ግጥም ብቻ 📘
65.6K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ጥበብ
//////////////////////////
የቆሰለች ጉድፍ ነብሴን፣
አውሬ የሆነች ማንነቴን።
አንቺ ቀርበሽ አላመድሻት፣
በመዳበስ ዝም አስባልሻት።
የኔ ሂሶጵ
ከጉድፌ ያነፃሽኝ፣
ዘማዊ ነህ
ብለሽ እንክዋን ያልገፋሽኝ፣
አንቺን ላጠምድ
ልሰርቅሽ ስል የሰረቅሽኝ፣
ሌባ ስሆን
ዘብ ጠባቂሽ ያደረግሽኝ፣
ከሺ እንዳልሄድኩ
ካንቺ እንዳልርቅ ያለገመድ የጠለፍሽኝ።
ቃልሽ አስማት
እጅሽ ደግሞ የአስማት በትር፣
ከነካሽኝ ተቀይሬ
ካንቺ ስር ነው እኔ ማድር።

ያንቺስ ይገርማል፣

ሰለሞንስ ያውቀው ይሆን
ይህን ጥበብ፣
በነካው ሰው
መጠበቅን ወይ መከበብ።
በታሪክስ ይኖር ይሆን
ቁርጥ አንቺን የመሰለ፣
ተቅበዝባዥን በማላመድ
ከቤቱ ስር ሰው ያዋለ።

እሷ
ያጠመደች እኔን አሳ፣
ያለመረብ በዳበሳ።
የያዘችኝ እኔን እሳት፣
ያለውሃ በእጅዋ ብልሃት።

እኔም ብሄድ ዞሬ ከስዋ፣
ይሄ ልቤ ፍቅር አይረሳ።

ማን አስተማራት ይህን ጥበብ፣
በዝምታ ዳብሳ
አገኘች የኔን ልብ፣
ማን አስተማራት?
ማን አስተማረሽ?
ማን?


