ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ለሀሳቤ ረሀብ
ነሽ ጥም
ቀን ከሌት ባስብሽም
አላስታግስ
አልረካሽም


ሌት ነሽ ብርሀናማ
ሲነጋጋ
ወይ ሲጨልም
መልክሽ መንታ
ሆኖ አይለይም ።






አለሽኝ እያልኩ እያለ
ደሞ የሄድሽ ይመስለኝና
ህልም ነው ብዬ እንደመባነን
ከሀሳብ እንደመንቃት እልና

ሌላ ህልም

ሌላ ሀሳብ
.
.
.
.
.
.
.
ምክያስ አለምሰገድ (mik)

@getem
@getem
@getem
👍2412🔥1
, ፍልቅልቅ

ለጋው ሽንጥሽ ጯርቃ እጆችሽ
ጣፋጭ ማዛ ውብ ጠረንሽ ጨዋታዎችሽ
የልጅነት ፍልቅልቅ ጥርስና አይኖችሽ

አሁንማ ተቀይረው ጎልማሳ ሆነው
በቨሰለ ድርብ ስጋ ተሸፍነው ተከድነው
እንደድሮው ባይታዪም ከሩቅ ገነው
ብቻ ግን ባዬኋቼው ዳግመኛ የኔ ሆነው

መቼም እኔ ጭቀቴ ሀሳቤ ብዙ
ያባክነኛል ያንቺ ፍቅር መዘዙ

ማዕበል ፍቅርሽ ከልቤ ላይ ቋያ ፈጥሮ
ህዋሳቴን ያናውጣል እስትፋሴን ተቆጣጥሮ
ውብ ቀለምሽ ጣፋጭ ማዛሽ ጎልቶ ነጥሮ
ዳንኩኝ ስል ይገለኛል ይጥለኛል አሽቀጥሮ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
👍2210👎3
ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

እፈራለሁ እንዳልነገርሽ የውስጤን ውስጥ ጉዳጉዱን
እንዳትርቅህ የሚል ሃሳብ አሳሰበኝ እግዞ ስንቱን
ይበላኛል ንዴት ስሬን
አይታከክ እንዳላከው
ምን ስትይኝ ፈዛዛ ሆንኩ
ንፁህ ልቤን የባረከው
እቀናለሁ ሳይሽ ደግሞ
ሆኖ አንገትሽ ሌላ ዘንዳ
እህትህ ናት ይላል ልቤ
አካል ስጋ ሆኖ ባዳ
ጉደኛ ነኝ ኧረ እኔማ
ጉዴ ገና ያላለቀ
ጓደኛ ነን በሚል ሰበብ
እሳት ፍቅሬ ያልተወቀ
አልታጠኩም የድፍረት ሻሽ
ለመናገር የፍቅሬን ቃል
ይነደዋል የዋህ ሆዴ
ጥርሴ ደግሞ ስንቴ ይስቃል
ሲያወሩሽ ባያቸው እንደው የድንገቱን
    አሳሰበኝ እግዚኦ ስንቱን።

ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
43👍30😱5😢5🔥3😁1
የዘዉትር ምኞቴ
.
.
.
ከምድር ርቆ፤
በሰማይ መንሳፈፍ፤
ከምርምር ረቆ፤
በደስታ መሰለፍ።

