ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የት ልንደርስ?
(ሳሙኤል አለሙ)

[እ--ወ--ድ--ሃ--ለ--ው
እ--ወ--ድ--ሻ--ለ--ው]
ባንዲት መኺና ፥ ሞልተው ሊሳፈሩ
መልዕክት መጣና
ተቀጣጠሩ።

እንደ ደረሱ...
ከአፍ መናኸሪያ ፥ ወደ ልብ ሊጓዙ
ለጉዞኣቸው መዳረሻ
ቆሎውን ኩኪሱን ገዙ።

ሊሞላ...ሊሞላ...ሊሞላ
ሊሞላ ሲል
አንተ ነ-ሃ
አንቺ ነ-ሻ
በመሃል ስንባባል
ለካስ ቃል ይደነግጣል።

ይኸው እያቸው...
የሞላውን ትተው ፥ በኔና ባንቺ ኩርፊያ
ይኸው እያቸው...
ወደ መጡበት ፥ ሊመለሱ በጥድፊያ
ይኸው እያቸው...
የጋራ ቃላችንን
ነጥለን ስናሳፍራቸው።

[እ]--[ወ]--[ድ]--ሻ--[ለ]--[ው]
--- --- --- --- --- --- ---
[እ]--[ወ]--[ድ]--ሃ--[ለ]---[ው]

#ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu


@getem
@getem
👍3510🔥3
እንቆቅልሽ ?
ምን አውቅልሽ
ድንግል ልጅ አገርድ ሁለት ልጆች ያሏት
አንድኛው ሲገላት ሌላው የሚሞትላት
ይቺ ምስኪን እናት መልስልኝ ማናት
ብለሽ ስጠይቂኝ
ምናውቅልሽ ስልሽ ሀገር ስጠኝ ያልሽኝ
ሁሉ በእጄ ብለሽ መልኳን ያጠፋሽው
የዝች እናት ሀገር
ግማሽ ገፅታ ነኝ ገለሽ የቀበርሽው

   By ዮም ብዕር

@getem
@getem
@getem
67👍32🔥14🤩8
, ፃዲቅ መሳይ

ነጠላ ለባሽ ፃዲቅ መሳይ
ውብ ሸጋ ልጅ አምሮባት ሳይ
ድንገት ተንደርድሬ ተጠጋኋት
ትኩር ብዬ ደግሞ አዬኋት
አዬኋት አው አዬኋት
ድብቅ ሚስጥር የልቤን በር ከፈትኩላት
ትገባ እንደው ብዬም ፈቀድኩላት
ልቧን ሳላውቅ ከሷስ ሌላ አለም ይብቃኝ
እያልኩ አወራለሁ መስሎኝ ልፅድቅ ምታበቃኝ
ፃዲቅ ያልኳት ለነብሴ የምትሆን
እንኳን ለኔ ለራሷም ሳትሆን
ነጠላ ለባሽ ፃዲቅ መሳይ ያረባች
ለራሷም ሳትሆን እኔን ይዛኝ ሲኦል ገባች

By @Habtishe01

@getem
@getem
@paappii
👍44😁2210😱4😢2
ጠያቂ
👇
ካየ ወዲያ በዓይኑ
እጣ ሲጣጣሉ
በልብስ ፣ በከፈኑ
ኢየሱስ ላይ ጅራፍ
እየሱስ ላይ በትር
ሳቁን ነጠቁበት
የዛን ደቀ መዝሙር።
ከፍቶት ቆየ ዘመን
በእንባና በሀዘን…
ቆየ ሳይገልጥ ከንፈር
ኑሮው ሲመረመር
ከዛች ቀን በቀር…
ያ ምስኪን ሙሽራ
በኗሪነት ተስፋ
የሰርጉን አልባሳት
ሸማውን ሊያሰፋ
በገቢያ ፣ እስኪያው
መቼ ነው ዮሀንስ
ትንሽ የፈገገው?

