ግጥም ብቻ 📘
65.7K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ካለብኝ ጸባይ

የግንባር ስጋ ነው እንደሚሉት አይነት ሆኖ ባህሪዬ
ነገሬ ፊት ለፊት ቀጥታ መጥራት ነው ሰውን ተፈጥሮዬ
አህያን አህያ ቅልን ቅል ብዬ😊😊

አንበሳን አንበሳ ቀፎውንም ቀፎ ብዬ የምጠራ ሁሉን በቀጥታ
ምን ይሉኛል ብዬ ሳይኖረኝ ይሉኝታ🤷‍♀🤷‍♀
  ተፈጥሮዬ ነዋ

"ጦቢያ"እንደጻፈችው

@getem
@getem
@getem
👍274👎3
ማር ወለላ ከከንፈሯ
ውበት አላት ከምግባሯ
ባነጋገር ምትቆርጥ ጥም
ስትቀመስ የምትጥም
ቅመሜ ናት ለመኖሬ
የወስጥ ቁልፍ የሚስጥሬ
ተፈጥሯዊ መልከ ሸጋ
ቀን ሲጨልም የምትነጋ
ባህሪዋ ወይናደጋ
የተሰጣት ፍቅረ ፀጋ
ከሷ
      ጋ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
🔥26👍1413
መተያየት በዝምታ
መተፋፈር ደግሞ ላፍታ
መፈራራት ለማናገር
ጉድ ሲቀለብ በጉድ ሀገር
መተያየት ዝም ብቻ
ፈገግ ማለት በፍራቻ
ፍርሃት ፍርሃት ለፍቅር ቃል
አላማውራት ያራርቃል


ዮኒ
     ኣትን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍6011🔥11🎉5🤩2
ሰው ነበርኩኝ

ተወለድኩኝ
(ከመሀፀን ወደኩኝ )
አለቀስኩኝ
(ሀዘን ገባኝ ሰው ፈለኩኝ )
አፌን ከፈትኩ
(የሆድ ጥልቀት አወኩ )
በቃኝ አልኩ
( በእድሜ ሰከንኩ )
ጠረን ለየሁ
( ምቾት አየሁ )
ቋንቋ ለመድኩ
(በቆፈሩት ወረድኩ )
መልክ ለየሁ
(እኔን አወኩ  አዲስ ካየሁ )

አንተ ግን ለቤቴ
( እንግዳ ላጥንቴ )
ሆነህ የሩቅ ሩቅ
(እንደ ዘመድ እንቅ )
ለምን አደረኩህ ....?

ሴት ነበርኩኝ

የተጣፈ እጣዬ
( ግልጥ ጎባጣዬ )
ሊያውም በእኛ መንደር
( እንቢ ነው መግደርደር )
እያለ ከሚረግጥ
( በዘመን ረመጥ )
በዘር ማን ዘር እሳት
(የምትቃጠል ሴት) !!!

ጨዋ እኮ ነበርኩኝ

አፈነገጥኩልህ
( እራሴን ተውኩልህ )
ወፍ ሆንኩልህ ጫጩት
(ሳይበር እንደ ቀጩት )
ረግጬ ህጌን
(ገላምጬ ወጌን)

ክር እኮ ነበረኝ

የገባሁት ኪዳን
( የመነንኩለት ሀቅ በነፃ ለመዳን )
የወሰዳት ነፍሴን
( ያሳረፈኝ ምናብ ቆርጦ ግሳንግሴን )

ጌታ እኮ ነበረኝ

የልቤ ጉልበቱ
(ሰርክ መስዋእቱ )
የምገብርለት
(ያደረገኝ ዐለት )

ብዙ ነኝ 

የማላውቃት እኔ
( ተለየች ከጎኔ )
ወጣች አፈትልካ
( እኔን ላንተ ልካ )