@abela_black


@getem
@getem
@getem
29👍3🔥1
እኔ
ባይተዋር
የእፍታ ብናኝ
በየሄድኩበት ዕምባ ሚቀናኝ፤

በዬጥላው ስር የምሰባበር
ያለ በረሃ የማላውቅ ሀገር፤

ከቁር ከሐሩር የተወዳጀሁ
ገና ሽል ሳለሁ ኑሬ ያረጀሁ፤

ድስቴ
ምጣዴ ያልተሟሸልኝ ፤
ከማማጥ በቀር
ወልዶ መደሰት የማይኾንልኝ፤

-

እኔ
ባይተዋር
የዕጣ ፍርደኛ
ለጊዜ በደል የሌለኝ ዳኛ፤

የጊዜ ንጉስ
ያለገላጋይ የሚበድለኝ
ከማደግ በቀር ጥላት የሌለኝ፤

ልክ እንደ ብናኝ
ያነስኩ የሳሳሁ
ስበርር የምኖር እየተገፋሁ፤

ድንገት ተነስቶ ሰው የሚርበኝ
በየትከሻው ማልቀስ የሚያምረኝ፤

በየትከሻው ጎጆ የሰራሁ
ከሰው የምኖር ሰው እየፈራሁ፤

-

እኔ
ባይተዋር
የምርጫ ጌታ፤

ሀገሬ ማዶ
ከጉም ኮረብታ፤
ለብሶ የሚኖር የጭጋግ ኩታ፤

ዘሬ መከራ
አድባሬ ዋይታ
የማይሞላልኝ ሳስር ስፈታ ፤

አባቴ ለቅሶ
እናቴ ለቅሶ
ሕይወት ያቆመኝ ያለ ምሶሶ፤

ቢገልጡኝ ቁስል
ቢነኩኝ ቁስል
ቶሎ ሚደክመኝ ገና አረፍኩኝ ስል፤

-

እኔ
ባይተዋር
ፎካሪ ሽፍታ
ጫካ የማድር ድቤ ስመታ ፤

ሐዘኔን ትቼ የማልሰደድ
ያለ በረሃ ሀገር የማልለምድ ፤

እንጀራዬ ዕውር
ወጤ ደንቆሮ
ሳለቅስ የምውል ግዋሮ ለግዋሮ፤

እኔ
ባይተዋር
የድብርት ራት
ከወዳጅ በቀር የሌለኝ ጥላት።

By Tewodros kassa

@getem
@getem
@paappii
60😢16🔥9
'ደሀ አይደለሽም!'
~~~~~
ተወጣጠ
ርሽ አሉ
   ቆዳሽ እስኪጠብሽ
ተመፃደቅሽ አሉ
   መልክሽ እስኪበልጥሽ፤
ደግሞም ብለሽ ብለሽ
   ንቀት ጀመርሽ አሉ ትናንትን ረስተሽ፣
ዛሬን ብትጎብዢ
   በሰው 'ሰው' ብትሆኚ ሰውነትን ትተሽ!
~~~~
የሆነውስ ሆኖ
ወቃሽ ተቺሽ በዝቶ
    ብንጠላሽም እኛ፣
ማድረግሽ አይቀርም
  በገንዘብ በሀብትሽ
    እኛኑ ዘበኛ፤
እሱ አልበቃ ብሎም
  በአሽሙር በሀሜት
     ወጋ ቢያደርጉሽም፣
ይፈሩሻልና
  ፊትለፊትሽ መጥተው
    አይናገሩሽም.....






   ደሀ አይደለሽም!!!!!!!!

By @Weyblann    ያቡ

@getem
@getem
@getem
75🔥19👍12😢3😱1
(ምን መሰለሽ? )

ሌላን ሴት ጠይቀው
‘እሺ’ የተባሉ …
በርግጥ ለአንዲት ቀን
ፈክተው ይስቃሉ።

ሆኖም የገረመን

አንቺን ተለማምጠው
‘እንቢ’ ብለሽ እንኳን
ድግስ ደግሰዋል..
ዳስ ጥለዋል ድንኳን።

‘እርሷን ሞክሪያለሁ’
ብለው ስላወሩ
ስንቱን ሰው አየነው
ኮርተው ሲከበሩ።


(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@paappii
62😁25🔥13👍3🤩3🎉2
ዉርደት እና ኩነት

እንደአካሄዳቸው
በመንታ መንገድ ላይ
ፍቱን ታዳኝ ናቸው...
አንዱ በጋለው ናስ
ከሰል ይደርባል...
ሌላኛል ሲደላው...
ደርቦ ሲሞቀው
ውስጥ ውስጡን ይቀልጣል
ውጪው እንደከሰል
ጠቁሮ ሳያበቃ...
ከማገዶው ገደል...
ከፍሙ ስር ያድራል
ሊነቃ ይልና....
..................
በዘብ ጣሩ ዘልቆ
ፍሙ ለገረፈው...
አንድ ጥያቄ አለው...
..........................
ማጀት ባልጠፋበት
ምቾት ሀገር ሆኖ
ከተድላው ሰመመን
በደን ስንከራተት....
እሳቱ ሳይነካኝ ፍሙ ስር ተኝቼ
ባድር ምን አለበት??...

በኢያሱ ከበደ
ታህሳስ 7, 2018 ዓ.ም

@getem
@getem
@paappii
27🔥5👍1🤩1
ነጠብጣብ ሀሳቦች
(በእውቀቱ ስዩም)

በዘመን አየር ፤ ጫጫታው ከብሮ
በጩኸት መሀል፤ ዜማ ተቀብሮ
ጆሮ ግንባር ላይ፥ ቤቱን ለመስራት
እንዳልፈለገ
ወደ ማጅራት
አፈገፈገ::
****
የሞሰቡን ወግ፥ ፌስታሉ ወርሶት
ለምለሙ እንጀራ ፥ ረድኤት አንሶት
ቢጎርሱት እንባ ፥ ቢውጡት ብሶት !
****

ምንገዱ ሁሉ ፥የሚያሰናክል
ቁልቁለት ሲያዝል ፥ የዳገት ያክል
ስኬት በስኒ፥ ላባችን በጋን
በወግ ለመሞት ሁሌ እየተጋን
መኖር ዘነጋን::

By Bewuketu seyum

@getem
@getem
@paappii
75🔥6👍5🤩4
ባልጀራዬ ላልኩት ሚስጥር ብዬ ብነግረዉ ፤

እሱም ለባልንጀራዉ አትንገር ብሎ ነገረዉ፤

ሲቀንስና ሲጨምር ለራሱ እንደተመቸዉ፤

ዞረ ዞረና ሚስጥሬ እኔ ጋር ደርሶ አረፈዉ።

[ ዔደን ታደሰ ]
@topazionnn
@getem
@getem
😁47👍3412🤩5
             ናፍቆ....

