ግጥም ብቻ 📘
65.6K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ባልጀራዬ ላልኩት ሚስጥር ብዬ ብነግረዉ ፤

እሱም ለባልንጀራዉ አትንገር ብሎ ነገረዉ፤

ሲቀንስና ሲጨምር ለራሱ እንደተመቸዉ፤

ዞረ ዞረና ሚስጥሬ እኔ ጋር ደርሶ አረፈዉ።

[ ዔደን ታደሰ ]
@topazionnn
@getem
@getem
😁47👍3412🤩5😱1
             ናፍቆ....

ቦታ ምረጫ ትቶ ሲበላ ከኔውጋ
እረፍት አየነሳ አልተኛ እስኪነጋ
መባነን ልማዴ በሸለብታው መሀል
አምጣልኝ እያለ ናፍቆትሽ ይጮሀል
ሊያይሽ አስቦ በአካል እንድትመጪ
ቢጠራሽ ደመና ጋርዶሻል አትወጪ
ላላለቀው ፍቅር መለየት ለቀጣው
ተሸክሜ ምዞር ከልቤ አላጣው
ግር እንዳለኝ ግራው ለኔ አዘምብሎ
ከአይኔ ሲያውለው ያለፈውን ስሎ
አካላቴ ደክሞ አልታዘዝ ብሎ
የሚያረገው ጠፍቶት በትዝታ ዝሎ
ዛሬም ማዶ ያያል ፀሀይ ብትወጣ
ከተራበሽ ልቤ ይዛሽ እንድትመጣ...።

By #nimo

@getem
@getem
@getem
50👍10🔥3😢3
የፈገግታዬ ጦር
//////////////////
በጥርሴ የገደልኩት
የጠላት ጋጋታ፣
ሶምሶምን ያስንቃል
ቢወዳደር ላፍታ።
የወንጭፍ ውርወራ
የበትር ዱላቸው፣
የቃላት የስድብ
የንቀት ጦራቸው፣
የጠለፈኝ ገመድ
የነሱ እቅዳቸው።
የወደኩኝ ለታ
ያረፈብኝ ትቢያ፣
ቀና አልኩኝ ሲባል
ጠላቴ እንደ አጥቢያ።
ከከፍታ ቆሞ
ዝቅ ብሎ ቢያየኝ፣
በሳቄ ገደልኩት
ገና ቀና እንዳልኩኝ።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
46🔥14😁11👍5🤩1
እግዜር ስላንቺ ይፈራኛል


እክለፈለፋለሁ
የመልዓክት ስልኮች
ላንቺ ሲደውሉ
ይወስዱሻል ብዬ
እኔ ሳዋራቸው
ይኮላተፋሉ.....
ይርበተበታሉ....
የማፍቀሬን ስስት
ልኩንም ያውቃሉ

ተላኪ መልዓክት
ከወደቅሽባቸው
የህመም አልጋዎች
መጠው ቢፈልጉም
የቱ ጋር ነው የወደቅሽው
ከእኔ በቀር እንኳ
መልዓክትም አላወቁም

ደብቄሻለሁና
ከእግዜር ጋ አኩኩሉ
ሞትም እኔን ፈርቶ
እግዜሩን ይዋሻሉ

ቢዋሹም ስዋዋል
የሰማይን መሬት
ለእረፍትሽ እንዲሆን
ገነት ታንሳለች
የእቅፌን ሚዛን
የመዘንኩት እንደሆን

ጉሙን አጭጄው
ለወደቅሽበት ትራስ ለማድረግ
ደረት ላለው ልብ
ምን ይሰራል ከቶ ቁስን ማፈላለግ
.....ልክ እንደሰርግ

መልዓክት ይፈሩኛል
ሊጠሩሽ ሲመጡ ሰፈር ሲጠይቁ
የስስቴን መጠን
የማፍቀሬን መጠን
ልኩን ስለሚያውቁ

እግዜር ይፈራኛል
አንቺን በመውድ ውስጥ
እኔ እንዳልወሰድ
ታማ አልጋ ለተኛች
ፍቅረኛ ላለችው
ታስፈራለችና
ሞት የሚሏት መንገድ


ንዴቴ እጥፍ ነው
ያውቁታል ስስቴን
የመንሰፍሰፍ ጦሩ
ያልታዘዙትን ሟች
እንደሚያመጡ ሲያውቁ
መልዓክትም ፈሩ
ለምን...?
ስልኩን ሲደውሉ
አንቺን ጠራው ብለው
እኔን ስለሚጠሩ