እንደ ሰው ....
(ሞትን እንድቀምሰው)
እንደ ሴት
( እንዳምጥ  በምሬት )
እንደ ጨዋ
( እንድፈተን እንድሰዋ )
እንደ አማኝ
(እንድቀበል ሳይቀማኝ )
እንደ ድኩም
( እንዲያነቃኝ ህማም ኩርኩም )
እንደ ብዙ
(አንድ እንድሆን ጠፎ ጓዙ )
ህግ አዝዬ
(ትምክት ልቤን እንዳይንጠኝ )
ተኝቼ እንድነቃ
(አንተን መርጦ ሰጠኝ)

(በእምነት )

@getem
@getem
@getem
44👍35🔥5
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ
ወዮለት ደመና ።

ወፍ አይዘምርልሽ
ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ ።

ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ ።
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ ።

ክነፍ በዪኝ ልክነፍ
እረፍ በዪኝ ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።

By Hab Hd

@getem
@getem
@paappii
68👍29👎19🔥9🤩9😁4🎉2
( የድሮ ባሏ )
==========

እባክህ አምላኬ ተሰምቶ የማያውቅ
ግለጥልኝ ቃላት
የቀደመ ባሏ ደራሲ ነው መሰል
የለም እኮ ያላላት  ....

እርሱ አሐዱ ብሎ
በሳመው ከንፈር ላይ እኔ እየደገምኳት
ቃላት አሽሞንሙኖ
የነገራትን ፍቅር እኔ እያስታወስኳት
መሰረት በጣለው
ስውር ርስቱ ላይ ሠርክ እየደከምኩኝ
ልቧ ላይ ምንኖረው
እርሱ እየደመቀ እኔ እየፈዘዝኩኝ !!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
😁7136👍26😢11🔥2
ብታውቂ!
***
ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ
መንፈስን ካዚም እስራት
እንደምታላቅቂ
ብታውቂ!
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታውቂ
****
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኩሴውን ከሱባዔ
ፈላስፋውን ከጉባዔ
እንደምትጠሪ
ብታውቂ !
**"
እንኳንስ በኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!

By በውቀቱ ስዩም

@getem
@getem
@paappii
97👍30🔥8🤩4👎1
ቁራኛ
ዘመን ያላዳነኝ
ያልፈታኝ ርቀት
ተአምር ያላነጻኝ
ያልፈወሰኝ ጥምቀት
ከናፍቆት ሚነጥል
የታጣልኝ ዳኛ
እድሜ ይፍታህ ያሉት
የፍቅር ምርኮኛ
ሆንኩልሽ ቁራኛ።
           

By @poetkidus

@getem
@getem
@paappii
37👍19😁5👎2🔥2
ዘንባባን አስቀምጦ ከመናፍቅ
ጉዞ ዘላለም መበጠር
ፍቅር ሳያውቅ ኖሮ የካደ
አንደበት ከህልሙ መስፈንጠር
ሲቃዡ ነው ማደር
ስርን ነቅሎ መኖር
ስር ሰዶ መመንጠር
የፍቅር እናት ክዶ በውሸት
አብነት ዘላለም ማመስጠር

  by @ygolaw16

@getem
@getem
@getem
👍3715😁7👎6🔥1🎉1
¯
..‎ተስማምቶኛል  ፀሀይነቷ
‎መጥፋትን አልሻም ከፊትለፊቷ
‎ ያለርህራሄ  ብትወርድም በላዬ
‎ንዳዷ ጥሞታል ለውርጫም ገላዬ

‎ልዩ አረገችኝ
‎ቀየረች ፍጥረቴን ፣
‎ከጥላ መሸሽ...
‎ከጥላ መጠለል አድርጋው ህይወቴን።


by @yoseph_Gezahegn

@getem
@getem
@paappii
26👍8🤩2🔥1
ሁሉንም ነበረች
አለሌም ጭምትም
እሬትም ወተትም
እሾህም በለስም
በራድም ትኩስም
አሳቢም
ተግባቢም
ሳቂታም ፡ አልቃሻም
አሁን ምንም ነገር
ለመሆን አትሻም።

