ግጥም ብቻ 📘
65.7K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram

    የአብስራ ሳሙኤል
         ⁂

ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ
ማለፊያ ምግባር ምን ሰራህ
በኖርክባት ስንዝር እድሜ
ምን'ን ዘርተህ ምን አፈራህ

እንዴያው ሲያስበው ይጨንቀኛል
ነፍሴን እንዳል'ጥላት እፈራለሁ
ፈራሽ ገላ ተጫምቼ
ስንት ዘመን እኖራለሁ

የእንባ ብዕር ከሚጠቀስበት
መዝገብ እንዳላሰፍር
መሾ ከሚወርድበት
ክብሬን እንዳላሳፍር

ለመንግስትህ እጨኝ ባልልም
ከመከራው ጠብቀኝ
የኔ እውቀት አያድነኝም
መልካሙን አንተ አሳውቀኝ

ለማትሞላ ጎደሎ ምድር
ህልም ነው ወዳልከው ስትለፋ
ተስፋ ነው ወዳልከው ስትገፋ
ማረፍ አይቀርምና ታርፋለህ
መሞት አይቀርምና ትሞታለህ

ማለፊያ ምግባር የሚሆን
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ

የበገና ክር መወጠር
ለዜማው መጣም ነው'ና
ምስገና መባ እንዲሆን
የህይወትህ ጥኡም ቃና

ለመንግስትህ እጨን ባንልም
ከመከራው አንተ ጠብቀን
የ'ኛ እውቀት አያድነንም
መልካሙን አንተ አሳውቀን

        ⁂
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ ?


@getem
@getem
@getem
53🔥3🤩1
"ባሏን በሞት ያጣች ሴት ደብዳቤ"
.
ከገነት ላለኸዉ
.
የ'ግር እሳት ሆኖ ቢገርፈኝ መለየት ፍም እሳቱ፤
ልቤን አቀጣጠላት የናፍቆትህ ስር ግለቱ፤

በዛች የቀን ጎዶሎ ጥቁር ሞት አንተን ሲጠራ፤
እኔንም ጠርቶኝ በነበር ብጓዝ ከፍቅሬ ጋራ፤

ካንተ መራቅ አይሆንልኝ፤
ሌጣ ሆኜ አያምርብኝ፤

ዘወትር..መቃብርህን አቅፌ ስስም 'ዉላለሁ፤
ነጋ ጠባ..ስምህን ስደጋግም አድራለሁ፤

ያዩኝ በሙሉ.........

አበደች እያሉ ሲያሸሙሩብኝ፤
ከመቃብር አድራ ተለከፈች ሲሉኝ፤

መች ጆሮ ሰጠሁኝ መች አዳመጥኳቸዉ፤
ሞቷል እርሽዉ ሲሉኝ ላይኔ ጠላኋቸዉ፤

አይገባቸዉማ..........

