ግጥም ብቻ 📘
65.7K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
“ስኬተኛ ማነው ?”
ብዬ ጠየቅኋቸው
ታዋቂ አመጡልኝ
ይሄ ነው መልሳቸው ።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

አሳዩኝ ከበርቴ
ባለ ንብረት ፣ ነዋይ
እንደዚህ ያለውን
ቀና ብዬም አላይ።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

አመጡልኝ ምሁር
ፊደል የቆጠረ
የተመራመረ
ይሄም አልሰመረ።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

ጠሩ ባለ ጥበብ
በጥሁፍ በቅኔ
ያስገኘልን ረብ
(በርግጥ ጥሩ ነበር
እንደዚህ ሲታሰብ )
መልስ ግን አይደለም።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

አንድ አጩ ቀጥሎ
ጽድቁን አደላድሎ
ያናናቀ ሞቱን…
የቃል ጥሩር ለብሶ
ያስታጠቀ ነፍሱን…

አገኙብኝ መልሱን !

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
👍4730🤩3
ወዳንቺ እዘረጋለሁ!
ባድግ ብዬ
ባውቅ ብዬ
አንዳች ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ!

መቃብር ቤቴን ማሞቂያ
የሙት መንደሬን ማድመቂያ
ካለፉም ወዲያ መታወቂያ…
የምትሆን
አንድ ሀተታ
አንድ እውነታ
የህይወትን ምናልባት
የመኖርን እልባት
አውቃት ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ!

ከሰማይ በታች አዲስ ነገር
ከምድር ከፍ ብሎ የሚነገር
“የከንቱ ከንቱ” የምትባል
የአላዋቂን ፈላስፋ
በአፍጢሙ የምትደፋ
ስታቅፊ ዐለም እንደሚጠቀለል
ስትገፊም ሰውነት ከላባ እንደሚቀል
ስትስሚ ኢምንት እንዲሆን ጠፈሩ
ስትነክሺም ማንነት እንደሚበተን አፈሩ…

ይቺን ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ
የህይወት መስመሬን ማንቂያ
ውሎ አዳሬን መደበቂያ
ተስፋ ህልሜን መታረቂያ
የምትሆን
አንዲት ሁነት
አንዲት ኪነት
የመክረምን ፍልስምና
ከንቱነት ላይ ውብ አድርጋ ሸምና
ታውቀኝ ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ ካልተረሳሁ ምናልባት።

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
👍3117
@getem
     @getem
          @getem
👍282
ለተለያዩ የማስታወቂያ፣ የዘፈን ክሊፕ እና ድራማዎች ስራዎች በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ የሚኖሩ ሰዎችን ካስት ማድረግ እንፈልጋለን። - እድሜያቸው ከ35-45 - ከ25-30 - ከ10-18 ያሉ ወንዶችን እና ሴቶችን በአስቸኳይ እንፈልጋለን። የሚከተሉትን በቴሌግራም ይላኩልን። - 1 ሙሉ ሰውነት የሚያሳይ ፎቶ - 1 ከወገብ በላይ - 1 ፈገግታ የሚያሳይ ፎቶዎችን - ስም ስልክ እና እድሜ በሚከተለው አድራሻ ይላኩልን። https://t.me/Ribki30 ስልክ የሚደወልላቸው ለስራው ሲመረጡ ብቻ ስለሆነ በትዕግስት ይጠብቁ ዘንድ እንጠይቃለን።
👍193
ነበርሽ ፤…
የጠዋት ፀሐይ
በቀስታ ደም የምታሞቅ ።

