ግጥም ብቻ 📘
65.6K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
..........


በመዳፌ ጠፈር ዳሳሽ
በኣይኖቼ ህዋን አሳሽ
አፈር ድንጋዩን መርማሪ
ፀሀይን በጥፊ ኣብራሪ
ጨረቃን በኩርኩም ቀባሪ
በውርቅያኖስ የምግሞጠሞጥ
ከንፋስ እጥፍ የምሮጥ
ጉም ዘጋኝ በመዳፌ
በኖህ መርከብ ቀዝፌ
ከጥፋት ውሀ ተርፌ
ቅንጥብ ዘንባባ ቀጥፌ
ኣዲስ ምዕራፍ የማበስር
ብኩርናዬን የማልሸጥ በምስር
በኮከብ ወደም ምጫወት
የማድር ከኣብርሀም ቤት
እንግዳ ያልሆንኩኝ እንግዳ
የሩቅ ዘመድ የቅርብ ባዳ
ከጲላጦስ ሸንጎ የምፋረድ
በደመና ይምራመድ
   ከሰባሰገሎች ኣንዱ
ወርቅ እጣን ከርቤ የገበረ
ንጉሱን ከበረት ኣይቶ እረኛውን ያከበረ
ከድንጋይ ከህጻናት ጋር
ሆሳእና ብሎ የዘመረ
እኔ ነኝ ብኩኑ ባሪያህ የጥበብህ ማሳያ
የሀዲስ ኪዳን ነብይ የኦሪት ሀዋርያ
   በሀሳቤ እሩቅ ተጎዝ
ባካሌ ከቅርብ የማድር
ቅንጣት እምነት የጎደለኝ
የሚነቅል የተራራን ስር
እንኳንስ በደመና ላይ
በጠፈር ሰማይ ምድሩ
ሸክም ሆኖ የከበደኝ
የኣካሌ ክፋይ ኣፈሩ
ጉም መጨበጥ የምመኝ
የእጄን መና ለቅቄ
በሀሳብ ከኣብርሀም ያደርኩ
ከመንገድ መሀል ወድቄ
በኮከብ ወደሙ ቀርቶ
ጠጠር ማንሳት ያቃተኝ
ፍቅር መስቀል ይመስል
በየቀን የሚያቃትተኝ
አንድ ቀን ጠግቦ ለማደር
ብኩርናዬን የምሰዋ
ባገሬ መኖር ያቃተኝ
እንኳን በጠፈር ህዋ
ኣንድ ጉንጭ ውሀ የምለምን
ውርቂያኖስ መሉ ተፍቼ
ከሰገባ የማድር
ከስልክ እንጨት ስር ተኝቼ
ከጥፋት ውሀ ታዳሚ
ወይ ኣልድን ወይ ሰጥሜ ኣልሞት
እስትንፋስ አልባ የሆነ
የምኖሮ ትርጉም ኣልባ ህይወት
የኖህም መርከብ የራቀኝ
ለምግብ ጥንብ ኣንሳ የነቀኝ
መሲህ ፍለጋ ወጥቼ
ነብይ ይዜ የተመለስኩ
ሰባሰገል ተብዬ
ከሄሮድስ ጭፍሮች ያበርኩ
እንኳንስ ፀሀይ በጥፊ
ውቧን ጨረቃ በኩርኩም
ዝንብ ሽ ማለት ያቃተኝ
ሀሳቤ ብናኝ እንደ ጉም
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
በህልሜ ሁሌ ከደጅህ
ስነቃ ከተራራው ስር
ደራሽ በሌለበት ምድር
በሲቃ ድምጽ የምጣራ
ከመብረቅም በሚያስፈራ
የቅንጣት እምነቴ ተራራ ኣነቅል ቢለኝ
ተራራ ያሸከመኝ
ከገነት ያላደርኩ ከሲኦል ያልገባው
መሲሁን ጠቋሚ ኣንድ ኮከብ ያጣው
ወይ ድኜ ኣልድን ከስሜ አልጠፋ
ከፈራጅ ችሎት ዳኛ የማስከፋ
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
ወድቄ ያለው ከግርህ
ፍቅርህን የምሻ ልቤን ኣሽችቼ
ልክ እንደ ኣይሁድ ጎኑን ወግቼ
ከእቅፍህ ውስጥ ማደር የምመኝ
ብኩኑ ልጅህ
ባሪያህ እኔ ነኝ


