመሩን፤
ዛሬም ትክክል ነው፣
ሌሎች የሚነግሩን።
🖋ON
@getem
@getem
@getem
❤29
ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ
ሳስታውሳት ስትረሳኝ
ኢትዬጵያ ወባ ሆናብኝ
ራሴ...ለአንገት ከብዳብኝ
ሀገር ጀርባዋን ስታሳየኝ
ስተን እንደ ሽታ
ወገን ሚባል ጠፋኝ ረግፎ በበሽታ
ሀገርማ
ጫንቃዋማ
ቆስሏል እንደ ንፍሮ
ሀገርማ ፊቷማ
ተቀባብቷል በፊልትሮ
ህዝብ ሚሉት እየሰመጠ
ጉድጓድ ደርሷል የግል ኑሮ
ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ
ሳስታውሳት ስትረሳኝ
እያደርኩ እየሞትኩኝ
ጥንብ አንሳ ላያነሳኝ
ሰው መሆንጥሎኝ
አውሬ ነው የሚያነሳኝ
ብቻ ጭዱ ያለቦታዋ
እኔን ማቀፍ ለምን ሻተች
ሀገር ታጥባ ወታ
በእኔ እቅፍ እየሸተተች
ለመሽተቴ አትፍረዱ
እንባዬ ነው የሚያወዛኝ
ሳቅ ባክህ አይባልም
ሀገር ሞቶበት ላለ ሀዛኝ
ሀገር ወባ ሆና
ስታንቀጠቅጠኝ በትኩሳት
መቼም ህመሜ ናት
አንዳንዴ አይነግሩትም
ህመምን ጠልተው አይጠሉትም
እያንቀጠቀጠችኝ
እያብረከረከችኝድ
በጭድ ቤቷ እየኮሰኮሰችኝ
ወባ ሆና እያመመችኝ
ትታ የማተወኝ
ትቼ የማልተዋት
ሀገር አለችኝ
By @geez_mulat
@getem
@getem
@getem
ሳስታውሳት ስትረሳኝ
ኢትዬጵያ ወባ ሆናብኝ
ራሴ...ለአንገት ከብዳብኝ
ሀገር ጀርባዋን ስታሳየኝ
ስተን እንደ ሽታ
ወገን ሚባል ጠፋኝ ረግፎ በበሽታ
ሀገርማ
ጫንቃዋማ
ቆስሏል እንደ ንፍሮ
ሀገርማ ፊቷማ
ተቀባብቷል በፊልትሮ
ህዝብ ሚሉት እየሰመጠ
ጉድጓድ ደርሷል የግል ኑሮ
ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ
ሳስታውሳት ስትረሳኝ
እያደርኩ እየሞትኩኝ
ጥንብ አንሳ ላያነሳኝ
ሰው መሆንጥሎኝ
አውሬ ነው የሚያነሳኝ
ብቻ ጭዱ ያለቦታዋ
እኔን ማቀፍ ለምን ሻተች
ሀገር ታጥባ ወታ
በእኔ እቅፍ እየሸተተች
ለመሽተቴ አትፍረዱ
እንባዬ ነው የሚያወዛኝ
ሳቅ ባክህ አይባልም
ሀገር ሞቶበት ላለ ሀዛኝ
ሀገር ወባ ሆና
ስታንቀጠቅጠኝ በትኩሳት
መቼም ህመሜ ናት
አንዳንዴ አይነግሩትም
ህመምን ጠልተው አይጠሉትም
እያንቀጠቀጠችኝ
እያብረከረከችኝድ
በጭድ ቤቷ እየኮሰኮሰችኝ
ወባ ሆና እያመመችኝ
ትታ የማተወኝ
ትቼ የማልተዋት
ሀገር አለችኝ
By @geez_mulat
@getem
@getem
@getem
❤39👍5🔥2
የሰካራሙ ፍልስፍና ✍️
እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል
እንደዚህ ይለዋል በሰካራም ድምጡ
በደልና መፅድቅ እንዲለዋወጡ...