በድኔን አስቀርታኝ መከረኚት ልቤ፤
አብራህ እንደሄደች አያዉቁም አሳቤ፤

ነፍሴ ከነፍስህ ጋር እንደተሳሰረች፤
ዳግም ላትነጠል እንደተጋመደች፤

ከጎኔ ባለገኝህም አይዞሽ ባትለኝ አንዴ፤
ጠረንህ ቢናፍቀኝም ባታባብለኝ ዉዴ፤

መቼም ላይጠፋ ከእኔነቴ፤
ዛሬም ህያዉ ነው ፍቅርህ ናፍቆቴ።

በዔደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn

@getem
@getem
28😢11🤩2👎1
መኖሬ ከሆነ


እግሬ እንዳይራመድ
ልቤ ሲያጠምድ ወጥመድ

ልርቅ ስል ከሁሉ
ሲቀርቡኝ በሙሉ
አሉልኝ ያልኩኝ ለት
ብትንትን ሲሉ

በቅፅበት ደስታ
ስረሳው ሀዘኔን
ትንሽ ፈገግ አልኩኝ
ላነባው ዘመኔን

ወይ አለምን ንቄ
አልመነንኩ ከደብሩ
ወይ አልተሳካልኝ
አልተመቸኝ ምድሩ

መኖሬ ከሆነ ይቅርብኝ
ግድየለም ውሰደኝ እግዜሩ ።

By ኢዮብ_ዮሚን

@getem
@getem
@paappii
52😢7🤩1
ጥራታቸውን የጠበቁ የአውሮፓ ቦንዳ አልባሳት እና ጫማዎች መሸጫ 👌👏

አድራሻ 24 ሲድራ ሆቴል ጀርባ ወደ 40/60 መግቢያ 20 ሜትር

🤳 0913803516
7🔥3👍1
" አሜን"
          ( ግዮናይ ነኝ)!፧
አንቺ ጋር ለመኖር...
ሺ ቁልቁል ወርጄ  ብዙ ዳገት ወጣሁ፣
ዳኛ ሳይፈርድብኝ...
እንደ ወንጀለኛ    በኑሮ ተቀጣሁ፣
ያ'ርባ ቀን ዕድሌን  እጣ ፈንቴን አጣሁ።
  *                  *                  *
ህይወትን ተራብኩኝ...
እንጃ ስለ ፍቅር   ጥላቻን ተጠማሁ፣
ይኸው ደሞ ዛሬ...
እንለያይ የሚል   ካ'ንደበትሽ ሰማሁ።
አሜን ያደርግልኝ...
እዛ ማዶ ልጓዝ   ፍቅርሽን አልፌ፣
(አልጋዬ የት ነበር?)...
እስኪ ጋደም ልበል  ናፍቆኛል እንቅልፌ።
   *                  *                  *
ሰውነቴ ሁሉ...
እንደ ብሉይ ኃጢያት  ለምጻም ሰው መሰለ፣
ፈጣሪ ያውቀኛል...
ህይወቴ ላ'ንቺነት   ብዙ እንደ ቆሰለ።
ልሽሽ ካለሽበት...
ምድር እስከምታልቅ  በሌትና ቀትር፣
ባህር እንኳን ባገኝ...
ሙሴ ይሰጠኛል   የመክፈያ በትር።

@getem
@getem
@paappii
34👍2🔥2🤩2
ድክም ብል በሂወት መንገድ
እግሬ ቢዝል ብሰናከል
ቆፈን ብለብስ ለገላዬ 
ቁራሽ ዳቦ ብከለከል
ቀን ቢገፋኝ ካለሁበት
ከከፍታ ብወረወር
"አትመጥንም" ብባል በአፍ
ከአመት አመት በቀን በወር
አይኔ ደምን ሰርክ ቢያነባ
እቅድ ግቤ ቢፋለስም
ዳና ትግሌን አደብዝዘው
ያለ ስሜ ቢሰጡኝ ስም

አትጨናነቂ
ዝምብለሽ ሳቂ!

አታውቂምና ነው!
ቀን የገፋውን ሰው ቀን እንደሚያነሳው
ፈጣሪ ላልከዳው እሱ እንደማይረሳው

አታውቂምና ነው!
ዝቅ ያለ ሰው ሁሉ ከፍታ እንደሚያገኝ
ማርያም
ማርያም ላለ ፈጣሪ እንደሚገኝ

አታውቂምና ነው!

ሞን ያስለቅስሻል ለምን ትጨነቂ
ሁሉ በርሱ ይሆናል ዝም ብለሽ ሳቂ
ቀን ሳይገፋ አያልፍም ቀን
አልፈጠረብሽም ምንድነው ሰቀቀን

ለኔ ብለሽ አትድከሚ
አይብረድሽ ፍርሃት ቁር
ጊዜ አይፈጅም ለመልስማ
ካምላክ ሄጄ ብቆረቁር

አትጨናነቂ
ዝም ብለሽ ሳቂ!

ተስፋ መቁረጥ አይነበብ ካካል ገፅሽ ከመልክሽ ላይ
ሀይል ብርታቴ ይጨምራል የፊትሽን ፈገግታ ሳይ።
አንዲት ቅንጣት እንባ እንዳላይ ተደርድሮ ከጉንጭሽ ስር
ቀን እንደሆን አመሏ ነው ልታነሳ ምትሰረስር።

አትጨናነቂ
ዝም ብለሽ ሳቂ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
40👍5🔥1🎉1
የሚጠቅመኝን ፥ አልወደድኩትም
አልጠቀመኝም ፥ የወደድኩትም ።

ከማን ጋር ልሁን ?
ከምወደው ? ወይስ ... ከሚጠቅመኝ ጋር ?
ተንገዳገድኩኝ ፥ በጭንቀት ስካር !

የቱን ላስቀድም ? የቱ ይበልጣል ?
የቱ ያከስራል ? የቱ ያወጣል ?
እንዴት የሰው ልጅ
ምርጫ ተሰጥቶት ፥ ነጻነት ያጣል ?