   By  @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍3317😱5🔥3
ድልድይ ቢሆን ልብህ
ወደ ህይወት መሄጃ
ሞቼ አለመቅረቴን
መነሳቴን እንጃ
ማሻገርህን ያየ
ቢመሰክርም ሰው
ትረፍ ለሌላ ሟች
እኔ እንደሁ ሳይህ ነው
የምትፈራርሰው

By ዘማርቆስ

@getem
@getem
@paappii
22👍16🔥2
የዚች አለም ችግር
     ሁሌም ወደኋላ
የተራበው ቀርቶ
     የጠገበው በላ
እንዲህ ነው ምሳሌው
ሲተነተን ፍቺው
አንቺም የሌላ ሰው
እኔም ደግሞ ያንቺው

አወይ የኔ ህይወት
አወይ የኔ ተድላ
የማፈቅርሽ እኔ
የሚበላሽ ሌላ

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍3911😁9🔥5😱1🤩1
👍74🔥2😱1
አቦ.. እግዜር ተወኝ
'
'
ለምንድነው የማትጠራኝ
ለምንድነው የጠፋሁት
ቅዳሴው ሲሰማኝ
ቢራ ቤት ነው የነበርኩት

ለምን ከፋኝ በጭስ መሃል
ሳየው ያንተን የአምላክ ምስል ፣
መከራም እንዲህ ነው
ባለበት እዳ ነው አምላኩን የሚስል ፣

በቢራው አራፋት
በጃምቦው ብርጭቆ
ሀዘንህ ሲታየኝ ፣
ጨልጬ ብጠጣው
የማላይህ መስሎኝ ፣

ባዶ እስኪቀር የስካሬ ሞራል ፣
በማላውቀው ታምር
በማውቀው ቤተስኪያን
ድምፅህ ልጄን ይላል ፣

ለምን

ለምን እኔን ጠራህ
አሉህ አይድል በአጥርህ ፈርጡ
እነሱን ያዛቸው እኔን እንደሆነ
የለሁ ካጥረ ገጡ ፣

ተወኝ ልጠጣበት
ተወኝ አታሰማኝ የእርጋታህን ቃል ፣
ሙዚቃ ስጨምር ጭፈራ ሳበዛ
ለሽንት እንደወጣሁ
ያንተ ድምፅ ይሰማል ፣

ለምን...?እኔ መረጥክ
ተወኝ እግዜር ባክህ
ተወኝ ተወኝ አቦ ፣
አንድ በግ ስትፈልግ
ጠፍተው እንዳይቀሩ
ያሉልህ በደቦ ፣

እንዲህ ስናገር በሲጃራው መሃል
በጭሴ ውስጥ ቅርፁ
ያንተን መልክ ያሳያል

በስካሬ መሃል ይታየኛል እኔ
የሰከረ አምላክ የሰከረ ምስል ፣
አምላክም እንዲህ ነው
ባለበት እዳ ነው ጠፊ ልጁን ሚስል ፣

'
ግዕዝ ሙላት 🦘
@geez_mulat

@getem
@getem
@getem
👍5420😢11🤩3👎2🔥2🎉1
በድቅድቅ ጨለማ ወንበሬን አውጥቼ

መሀል መሬት ላይ ጨረቃ እሞቃለው

ወፎች ሲዘምሩ ቁጭ ብዬ አደምጣለው

ወደ ላይ ቀና ስል...

የጨረቃ ብርሃን አይኔን ይወጋኛል

ሙቀቷ እሳት ሁኖ በላብ ያጠምቀኛል



           ''አ      ዎ!      አሁን ይበቃኛል''

          ''ከዚ በላይ ብቆይ ምቀልጥ ይመስለኛል''

          ብዬ አሰብኩና...



ጥላውን ፍለጋ ወደ ቤቴ ገባው

ከቆጡ አልጋዬ ለመተኛት ሳስብ...

የ አልጋው ዝቅታ ሰላም ስላልሰጠኝ

ከፍ ካለው ቁርበት ከላይ ተንጋለልኩኝ..