ነበርሽ ፤…
የዓለት ስር አበባ
ድንጋይ ተደብቆ የሳቃት ።

ነበርሽ ፤…
ልሙጥ የሻይ ብርጭቆ
ወገብሽ የሚያቃጥል ፤

ቀስ አድርገው
አለሳልሰው
እፍፍ ብለው
ልካቸው ድረስ አብርደው
በከንፈርሽ የሚቀምሱሽ ፤

ነበርሽ ፤…
ለሕይወት ተኩል
ለሞት አምስት ጉዳይ ።

ቴዎድሮስ ካሳ

@getem
@getem
@getem
👍4811👎3🤩3
ዕዳዋ የለብኝ~አበዳሪ አይደለች
ደም አልተቃባችኝ~ዘመድ አልገደለች
አላስቀየመችኝ~ተናግራ ክፉ ቃል
እንከን አጣሁ ተብሎ~ሰው እንዴት ይራቃል?
ወይ አይደለች ሻማ~ጨርሼ አላነዳት
አንዳች አልሰረቀች~እንዳላሳድዳት
እንዴት ብለከፍ ነው~ስትርቅ የምወዳት?

ዘማርቆስ
By @wogegnit

@getem
@getem
@getem
58👍26😢6
❝ ሣቅ ተከሽኖ ግጥም ተመጥኖ ❞ ታላቅ የመክፈቻ ፕሮግራም በግዮን ሆቴል !

  ዘሃ ኢቨንትስ ከግዮን ሆቴል ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት ፤ 4ተኛ መድረኩን አርብ ታህሣሥ 25 - 2017 ዓ.ም ምሽት ከ10 : 30 ጀምሮ ያቀርባል ።

ጋሽ አያልነህ ሙላት ፣ ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህና ኮሜዲያን ደረጄ ሀይሌ የክብር እንግዶቻችን ናቸው ።

  የምሽቱ ፈርጥ ልዩ የክብር እንግዳችን አርቲስት ዓለም ፀሀይ ወዳጆ ናት ።

ደራሲና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም እና ሰለሞን ሳህለ ውብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ።

  ኮሜዲያን ናሆም በየነ መድረኩ ላይ ይደምቃል ፤ የአብጸጋ ተመስገን የተከሸነች ወግ አዘጋጅቷል ፤ ፈገግታ ባንድ ጥዑም ሙዚቃዎቹን አሰናድቷል ፣ ሒስ ፣ አጭር ፊልም ፣ ስዕልና ሌሎች ብዙ ትርዒቶች ተዘጋጅተዋል ።

  ለበለጠ መረጃ በ 0935697143 ይደውሉ ።

የ YouTube ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👍

https://youtube.com/channel/UC9ItbVvxXMLV7QIT-rCJyTg?si=Mj5GlhjsE1ZvBtjM

@getem
@getem
👍20🤩32
አቀርቃሪ አሉኝ፣
ቀና ብሎ ማየት መራመድ ሲሸሸኝ፣
ሊያብድላት ነው አሉኝ፣
በቁሜም በሕልሜም ቅዠት ሲረብሸኝ።

ሊረታ ነው አሉኝ፣
ስንቀጠቀጥላት ስሟ ትዝ ሲለኝ፣
ትክክል ናቸው ወይ፣
እኔ ከምወስን እናንተ ንገሩኝ?

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@getem
31👍17🤩7👎3😁2
.............