ቦታ ምረጫ ትቶ ሲበላ ከኔውጋ
እረፍት አየነሳ አልተኛ እስኪነጋ
መባነን ልማዴ በሸለብታው መሀል
አምጣልኝ እያለ ናፍቆትሽ ይጮሀል
ሊያይሽ አስቦ በአካል እንድትመጪ
ቢጠራሽ ደመና ጋርዶሻል አትወጪ
ላላለቀው ፍቅር መለየት ለቀጣው
ተሸክሜ ምዞር ከልቤ አላጣው
ግር እንዳለኝ ግራው ለኔ አዘምብሎ
ከአይኔ ሲያውለው ያለፈውን ስሎ
አካላቴ ደክሞ አልታዘዝ ብሎ
የሚያረገው ጠፍቶት በትዝታ ዝሎ
ዛሬም ማዶ ያያል ፀሀይ ብትወጣ
ከተራበሽ ልቤ ይዛሽ እንድትመጣ...።

By #nimo

@getem
@getem
@getem
48👍10🔥3😢3
የፈገግታዬ ጦር
//////////////////
በጥርሴ የገደልኩት
የጠላት ጋጋታ፣
ሶምሶምን ያስንቃል
ቢወዳደር ላፍታ።
የወንጭፍ ውርወራ
የበትር ዱላቸው፣
የቃላት የስድብ
የንቀት ጦራቸው፣
የጠለፈኝ ገመድ
የነሱ እቅዳቸው።
የወደኩኝ ለታ
ያረፈብኝ ትቢያ፣
ቀና አልኩኝ ሲባል
ጠላቴ እንደ አጥቢያ።
ከከፍታ ቆሞ
ዝቅ ብሎ ቢያየኝ፣
በሳቄ ገደልኩት
ገና ቀና እንዳልኩኝ።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
45🔥14😁11👍5🤩1
እግዜር ስላንቺ ይፈራኛል


እክለፈለፋለሁ
የመልዓክት ስልኮች
ላንቺ ሲደውሉ
ይወስዱሻል ብዬ
እኔ ሳዋራቸው
ይኮላተፋሉ.....
ይርበተበታሉ....
የማፍቀሬን ስስት
ልኩንም ያውቃሉ

ተላኪ መልዓክት
ከወደቅሽባቸው
የህመም አልጋዎች
መጠው ቢፈልጉም
የቱ ጋር ነው የወደቅሽው
ከእኔ በቀር እንኳ
መልዓክትም አላወቁም

ደብቄሻለሁና
ከእግዜር ጋ አኩኩሉ
ሞትም እኔን ፈርቶ
እግዜሩን ይዋሻሉ

ቢዋሹም ስዋዋል
የሰማይን መሬት
ለእረፍትሽ እንዲሆን
ገነት ታንሳለች
የእቅፌን ሚዛን
የመዘንኩት እንደሆን

ጉሙን አጭጄው
ለወደቅሽበት ትራስ ለማድረግ
ደረት ላለው ልብ
ምን ይሰራል ከቶ ቁስን ማፈላለግ
.....ልክ እንደሰርግ

መልዓክት ይፈሩኛል
ሊጠሩሽ ሲመጡ ሰፈር ሲጠይቁ
የስስቴን መጠን
የማፍቀሬን መጠን
ልኩን ስለሚያውቁ

እግዜር ይፈራኛል
አንቺን በመውድ ውስጥ
እኔ እንዳልወሰድ
ታማ አልጋ ለተኛች
ፍቅረኛ ላለችው
ታስፈራለችና
ሞት የሚሏት መንገድ


ንዴቴ እጥፍ ነው
ያውቁታል ስስቴን
የመንሰፍሰፍ ጦሩ
ያልታዘዙትን ሟች
እንደሚያመጡ ሲያውቁ
መልዓክትም ፈሩ
ለምን...?
ስልኩን ሲደውሉ
አንቺን ጠራው ብለው
እኔን ስለሚጠሩ