ግዕዝ ሙላት
@GEEZ_MULAT

ስለ ሁለቱ የሞቱ ፍቅረኞች መታሰቢያ

@getem
@getem
@getem
34👍2👎2
በጅምር የቀረ
////////////////
ከትላንቷ ሚያርቅ
ከነገ ሚያግባባት፣
ከዝሙት አለሟ
አሽሽቶ ሚያርቃት።
ያቺ ዘማዊ ሴት
ትልቅ ግንብ ገነባች፣
ሰራችው ቆለለች
ከትላንት ራቀች፣
የሀጢያት ቡትቶን
አውልቃ እየጣለች።
ከዘመናት በኋላ
መኖርን ስትጀምር፣
ታሪኳን የሚያውቁ፣
የድንጋይዋን ክምር ይገፉባት ጀመር።
ወንጭፋቸው የእሳት
የጠጠር ግርፋት፣
የስሜት ልባቸው
ተመለሺ እያላት።
ሴትነቷ ጎልቶ
ሰውነት ተረስቶ፣
የዝሙት እጃቸው
ካብ ድንጋይ አንስቶ።
ደጋግመው ወገሯት
ደጋግመው ገፉባት ፣
የኔ ያለችው አጥር
እማይሆን ሆነባት፣

ትላንት ከሷ በራፍ
እንሙት እንዳላሏት፣
ትላንት ከሷ ገላ
አንውጣ እንዳላሏት፣
ስንት ቃል ውለታ
እንዋል እንዳላሏት።
በገንዘብ በቁጥር
የገዙትን ገላ፣
በዲናር የያዙት
የሴትነት ወዟ።
አውልቃው ብትወጣ
መኖር ልትጀምር፣
በግንቧ ፍርስራሽ
ከተቷት መቃብር።


@abela_black

@getem
@getem
@getem
48🔥26👍8🤩2
እሳት
/////////////////
እንደ ከሰል ፍሙ
ንዳድሽ ቃጠሎ፣
ባናገርሽኝ ቁጥር
ንዴቴ አይሎ፣
ጨጓራ ኩላሊት ምን የቀረሽ አለ
ባንቺ ውስጤ ተቃጥሎ።
ከፍምም ፍም አንቺ፣
ምታንገበግቢ የምታስደስቺ ።
ሙቀትሽ ሙቅ አይደል
በጣሙን ያነዳል፣
ማንስ አንቺን ችሎ
ሁሌ ይቃጠላል።

እኔ፣

አንቺን እያፈቀርኩ
ብታፈን ብቃጠል፣
እኔ እየቀለጥኩኝ
አረኩሽ ነበልባል።
ፍቅር ይሉት እሳት
አንቺ የሱ ትኩሳት፣
ንዳድ ከቃጠሎ
አርገውት ልቤን ቤት።
ምድጃ አካሌ ውስጥ
እሳት ሆነሽ አንቺ፣
ፍቅርሽ ውሃ አድርጎ
አዛመደኝ ካንቺ።
አቃጥይ አንድጂኝ
መላ አካሌ እስኪተን፣
የዘነብኩኝ ለታ
እንዳደርግሽ ሰከን።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
29🔥7👍1
ትንሽ ቦታ _
* * * * * * *

በዚህ ዓመት . . .
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ትንሽ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ብቻ መሰደጃ . . .
ምን-አለበት…?
ለምን-አልባት ብንተውለት…?

ፍጹም መሆን ስለማንችል…
ትንሽ ባዶ እንዋዋል
በልባችን ደግ በኩል
ለአንጎላችን መላወሻ - ትንሽ ቦታ እንተውለት
“ምን-አልባት” የምንልበት…!

ልክ እንደ አምና ለዚህ ዓመት
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሰር ይቅር ማያ
ይቅር ብንል መታሰሪያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ
ጥግ ድረስ የለም ስራ
ጥግ ድረስ የለም ፋታ
በልባችን ደግ በኩል
እንፈልግ ባዶ ቦታ
የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ
ለዘመን መለዋወጫ
* * * * * * * * * * * *

By ነቢይ መኮንን

@getem
@getem
@paappii
53👍11🔥7
.....