መላሽ
👇
ትንሽ ከንፈር መግለጥ
የፊት ገፅ መለወጥ
መስሎን እንጂ መሳቅ
የሀዘንን ቅኔ
ከቶ ስለማናውቅ
በዚህ በከተማ
በዚህ በትርምስ
በሰው ነጭ ግብስብስ
ነገን አለሁ ብሎ ፣ በሚኳትነው
ስንቱ ሞት መልዓክ ነው
ትንሽ ፈገግ ብሎ
በሳቅ የሚያለቅሰው!

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
👍4613🔥9
Audio
ያየህ ሰዉ በሙሉ ብርቱ ነዉ ይልሀል
ስትደክም አያዉቁህም በደጉ ያሙሀል

ታለቅሳለህ አይደል ትደክማለህ አይደል
ይርብሀል ይጠማሀል አይደል?

አንተም እንደሰዉ ተሰብረህ ተከፍተህ ታዉቃለህ አይደለ?

እንዴት አወክበት ........
እያነቡ እስክስታ
ማነዉ ያስተማረህ......
ስቆ ማለፍ
አይቶ መተዉ
ተማሮ ማመስገን
ተዳክሞ መጀገን

ማን😊

💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
👍3123😱4
ለግጥም አፍቃሪያ በሙሉ:-

የፊታችን ቅዳሜ አራት ኪሎ በሚገኘው በ #ዋልያ_መፅሃፍ_መደብር የ50ገጣሚያን ስራ የሆነው #ክንፋም_ከዋክብት የተባለው የግጥም መድብል ይመረቃል። እናም የለቱ ለት በ10 ሰአት ላይ በአካል በመገኛት ቀኖትን ያሳምሩ!!


@getem
@getem
👍255
ሲኖር የሚገርመኝ
አይደለም እንደ ሟች
ይሄ ሁሉ ተጓዥ ፣ ይሄ ሁሉ ዘማች ፤
ሁሉም ጥሬ አሳሽ ፣ ስብስብ ነው የዶሮ
አነር ያድነዋል ፣ እንደ ዱር መንጥሮ።
ከስብስቡ መኃል ፣ ባለቀን ሲነጠቅ
ሌላው ዶሮ ይጮኃል ፣ ፈርቶ በመሳቀቅ።
ሲሞላ ግን አፍታ
እየው አበክረህ
ወንድሙን የሸኘ
ያን አልቃሻ ዶሮ
ጥሬ ይናጠቃል
ዛሬም እንደ ዱሮ።
አይገርምም ?
አይደንቅም?
የሞት ማግስት ወጉ
አነርን ይረሳል የዶሮ ዝንጉ።
🐓

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
👍2521🔥6🤩1
የአንቺ ፍቅር ግራ የኔ ደሞ መሀል ፣
አንቺ እንድታምኚኝ በ44ቱ መማል።
ሆኖብኝ ፍቅርሽ የህልም ዉብ አዳራሽ ፣
መነሻ የሌለዉ ያላገኘ ደራሽ።
አንቺ አንድ አይነት ሰዉ ማትለዋወጪ፣
እኔ በአንቺ ፍቅር ፀባዮቼን ቀጪ።
ወይ የአንቺ አልሆንኩ ወይ የሌላ ሰው፣
በልቤ ይዤልሽ በዉሸት ልካሰዉ።



አንቺ ስትወጪ በብሶት የተገጠመ
ቀን ሰኞ 05:10 ሌሊት
ማጀቢያ ሙዚቃ : ልዑል ሲሳይ (አልጠላሽ)
ምንጭ:(እሷ)(ለዘላለም ተፈቃሪ)
ገጣሚ: እኔ (ለጊዜዉ አፍቃሪ)

Papiel16

@getem
@getem
@getem
25👍14😁11😱4😢4🤩2
, ( እንኳንም አወኩሽ )