አይኖቼን ገልጬ ድብን ብዬ ተኛሁ

ሰዉን እየረበሽኩ በደንብ አንኮራፋሁ

እንቅልፌ ሲመጣ ...

እንቅልፌ ሲመጣ ከ ሰመመን ነቃሁ;




          ነግቷል መሰለኝ ሰማዩ ጨልሟል

          ኮከቦችም አሉ ደመናም ደምኗል

          ሊዘንብ ነው መሰል ልብሴን ቶሎ ላስጣ

          ዝናብ ዘንቦ ሳያልቅ ፀሀይዋ ሳትመጣ::



    ዘይድ ሁሴን
   ታህሳስ -15 -2017

@getem
@getem
@getem
61👍45😁28🤩9👎4🔥1
ሎጥ ነሽ
🦘

ቅጥልጥል ፥ብግንግን ፥እርር እምር  ፤
ዝምም፥ ልምም ፥እድር ፤
እፍን፥ እምቅ ፥ላጀብ ፥ብድር ፤
ለወዝ ላይላፋ ፥ለዳገቱ ስብር ፤
ተንስኢ ላስነግር ፥በዋጉ ሰው አንዲር ፤
እኛ...እ'ድር..እኔ ላብር ፥ለራስ ሳድር ፣
ላለም ደረት ንፍት፥ ለራስ አንገት ስብር

'
'
ላክል ፤
ባክል ፤

ላንስ ፤
ዳንስ ፤

አይሆን ላይሆን ፥
ላገር ስሪያ ማሰሪያ ፣
መች አምሳሏ ነበረ፥
ያከበረችው ጥያ ፣
ቀጥ ብላ ማንጋጠጥ፥
ሎጥነሽ ወይ ?ኢትዬጵያ....
'
'
ግዕዝ ሙላት 🦘
@geez_mulat

@getem
@getem
@getem
👍318🔥5😱3
“ስኬተኛ ማነው ?”
ብዬ ጠየቅኋቸው
ታዋቂ አመጡልኝ
ይሄ ነው መልሳቸው ።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

አሳዩኝ ከበርቴ
ባለ ንብረት ፣ ነዋይ
እንደዚህ ያለውን
ቀና ብዬም አላይ።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

አመጡልኝ ምሁር
ፊደል የቆጠረ
የተመራመረ
ይሄም አልሰመረ።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

ጠሩ ባለ ጥበብ
በጥሁፍ በቅኔ
ያስገኘልን ረብ
(በርግጥ ጥሩ ነበር
እንደዚህ ሲታሰብ )
መልስ ግን አይደለም።

አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …

አንድ አጩ ቀጥሎ
ጽድቁን አደላድሎ
ያናናቀ ሞቱን…
የቃል ጥሩር ለብሶ
ያስታጠቀ ነፍሱን…

አገኙብኝ መልሱን !

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
👍4730🤩3
ወዳንቺ እዘረጋለሁ!
ባድግ ብዬ
ባውቅ ብዬ
አንዳች ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ!

መቃብር ቤቴን ማሞቂያ
የሙት መንደሬን ማድመቂያ
ካለፉም ወዲያ መታወቂያ…
የምትሆን
አንድ ሀተታ
አንድ እውነታ
የህይወትን ምናልባት
የመኖርን እልባት
አውቃት ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ!

ከሰማይ በታች አዲስ ነገር
ከምድር ከፍ ብሎ የሚነገር
“የከንቱ ከንቱ” የምትባል
የአላዋቂን ፈላስፋ
በአፍጢሙ የምትደፋ
ስታቅፊ ዐለም እንደሚጠቀለል
ስትገፊም ሰውነት ከላባ እንደሚቀል
ስትስሚ ኢምንት እንዲሆን ጠፈሩ
ስትነክሺም ማንነት እንደሚበተን አፈሩ…

ይቺን ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ
የህይወት መስመሬን ማንቂያ
ውሎ አዳሬን መደበቂያ
ተስፋ ህልሜን መታረቂያ
የምትሆን
አንዲት ሁነት
አንዲት ኪነት
የመክረምን ፍልስምና
ከንቱነት ላይ ውብ አድርጋ ሸምና
ታውቀኝ ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ ካልተረሳሁ ምናልባት።