እኔ ለዚች ሀገር
   የማልጠቅም ዜጋ
ስራን የማልሰራ
    ውዬ ማድር በአልጋ፤
ሀገሬን መጉዳቱ
    ሁሌ ስላስጠላኝ
እንዲህ ለሚል ፀሎት
     የእግዜር ደጅ አስጠናኝ፤
'በማር ወተት አርጋ
   አሳድጋ አድርሳ
ዛሬ ፂም አብቅሎ
   ውለታን ለረሳ፣
ከሀዲ ነው እንጂ
  ሌላ ምን ይባላል
ድሮም ለሀገር ማይሆን
  ከዚህ ምን ይሰራል፤
እናም አምላኬ ሆይ
  የምኞቴን አይተህ
     ይቺን ከሰማከኝ፣
ትንሽ ትልቅ ሳልል
  ጠንክሬ እንድሰራ
    አሜሪካን ላከኝ'!

by ያቡ

@getem
@getem
@getem
😁7638🤩8👍3🔥1
ምርጫ
////////
ሺ ገዳይ ነሽ አሉ
ባንቺ የታለሉ፣
ካንቺ እየደረሱ
ስንቶች ስንቴ ማሉ።
እግዜር በእጁ ጭሯት
ተወርዋሪ ኮከብ፣
ጭራዋን አርዝማ
ምትዞር በወንዶች ልብ።
ዘብ አዳኝ በፍቅሯ
ስንቱ ከሷ ደርሶ ጠባቂ እየሆናት፣
አዲስ መጤ ነኝ ባይ
እንደቀልድ ቢመኛት፣
ዱላቸውን ቀማሽ
ሳይቀርብ ሳይጠጋት።

ውበትሽ ብርሀን
ጊዜ እንደሰማይ፣
ሆኖ ቢከተልሽ
ወንድ ሁሉ አገልጋይ።
ጭረሽ የፍቅር እሳት
አንቺ ተወርዋሪ፣
ከስንቱ ህይወት ውስጥ
ስትሰዋወሪ።
በምርጫ ተከበሽ
በዝቶ ፍላጎትሽ፣
ሳሩ ለምለም ገላሽ
ጤዛ ደግሞ ጊዜሽ።
በችኮላ ሄደው
በፍጥነት ቢበሩ፣
እኒያ አዳሞችሽ
ድንገት ተሰወሩ።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
27👍5
ሳይገጣጠሙ
----------------------

ምኞትና ክስተት
ሳይገጣጠሙ

መንገድ ላይ ተላልፈው
ህይወት ጠፋ ጣዕሙ

By Nibret teka

@getem
@getem
@getem
67👍11🔥5🎉3
ውብ የነበረች
የሸክላ ስኒ
የተሰበረች 
ወድቃ ከደጄ ፤
ሳያት ከውስጧ፡ ራሴን አይቼ
ባዝን ባነሳት ፡ ጠርዟ ቢላዋ
ቆርጣኝ በደሜ፡ ሟልጮ ገላዋ
ዳግም ወደቀች፡  ከጄ አምልጣኝ
እንኳን ወደቀች  ፡ እግዜር አወጣኝ።
እንኳን ሰበርኩት ፡ ስባሪ ጎኗን !
እንኳን አንስቼ ፡ ስጥል በድኗን
ተላለፈብኝ ፡ በእጄ ጥፋቷ
አባት ሆንኩለት ፡ ለየቲም ሞቷ።

አንዲት የሸክላ፡ ስኒ ተሰብራ
ወዟን አፍስሳ ፡ ላፈር ገብራ
ጣይዋ ሳይገኝ ፡ ባያት ተቀብራ
ገሏን አንስቼ ፡ ዳግም ስጥላት
ነበረች ተብሎ፡ ተለቀሰላት ፤
ትኩስ እንዲባል፡ ደረቅ አጽሟ
ምክንያት ተገኘሁ ፡ ቃኤል ወንድሟ
ከእንግዲህ ይረፍ ፡ጸጥ ይበል ደሟ።