እንኳንም አወኩሽ እንኳን አፈቀርኩሽ
ፀንተሽ ባትገኝም ፀንቼ እንዳመንኩሽ
እንኳንም አወኩሽ እንኳን አፈቀርኩሽ

አንቺን አቶ መኖር ህይዎት ቢከብደኝም
ለፍቅርሽ ታምኘ መሞቴ አልከፋኝም
አንቺ ግን ጨካኝ ነሽ
ሙት ብለሽ ገለሽኝ ግን አልቀበርሽኝም
ፍቅርሽ ማዕበል ሰርቶ ቢፈጀኝ እንደፍም
ለደስታሽ እዬኖርኩ ደስታሽን አልነቅፍም

እንኳን ጥለሽኝ ሄድሽ ከወደድሽው ጋራ
እንኳን ጥለሽኝ ሄድሽ ካፈቀርሽው ጋራ
እኔ እንደው
በደስታሽ እኖራለሁ ናፍቆትሽን ስጋራ
አዬሽ የከዳን መርቆ ሸኝቶ ሚናፍቅ
የእኔ አይነቱ አፍቃሪ የት ይገኛል ቢጠበቅ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
42👍24🔥5
( እያጠፉ ማረኝ ... )
==============

አምላኬ ...
ልቤ ከመንፈስህ
በቅጽበት ሲለያይ በቅጽበት ሲገጥም
ዘፈኔን ሳልጨርስ ትዝ ይለኛል ወረብ
የአባቶቼ ጥምጥም .....

ዘርፌ ስመለስ ፊትህ ተንበርክኬ
ለጉድ አነባለሁ
ዘሙቼ ሳበቃ በኃጢአት አልጋዬ
ጸጸት እጀምራለሁ
ብቻ ትቼሀለሁ ብቻ አልተውኩህም
ህግህን አፍርሼም ትናፍቀኛለህ
ልቤ አይረሳህም ....

እንጃ ለሰው ጆሮ
ነገር አኳኋኔ ቢጥምም ባይጥምም
በሞትክበት ቅጽበት ላዳንከኝ ደግ አባት
በበደሌ ቅጽበት ማረኝን አልተውም !!

@Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
60👍23🔥6🤩3
ጨረቃ


ነፋሱ ይነፍሳል
ውርጩ ይጋረፋል
አራዊት ይጋፋል
ሰካራም ይዘፍናል
ጨለማውም ገኗል


ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ
በሌት እያዜምኩት
ቀጠሮ ይዤ ነው
ደጅ የተቀመጥኩት
ከጨረቃ ጋራ
የሆዴን ላወራት
ህመሜን ልነግራት

እንዴትነሽ ጨረቃ አንቺ እንደምን አለሽ
ለኔ አትታይኝም ምን ነው የከለለሽ
ምነዋ ጨረቃ ለኔ የለግምሽው
ፍርሀቴን እያወቅሽው
ለጥቁሩ ጨለማ ቦታ የለቀቅሽው
ምነዋ ጨረቃ
ቀረሽ በፈረቃ

ህልቆ መሳፍርቱ
ቢከትም ከቤቱ
እዬጠበኩሽ ነው ልቤን አምነዋለሁ
ታረፍጃለሽ እንጂ አትቀሪም አውቃለሁ

አትቅሪ ጨረቃ

By Kerim

@getem
@getem
@paappii
40👍23🤩3🔥2
Poem.ogg
2.1 MB
7👍4
የሙህር አፍቃሪ


የሙህር አፍቃሪ በፍቅር የተቀጣ
በቆንጆ ልጅ ውበት
ጥበቡን ተነጥቆ እሱነቱን ያጣ
ሀሳብ በመወጠን ሲያወርድ ሲያወጣ

ኩርምት ባለ አንጀቱ ተጠብሶ እየሳቀ
ከለታት አንድ ቀን እንዲህ ሲል ጠየቀ
ከእግዚሔር የተሰጠኝ ጥበብና እውቀቴ
ፍቅርን የሳልኩበት የታል ወረቀቴ
እያለ ዘመኑን ይገፋል
እንባውን አፍስሶ እንደ ውሃ ያጎርፋል
ፍቅርን እየሳለ ውበትን ይፅፋል
ይፅፋል ይፅፋል ይፅፋል ይፅፋል
ስንቱ የጥበብ ንጉስ ምሁር እንዳልነበረ
የማይገባውን ሰው እያፈቀረ
የጎዳና ፃፊ አፍቃሪ ሆኖ ቀረ።