ትብታብ አይደለም ድግምት
ደብተራ አይደለም አስማት
ንጹሕ ፍቅር ነው ምናኔ
ለሚወዱት የመሞት ጭካኔ
እንኳን አሁን፤ከገላዬም ደም ቢነጥፍ
ደምስሬም ጅማቴም
ስምክን ነው የሚጥፍ
ዘረ ደሀ አፈቀርሽ
ዘራችንን አረከሽ
ብለው ቢያጠምቁኝም
ለፍቅርህ ስለሆን
የክፉዋች ጸበል፤መድን አይሆነኝም
ይልቅ በዛብህ፤አንጀትክን ሰብስብ
ከዛሬ ይልቅ፤ነገህን አስብ
አይዞህ በዛብህ፤ይህን ቀን ቻለው
ሰብለ ወንጌልህ
ከአትሮንስ ወርጄ ተጠፍሬያለው
ግን አትሳቀቅ፤ይህም ቀን ያልፈል
የክፉ ጅራፍ፤ጽናት ይጽፉል
የሚለው ቃሏን፤ከፍቅሩ ሰምቶ
በተስፋ አባብሎ፤ልቡን አጽናንቶ
ከተማ ገብቶ ቢጠብቃትም
ወንጌሉን ካሻው አላገኛትም
የእግዜር ኑዛዜ፤የእውነት ቃሉ
የአዳም ጥፋት፤የአምላክ አምሳሉ
የሄዌን ስህተት፤ክፉይ አካሉ
አትብላ ካለው፤ከፍሬው በልቶ
ፍቅርን በደለው፤የሞት ሞት ሞቶ
ግን በበዛብህ፤ቃሉ ልዩ ነው
ከህይወት መስቀል፤አዳኙ ማነው
አዳም ከበላው፤በለስ ሲያላምጥ
ከወንጌል ይልቅ፤ልቡን ሲያስበልጥ
ፍቅርን በደለው፤የኑሮ ጣጣው
በቃሉ አኑሮ በእውነቱ ቀጣው
ድሮም ያን ጊዜ፤በኦሪት ዘመን
ክፉ ጎልያድ፤በሀይል ሲዘምን
ጉልበቱን ነስቶ፤መሬት ያኖረ
ጠጠሩ ሳይሆን፤እምነት ነበረ
በማፍቀር እምነት፤ነፍሱን አጽንቶ
ቢጠብቃትም ከተማ ገብቶ
ወንጌሉን አጣት፤ከባዕድ ሀገር
የህመም ጥልቁን፤ለማን ይናገር
ህልሙን አለሙን፤ሁሉንም ትቶ
አቅሉን እስኪስት፤ወንበዴ እጅ ገብቶ
በፍቅር መስቀለ የተሰቀለ
ኤሎሄ አይደለም፤ሰብለ ነው ያለ
የእግዜር ማቅ ለባሽ፤አንቺ መነኩሴ ሴት
እረፍትን ፍለጋ፤ከገባሽበት ቤት
ካልጋ ያገኘሽው፤እሱ ነው ወንጌልሽ
ጣር ባሰረው ድምጸት
ሰ...ሰ..ሰብለ ብሎ የሚልሽ
እንዲ ነው ፍቅር፤እንዲ ነው ስቅለት
እንዲ ነው መሞት፤እንዲህ ነው ድህነት
ፍቅር ቢበድል፤የእውነት ልኩ
ወንጌል ያጣ ሰው፤ወንጌል ነው መልኩ

Based on ፍቅር እስከ መቃብር

    by  @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍3731😁1
የነገዬ ምርኩዝ የትናንት መፅናኛ

የህይወቴ ትርጉም የጊዜ መዳኛ

መራመጃ መንገድ ህመምን አስረሽ

የፅልመቴ መብራት እኔን አስታዋሽ


          ጣዕም ሰጭ ስኳር ህይወት ማጣፈጫ

          የዛሬን ትካዜ

          የዛሬን ፍዛዜ

          በያልፋል ደስታ ስሜት መቀየጫ


የዋሻ ውስጥ ጮራ ፍንጣቂ ብርሀን

የህይወቴ ካርታ የመርከቤ ካፕቴን

ትርጉም አልባን እኔን ሀዘን የወረረኝ

ከጥልቅ ትካዜ ውስጥ ወዝውዞ ያነቃኝ

ተስፋ ነው ሻማዬ...

ተስፋ ነው ሻማዬ

የትናንትን ፅልመት ዛሬን ያበራልኝ
     
By ዘይድ ሁሴን
   ታህሳስ -27 -2017

@getem
@getem
@getem
34👍30😢4🔥1

.
ልደትህን ሳስብ
ሳነሳና ስጥል

በጥሞና ሆኜ
ደግሞ ሳሰላስል

ንጉሥ ሆነህ ሳለ....