ኖራለች ከልቧ
ስታልም ስትነካ
ስትጨልም ስትፈካ
ሲቆላት
ሲደላት
ሲከፋት ሲመቻት፥
ለምን እንደሆን እንጃ
ሰው መሆን ሰለቻት!።

© @mikiyas_feyisa

@getem
@getem
@paappii
45👍27😢17🔥6😱1
(የአብስራ ሳሙኤል)

1....
ተይው
መች ተናግሮ ያቃል
የልቡን
ሀሳቡን
ወንድ አይደለ
እያነባ ይስቃል
ደና ነኝ እያለ
አለ
መኖር ካሉት
በእግዜር ምስጋና ቢኩሉት
በፈገግታ ቢቀበር እንባ
ወንድ አይደለ
ይመስገነው ብሎ ገባ
በትጨልምም
በትዘምም
ዙፋኑ ናት
ጎጆው ..... ማጀቱ
ቤቱ
የጻፈበት ገድል
የኑሮ ድል
የወዝ ዋጋ የላብ ፍሬ
ደና ነኝ ለዛሬ
2....
ተይው
ወንድ አይደለ
መች ደህና ሆኖ ያቃል
ደህና ነኝ እያለ
በገረባው
በሲጃራው
በእጣን ጢሱ
የተረሱ
መአት ብሶት
የጭስ ለቅሶ
አይን ያሟሿል
ሌላን ደርሶ
ሆድ አስብሶ
ግን ግድ ነው
ዛሬ የዱአ ከተገኘ
ይመስገን ነው
ደህና ነን ነው
3....
ተይው
ወንድ አይደለ
ባሬላ ጭኖ
ኩንታል ተጭኖ
መሪ ጨብጦ
ከብቶች እረግጦ
ባመጣት ሀሴት
ላፈቀራት ሴት
የ አበባ ጉንጉን
የወግ የወጉን
የወርቅ ሀብል
የባዕድ መብል
በርገር
ቢዛ
ማክያቶ
ተገባብዞ
ተጎንጭቶ
ሩም ይዞ
ባናት ባናት መዳራት
ፍቅር መስራት
ከሰመረ ገላዋን
ካልሆነም ጸጸት ታቅፎ
ትዝታ በውሀ አራግፎ
ደህና ነኝ ነው
ወንድ አይደለ
የልቡን ጠባሳ የሚያወራ ማን ነው
4....
ተይው
አትጠይቂው
እንዴት ዋልክ እያልሽ ?
ላትጸድቂ በነፍሱ
ደህና ባይሆን እንኳ
ደህና ነኝ ብቻ ነው
የወንድ ልጅ መልሱ!

By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
43👍20🔥7
ደመናማ ገጾች.
(የሞገሴ ልጅ)
ምሽት እየጓጉ-
ጭለማን ተግነው - ብርሃንን ሽሽት፣
ብዙዎች ኖረዋል,
መታየት ፈልገው ጠልቷቸው መታየት።

ደመናማ ገጾች-
ተፈርተው መኖሩን - ከክብር ያልቆጠሩ፣
ጭለማን መዋያ፣
መጽናኛ አድርገው - ሲነጋ አደሩ።

By @tafachgitm

@getem
@getem
@getem
18👍8🔥3
‎ያንድ ቀን ምሽት : ብርድ ቆፈን ሽሽት
‎ሌቱን ማነጋበት እግዜርን ጠይቄ
‎የሷን ቤት ጠቆመኝ አደርኩኝ ዘልቄ

‎ተንኮል እንደነበር ልቤ መች አጣው
‎ሌቱንም ፍቅሩንም አንግቼለት ወጣሁ።

By @yoseph_gezahegn

@getem
@getem
@paappii
27👍6🤩3🔥1
አበቦችህ አሉ ጠንዝለው ደርቀዋል
አበቦችህ አሉ ግን የሉም ሞተዋል
ጠረናቸው ጎልቶ ካልጋየ አጠገብ ጠዋት ማታ ቢሸተኝ
አንተን ቢያስታውሱኝ
ሞተው ነው ሚኖሩት ሂወት የላቸውም
ደርቀዋል ግን አሉ ደሞ አልጣልኩአቸውም
ሄደሃል ላትመጣ አንተም እንደዚአው ነህ
አትለመልምም ከረፈደ ኋላ ውሃ እያጠጣውህ::

By lily

@getem
@getem
@getem
👍1814👎2
ማህሌተ ገንቦ

ባጭር ቀረን ስንል፣ እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን ለኩሰው ላበሩን

ቺርስ!!