By @Habtishe01

@getem
@getem
@paappii
35👍24🔥5🤩5
, የታለች ሄዋኔ

ከእግራ ጎኔ ላይ ቆርሰኸ የፈጠርካት
የህይዎቴን አጋር ለኔ ያስቀመጥካት
ንገረኝ አምላኬ የት ነው የደበካት
የታለች ሄዋኔ መቼስ ይሆን ወደኔ ምትልካት

ስጋዬን እንዳላሰክስ ከማትሆነኝ ሄዋን
እስክሰጠኝ ቼኮልኩ አምላክ የኔን ሄዋን
ፍቅሯን ተጠማኋት ናፈኩት ገላዋን

መቼስ ለእኔ ብለህ እግዚሔር ከዋልክልኝ
ፀሎቴንም ሰምተክ ፈቃድህ ከሆነልኝ
አደራ ሄዋኔን እስከክብሯ ላክልኝ።

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
35👍28😁14🎉4
በማስመጥ ልምድሽ እየደለልሽው
ልቤን ምንጭ ውሃ የምታደርጊው
አትሽኮርመሚ ባይሆን ላግዝሽ
ምን አይነት ባል ነው የምትፈልጊው?

እንደኔው አይነት?
ግን ደግሞ ሀብታም
አባካኝ ይሁን ወይስ ስስታም ?
አለባበሱስ
መልኩስ
ቁመቱስ
እንደኔው ይሁን ቁርጥ እራሴን
ሱሪዬን ወስዶ ይቀይር ኪሴን?

እሺ ፀባዩስ?
አሁንም የኔው ተጫዋች ፍቅር
ሁሉንም ይውረስ?  የትኛው ይቅር?
አንዳንዱ ማለት  መሳቅ ማበዴ
ተዛዝሎ መሮጥ የደሃ ቀልዴ?

አዪዪዪዪ ..
አትማይ
አልፈርድብሽም ትተሽ ስለሄድሽ
ስልጣን ገንዘቡ ስለማረከሽ
ቅንጡ ቤቱ ድር ሲያደራበት
በእኔ ኪራይ ቤት ምን አሳከከሽ

ሚሉሽን ተዪ
ከመውደድ በላይ ምቾት ይበልጣል
ኑሮ ካማረ ፍቅር እራሱ
ሲያድር ይመጣል

ጥሩ ነው ያረግሽው
ምን አንጓተተሽ መጥቶ ላይጠቅም
መያዝ ነው እንጂ
ጊዜያዊ ስሜት  አያዛልቅም።

ይኸውልሽ ውዴ
ወንድ ባዳ ነው አስር ይወዳል
ብትወጂው እንኳን
ያለፈለት ለት  ትቶሽ ይሄዳል።
ወጣት አትመኝ
ወርቅ ልብሽን የትም አታስጪ
ቦርኮ አይጠቅምሽም
ለልጅሽ ስትይ ያለው ምረጪ

ትተሺኝ ሂጂ
አምነሽ ቁረጪ ልብሽ ቢፈራም
እስከምታረጅ
ፍቅር ህልም እንጂ ጎጆ አይሰራም።

የኔ ውብ አለም
የኔ ተወዳጅ
ልቤን ዶግ አመድ የምታደርጊው
አንቺ አትልፊ  እኔው ልዳርሽ
ምን አይነት ባል ነው የምትፈልጊው?