በጠባብ ሰዉነት
ከሰማይ መዉረድህ

ከበጎቹ ግርግም
ወርደህ መተኛትህ

ነገረ ልደትህ
በታወሰኝ ቁጥር

እኔን ይገርመኛል
እጹብ ያስብለኛል

የዓለምን ደስታ
ብስራትን የሰሙ

እነዛን እረኞች
መሆን ያስመኘኛል።

By ዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
72👍20👎1
እንኳን አደረሳችሁ✝️

@getem
30👍8
ቢሆንም


ፍቅር ይሉት ጣጣ  ሲፀነስ
ሰው ከሰውነቱ ላይ  ሲቀነስ
አይተናል
          
አይተናል  የነበር ፍቅር ሲለፈፍ
በከሸፈ ፍቅር   ጤንነት ሲቀሰፍ
አይተናል


ፍቅር  የመርገምት ቃል እስኪመስለን
ከእጦት በላይ  ንቀታቸው ያቆሰለን
አይተናል


በጫማቸው  በረገጡን
ከትቢያ ላይ  ባስቀመጡን
ላቀመሱን የፍቅርን ፅዋ  መራር ጣዕም
ልክፍት ነውና
    ይሄው እስከዛሬ  እንፅፋለን ግጥም


ቢሆንም

በዬ ዘፈኑ  ሆድ የባሰን
የናፍቆት ህመም የዳበሰን
አንድ ሰው ለመውደድ   ዘመናት ያነሰን
ስንት አፍቃሪ አለን
         የትዝታ ፈረስ  ወስዶ  ሚመልሰን


የማይመጣ እንደሚጠብቁ  ቢታወቅም ቅሉ
በአልኮል በሲጋራ  በጫትም ገረባ የተጠለሉ
ከእልፍ አእላፍ የበዙ   ስንት ልቦች አሉ ?


By kerim
@poem2513

@getem
@getem
@getem
👍6424
ባያቸውስ ኖሮ ?
(ሚካኤል አስጨናቂ)

እርግት ያለች ወተት
ስክን ያለች ቡና …
ይሄን ችኩል ዘመን
አልዋጀችምና …
ተንገበገብኩላት
ተሳተብኝ አቅሌ
ሆንኩላት ባተሌ ።

ጥልል እንደ ጠላ
ኩልል እንደ ጠበል
ከአንገቷ ስር ገነት
ገድ ጥሎኝ ብጠለል
አ..ን..ሰ…ፈ…ሰ…ፈ…ች….ኝ
አ…ር..ገ…ፈ...ገ…ፈ…ች…ኝ
ቃላት ሳ’ተነፍስ
ጥርሶቿን ሳትገልጥ
ቅቤ ሆነ ልቤ..
ገጽዋ ላይ ሲቀልጥ ፤

ያን ጊዜ ተቃናች !
ብታጣብኝ ኩራት
ስስ ጎኔ ቢገርማት
(ዓይኖቿ ፍም እሳት)
አንገቴን ሰበርኩኝ
ፈርቼው ይሄን ፍም
ቢሆንም …
ቢሆንም …
ለዓይኖቿ አፀፋ
መስጠት ሳልፈልግም
ለንቋሳው
……………………….. ተንጋለልሁ
ለዚ’ች ሞቃት ግርግም
:
ደረቷ ላይ ፍግም !

@getem
@getem
@paappii
👍468🤩2
መኖር መኖር መኖር!

(በእውቀቱ ስዩም)

በማይ በምሰማው
አንዳንዴ ስገረም
ህይወት ከናላማው
ስህተት ይሆን እንዴ፤ በሞት የሚታረም?
ማለት ይቃጣኛል
የዚህ ዓለም ኑሮ
ጥያቄ ወርውሮ
ምላሽ ያሳጣኛል፡፡

ደሞ አንዳንዴ ሳስብ
ስለሰው ልጅ ስራ
የሰናፍጭ ቅንጣት በምታክል ጥበብ
የሚንድ ተራራ
በጨለመ ምድር፤ ብርሃን እሚዘራ
በሰማይ ጎዳና፤ ወፍ የሚያሰማራ
ባህርን የሚያጠምድ ፤መብረቅ የሚገራ፤