ፊታችንን አይተው እንደተቸገርን፣
ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስከንለምናቸው፣
ቆመው ላልጠበቁ

ቺርስ!!

ወድቀው ለማይጥሉ፣ ነግሠው ለሚያነግሡ ነውራችንን አይተው፣ ልከ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው፣ ፈጥነው ለሚረሱ

ቺርስ!

ላባ ላረጉልን፣ የመከራ ሸከሙን
ቀልደው ላሳቁን፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ
ሥጋ ለበስ ትንግርት፣ ሆነው ላስደመሙን

ቺርስ!!!!

By bewuketu seyum

@getem
@getem
@paappii
65👍18🔥4🎉3
( እግዜርና ሴት )
============

ምንም ብታማርር
ምን ብትበድላቸው
እግዜርና ሴት ልጅ
በዚህ አንድ ናቸው
:
ለይቅርታ ሲሹህ
ትወደኛለህ ወይ ??
ሁሌ ጥያቄአቸው !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
107👎23👍19😁11🔥3
(የአብስራ ሳሙኤል)


¶ከህይወት ዳርቻ¶
¶የኔና የአንቺ ብቻ¶
<ሆነን>
<ደርሰን>
°°°°ስናይ ተመልሰን
ትዝ አለኝ ትዝ አለሽ
ከትዝታ አይሸሽ
የመጀመሪያው ቀን
ደርሶ ያስተዋወቀን
ከፍጡር ነጥሎ ያውም ከወንድ ዘር
ያርባ ቀን እድሌ ባንቺ ሲመነዘር
መሄጃ ያጣውን እያንከላወሰ
...........ከደጅሽ ደረሰ
የሰናፍጭ ቅንጣት
አንቺን ላለማጣት
የተሳልኩ ይመስል
ውብ የሆነ ምስል
፨ከሙሉ ቀሚስ ጋር ከተሸነሸነ፨
፨የሚያምር ሹሩባ የተጎነጎነ፨
፨ከጉንጮችሽ መሀል፨
፨፨አለች ትንሽ ስርጉድ፨፨
አቤት የእግዚያብሄር ጉድ!!!
ምን ሲል ጋረደበት ?
የወንዱን ልቦና
አልተነካሽ ገና
ያ-ሁሉ ቦዘኔ ደጅሽ ሲርመሰመስ
ሴትነትሽ አይረክስ!።

፨፨፨
ከህይወት ዳርቻ
የኔና አንቺ ብቻ
<አልፈን>
<አሳልፈን>
°°°°ስናይ ተመልሰን
ትዝ አለኝ ትዝ አለሽ
ጀንበር ፀንታ ስትሸሽ
እንዲው ስውተረተር
ሰው የመሆን ነገር
ሞልቶ ለማይሞላ
ሆዴ ስሻ መላ
ጉልበት ሲበዘበዝ
አንቺን አይቶ መፍዘዝ
ምን እድል አመጣሽ
የቱ እምነቴ ቃጣሽ
<ወደምሰራበት>
<ወደምትሰሪበት>
እግዜር ሲያገጣጥም
የዕጣ ፈንታ ግጥም
አንቺን ከኔ ጻፈ
...አንድ ቀን አለፈ...
...ሁለት ቀን አለፈ...
አይንሽን ለመድኩት
መተያየት በዛ
እንዲሁ እንደዋዛ
ተግባባን እንደቀልድ
ተያይዞ መንገድ
...መሸኛኘት በዛ....
....መገባበዝ በዛ....
እንዲሁ እንደዋዛ
¶ወደድኩሽ ወደድሺኝ¶
¶ጠየኩሽ እሺ አልሺኝ¶
በአብርሀም ጋብቻ
የኔና ያንቺ ብቻ
ጭብጨባ ያልበዛበት
ረብሻ ያልበዛበት
ተጸነሰች ህይወት።.....