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
👍3117
@getem
     @getem
          @getem
👍282
ለተለያዩ የማስታወቂያ፣ የዘፈን ክሊፕ እና ድራማዎች ስራዎች በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ የሚኖሩ ሰዎችን ካስት ማድረግ እንፈልጋለን። - እድሜያቸው ከ35-45 - ከ25-30 - ከ10-18 ያሉ ወንዶችን እና ሴቶችን በአስቸኳይ እንፈልጋለን። የሚከተሉትን በቴሌግራም ይላኩልን። - 1 ሙሉ ሰውነት የሚያሳይ ፎቶ - 1 ከወገብ በላይ - 1 ፈገግታ የሚያሳይ ፎቶዎችን - ስም ስልክ እና እድሜ በሚከተለው አድራሻ ይላኩልን። https://t.me/Ribki30 ስልክ የሚደወልላቸው ለስራው ሲመረጡ ብቻ ስለሆነ በትዕግስት ይጠብቁ ዘንድ እንጠይቃለን።
👍193
ነበርሽ ፤…
የጠዋት ፀሐይ
በቀስታ ደም የምታሞቅ ።

ነበርሽ ፤…
የዓለት ስር አበባ
ድንጋይ ተደብቆ የሳቃት ።

ነበርሽ ፤…
ልሙጥ የሻይ ብርጭቆ
ወገብሽ የሚያቃጥል ፤

ቀስ አድርገው
አለሳልሰው
እፍፍ ብለው
ልካቸው ድረስ አብርደው
በከንፈርሽ የሚቀምሱሽ ፤

ነበርሽ ፤…
ለሕይወት ተኩል
ለሞት አምስት ጉዳይ ።

ቴዎድሮስ ካሳ

@getem
@getem
@getem
👍4811👎3🤩3
ዕዳዋ የለብኝ~አበዳሪ አይደለች
ደም አልተቃባችኝ~ዘመድ አልገደለች
አላስቀየመችኝ~ተናግራ ክፉ ቃል
እንከን አጣሁ ተብሎ~ሰው እንዴት ይራቃል?
ወይ አይደለች ሻማ~ጨርሼ አላነዳት
አንዳች አልሰረቀች~እንዳላሳድዳት
እንዴት ብለከፍ ነው~ስትርቅ የምወዳት?

ዘማርቆስ
By @wogegnit

@getem
@getem
@getem
58👍26😢6
❝ ሣቅ ተከሽኖ ግጥም ተመጥኖ ❞ ታላቅ የመክፈቻ ፕሮግራም በግዮን ሆቴል !

  ዘሃ ኢቨንትስ ከግዮን ሆቴል ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት ፤ 4ተኛ መድረኩን አርብ ታህሣሥ 25 - 2017 ዓ.ም ምሽት ከ10 : 30 ጀምሮ ያቀርባል ።

ጋሽ አያልነህ ሙላት ፣ ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህና ኮሜዲያን ደረጄ ሀይሌ የክብር እንግዶቻችን ናቸው ።

  የምሽቱ ፈርጥ ልዩ የክብር እንግዳችን አርቲስት ዓለም ፀሀይ ወዳጆ ናት ።

ደራሲና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም እና ሰለሞን ሳህለ ውብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ።

  ኮሜዲያን ናሆም በየነ መድረኩ ላይ ይደምቃል ፤ የአብጸጋ ተመስገን የተከሸነች ወግ አዘጋጅቷል ፤ ፈገግታ ባንድ ጥዑም ሙዚቃዎቹን አሰናድቷል ፣ ሒስ ፣ አጭር ፊልም ፣ ስዕልና ሌሎች ብዙ ትርዒቶች ተዘጋጅተዋል ።

  ለበለጠ መረጃ በ 0935697143 ይደውሉ ።

የ YouTube ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👍

https://youtube.com/channel/UC9ItbVvxXMLV7QIT-rCJyTg?si=Mj5GlhjsE1ZvBtjM

@getem
@getem
👍20🤩32
አቀርቃሪ አሉኝ፣
ቀና ብሎ ማየት መራመድ ሲሸሸኝ፣
ሊያብድላት ነው አሉኝ፣
በቁሜም በሕልሜም ቅዠት ሲረብሸኝ።

ሊረታ ነው አሉኝ፣
ስንቀጠቀጥላት ስሟ ትዝ ሲለኝ፣
ትክክል ናቸው ወይ፣
እኔ ከምወስን እናንተ ንገሩኝ?