ግዕዝ ሙላት
@GEEZ_MULAT

ስለ ሁለቱ የሞቱ ፍቅረኞች መታሰቢያ

@getem
@getem
@getem
32👍2👎2
በጅምር የቀረ
////////////////
ከትላንቷ ሚያርቅ
ከነገ ሚያግባባት፣
ከዝሙት አለሟ
አሽሽቶ ሚያርቃት።
ያቺ ዘማዊ ሴት
ትልቅ ግንብ ገነባች፣
ሰራችው ቆለለች
ከትላንት ራቀች፣
የሀጢያት ቡትቶን
አውልቃ እየጣለች።
ከዘመናት በኋላ
መኖርን ስትጀምር፣
ታሪኳን የሚያውቁ፣
የድንጋይዋን ክምር ይገፉባት ጀመር።
ወንጭፋቸው የእሳት
የጠጠር ግርፋት፣
የስሜት ልባቸው
ተመለሺ እያላት።
ሴትነቷ ጎልቶ
ሰውነት ተረስቶ፣
የዝሙት እጃቸው
ካብ ድንጋይ አንስቶ።
ደጋግመው ወገሯት
ደጋግመው ገፉባት ፣
የኔ ያለችው አጥር
እማይሆን ሆነባት፣

ትላንት ከሷ በራፍ
እንሙት እንዳላሏት፣
ትላንት ከሷ ገላ
አንውጣ እንዳላሏት፣
ስንት ቃል ውለታ
እንዋል እንዳላሏት።
በገንዘብ በቁጥር
የገዙትን ገላ፣
በዲናር የያዙት
የሴትነት ወዟ።
አውልቃው ብትወጣ
መኖር ልትጀምር፣
በግንቧ ፍርስራሽ
ከተቷት መቃብር።


@abela_black

@getem
@getem
@getem
47🔥24👍8🤩2
እሳት
/////////////////
እንደ ከሰል ፍሙ
ንዳድሽ ቃጠሎ፣
ባናገርሽኝ ቁጥር
ንዴቴ አይሎ፣
ጨጓራ ኩላሊት ምን የቀረሽ አለ
ባንቺ ውስጤ ተቃጥሎ።
ከፍምም ፍም አንቺ፣
ምታንገበግቢ የምታስደስቺ ።
ሙቀትሽ ሙቅ አይደል
በጣሙን ያነዳል፣
ማንስ አንቺን ችሎ
ሁሌ ይቃጠላል።

እኔ፣

አንቺን እያፈቀርኩ
ብታፈን ብቃጠል፣
እኔ እየቀለጥኩኝ
አረኩሽ ነበልባል።
ፍቅር ይሉት እሳት
አንቺ የሱ ትኩሳት፣
ንዳድ ከቃጠሎ
አርገውት ልቤን ቤት።
ምድጃ አካሌ ውስጥ
እሳት ሆነሽ አንቺ፣
ፍቅርሽ ውሃ አድርጎ
አዛመደኝ ካንቺ።
አቃጥይ አንድጂኝ
መላ አካሌ እስኪተን፣
የዘነብኩኝ ለታ
እንዳደርግሽ ሰከን።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
29🔥7👍1
ትንሽ ቦታ _
* * * * * * *

በዚህ ዓመት . . .
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ትንሽ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ብቻ መሰደጃ . . .
ምን-አለበት…?
ለምን-አልባት ብንተውለት…?

ፍጹም መሆን ስለማንችል…
ትንሽ ባዶ እንዋዋል
በልባችን ደግ በኩል
ለአንጎላችን መላወሻ - ትንሽ ቦታ እንተውለት
“ምን-አልባት” የምንልበት…!

ልክ እንደ አምና ለዚህ ዓመት
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሰር ይቅር ማያ
ይቅር ብንል መታሰሪያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ
ጥግ ድረስ የለም ስራ
ጥግ ድረስ የለም ፋታ
በልባችን ደግ በኩል
እንፈልግ ባዶ ቦታ
የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ
ለዘመን መለዋወጫ
* * * * * * * * * * * *

By ነቢይ መኮንን

@getem
@getem
@paappii
53👍11🔥6
.....