፨፨፨
ከህይወት ዳርቻ
የኔና አንቺ ብቻ
<ሆነን>
<ደርሰን>
°°°°ስናይ ተመልሰን
መኖርም ያረካል
ውጥኔም ይሳካል
ውል ለሌለው ሀሳብ
ስለሆንሺኝ ርካብ
ዘመን ማሸገሪያ
ባህሩን ማስገሪያ
ከጉንጮችሽ መሀል
፨አለች ትንሽ ስርጉድ፨፨
ሳምኳቸው እንደጉድ ።

By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
48👍24🎉3🔥2😱1
🌜🌜🌜🌜
.
.
.....ትዝ ይልሃል ያኔ
እቅፍህ ከተኸኝ ተቀምጠህ ከጎኔ፤

በተመስጦ ሆነን ጨረቃን ስናያት፤
ልባችን ያለዉን በሚስጥር ስንነግራት፤

ትዝ ይልሃል አይደል.......
ላልከዳህ ላትከዳኝ በስሟ ስንምል፤

ዛሬ ቀኑ ከፍቶ ቅናት ይሆን በደል፤
.....አመል አይሉት እድል፤
መሐላችን ጠፍቶ ተጓዝን ለየቅል፤

መገኘት ከፈለክ ከምንወደዉ ስፍራ
.....እጠብቅሃለሁ ከጨረቃ ጋራ።
.............................................


by ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
50👍21🔥5
(የአብስራ ሳሙኤል)