እንዲህ ተናገረ...
" ሰማያት ያለኸው፣ እግዚያር ሆይ ጌታዬ
ሃሳብ ቢጤ ላንተ፣ በፊትህ ከታዬ
ምን መሰለህ እግዚያር...
በዚህኛው አለም በምንኖርባት፣
ሰዎች በተቃርኖ መርህ ይኖራሉ
ተው!...ስትል ጥሰው፣
አድርግ ያልካቸውን መቼ ያደርጋሉ?
እኔንም ተመልከት...
አትስከር ያልከውን፣ ትዛዝህን ልጥስ
ዘውትር እየጠጣው፣ ዘውትር ለምን ላልቅስ?
ስለዚህ እግዝያር
ለዚህ ተቃርኖ ዛር
አንድ መፍትሔ አለኝ...
አታድርግን ጓግተን ከምንላወሰው
ህግጋት ቀልብሰህ ብትቃረን ከሰው
እጥር ምጥን ያለች፣ ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?...
(ቤተ መቅደስ እንዳትመጡ
የወይን ጠጅ ሂዱ ጠጡ
ቅድስናን እንዳትኖሩ
በደል ብቻ ሂዱ ዝሩ)...
በዛች ትንሽ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?
እኔንም ተመልከት...
እዚህኛው ዓለም ላይ፣ ሰው ተቃርኖን ተግቶ ይከውናል
እንዳትመጡ ስላልክ
ፍቃድህን ልጥስ፣ ምናልባት መቅደስህ እመጣ ይሆናል።"
"
እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል።
ፈጥረህ ትንሽ ድግስ
አድርግን አታደርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ
¶
በደል አቅፎ እየኖረ፣ እንዲያ ያመካኛል
ሐጥያት መፅደቅ ቢሆን፣ እያለ ይመኛል።
ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
እንዲያ ብታደርግስ።
By ሰምረ የሽዋስ
@getem
@getem
@getem
እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል
እንደዚህ ይለዋል በሰካራም ድምጡ
በደልና መፅድቅ እንዲለዋወጡ...
እንዲህ ተናገረ...
" ሰማያት ያለኸው፣ እግዚያር ሆይ ጌታዬ
ሃሳብ ቢጤ ላንተ፣ በፊትህ ከታዬ
ምን መሰለህ እግዚያር...
በዚህኛው አለም በምንኖርባት፣
ሰዎች በተቃርኖ መርህ ይኖራሉ
ተው!...ስትል ጥሰው፣
አድርግ ያልካቸውን መቼ ያደርጋሉ?
እኔንም ተመልከት...
አትስከር ያልከውን፣ ትዛዝህን ልጥስ
ዘውትር እየጠጣው፣ ዘውትር ለምን ላልቅስ?
ስለዚህ እግዝያር
ለዚህ ተቃርኖ ዛር
አንድ መፍትሔ አለኝ...
አታድርግን ጓግተን ከምንላወሰው
ህግጋት ቀልብሰህ ብትቃረን ከሰው
እጥር ምጥን ያለች፣ ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?...
(ቤተ መቅደስ እንዳትመጡ
የወይን ጠጅ ሂዱ ጠጡ
ቅድስናን እንዳትኖሩ
በደል ብቻ ሂዱ ዝሩ)...
በዛች ትንሽ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?
እኔንም ተመልከት...
እዚህኛው ዓለም ላይ፣ ሰው ተቃርኖን ተግቶ ይከውናል
እንዳትመጡ ስላልክ
ፍቃድህን ልጥስ፣ ምናልባት መቅደስህ እመጣ ይሆናል።"
"
እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል።
ፈጥረህ ትንሽ ድግስ
አድርግን አታደርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ
¶
በደል አቅፎ እየኖረ፣ እንዲያ ያመካኛል
ሐጥያት መፅደቅ ቢሆን፣ እያለ ይመኛል።
ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
እንዲያ ብታደርግስ።
By ሰምረ የሽዋስ
@getem
@getem
@getem
❤23🔥13👍2🤩1