እኔ ለዚች ሀገር
   የማልጠቅም ዜጋ
ስራን የማልሰራ
    ውዬ ማድር በአልጋ፤
ሀገሬን መጉዳቱ
    ሁሌ ስላስጠላኝ
እንዲህ ለሚል ፀሎት
     የእግዜር ደጅ አስጠናኝ፤
'በማር ወተት አርጋ
   አሳድጋ አድርሳ
ዛሬ ፂም አብቅሎ
   ውለታን ለረሳ፣
ከሀዲ ነው እንጂ
  ሌላ ምን ይባላል
ድሮም ለሀገር ማይሆን
  ከዚህ ምን ይሰራል፤
እናም አምላኬ ሆይ
  የምኞቴን አይተህ
     ይቺን ከሰማከኝ፣
ትንሽ ትልቅ ሳልል
  ጠንክሬ እንድሰራ
    አሜሪካን ላከኝ'!

by ያቡ

@getem
@getem
@getem
😁7334🤩7👍3🔥1
ምርጫ
////////
ሺ ገዳይ ነሽ አሉ
ባንቺ የታለሉ፣
ካንቺ እየደረሱ
ስንቶች ስንቴ ማሉ።
እግዜር በእጁ ጭሯት
ተወርዋሪ ኮከብ፣
ጭራዋን አርዝማ
ምትዞር በወንዶች ልብ።
ዘብ አዳኝ በፍቅሯ
ስንቱ ከሷ ደርሶ ጠባቂ እየሆናት፣
አዲስ መጤ ነኝ ባይ
እንደቀልድ ቢመኛት፣
ዱላቸውን ቀማሽ
ሳይቀርብ ሳይጠጋት።

ውበትሽ ብርሀን
ጊዜ እንደሰማይ፣
ሆኖ ቢከተልሽ
ወንድ ሁሉ አገልጋይ።
ጭረሽ የፍቅር እሳት
አንቺ ተወርዋሪ፣
ከስንቱ ህይወት ውስጥ
ስትሰዋወሪ።
በምርጫ ተከበሽ
በዝቶ ፍላጎትሽ፣
ሳሩ ለምለም ገላሽ
ጤዛ ደግሞ ጊዜሽ።
በችኮላ ሄደው
በፍጥነት ቢበሩ፣
እኒያ አዳሞችሽ
ድንገት ተሰወሩ።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
26👍5
ሳይገጣጠሙ
----------------------

ምኞትና ክስተት
ሳይገጣጠሙ

መንገድ ላይ ተላልፈው
ህይወት ጠፋ ጣዕሙ

By Nibret teka

@getem
@getem
@getem
66👍11🔥5🎉3
ውብ የነበረች
የሸክላ ስኒ
የተሰበረች 
ወድቃ ከደጄ ፤
ሳያት ከውስጧ፡ ራሴን አይቼ
ባዝን ባነሳት ፡ ጠርዟ ቢላዋ
ቆርጣኝ በደሜ፡ ሟልጮ ገላዋ
ዳግም ወደቀች፡  ከጄ አምልጣኝ
እንኳን ወደቀች  ፡ እግዜር አወጣኝ።
እንኳን ሰበርኩት ፡ ስባሪ ጎኗን !
እንኳን አንስቼ ፡ ስጥል በድኗን
ተላለፈብኝ ፡ በእጄ ጥፋቷ
አባት ሆንኩለት ፡ ለየቲም ሞቷ።

አንዲት የሸክላ፡ ስኒ ተሰብራ
ወዟን አፍስሳ ፡ ላፈር ገብራ
ጣይዋ ሳይገኝ ፡ ባያት ተቀብራ
ገሏን አንስቼ ፡ ዳግም ስጥላት
ነበረች ተብሎ፡ ተለቀሰላት ፤
ትኩስ እንዲባል፡ ደረቅ አጽሟ
ምክንያት ተገኘሁ ፡ ቃኤል ወንድሟ
ከእንግዲህ ይረፍ ፡ጸጥ ይበል ደሟ።

ለየቅል አብረን ፡
አጉል ተሰብረን ፡
ገል ሆነን ኖረን ፡
ድንገት ተያይተን ፡
ለእቅፍ ጓጉተን ፡
ከወደቅንበት  ፡ ለመነሳሳት ፤
እጆቻችንን  ፡ ስንዘረጋጋ
በስባሪያችን  ፡ ብንወጋጋ ፤
ደም አስተያይተን  ፡ እንዳንላቀስ
በቁስሎቻችን  ፡ እንዳንካሰስ
ከጅ እንጣጣል ፡ እንከሳከስ
እንከሳከስ ፡ እስክንልም ድረስ
በሰባራችን ፡ እስካንታወስ ፤
ቅርፅ ቅጣችን  ፡ እስከሚረሳ 
ሞተን ፈራርሰን  ፡ እስክንነሳ

እንከሳከስ  ፤

ደቃቃ ሲሆን  ፡ ገላችን ብናኝ
ንፋስ አንስቶን ፡ ባየር ላይ ስንናኝ
አቧራ ሆነን  ፡ እንድንገናኝ።

By Rediet Aseffa

@getem
@getem
@paappii
33🔥8
በግና ቢላ
======

ይኸው ስንት ዘመን
ሞረዱ አልስል ብሎ
ብረት እያፋጨ
አራጅ ይታገላል ...