ከቀለሞች መሀል ፤ ምስል የሚያነቃ
ከዝምታ መሀል፤ የሚያፈልቅ ሙዚቃ
በቃሉ በጣቱ
በቅመም ቅንጣቱ
ዘልቆ የሚያክመኝ
እንደ ሳንዱቅ ከፍቶ፤ መልሶ እሚገጥመኝ
ይህንን ሁሉ ሳይ፤ ህይወት እየጣመኝ
መኖር መኖር መኖር፤ መኖር ነው የምመኝ ፤

@getem
@getem
49👍30🔥10😱2
አለመሳቅ እኮ ይቻላል...
-----------------------

አለመሳቅ እኮ ይቻላል -
አለማልቀስ ነው ጭንቁ፣
የመንፈስን እንጉርጉሮ -
በመንፈስ እምባ ማመቁ፣

ውስጥ ውስጡን እየደሙ -
በቀቢፀ ተስፋ መድቀቁ፣
ለተስለመለመች እውነት -
የደም ደብዳቤ ማርቀቁ፣

በቅሬታ ሰደድ እሳት -
ህዋሳትን መጨፍለቁ፣
አለመሳቅ እኮ ይቻላል -
አለማልቀስ ነው ጭንቁ።

- ደበበ ሰይፉ

@getem
@getem
@paappii
71👍45🔥7🎉4
ሰይፉ ወርቁ

@getem
@getem
55👍31
አንተ እንባዬ ምረጥ
ልግለጥህ?
ልዋጥህ?
ላፍንህ?
ልልቀቅህ?
ላፍስስህ
ላምቅህ?
ምን ላርግህ? ምከረኝ
ምንድነህ? ንገረኝ

እህል ትሆን ጠፊ?
ወይስ ሽል ነህ ገፊ?
በጊዜ ልወቅህ...
ላቅርብ ወይ ላርቅህ...
አጫጅ ነህ አራሚ?
ተጓዥ ነህ ከራሚ?
አላፊ ነህ ቋሚ?
ምንድነህ?
ምን ላርግህ?
ላግድህ?
ላውርድህ?
ጋርጄ ልካድምህ?
አውርጄ ልካድህ?
ቢያፍኑህ ቀሪ ነህ?
ቢለቁህ ኗሪ ነህ?

እንባዬ ምን ላድርግህ?
ላስርግህ?
ልጥረግህ?
እንዳ'ይን እንዳ'ፍንጫ
ቋሚ መገለጫ
መታወቂያ መልኬ ፡ ሆነህ ትኖራለህ?
ወይስ ላ'ንዴ ወርደህ፡ በዚያው ትቀራለህ?

አንተ እንባዬ ምረጥ
ላብስህ?
ላልብስህ?
ወይስ እንዳላየ፡
ከኔ የወጣ ሁሉ፡
የኔ አይደለም ብዬ
ልተውህ እንባዬ?

ወይስ ልገላገል?
እውነቱን ልናገር?
እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ
እያልኩኝ ከማበል
አላውቅህም ልበል?

By #red-8

@getem
@getem
@paappii
50👍38🔥8
አንቺን ያየ ምድር አንቺን ያየ ሰማይ

ስንት ዐመት ቀጠለ በስፍር ዕድሜው ላይ?

።።።።።።።።

በጠለቅሽበት ጥግ

መውጣት ስላቅ ሆነ ፀሐይ ቀረች አፍራ

እኔም ደስታ እንዳለው

ማልቀስ ይከብደኛል በሳቅሽበት ስፍራ።

የት ቆሜ እንባ ላፍስስ የት ልበል እዬዬ

በሳቅሽ የፈካ

አይታዘበኝም ዛፍ ቅጠሉ እያዬ?