ለየቅል አብረን ፡
አጉል ተሰብረን ፡
ገል ሆነን ኖረን ፡
ድንገት ተያይተን ፡
ለእቅፍ ጓጉተን ፡
ከወደቅንበት  ፡ ለመነሳሳት ፤
እጆቻችንን  ፡ ስንዘረጋጋ
በስባሪያችን  ፡ ብንወጋጋ ፤
ደም አስተያይተን  ፡ እንዳንላቀስ
በቁስሎቻችን  ፡ እንዳንካሰስ
ከጅ እንጣጣል ፡ እንከሳከስ
እንከሳከስ ፡ እስክንልም ድረስ
በሰባራችን ፡ እስካንታወስ ፤
ቅርፅ ቅጣችን  ፡ እስከሚረሳ 
ሞተን ፈራርሰን  ፡ እስክንነሳ

እንከሳከስ  ፤

ደቃቃ ሲሆን  ፡ ገላችን ብናኝ
ንፋስ አንስቶን ፡ ባየር ላይ ስንናኝ
አቧራ ሆነን  ፡ እንድንገናኝ።

By Rediet Aseffa

@getem
@getem
@paappii
34🔥8
በግና ቢላ
======

ይኸው ስንት ዘመን
ሞረዱ አልስል ብሎ
ብረት እያፋጨ
አራጅ ይታገላል ...

በቢላው መዶልዶም
እድሜው የበዛ በግ
በጭንቅ በሰቀቀን
ያው'ሳሩን ይበላል ..

እውነት አይካድም
አንዳንዴ ከህያው
ግዑዙ ይራራል !

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍2322🔥2
አልወስድሽም
///////////////
በጉልበት ፈጀሁት
ህዝበ አዳሙን ሁሉ፣
አላይም አልደርስም
አንቺ ዘንድ እስኪሉ።
ገንዘብ እንደ ቅጠል
ሚበቅል ይመስል፣
በስጦታ አንቺን
ቀን በቀን ስከልል።

ከአድማስ ወድያ
ከጀንበር ስር፣
ግዛት ቦታን ሳሰማምር፣

አበባ አንቺን የማይተኩ
ፅጌሬዶች ስደረድር።
ተራሮችን ስቀርፅልሽ፣
ያንቺን ውብ መልክ ላስይዝልሽ።
የዛፍን ቅርፅ ስቀይረው፣
ታላቅ ፍቅሬን እንዲገልፀው።
ዳመኖችን ስስልልሽ
እንድትወጂው ሳደርግልሽ፣
ከሰማይ ዳር ቀስቴን ይዤ
ደመና ላይ ሳሰፍርልሽ፣

አንቺ አላየሽ፣
ይህ ፍቅሬንም አላስተዋልሽ፣
ስጦታዬን አልተቀበልሽ፣
ግዛቴንም ከቶ አልፈለግሽ፣
እንዲሁ ብቻ ዝም ብለሽ
እኔን ጥለሽ መናኒ ሆንሽ።

ሁሉን ባደርግ ብሰጥሽም፣
አንቺን አንቺ ካደረገሽ
ከፈጣሪስ አልወስድሽም።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
43👍4
የነፍሴን ጫጫታ፤
የዉስጤን ግርታ፤

በቃላት ሰድሬ፤
ሐረግ አዋቅሬ፤

ሰ ር ዤ፤
ደ ል ዤ፤

ስሜቴን አርቅቄ፤
ሀሳቤን ጨምቄ፤


ጭንቀቴን ጠፍፌ፤
በወረቀት ፅፌ፤

ጨምድጄ፤
ቀድጄ፤

ክብሪቱን፤
ለኮስኩት፤

በእሳት፤
አ ነ ደ ድ ኩ ት፤

በአመድ በጭሱ፤
ህይወቴን አየሁት።

[ ዔደን ታደሰ ]

@topazionnn
@getem
@getem
29🔥22👍9
ቤተሰብ ሳልጦር
ፈርቼ እያደርኩ ኑሮን እንደጦር
እንኳን ለሌላው ሳልሆነ ለራሴ
ልክ እንደ ሙሴ
በምድረ በዳ
ነፍሴን ሳልሸክፍ ሳልሰናዳ
ባዲስ መቃብር ገላዬን ሳልከት
ዐይመጣም ቀኔ ነፍቶ መለከት
ብቁ መሆኔን ሳይመለከት።
መች እበቃለሁ?
ይህንን መኖር
እንደምሰፋው ጠንቅቄ አውቃለሁ።