ችግር ግሳንግሱን፤
ከመሬት ወርዉሮ፤
ጭንቅና ህመሙን፤
ስቃዩን አባርሮ፤

ከወፎች ዝማሬ፤
በጋራ መቋደስ፤
በምናብ ሀገሬ፤
ተፈጥሮን ማወደስ።
.........................................
በዔደን ታደሰ እንደተፃፈ
@ediwub
@getem
@getem
@getem
29👍11
Forwarded from Studio Anaya (Ribka Sisay)
አዲስ አበባ የምትገኙ በፅዳት የተያዘ ቆንጆ ቤት ያላቹ ለተለያዩ ማስታወቂያዎች ቤቶችን እያየን ስለሆነ የኪችን የሳሎን እና የመኝታ ቤት በደንብ የሚታዩ ጥሩ ፎቶዎችን ከእያንዳንዱ 3 ከስልካቹ ጋር @Ribki30 ላይ ላኩልን።
7👍6
እግዜር ግን ታያለህ?
እሷ እኛን ለመርዳት
መፈሸን ሳያምራት
በረዣዥም ቀሚስ ፣ እግሯን ብትሸፈን
ፀጉሯን በቀይ ሻሽ ፣ አግታ ብታፍን ፤
ብትመጥን ፣ ሳቋን
ብትሰበስብ ፣ ጣቷን
ብትሸሽ ፣ ብትሰወር
ቀን ባትወጣ ሰፈር
እኛን ላለመጣል
በውበቷ ዘገር …
ብትለፋ ብ’ተጋ
ለነፍሳችን ዋጋ
ከፈጠርካት ኋላ
ከስማም እንድታምር
ተሰናክለን ቀረን…
እሷ ምንም ብ’ጥር።


በማን ልትፈርድ ይሆን?

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
👍1711🔥11👎2😁1🎉1
, ጥላ ነው አመልሽ

ሰማይ አንቃሮ የሚያዬው
መቼም ሳይደክመው አንገቴን
ኮከብ መቁጠሬን አልተውም
እንጨት ሰብሬ ጎጆ መስራቴን

ኖረሽ ሳትጠቅሚ ለሀገር
እኛም ሳናውቀው ሞተሽ
ተናገርሽ አሉ እጅ አውጥተሽ
ከመቃብር ላይ ዎተሽ
እሳር ቅጠል ሆኖ አንቺ እንደው ዘመድሽ
የኔ አዘን የኔ እንባ የኔ ሞት አይገድሽ
አንቺ እንደው መባከን ነው ድልሽ
አንቺ እንደው ጥላ ነው አመልሽ

ጥላ የዛፍ ጥላ የቤት ጥላ የቆጥ ጥላ
ከጨረቃ
ከኩቫኩብት ከፀሀይ ብርሃን ጋር የሚጣላ
ክፉ አመልሽ ጠዋት ታይቶ ማታ ጠፊ
ሲናገሩሽ ተሎ አኩራፊ ታዳሚሽን ገራፊ
ደጋፊና መራጭሽን ሆነሽ ገፊ
ታዲያ ለዚህ ሁሉ ወዳጅሽ ሳጠቅሚው
በምን አቅምሽ ነው
ከጥበብ ጋር ግብግብ የምትገጥሚው
ከሞትሽበት ከመቃብር ገና ዎተሽ
በጥላቻ ከፈታሻት ሚስትሽ ገና ታርቀሽ
ይልቅ ክፉ ጥላ አመልሽ
ጠልፎ እንዳይጥልሽ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
22👍18🔥1🤩1
የመስቀል ወፍ ቢልኳትም
መናፈቅን አታወጣው
መልስ ቶሎ እየተባለች
አክርማ ነው 'ምታመጣው

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem
33👍16🤩4🔥3
።  ።  ካለሽ አለሁ።። 

አንቺ ጎኔ ካለሽ ፀሀዪ ይደምቃል፣
ፍቅርሽ ገደብ የለዉ ከፍቅርም ይልቃል።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ጨረቃ ታንሳለች፣
ዉበቷ ያንስና ታቀረቅራለች።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ሳቄ ይመነጫል፣
ምንም ሆነ ምንም ጥርስን ያስከፍታል።
ገነትን ሳላየዉ ገነቴ ነሽ ብልም፣
ገነት እንደሚያምር አልጠራጠርም።
የሚያስጠላዉ ነገር
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ ፀሀይ ትጠፋለች፣
ማማሯ ያልቅና ወዲያው ትረግፋለች።
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ የለችም ጨረቃ፣
አንቺን ለመፈለግ ገብታለች መሰለኝ ባሕር ዉስጥ ጠልቃ፣
   ሄዳለች ርቃ።
ገነት እንደሚያምር ባልጠራጠርም፣
አንቺ ሲኦል ካለሽ መምጣቴ አይቀርም።
ስለዚህ ፍቅርዬ
የትም ብትገቢ እንጦሮጦስ ገደል፣
ተዘጋጅቻለሁ መከራን ልቀበል።
ምንም ብትሆኚ ሁሌ አፈቅርሻለዉ፣
ገሀነብም ግቢ እኔ ካለሽ አለሁ።