ምድር እንዳይንቀኝ

በወንዙ በሀይቁ ቀልዬ እንዳልገኝ

በነፋሱ ትዝብት እንዳላንስ ወድቄ

ለፍጥረት እይታ በሳቅ አሸብርቄ

እስቃለሁ ለጉድ እንከተከታለሁ

እንጂማ

ሳቅሽ ዳር ብፈለግ የእውነት የታለሁ?



እና የኔ ኪዳን

መቼ ልትወጪ አሰብሽ?

እንዳያፍር ምድር እንዳያፍር ሰማይ

እግዜሩም አልሠራም ጠልቆ ሚቀር ፀሐይ!

አባባይ ሆንኩልሽ የእሹሩሩ ካድሬ

ጨለማውን በሳቅ ሳባብል አድሬ

እንቅልፍ ቢወስደው ከዛለ መዳፌ

እንባ እየናፈቁ መሳቅ ሆነ ትርፌ።

እንደሰው ሲደክመው ሌቱ ሲያንቀላፋ

አማጥኩኝ ለለቅሶ እህህህ አልኩኝ ለሳጌ

ሁሌ ምገኘው ግን ከፈገግታሽ ግርጌ።

የሳቅሽን ዘቢብ

ምን መልአክ ቀመሰው ምን አማልክት አየው

የፈገግታ ጭረት ፊቴ ማይለየው?

አንቺ…

ሕይወት ክንብል አለ ቆመ ተዘቅዝቆ

ዘላለም ይሠራል አንድ ቀን ተስቆ?



ዙሪያዬን ሳቅ ከቦኝ እምን ላይ ልደገፍ

እንባዬ ያምረዋል እዚም እዛም መርገፍ።

ያሰኘኛል ዋይታ

ዕድሜዬን ማዋዛት በሀዘን ማለዘብ

ግን ትልቅ ሀጢአት ነው

ከቁርባን ፊት ቀርቦ ቁርባኑን መታዘብ።

ሜሮን ነበር ሳቅሽ ሀዳስ የሳቅ ጠበል

ፅድቅ ነበር ለሰው

ያንድ ቀን ደስታሽ ስር ዳስ ሠርቶ መጠለል።



መቼ ልትወጪ አሰብሽ?

መቼ ልትመጪ አሰብሽ?

በፍጥረት ልብ ላይ ጎጆውን ቀልሶ

ሳቅሽ አንጀት በላ እንዳራራይ ለቅሶ።

አበባው ይስቃል

ቅጠሉ ይስቃል

እሾሁ ይስቃል ድንጋዩ ይስቃል

አፈሩ፣ እሳቱ ነፋሱ ይስቃል

አንዴም ሳያነባ ሰው እንዴት ይፀድቃል?

ሳቅሽ ወንጌል ሆነ ምጻት መፋረጃ

ውስጤ እንባ ደርድሬ

ለብይን ብጠራ አቋቋሜን እንጃ!

አቤት አቤት አቤት

ከአምላክ ከፍጡር ከማነው ወገኑ

ሺህ ኩነኔ መሃል ሳቅሽ መጀገኑ!

አንቺ የሳቅ ኪዳን

ሩቅ ነሽ ለህመም ቅርብ ነሽ ለመዳን

እኔ ግን ተመኘሁ

በፈገግታሽ በኩል እንባዬን ልነካ

አንቺ…

ማልቀስ በመፈለግ ሳቅ ይረክሳል ለካ።



አንድ ቀን ስቃልኝ

ስፍር ዕድሜዬ ላይ ዕድሜ መርቃልኝ

የሰማይ የምድሩን መሳቅ አስለምዳው

ልክ እንዳመጣጧ ብትጠልቅ ወዲያው

ሕይወት ድፍት አለ ቆመ ተዘቅዝቆ

ዘላለም ይሠ
ራል አንድ ቀን ተስቆ?

By yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
👍4330🤩4🔥3
ድንኳን አይጥሉለት፣
ጥየቃ አያውቀው፣
ሰአቱን መጠበቅ ቀን ማወቅ አይለቀው፤
ሁሌ አብሮ አይኖር፣
ሁሌ መጪ እንግዳ፣
ሁሌ ምቾት ነሺ የሰባት ቀን እዳ፤
ሁሌ ተባበይ ባይ፣
በመጣ በታየ፣
ሁሌ የመድሎ ልጅ በጾታ የለየ፤
ሁሌ ፊት አደብዛዥ፣
የዙር አመል ከላሽ፣
ሁሌ ተጠባቂ ሁሌ መቶ ረባሽ፤
የልምላሜ መልክ፣
ከመባረክ ጓዳ፣
የሔዋን እጣ ነው ክቡር የሤት እዳ።

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@paappii
32👍16🤩5🔥3
ባዶ እኮ ነች።
(የሞገሤ ልጅ)
መጀመርያ፣
ኑ እንፍጠር በመባባል አምላክ ራሱን ሳያማክር፣
ዘረጋግቶ፣
እውን ሆነው እስኪታዩ እስኪኖሩ ምድር ጠፈር፤
ለባዶነት፣
ያጨው ነገር ለመኖሩ ስለማናውቅ ምንም ባንል፣
ምድራችን ግን፣
ከአካሏ ተቀናንሰው ሳር ቅጠሉን እስክታበቅል፤
አሁን ጠባ፣
በቤት ላይ ቤት እንዲሰራ ሠው ወገኗን ያስገደደች፣
ዛሬ ሳንደርስ፣
ጅማሮዋን ብቸኝነት ያካረማት ባዶ እኮ ነች።
ልክ እንደሷ፣
ሃ ማለቴን አፍ ሳይሆነው ጅማሮዬን አብሮት ሳይቆም፣
አሁን መቶ፣
ሄደሽ መቶ ባዶነቴ መከበቤ ቢደመደም፤
ባዶነቴ፣
አዲሥ ሕይወት አዲሥ መንገድ እንዲያመጣ ምድር ሆኜለት፣
መከፋቴን፣
መቀየሩ ስለማይቀር ባዶነቴን ገጠምኩበት።

ገጠምኩበት..

አልወደኩም፣
ሆኖ ሲታይ ባልጣለው ፊት ላልወደቁት ሲመሰክር፣
ያሳምናል፣
የአይን አዋጅ ለሆነበት ዝናን ማድመቅ ቀሪን መቅበር።

አንድ አንዴ ግን፣
ግዳጅ ጥሎ ፎካሪ ላይ ተሽመድምዶም መዘባበት፣
ቀን ያወጣል፣
ወድያ ወዲህ ተንጎራዳጅ አምላክ ፈቅዶ ከዞረበት።

ያን እለት ግን..
ራሱን ሆኖ ከጣለው እጅ ተፍገምግሞ የተነሳ፣
ባዶነቱን፣
ምርኩዝ ስጡኝ ባላለ አፍ መተኛቱን እስኪረሳ፤
ተመርኩዞ፣
ሲደጋግፍ ቆሞ ሊታይ የራሱ ቀኝ ራሱ ሆኖ፣
ባዶነቱ፣
ኃይል ይወልዳል ብርቱ ጉልበት ከድካሙ ተሰናስኖ።

ባዶ አረግሺኝ?

እንኳንም ሆንኩ!
አንቺን ይድላሽ፣
ግን ጨርሰሽ አትራቂው ብቸኝነት ከሚጠላሽ!

ለምን አልሺኝ?

ካልሺኝ እማ..
ምንም መሆን ምንም ነው፣
ለባዶነት ልኩ ያንሳል፣
አለመኖር ካጣ ፍጥረት ጉድለት ሞልቶት በዝቅታው ሺ ይብሳል።

ባዶነት ግን..
እርቃን መሆን ሸክሙ ከብዶ፣
ቋጠሮውን ለማላላት፣
አዲስ መንገድ ይፈልጋል፣
አዲሥ ነገር ለማሳየት።

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@paappii
👍3216😱3🤩2😢1