¶በል እንግዲ እግዜር¶
መዝገብህን ክፈት ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ ስጋና አጥንት የሚሰረስር
እዚህ እታች ሰፈር
ማዳበሪውን እንዳነገተ
ሀይላድ ሲለቅም
መኪና ገጭቶት አንድ ህጻን ሞተ
°°°°°°ይሙት ግድ የለም°°°°
ነበር አልን እንጂ
የኖረው ህይወት ህይወት አይደለም
ትራፊ እንጀራ ለዕልፍ አዕላፍ ያቀራመተ
ባርከው እያለህ
°°°°°°°°°°°ሳትባርክለት እርቦት የሞተ
ቀብሮት ወንድሙን
ከአይኑ አብሶ የእንባ ደሙኑ
።።።።።።ኑሮን ሊጋፋ።።።።።
ለሀይላንድ ልቃሚ አንገት ቢደፋ
""""     """""    """""
ያው እንደወጣ አልተመለሰም
እንደ ጥያቄው እንደ ምኞቱ
የሱን አልን እንጂ
ታሪኩ እራሱ ታሪክ ነው የስንቱ.....
፨፨፨
፨፨፨፨
¶በል እንግዲ እግዜር¶
መዝገብክን ክፈት ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ ስጋና አጥንት የሚሰረስር
[ደሞም አንዲት ሴት]
የቀሚስ ቅዷ የጭኗ ቁስል
የአርብ ዕለት ጌጥክን ግርፋት ምስል
እንደከተበ
አይኖ በምሬት
የራሄል እንባ እያዘነበ
ስታልጎመጉም እንዲ ትል ነበር
የጫንክብኝን የህይወት ቀንበር
<ችዬ ስጋፋው>
ስለምን ወንዱን ስሜት አስከፋው
<የገፋ ባሌን>
ዝሙት ሀጥያቱን ገና ሳለምደው
<ከሞት መራራ>
ብልቱ መርቶ የሚያራምደው
<በእናቱ እንጀራ>
በሰባ እጆቹ ጨፍልቆ ይዞ
የሴት ገላዬን በቁም ገንዞ
¡በድን ሲያስቀረኝ!
ቂም እንዳይመስልህ
በእንባ ዘለላ የሚያናግረኝ
<ይልቅ መዳፍክን>
የአንገት ማህተቤን ወሰድ ከህይወቴ
<አንቆ ሲደፍረኝ>
°°°°°°°°°°°ምስለ ስዕልህ ገዝፎ ከቤቴ
ተስፋ እንዳይሆነኝ
ስንቅ እንዳይሆነኝ
ኖረህ ዝምታ እያስደፈረኝ
ሆድ ይፍጀው እንጂ
ችዬ ያልነገርኩህ ብዙ ነበረኝ።.....
፨፨፨፨፨፨፨
¶በል እንግዲ እግዜር¶
መዝገብህን ክፈት ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ ስጋና አጥንት የሚሰረስር
......ደሞም ትዝ አለኝ......
አንዱ ፈላስፋ የተናገረው
ከትቦ ያኖረው
የዚህ አለም ቁስል የዚህ አለም ብሶት
ውርቂያኖስ በእንባ እንደመለካት
ተጠማው ያለን በሀሞት ማርካት
<እየቀበሩ>
ማማረር ሀጥያት ብሎ መመካት
<ነድያን አልፎ>
ዲያቆን ፍለጋ መቅድስ ማንኳኳት
.......ደሞም ትዝ አለኝ
ትዝ አለኝ ብዙ........
በሀረግ በስንኝ እንዴት ይቋጠር
ጋን ተሸክሞል ሰው እንደጠጠር
ይልቅ ዝም ነው
ሁሌም ዝም ......ዝም
የዚህ አለም ቁስል የዚህ አለም ብሶት
የትኛው ጠቢብ ደራሲ ደርሶት ?
የትኛው አምላክ እንባን አብሶት ?
ይልቅ ዝም ነው
ሁሌም ዝም..... ዝም
ሰሚ ሳይኖረን አንናዘዝም
፨፨፨፨፨፨
እናም በል እግዜር
መዝገብክን ዝጋው ጆሮ ዳባ አልብስ
የሰማ ሳይሆን
ስሙኝ ያለ ነው የሚያደባብስ

By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@getem
👍3619🔥6👎2😁1🎉1
(የአብስራ ሳሙኤል)

አይገርምም ታፈቀርኛለች
አይገርምም አፈቅራታለሁ
.
.
.
አይገርም
ነጠላ ነፍሶች
በህይወት መንገድ ያልተቆራኙ
አይን ለአይን ሲገናኙ
ምን አሸፈተሽ ምን አሸፈተኝ
የመቅደስ ዕጣን ናርዶስ ሸተተኝ
መግነዜን ፈታሁ ቁስሌ ዳነ
አይገርምም
ግን ይሄ ሁሉ ስለምን ሆነ
.
.
.
.
አይገርም
በጤዛማ ሳር በረሰረሰ
አፌ ከንፈርሽን እንደ ጎረሰ
ጋደም ብለን
ሽቅብ እያየን ሰማይ ሰማይ...ዪን
ጨረቃ አታምርም ብለሽ ስትስቂ
የኮከብ ፍላጭ የአደይ ውዳቂ
የሆነ ገላሽ
ከፊል ተገልቦ አያቃተተኝ
ምን አዘሞተሽ ምን አዘሞተኝ
.
.
.
አይገርም ታፈቀረኛለች
አይገርምም አፈቅራታለሁ
.
.
.
<ፍቅር የሚሉት ጦሶ>
በውደድ ጠልፎ እያቆራኘን
<ጠፈር ያለምነው>
ካፈቀርናት ሴት እቅፍ ተገኘን
""    ""       እንኳን ተገኘነን!
ጥበብ ቢበዛ እውቀት በረቅም
የኖረው እንጂ
የፍቅርን ትርጉም ያልኖረው አያቅም ።
.
.
.
አይገርምም ታፈቅረኛለች
አይገርምም አፈቅራታለሁ

By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@getem
👍2216🎉1