ፈጣሪ ራሱ
ከዚህም ከዚያም እያማረጠኝ
መሐል መንገድ ላይ ከሚያፋጥጠኝ
ምናል ከሁሉም ፥ ሁሉን ቢሰጠኝ ?!

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
68👍13😁7🔥3🤩2😱1
በምድር ፍትህ የለም
      .........................
ለእውነት የሚቆም ራሱን የካደ
ከራሱ አስበልጦ አምሳሉን የወደደ
የአዳም ዘር ሆኖ በምድር ስለሌለ
ፍትህ በቃል ብቻ ተመዝግቦ ዋለ::
              ፠፠፠፠
ባለንባት አለም የኔም ያንተም ጠባይ
ለምድር ይቅርና ያስፈራል ለሰማይ::
እናም!... . 
      ፍትህ ለእገሊት!
ፍትህ ለእገሌ!
     ፍትህ.......ፍትህ......!
ፍትህ........!
እያሉ መጮህ አንዳችም አይሰራም
እንኳንስ ለሰው ልጅ
ምንኖርባት ምድር ለንጉስ አትራራም፡፡

By @Abuugida

@getem
@getem
@paappii
49😢14👍6🔥4
ጨዋታዉ ፈረሰ
.
.
ልጅነቴ ልጅነትህን፤
       ለጋነትህ ጮርቃነቴን፤
በትዝታ እየቃኘሁ፤
        ሳቃችንን እየሰማሁ፤
በትዉስታ ምልሰት፤
       በጥሞና ስመለከት።
በድንጋይ ከታትፈን፤
           ማባያ ጨምረን፤
መረቁን ከልሰን፤
          የሰራነዉ ጎመን።
ለሚመጣዉ ዘመን፤
          የእቃቃ ሰርጋችን፤
ሚዜ ስናዘጋጅ ፤
         መኖርን ስንዋጅ፤
ወረቀት ቀዳደን፤
            ቦጭቀን፤ 
ቦጫጭቀን፤
           እየጎዘጎዝን፤
ሰፈር ስናበላሽ፤
       መንደር ስናቆሽሽ፤
ቡና አፍልተን፤
        ቁርሱን በልተን፤
ደግሞ ስንጣላ፤
        ይጠፋናል መላ፤
ኩርኩም ስንቃመስ፤
          ጮኸን ስንዋቀስ፤
መተቃቀፍ በማግስቱ፤
         መንከባለል በክረምቱ፤
ስንቱ አለፈ በጊዜያቱ።
              የእቃቃ ቤታችን፤
ያለምነዉ ኑሯችን፤
          ጨዋታዉ ፈረሰ፤
ዳቦዉ ተቆረሰ።

በዔደን
ታደሰ
@topazionnn

@getem
@getem
63👍4🔥4

[የውሃ ውርደቱ — የዥረት ቅሌቱ......
«መመለሱ ላይቀር ጎብጦ መደፋቱ ፤
"ፋውንቴን ነህ" ተብሎ ወደ ላይ መውጣቱ ።» ]



እኔ ገራም የምንጭ ውሃ .....
ኩልል ያልኩኝ ድምጽ አልባ “ማይ” ፤
ተራራ ላይ የቆምሽውን ክንፋም ውበት
በሩቅ የማይ ።

ክብርስ ለእኔ መውረድ ነው
መፍሰስ ቁልቁል በመሬት ፣
አንቺ ደግሞ ከከፍታው
በክንፍሽ አቅም መቆዬት ።

እንዳይሆን አርጎታል መቼም
ተፈጥሮ ነው እንቆቅልሽ ፤
እንዳንቺ ወደ ደመና
ከፍ ማለት ምን አውቅልሽ?!
ዥረት ነኝ እንዳ
ኗኗሬ
"ውረጅ እንውረድ" ነው
ምልሽ ።



መቼም ኗሪ ዝም አያውቅም ....
ይበልሽ ያሻውን ይፍረድ ፣
ዝቅ በይ “ውረጅ እንውረድ” ።



እንደዚህ ነግሬሽ እንጂ
መሪር ሀቁን አሳውቄ ፤
ውሃ ብሆን (እንዳመሌ)
አልወስድሽም አሳስቄ ።



ውብዬ ...
(ወደድኩም ብዬ.....)
ወዳ
ንቺ ሽቅብ ለመውጣት
ብሞክር እንኳን አልደርስም ፤
ተፈጥሮ ሕጉን አልጥስም ።

አንቺ ግን የመጣሽ እንደሁ.....