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@getem
31👍17🤩7👎3😁2
.............



ትብታብ አይደለም ድግምት
ደብተራ አይደለም አስማት
ንጹሕ ፍቅር ነው ምናኔ
ለሚወዱት የመሞት ጭካኔ
እንኳን አሁን፤ከገላዬም ደም ቢነጥፍ
ደምስሬም ጅማቴም
ስምክን ነው የሚጥፍ
ዘረ ደሀ አፈቀርሽ
ዘራችንን አረከሽ
ብለው ቢያጠምቁኝም
ለፍቅርህ ስለሆን
የክፉዋች ጸበል፤መድን አይሆነኝም
ይልቅ በዛብህ፤አንጀትክን ሰብስብ
ከዛሬ ይልቅ፤ነገህን አስብ
አይዞህ በዛብህ፤ይህን ቀን ቻለው
ሰብለ ወንጌልህ
ከአትሮንስ ወርጄ ተጠፍሬያለው
ግን አትሳቀቅ፤ይህም ቀን ያልፈል
የክፉ ጅራፍ፤ጽናት ይጽፉል
የሚለው ቃሏን፤ከፍቅሩ ሰምቶ
በተስፋ አባብሎ፤ልቡን አጽናንቶ
ከተማ ገብቶ ቢጠብቃትም
ወንጌሉን ካሻው አላገኛትም
የእግዜር ኑዛዜ፤የእውነት ቃሉ
የአዳም ጥፋት፤የአምላክ አምሳሉ
የሄዌን ስህተት፤ክፉይ አካሉ
አትብላ ካለው፤ከፍሬው በልቶ
ፍቅርን በደለው፤የሞት ሞት ሞቶ
ግን በበዛብህ፤ቃሉ ልዩ ነው
ከህይወት መስቀል፤አዳኙ ማነው
አዳም ከበላው፤በለስ ሲያላምጥ
ከወንጌል ይልቅ፤ልቡን ሲያስበልጥ
ፍቅርን በደለው፤የኑሮ ጣጣው
በቃሉ አኑሮ በእውነቱ ቀጣው
ድሮም ያን ጊዜ፤በኦሪት ዘመን
ክፉ ጎልያድ፤በሀይል ሲዘምን
ጉልበቱን ነስቶ፤መሬት ያኖረ
ጠጠሩ ሳይሆን፤እምነት ነበረ
በማፍቀር እምነት፤ነፍሱን አጽንቶ
ቢጠብቃትም ከተማ ገብቶ
ወንጌሉን አጣት፤ከባዕድ ሀገር
የህመም ጥልቁን፤ለማን ይናገር
ህልሙን አለሙን፤ሁሉንም ትቶ
አቅሉን እስኪስት፤ወንበዴ እጅ ገብቶ
በፍቅር መስቀለ የተሰቀለ
ኤሎሄ አይደለም፤ሰብለ ነው ያለ
የእግዜር ማቅ ለባሽ፤አንቺ መነኩሴ ሴት
እረፍትን ፍለጋ፤ከገባሽበት ቤት
ካልጋ ያገኘሽው፤እሱ ነው ወንጌልሽ
ጣር ባሰረው ድምጸት
ሰ...ሰ..ሰብለ ብሎ የሚልሽ
እንዲ ነው ፍቅር፤እንዲ ነው ስቅለት
እንዲ ነው መሞት፤እንዲህ ነው ድህነት
ፍቅር ቢበድል፤የእውነት ልኩ
ወንጌል ያጣ ሰው፤ወንጌል ነው መልኩ

Based on ፍቅር እስከ መቃብር

    by  @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍3731😁1
የነገዬ ምርኩዝ የትናንት መፅናኛ

የህይወቴ ትርጉም የጊዜ መዳኛ

መራመጃ መንገድ ህመምን አስረሽ

የፅልመቴ መብራት እኔን አስታዋሽ


          ጣዕም ሰጭ ስኳር ህይወት ማጣፈጫ

          የዛሬን ትካዜ

          የዛሬን ፍዛዜ

          በያልፋል ደስታ ስሜት መቀየጫ


የዋሻ ውስጥ ጮራ ፍንጣቂ ብርሀን

የህይወቴ ካርታ የመርከቤ ካፕቴን

ትርጉም አልባን እኔን ሀዘን የወረረኝ

ከጥልቅ ትካዜ ውስጥ ወዝውዞ ያነቃኝ

ተስፋ ነው ሻማዬ...