ማትስ ትምህርት እየተማርኩ xን ስፈልግ የተፃፈ ግጥም
ቀን ማክሰኞ 08:00 ቀን
ማጀቢያ ሙዚቃ : አለምአየሁ ኤርጶ ( ባይተዋር )
ምንጭ : እሷ ( xን እየፈለገች )
ገጣሚ : እኔ ( ስፈልግ አንቺን አገኘዉ )
.
By @papiel

@getem
@getem
@getem
👍57😁4422🔥8😱5🤩3
#የኔ_ሴት
.
.
.
ያየኝ የለም ቆላ አልወጣሁም ደጋ፣
አልንከራተትም የኔን ሴት ፍለጋ።
ይሁን ካለ አምላክ ከፈቀደው ጌታ፣
ያመጣት የለም ወይ ካለሁበት ቦታ።

✍️ ዓቢይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
70👍29🔥7🎉4🤩2
ላገባሽ ነው እንዳታገቢኝ
'
'

አመጣጤ እንዳየሽው
ሚያምር መስሎሽ አትሸወጅ
ምላስ ስንት ያሳልማል
ወንድ እስኪዝ በእጅ

አልጋየ ላይ እትት ስልሽ
ስታለፊኝ ከሌት አዳር
የሴት ልብ ሞኝ ነው
ከተወራ ስለትዳር

ላግባሽ ግን አታግቢኝ
ላግባሽስ አልፈልግም
ካልጋ ቤት ካልሆን በቀር
በቀለበት አንሰርግም

/ ላገባሽ ግን አልፈልግም.../

የሴት ጫካ ገብቼ
ሳድን ሳካልል
አንቺን ድንግል ህፃን
ጣለሽ ከመሃል

እንደው ላልጋ አስቤሽ
ላግባሽ ላግባሽ ስልሽ
ጠዋት ልፈታሽ ነው
አትመኝኝ ባክሽ

አግባኝ አግባኝ አትበይ
አፈቀርኩህ ፍቅር
ምናምንቴ ትዳር ፥
ኩችኩች ሆታሄ
ምናምንቴ ቁማር ፣
እኔ አልታመንም
እሽ ካልሽ ግን
ላግባሽ ከአንሶላየ ጋር ፥

አንሶላ ውስጥ ገብተሽ
" ልስጥህ ሴትነቴን "
ጠዋት እንለያይ
መልሽ ቀለበቴን

ቢጃማ አወላልቀሽ
ፊቴ ስትቆሚ
በራቁት ሰመመን
ወንድ ልጅ ዝም ካለ
ይቅርብሽ ማመን

ማፍቀሬን ሳስመስል
አይደለም የሴት
የአጋንንት ልብ ሸውዶ ይገዛል
ተይ አትመኝኝ
ወንድ ልጅ ሲያሸንፍ
ዝምታ ያበዛል

ላገባሽ ነው አልጋዬ ውስጥ
ልጥልሽ ነው ጥሎሽ ዕንባ
ላንድ ቀን ከሆነማ
ለአንድ አዳር እንጋባ

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii
👍6134😢17👎6🔥3😱3
Audio
ይነጋል
በዔደን እና አየሁ ተፅፎ እንደቀረበ
@topazionnn
@getem
@getem
15👍8
<<ምኗን ስመሃት ነው?>>
<<ማንም ያልነካትን ቦታ>>
<<ከአንገቷ ነው ከደረቷ?>>
<<ከምትፅፍበት ከጣቷ>>
<<እንዴት አርጓት ነበር?>>
<<ጥላኝ እስከምትበር>>
<<በል ንስሃ ግባ>>
<<አንድኛዬን...ቤቴ ስትገባ>>