«ቤቷ ነበር ያ ደመና ....
ቤቷ ነበር ያ ተራራ ፣
እዩዋት ክንፍ እንደሌላት
በዥረት ጀርባ ተሳፍራ ፣
ወረደች! አይ ተዋረደች
አጃዒብ ፍቅር! » ይባላል

ማ`ናችን ብንቀል ይቀላል?


By @Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
31👍3
ጊዜው ተቀይሮ
ፍቅር ጥምቡን ጥሎ
ብናኝ ትቢያ አክሎ
ሁሉ እንኳን ቢሆን ፥ የማይታመን
አንተ ግን እመን
አንተ ግን ታመን
አሁንም በግ ሁን ፥ በፍየል ዘመን ።

ግዴታ አይደለም
ወከባን መልመድ
ወቅትን መዛመድ
ከጊዜው እኩል ፥ አብሮ መራመድ
ስለዚህ ውረድ !

እምቢ በል ገግም
ቀስ ብለህ አዝግም ።
አጉል መሰልጠን አያስፈልግም ።

ክፋት የለውም
በወግ በወጉ
ለገዢ ሀሳብ ቦታ ቢለቁ
ያረጀን ነገር በአዲስ ቢተኩ
ግን ደሞ አሉ - የማይነኩ ።
በጊዜ ፍጥነት የማይለኩ ።

እስካሁን ከመጣው
ገናም ከሚያመጣው
ከቁስ ከማሽኑ
ዘመን የማይሽርህ ፥ አንተ ነህ ፋሽኑ ።

By Hab Hd

@getem
@getem
@paappii
50🔥6😱4🎉1
ዝብርቅርቅ ባለዉ በህይወት አዙሪት፤
ፍቺዉም ሳይገባኝ እንደዉ ስንከራተት፤

ሠርክ በጥበቃ በይሆናል ተስፋ፤
ይሞላልኝ መስሎኝ ስዳክር ስለፋ፤
በሰለለ ቅኝት ኑሮዬን ስገፋ፤

የቁሙ ቅዠቴ እጅግ አደከመኝ፤
በህልም መደሰት መኖር አታከተኝ፤

ትርጉም ያጣሁበት ብኩኑ ህይወቴ፤
መኖሬ ከጎዳኝ ይጥቀመኝ መሞቴ፤

ለመሞትም ለካ መመኘት አይበቃም፤
ቀኑ ካልደረሰ ትንፋሽ አይገታም።

ነጠላ አዘቅዝቄ ዘወትር እዬዬ፤
ራሴን ፈርቼ ስሸሽ ከጥላዬ፤

እንደዉ ምን ተሻለኝ?
ምንስ ነው የሚበጀኝ?
.................................................
በዔደን
ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
29👍4🔥2
#ከተጣሉ_ገፆች_መሃል

የፊቱን እያየ የኋላውን ትቶ
ማንነቱ ጠፍቶት እልህ ጋ ተጋብቶ
          ጎጆውን ቀልሶ
ማን እንደነበረ ረስቶት ጨርሶ
የገዛ እልሁ ደፋው ከፊት ደርሶ።

ብላችሁ ንገሩ
ላገር ለመንደሩ
በምን ጠፋ ቢሉ!

ንሸጣ: ጋሽ ደበበ ሰይፉ (በምን ሞተ ቢሉ)


ዮኒ
     ኣታን   @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍158
እንዴት ነሽ  ስላት
ሳቅ ታበዛለች
ትጫወታለች ፤

< አለሁ ! > 
ትላለች - እንደሞላላት
ቁስሏን የማላውቅ እዬመሰላት ፤

የዐይኗ መደፍረስ
የገጿ ሽክረት
የአንጀቷ ማረር
የልቧ ቁስለት

ጥልቅ ስቃይዋን እዬነገረኝ ፤
እርሷ ግን ሁሌም አንድ የምትለኝ ፤

- - - - - - - - -  አለሁ ደህና ነኝ !