ውጊያ ሳልገጥም ወይ ጦር ሳያምረኝ
በብርሃን ጣቶች ሳይመረምረኝ
ለምን አመጣኝ ምን ሊያስጀምረኝ?
በማያገባኝ ፍልሚያ ደክሜ
ያልቆሰልኩትን ህመም አክሜ
ድል ላላጣጥም
ሰው...
ተዋጋሁ አይልም ቀኑን ሳይገጥም።

በአንዳች አዚም ኮከብ ሳልገትር
ታምር ሳልሠራ በትንሽ በትር
ከሕይወት መዳፍ ሳላነብ እጣ
የኔውስ ነገ ባሻው ቀን ይምጣ!
ይመጣል ያሉት የታለ ታዲያ
አልጠብቀውም ከንግዲህ ወዲያ።

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
34👍3🔥2🎉1
~ቅፅበት~


ሩቅ ይመስላል እንጂ ጣሪያው ገመገሙ፤
የመሞት ሰመመን ቅርብ ነው ህመሙ፤

ስንዘር አትሄድም ከመኖር ለመውጣት፤
አንድ ክንድ አይርቅም መሞትን ለማምጣት፤

መኖር | አለመኖር
አለመኖር | መኖር

አሁን እያየሁት እየሳቀ ፊቱ፤
አሁን ዳመነና አለፈች ህይወቱ፤

አይቻታለሁኝ ትላንትና ወዲያ ገበያ ወጥታለች፤
ነፍስ ሩህ የላትም ዛሬ ግን ሞታለች፤

አሁን በቀደም'ለት ዘይሬው ነበረ፤
መገን የዱንያ ሰው ትላንት ተቀበረ፤

መኖር | አለመኖር
አለመኖር | መኖር

አቤት መልኳ ሲምር ስታሳሳ ብታይ፤
አሁን አፈር ለብሳ ሬሳ ሆነች ብካይ፤

ያ ጀግና ደንዳና ፈረጣማ ወጣቱ፤
ሞት ልግጠምህ ሲለው መች ቻለ ጉልበቱ፤

ሞሳ ህፃን ነበር ተስፋ የታጨቀ፤
የታዘዘም አይቀርም ህልሙን ተነጠቀ፤

መኖር | አለመኖር
አለመኖር | መኖር

አሁን ይሄን ስፅፍ በህይወት መኖሬ ባያጠያይቅም፣
አሁን ስታነቡት መኖሬን አላውቅም፤
ድንገት መጥቶ ጥርቅም!

By @Lawyerpoetry

@getem
@getem
@getem
48🔥9🤩2👍1😱1😢1
ስዕሉን አይለኩት
///////////////////
መመዘኛው መልኬ
ሚዛኑን ባይደፋም
የቁንጅናን መስፈርት
ከቶ ባላሟላም
የውስጤ ውብነት
ፊቴ ላይ ባይኖርም
ከነገሮች በፊት
እኔ ባልፈጠርኩት መልክ ብመዘንም
አለባበስ ጌጤ
ለእይታ ባይስቡም
ጎደለብኝ ብዬ
እራሴን አልጠላም
አለም ሸቀጥ አርጎት
መልኮች ቢመለኩም
በአካል ሙላት ጉድለት
ንግዱን ቢነግድም
የሰውነት ሚዛን
አይን ብቻ አይደለም
ሰውነት ለገባው
ማጣት ነው ማግኘት ነው
ብዙ ትርጉም አለው

እስኪ እናስበው

በብሩህ ሸራ ላይ
የሰአሊው ስዕል
ለእይታ ቀርቦ
በብዙ ሰው መሃል
ቢያዩት ጥበቡን
የሳለውን ስዕል
ከውዳሴ አንስቶ
በትችት ቢጥሉት
እነዚ ቃላቶች
ሰዓሊውን እንጂ ስዕሉን አይለኩት


@abela_black

@getem
@getem
@getem
38🔥8
ርእስ አጣን....

ዘማች ፈልገን ~ ቀምረን ደርሰን
ሆሄ ፊደላት ~ ቃላት አስሰን
እያሰባጠርን ~ እየፈጣጠርን
በስንኝ በአንጓ ~ አጥር እያጠርን......

   ሀሳቡን ጨምቀን ~ ቀርቦ ወረቀት
   በደማቅ ፅሁፍ ~ አስፍረንበት
   ብዙ ተጨንቀን ~ እንዴትም ብለን
   'በጎ' ን አንስተን ~ መጥፎውን ጥለን.....