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem
67👍33🔥9
ግጥም መፃፍ ምንም ነው
       በፈጠርኩት አንዳች አለም
ለደረሰብኝ ግን ግጥም ሚባል የለም

ይገርመኛል አንዳንድ ግዜ
     ግጥም ግጠም ስትይ ላንቺ
ጠንቋይ ለሱ አያውቅም ነው
             አንቺም ለኔ አትመቺ
ይገርመኛል አንዳንድ ግዜ
     እኔን ፃፈኝ ስትይ በቃል
ቃል ይከዳል
ቃል ይርቃል ለሚወዱት ይታወቃል
አንዱን ሃሳብ ለመጨበጥ
         ሃሳብ የትም ባክኖ ይቀራል
ለሚወዱት ለልብ ወዳጅ
     ግጥም መግጠም ያስቸግራል

የመውደዴን ትርጉም
በቃላት ሳልነግራት
    ታውቀዋለች ካይኔ
ግጥም ምንም ነው
ቃላት ምንም ነው
ለእንደሷና እንደኔ

አስር ብንዋደድ ብንከንፍ በፍቅር
ቃል የለኝም ላንቺ ግጥሙም ተይው ይቅር
ዝም ብዬ ልውደድ
ዝም ብዬ ላፍቅር

ገጣሚ ብባልም በሃሳብ በመስጠም
ላንቺ ሲሆን ጊዜ
ሲከብድ ግጣም መግጠም


ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍4110🔥3🎉2
ፍቺ በቃ ህይወት  እመቤቴን
አከሰልሽው አይደል ሰውነቴን
በቃ ተዪኝ ህይወት አልሰማሽም
የ'ስካሁን ገተታው አልበቃሽም?

ይመራል ኪዲዬን እዘኚልኝ

እኔም ልቅመስ እንጂ
ከውበቱ
እኔም ልኑር እንጂ
ከድሎቱ
አግቺኝ ማርሽን
ባናት ባናት
አቱኚብኝ እንጂ
የእንጀራ እናት

አይደብርሽም ግን ላንቺ እራሱ
ቀን በቀን ፈተና መነስነሱ
ተዪው ጅራፍሽን ወዲያ ጣዪው
አንጃግራንጃ ነው አርቲቡርቲ
እኔም እንደሰዎ ተመችቶኝ
እግዚአብሄር ይመስገን  ልበል እስቲ

አቦ ተመቺኛ  የኔ ቅመም
ስህተት ሰራህ ብለሽ አታኩርፊ
ልበ ቢስነቴን እያስታወስሽ
ጥቂት ጥፋቶቼን በሼ እለፊ

እመቤቴን ህይወት
ተረጋጊ
በአመት አንዴ እንኳን
እረፍት አርጊ
የት ሄድብሻለው
ካንቺ ጉያ
እረገጥሺኝ እኮ
እንደ አህያ

እመቤቴን ህይወት ከፋኝ በጣም
አመቤቴን ህይወት ተሳቀኩኝ
ከመኖር በስተቀር ዝቅ ብዬ
ሌላ ክፉ ነገር ምን አረኩኝ

እንዴ...

ፍቺ በቃ ወደዛ  አድቢልኝ
እንዳይኮረኩመኝ እጅሽ ታኮ
ብቻዬን አንጋለሽ አትደልቂኝ
እኔም ይከፋኛል  ሰው ነኝ እኮ

እንዴ..

ተስፋ እንኳን አድዪኝ ምናለበት
ለመኖር ልጓጓ  ብማረርም
እንደ ተልባ አትውቀጭ ሙከራዬን
ትዝብት ነው ትርፉ ሞት አይቀርም!


ፍቺኝ በቃ ህይወት!