ልዩ ፍጥረት ናት
አይደረሱባትም ፤

ስሟ ሕይወት ነው
ካልተሸከሟት አይረዷትም ፤

በሕመሟ መሳቅ
በቁስሏ ማጌጥ
ታውቅበታለች ፤

ልክ እንደ መሬት
ውኃ'ን ከእሳት ጋር ታቻችላለች ፤

ከራስ ቅራኔ
ከራስ ጋር ሙግት ቢኖርባትም ፤
ከመሳቅ በቀር
በሰው ፊት ማልቀስ አይኾንላትም  ፤

ደህና ነኝ ከሚል
ከአንድ ቃል በቀር ——
  ሌላ አይወጣትም ፤

እወድዳታለሁ ፤

ደህና ነኝ ስትል
ደህና እንዳልሆነች አውቅባታለሁ።

By Tewodros kassa

@getem
@getem
@paappii
88😢15🔥7👍4🤩1
የአብስራ ሳሙኤል

አባ "ደፋር'ሁን" ብለህ እንዳ'ስተማርከኝ፣
እደፍር ብዬ ጦሬን አነሳሁ፤
ግን ሰው ነኝና ለነፍሴ ሳሳሁ።

እናም አባ፣ ያንተንም ምክር ከንቱ ሳላስቀር፣
ጀግና ነኝ ብዬ እንዲው ባክኜ ከሜዳ እንዳልቀር።

     * * *
ከምክርህ ጦሬን፣ ከፍርሀቴ ጋሻን አበጀው፤
እንዲያ ሲሆን ነው ውረድ!

እንውረድ!
ሲሉ የሚበጀው።

ዝናቡ እስኪ'ጠል ሸሸት ማለት፣
ጠለል ማለት መፍራት አይከፋም፣
ውድቀት ነው ብለን ከሳቅንበት ስር፣
መማሪያ የሚሆን ጥበብ አይጠፋም!


by Yabisra Samuel

@getem
@getem
@paappii
48👍5🔥2
እኔ ጭምቱ ሰው
ፍቅር ተለክፌ
ከእድገት ሀገሬ
ለሷ ስል ከንፌ
ሮቤ አለች ሲሉኝ
ሮቤ በርሬ
ሳስስ ስፈልጋት
ስጠይቅ አድሬ
ሸገር ሄደች ሲሉኝ
ባቀና አዲሳባ
እንኳንስ አካሏ
ዳናዋም አልገባ

ባክኜ ባክኜ
ከደከምኩ በኋላ
ምፈልጋት ፍቅሬ
ታየች ከ አሰላ

ገላንን ዱከምን ቢሾፍቱን አልፌ
ከሞጆና ናዝሬት ወንጂ ተገኝቼ
በሶደሬ በኩል ልሂድ ወደ ዴራ
ኢትያን አልፌ እንድገኝ አሰላ።

መነ ጂረኛ ኮ አቲ ቤክተ ላታ
ዮካን ፉዴን ጎንደር ኮ ሊጣ
(ዋ ነን ጀዲ አኒስ አብዲን ሙራ
አፉራ ኬ ዴቤን በርባቸ ኬን ጆራ)

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
32👍9🔥9🤩4
ኪሴ፣ እኔ ፣ እግዜር
(ሳሙኤል አለሙ)

ዝር---ዝር
አምስት ብር
ዝር---ዝር
አስር ብር
ከኪሴ ቁና ፥ ሞልቶ ሲሰፈር
አላውቀውምና ፥ የነገን ነገር
ከንፈሬን እመጣለው።
ስምህን አዋጣለው።
(እግዜር ይስጥልኝ!)

እያለኝ፥ አለ-ማፈሬ
እያለኝ፥ የታጠፈው ብሬ
ባለ-መቀደዱ...
እያለኝ፥ የኪሴ ጨርቁ
ባለ-መተልተሉ...
ግን እንዴት ፥ ያጣ ስንመስል፤
እኔና ኪሴ ፥ አንዲት አንቆስል።

ስለማርያም ሲሉኝ...
ኖሮኝ እጄን እንዳልሰበስበው፤
ስለወላዲቷ ሲሉኝ...
እንዳጣ ሰው
ኪሴን እንዳልደባብሰው፤
ወይ በፀሐዩ
ወይ በዝናቡ
ወይ በንፋሱ
ብቻ ምልክት ስጠኝ ፥ የሚያስታውሱ

@getem
@getem
@getem
👍1814🤩1
" አይ ወጣትነቴ"
             ( ግዮናይ ነኝ)!፧
በባህል ታጥሬ  በ'ምነቴ እየኮራሁ:
ወጣትነቴ አልቆ  እንዳላረጅ ፈራሁ።

በመጠጥ ሰክሬ  ፖሊስ ሳላስቸግር:
ከመንገዱ ቆሜ  ሴቶችን ሳልፎግር።
ለነገ 'ሚበጀኝ  እውቀቱን ሳልቀስም:
ወይ እንደኩዮቼ  ሸጋ ከንፈር ሳልስም።