ቤቱን መተነው ~ ፍሰቱ አምሮልን
ሁሉ መልክ ይዞ ~ ሁሉ ሰምሮልን.....
ግን፤
በእውቀት መጀነን ~ ጥበብ አሳጣን
ለግጥማችንም ~ ርእስ አጣን

By @Weyblann

@getem
@getem
@getem
37👍6🔥4
ተወለድ በልቤ
/////////////////
በእስራኤል መንደር
ሕዝብ ሁሉ ሲቆጠር፣
ክርስቶስን አቅፋ ዬሴፍ ወሰሎሜ
ሄዱ ከድንግል ጋር።
ፈጣሪ አለማት
ከሀጢያት መዝገብ ላይ
ስሜን ሊፍቅልኝ፣
እንደተወለደ፣
እኔን መፃፊያ ላይ
እሱ ተፃፈልኝ።
ግና ምንያረጋል፣
አመፀኛው ልቤ
ሄሮድስን ይመስል፣
ያሳድደው ጀመር
ፈጣሪ ነው ሳይል።
ክርስቶስ ሲያንኳኳ
ሲጠራኝ በስሜ፣
የማርያምን ብቅል
እየፈጨሁ መልሴ፣
አንድ አንዴም ጨክኖ
ስስታሙ ልቤ፣
ለአምላክ ቦታ ጠፍቶት
ይህ ነብሴን አስርቤ።
ልቤን ቢለምነኝ
እግዜር ይስጥልኝ አልኩ፣
ሰጪው እንዳይገባ
ስንቴ ተከላከልኩ፣
በልደቱ እለት፣
ባይገባኝም እንኳን እንዳላሸበሸብኩ፣
ነግቶ መሸ ሲባል
በሀጢያት ፍቅር ወደኩ።

ተወለድክ ይሉኛል
አዎን አምኛለው፣
የኔን መወለድ ግን እጠራጠራለው፣
ተወለድ ልቤ ውስጥ
ያንስሀል አውቃለው፣
ትሁቱ አምላኬ
ሰው ንቀህ ማተወው፣
ሳልከፍትልህ ግባ
ላይህ እወዳለው፣
ጥቂት እንኳን ሳልኖር
ሞቼ መምጣቴ ነው።


@abela_black

@getem
@getem
@getem
41

.
ልደትህን ሳስብ
            ሳነሳና ስጥል

በጥሞና ሆኜ
         ደግሞ  ሳሰላስል

ንጉሥ ሆነህ ሳለ....

በጠባብ ሰዉነት
            ከሰማይ መዉረድህ

ከበጎቹ ግርግም
        ወርደህ  መተኛትህ

ነገረ ልደትህ
     በታወሰኝ  ቁጥር

እኔን ይገርመኛል
     እጹብ ያስብለኛል

የዓለምን ደስታ
      ብስራትን  የሰሙ

እነዛን እረኞች
   መሆን   ያስመኘኛል።

✍️ዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
62🔥9👍2
የኤል ነገር ድንቁ
ስራው እንግዳ ነው ፡ ለሀሳብ መርቀቁ
እሳት ሆኖ ሳለ
በከብቶች እስትፋንስ ፡ በፍጡር መሞቁ

ለነፍሳችን መዳን ፡ እኛን ደጅ ጠና
ሰው ዝንጉ ነውና
እንደ ሰው ተማረ ፡ እንደ ሰው አጠና
ከሃሊ ነውና
ማዕበል አቆመ ፡ ውሃው ታዞ ፀና

እንደ በኒ አደም በጥቂቱ አደገ
እንደ አምላክነቱ . .
ከሞት ሰው አስነሳ ህይወቱን ታደገ

ለአንድ ምስኪን በጉ ከሰማይ ወረደ
ሊያስጠጋን ከክብሩ በእኛው ተዋረደ

ሰማይን አስፍቶ
ምድርን ያዋቀረ ለፍቅር ዝቅ አለ !
ሁሉን የሚችለው
እንደማይችል ሁሉ ወዶ ተሰቀለ
የኤልሻዳይ መዳፍ በችንካር ቆሰለ !

የማዕዘን ድንጋይ
የነቢያት ትንቢት መርስኤ-መከራ
ስትወለድ ጊዜ የፈራንው ፈራ

by @sidrak_the_poet

@getem
@getem
@getem
33🔥5🤩2👍1