ተስፋ ነው ሻማዬ

የትናንትን ፅልመት ዛሬን ያበራልኝ
     
By ዘይድ ሁሴን
   ታህሳስ -27 -2017

@getem
@getem
@getem
34👍30😢4🔥1

.
ልደትህን ሳስብ
ሳነሳና ስጥል

በጥሞና ሆኜ
ደግሞ ሳሰላስል

ንጉሥ ሆነህ ሳለ....

በጠባብ ሰዉነት
ከሰማይ መዉረድህ

ከበጎቹ ግርግም
ወርደህ መተኛትህ

ነገረ ልደትህ
በታወሰኝ ቁጥር

እኔን ይገርመኛል
እጹብ ያስብለኛል

የዓለምን ደስታ
ብስራትን የሰሙ

እነዛን እረኞች
መሆን ያስመኘኛል።

By ዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
72👍20👎1
እንኳን አደረሳችሁ✝️

@getem
30👍8
ቢሆንም


ፍቅር ይሉት ጣጣ  ሲፀነስ
ሰው ከሰውነቱ ላይ  ሲቀነስ
አይተናል
          
አይተናል  የነበር ፍቅር ሲለፈፍ
በከሸፈ ፍቅር   ጤንነት ሲቀሰፍ
አይተናል


ፍቅር  የመርገምት ቃል እስኪመስለን
ከእጦት በላይ  ንቀታቸው ያቆሰለን
አይተናል


በጫማቸው  በረገጡን
ከትቢያ ላይ  ባስቀመጡን
ላቀመሱን የፍቅርን ፅዋ  መራር ጣዕም
ልክፍት ነውና
    ይሄው እስከዛሬ  እንፅፋለን ግጥም


ቢሆንም

በዬ ዘፈኑ  ሆድ የባሰን
የናፍቆት ህመም የዳበሰን
አንድ ሰው ለመውደድ   ዘመናት ያነሰን
ስንት አፍቃሪ አለን
         የትዝታ ፈረስ  ወስዶ  ሚመልሰን


የማይመጣ እንደሚጠብቁ  ቢታወቅም ቅሉ
በአልኮል በሲጋራ  በጫትም ገረባ የተጠለሉ
ከእልፍ አእላፍ የበዙ   ስንት ልቦች አሉ ?


By kerim
@poem2513

@getem
@getem
@getem
👍6424
ባያቸውስ ኖሮ ?
(ሚካኤል አስጨናቂ)

እርግት ያለች ወተት
ስክን ያለች ቡና …
ይሄን ችኩል ዘመን
አልዋጀችምና …
ተንገበገብኩላት
ተሳተብኝ አቅሌ
ሆንኩላት ባተሌ ።

ጥልል እንደ ጠላ
ኩልል እንደ ጠበል
ከአንገቷ ስር ገነት
ገድ ጥሎኝ ብጠለል
አ..ን..ሰ…ፈ…ሰ…ፈ…ች….ኝ
አ…ር..ገ…ፈ...ገ…ፈ…ች…ኝ
ቃላት ሳ’ተነፍስ
ጥርሶቿን ሳትገልጥ
ቅቤ ሆነ ልቤ..
ገጽዋ ላይ ሲቀልጥ ፤

ያን ጊዜ ተቃናች !
ብታጣብኝ ኩራት
ስስ ጎኔ ቢገርማት
(ዓይኖቿ ፍም እሳት)
አንገቴን ሰበርኩኝ
ፈርቼው ይሄን ፍም
ቢሆንም …
ቢሆንም …
ለዓይኖቿ አፀፋ
መስጠት ሳልፈልግም
ለንቋሳው
……………………….. ተንጋለልሁ
ለዚ’ች ሞቃት ግርግም
:
ደረቷ ላይ ፍግም !

@getem
@getem
@paappii
👍469🤩2