አወይ ወጣትነት...
በቅኔ ሳልዘምር  ሳልዘፍን ባ'ራራይ:
ወይ አንዷን አቅፌ  አልጋ ሳልከራይ።
ብላክ ሌብል ውስኪን ሳላንቆረቁረው:
የ'ግር አጣጣሌን  ምንም ሳልቀይረው።

ከሜዳ ሳልቦርቅ  ፈረስ እየገራሁ፣
ወጣትነቴ አልቆ  እንዳላረጅ ፈራሁ።

@getem
@getem
@getem
58😢17👎6👍5🤩1
ተስፋ?
.
.
እንደ እምዬ እቅፍ የምንናፍቀዉ፤
ዘወትር ሳንታክት የምንጠብቀዉ፤

ብርሃን እንዲሆን በምናብ የሳልነዉ
በልባችን ያለ ተስፋ ግን ምንድነው?
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
48
ፍቅር በዝምታ

ደስ የሚለው ህመም ሰውን የ መውደድ
አዎ ያማል እኮ ለማይገባው ሰው ጨርቅ ጥሎ ማበድ

ባንተ ደስታ መሳቅ የራስን ሀዘን ረስቶ
ደሞ ማዘን መጨነቅ ሀዘንክን አይቶ

ሁሉም ስላንተ ብቻ አንዳች ሳልል ለኔ
ያንተን ህይወት ኖራለው ባክኖ ስለ የኔ

እራሴን ገደልኩት የኔ ምለው አጣው
የኔን ደስታ የኔን ስሜት ከቶ ምን ዋጠው ?

እንዴት ነው የቻልኩት ሁሌ አንተን ማሰቡን
በሁሉም ቦታ ላይ ምስልክን መሳሉን

ለማን ይግባኝ ላቅርብ ላሰማ ስሞታ
ላንተ ብቻ ልቤ ሁሌም እየመታ

ማን ይገባው ይሆን ባወራ የሆዴን
ያልተፈቀደልኝን በጥልቅ መውደዴን

እኔማ መረጥኩኝ ችሎ መቆየቱን
ደና መስሎ መሳቅ መሰንበቱን

ልክ እንደ አምላኬ ልክ እንደ አንዱ ጌታ
ልቤ በ ሰው ፍቅር እየተንገላታ

ለካስ ፍቅር ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው
እራሱ ክርስቶስ የተሰቀለው ነው

ታድያ እኔ ማነኝ ወደድኩኝ የምለው
በፍቅር ምክንያት እንዲ የማነባው

ፍቅር ማለት ህመም መሆኑን ባወኩኝ
አንተን በ ማጣቴ እንዲህ ባላዘንኩኝ

መጥቼ እንዳልነግርክ ቤትኛው ድፍረቴ
በህይወቴ ሞልቶ የ ገዛ ጭንቀቴ

እንኳን ግድ ሳይሰጥክ ለኔ ምንም ሳትወደኝ
አድርጎት ፈጣሪ ድንገት እንኳን አንተ እኔን ብትወደኝ

የለኝም አቅሙ ልነግርክ የልቤን ትርታ
ስወድክ ኖራለው ሁሌም በ ዝምታ

ነሀሴ 12

By mhret

@getem
@getem
@paappii
61🔥6👍2
ቢራቢሮ ቢራቢሮ ቢራቢሮ ሆና ነፍሴ፣
መታገሉን አልችልበት ቀን እስኪያልፍ፤
ዝም ነው መልሴ።

እንደ ዛሬ ሆኖ አይቀርም
ነገም ቀኑ ይለወጣል፤
አሁን ትል ነው ያልኩት ገላ፣
ቀን ሲያሽረው ክንፍ ያወጣል።

እቀስማለሁ የአበባን ማር፤
እበራለሁ ከፍ ብዬ።
ጊዜ ደርሶ ያሻረኝን በረከቱን ተቀብዬ፤
ትልነቴን መሬት ጥዬ!

አንተም አንቺም ወገኖቼ፣
ቢራቢሮ ናት ነፍሳችሁ!
ትል እንዳለች አትግደሏት፤
ቀን የማያልፍ ቢመስላችሁ።

ከታገሱት እሺ፣ ካሉት፣
እንደ የ'አቅሙ ሁሉ ይገፋል።
መከራ የህይወት ድልድይ ነው —
የተጽናና ተሻግሮ ያልፋል፤
እምቢ ያለው ይቀጠፋል።


By @YabisraSamuel

@getem
@getem
@getem
41