በቢላው መዶልዶም
እድሜው የበዛ በግ
በጭንቅ በሰቀቀን
ያው'ሳሩን ይበላል ..

እውነት አይካድም
አንዳንዴ ከህያው
ግዑዙ ይራራል !

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍2120🔥2
አልወስድሽም
///////////////
በጉልበት ፈጀሁት
ህዝበ አዳሙን ሁሉ፣
አላይም አልደርስም
አንቺ ዘንድ እስኪሉ።
ገንዘብ እንደ ቅጠል
ሚበቅል ይመስል፣
በስጦታ አንቺን
ቀን በቀን ስከልል።

ከአድማስ ወድያ
ከጀንበር ስር፣
ግዛት ቦታን ሳሰማምር፣

አበባ አንቺን የማይተኩ
ፅጌሬዶች ስደረድር።
ተራሮችን ስቀርፅልሽ፣
ያንቺን ውብ መልክ ላስይዝልሽ።
የዛፍን ቅርፅ ስቀይረው፣
ታላቅ ፍቅሬን እንዲገልፀው።
ዳመኖችን ስስልልሽ
እንድትወጂው ሳደርግልሽ፣
ከሰማይ ዳር ቀስቴን ይዤ
ደመና ላይ ሳሰፍርልሽ፣

አንቺ አላየሽ፣
ይህ ፍቅሬንም አላስተዋልሽ፣
ስጦታዬን አልተቀበልሽ፣
ግዛቴንም ከቶ አልፈለግሽ፣
እንዲሁ ብቻ ዝም ብለሽ
እኔን ጥለሽ መናኒ ሆንሽ።

ሁሉን ባደርግ ብሰጥሽም፣
አንቺን አንቺ ካደረገሽ
ከፈጣሪስ አልወስድሽም።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
41👍4
የነፍሴን ጫጫታ፤
የዉስጤን ግርታ፤

በቃላት ሰድሬ፤
ሐረግ አዋቅሬ፤

ሰ ር ዤ፤
ደ ል ዤ፤

ስሜቴን አርቅቄ፤
ሀሳቤን ጨምቄ፤


ጭንቀቴን ጠፍፌ፤
በወረቀት ፅፌ፤

ጨምድጄ፤
ቀድጄ፤

ክብሪቱን፤
ለኮስኩት፤

በእሳት፤
አ ነ ደ ድ ኩ ት፤

በአመድ በጭሱ፤
ህይወቴን አየሁት።

[ ዔደን ታደሰ ]

@topazionnn
@getem
@getem
27🔥21👍8
ቤተሰብ ሳልጦር
ፈርቼ እያደርኩ ኑሮን እንደጦር
እንኳን ለሌላው ሳልሆነ ለራሴ
ልክ እንደ ሙሴ
በምድረ በዳ
ነፍሴን ሳልሸክፍ ሳልሰናዳ
ባዲስ መቃብር ገላዬን ሳልከት
ዐይመጣም ቀኔ ነፍቶ መለከት
ብቁ መሆኔን ሳይመለከት።
መች እበቃለሁ?
ይህንን መኖር
እንደምሰፋው ጠንቅቄ አውቃለሁ።

ውጊያ ሳልገጥም ወይ ጦር ሳያምረኝ
በብርሃን ጣቶች ሳይመረምረኝ
ለምን አመጣኝ ምን ሊያስጀምረኝ?
በማያገባኝ ፍልሚያ ደክሜ
ያልቆሰልኩትን ህመም አክሜ
ድል ላላጣጥም
ሰው...
ተዋጋሁ አይልም ቀኑን ሳይገጥም።

በአንዳች አዚም ኮከብ ሳልገትር
ታምር ሳልሠራ በትንሽ በትር
ከሕይወት መዳፍ ሳላነብ እጣ
የኔውስ ነገ ባሻው ቀን ይምጣ!
ይመጣል ያሉት የታለ ታዲያ
አልጠብቀውም ከንግዲህ ወዲያ።

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
26👍3🔥2🎉1