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
38👍28🎉5🔥2
ሰባራ ልብ

ሰባራ ልብ የፃፈው ከንቱ ግጥም
ስሜትን ሰቅዞ ባይዝም እንኳ ባይጥም
ያፍቃሪን ሰው ህይዎት ባይለውጥም
እኔ ግን እፅፋለሁ ፊደልን አያይዤ
ከተውሽኝ ቦታ ሰባራ ልቤን ይዤ

የጨረቃ የክዋክብት ድብቅ መረብ
ሰማይ ወርዶ ከምድር ጋር ቢቀራረብ
የሌት ነፋስ
ብርድና ውርጭ ገላዬ ላይ ቢረባረብ
በዶፍ ዝናብ ምድር ቢጥለቀለቅ
እኔ እንደው ከተውሽኝ ከዛ ቦታ አለቅ
ታነሽኝ እንደው መተሽ አንሽኝ
እባክሽ ከሰው አታነሽኝ
መልኬ ቢገረጣም ባንቺ ፍቅር ደዝዤ
ብዙ መንገድን በሃሳቤ ተጉዤ
እጠብቅሽ አለሁ ሰባራ ልቤን ይዤ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
37👍15🔥8🤩1
( መጋረጃ ... )
==============

የልብሽ በር መስታወት ነው
ሠርክ የሚያሳይ ትላንትሽን
ዘውትር ከእርሱ እያፈጠጥሽ
አታበላሽ ተይ ነገሽን ....

አትስበሪው አትቆልፊው
ከመታገል ላይቀር ፍርጃ
ተከልለሽ ምታርፊበት
እንኪ የፍቅሬን መጋረጃ !!

By Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
39👍26🔥7🤩2
በቀን እንደሞትኩ...
(ሳሙኤል አለሙ)

ከአፈሩ አፈሩን ጥለነው
ከሰማዩ ሰማያቱን አልፈነው
ሄድን ሄድንና...
ከፈጣሪ የፍርድ መንበሩ ጋር ደረስን፤
ተረኛ ነበርና...
ደጃፉ ላይ ወንበር ስበን ተቀመጥን።
ተረኛ እስኪጠራ ፥ እስኪገባ ፈጣሪው ጋ
ትዝ ይለኛል ፥ ባንዲት ርዕስ ስናወጋ።

ሞትኩኝ...
የሚላስ የሚቀመስ አጥቼ
ሞትኩኝ...
"ትን" ብሎኝ ብፌ አሰናድቼ
ሞትኩኝ...
አልጋ ላይ ላመታት እንዳልነበርኩ ማቅቄ
ሞትኩኝ...
ስዝናና ውዬ ስመለስ ደክሞኝ መሪ ለቅቄ
ሞትኩኝ...
በተኛኹበት ወዳጄ ባልኩት በሰው ታንቄ
ሞትኩኝ...
ሞትኩኝ ሲሉ ፥ ኹሉ ኹሉም በየተራው
በቀኑ እንደሞተ ፥ ኹሉ ሰው ሚያወራው።

እኔ ግን...
እኔ ግን...
በቅጡ መኖሬን
በቅጡ መሞቴን ስላላወኩ
በቀኔ ሳይሆን በቀን እንደ ሞትኩ
አስታውሼ ነበር ፥ የተናገርኩ!


ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@getem
@getem
32👍29😱5🔥1
በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

@getem
@getem
@paappii
👍5321😢7
አዲስ አበባ የምትገኙ ከ 38 - 43 አመት ያላቹ ወንዶች እና ሴቶች ለተለያዩ ማስታወቂያዎች እየመለመልን ስለሆነ በደንብ የሚታዩ ጥሩ 3 ፎቶዎችን ከስልካቹ ጋር @Ribki30 ላይ ላኩልን።

ስልክ ቁጥራችሁን መላክ አትርሱ!
👍61🔥1
ሰላም ይሄ ተስፋ የተጣለበት አዲስ airdrop ነው።

https://t.me/nordom_gates_bot/open?startapp=Dp2sj2

እድሎን ይሞክሩ!!
👍2