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
60👍29🔥8😱3🤩3😢1
Forwarded from Studio Anaya (Ribka Sisay)
አዲስ አበባ የምትገኙ በፅዳት የተያዘ ቆንጆ ቤት ያላቹ ለተለያዩ ማስታወቂያዎች ቤቶችን እያየን ስለሆነ የኪችን የሳሎን እና የመኝታ ቤት በደንብ የሚታዩ ጥሩ ፎቶዎችን ከእያንዳንዱ 3 ከስልካቹ ጋር @Ribki30 ላይ ላኩልን።
👍62
አፌ ቃላት ቢያጣ:
ልቤ ቢመኝሽም:
ሌላ ሰው ጋር ሆነሽ
ዳግም ቢያስብሽም:
    አልተቀየምኩሽም።

አልተቀየምኩሽም አፍቅሪ ሌላ ሰዉ:
ብጎዳም ግድ የለኝ ህጉንም
ብጥሰው ።
ደፍሬ ተጨንቄ አስቤ ቃል መርጬ ፣
አይንሽን ልክ እንዳየዉ ተመለስኩ ፍቅሬን ዉጬ።
ልነግርሽ ያሰብኩትን የፍቅሬን ፍቅር ቃላት ፣
እንዳየሁሽ ተዘጋብኝ ፣
ሰማይ ምድሩ ተናጋብኝ።
ልሳኔ ወዴት ገባ እንዲያ እንዳለፈለፈ ፣
አይንሽን እንዳየ የት ጥሎኝ አለፈ።
እረ በየት በኩል የቱስ ባህር ዋጠዉ ፣
አንዴ ተናግሮልኝ የትም ወንዝ ያስምጠዉ።


By @Papiel16

@getem
@getem
@getem
36👍24🎉2🤩2
, አሻጋሪ እና ተሻጋሪ

አሻጋሪው ከፊት ቆሞ ፎቶ ይነሳል
ተሻጋሪው ከኋላ ቆሞ ይተኩሳል
አሻጋሪው አምሮ ተሞሽሮ ይደንሳል
ተሻጋሪው ፅልመት ለብሶ ያለቅሳል
አሻጋሪው ምድርን ጭሮ ይቆፍራል
ተሻጋሪው ዘመድ አዝማ እያነባ ይቀበራል
አሻጋሪው ላገር ፈጠርኩ ያለው ልማት
ተሻጋሪው የቁም ፍርጃ ሆነበት ማት
ላንድም ቀን እርቅ ሳይፈጥሩ ሲገዳደሉ
አንድ ቀን ወደሰማይ አብረው ይሄዳሉ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
35👍18😢7🔥3🤩2
ኧረ ወገን
እየሰራን Major ሌላ ታሪክ ነው ይዞ እየመጣ ያለው!!

https://t.me/major/start?startapp=454803628
😁8👍3
የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።

የቱ ጋር መሰለህ?

በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴትን ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።

የቱ ጋር መሰለህ?

የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በዋዛ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ስትዘነጋ ፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።

ትዝ አለህ?

ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።

ያን ጊዜ ተከፋህ!

ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።

ትዝ አለህ?

መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?

ትዝ አለህ?

በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?

ትዝ አለህ?

የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
‘አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ? ‘
ብለህ ስትቆዝም … ?

እንዲያ ነው አይዋ…
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።

ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
‘ኧረ ስከን’ ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!

@getem
@getem
@getem
36👍28🔥4🎉4
ገነቴ
የልጅነቴ
ደስ የምትለኝ ፍርሃቴ
የምታሳደኝ ልክፍቴ
ገነቴ የኔዋ ገነት
የሰፈራችን እመቤት
አባዬ
ሊገርፈኝ
ለበጥ
ሲቆርጥ
በርሬ ወደ'ሷ ምሮጥ ።
በቀሚሷ የምትሸሽገኝ
በእቅፏ የምትከልለኝ
«በሞቴ» እያለች «በሞቴ»
ገነቴ
የልጅነቴ
እንደ ጥላ
እንደ ቡችላ
የማልጠፋ ከኋላዋ
«ማነው ?» «ምንሽ ነው ?» ሲሏት
ገልመጥ አድርጋኝ በኩራት
«ባሌ ነው» ምትል «የኔ ባል»
ያውም በሰዎች መሐል !
ድንብር - ድንብርብር ብዬ
ሮጬ የምሸሸጋት
ተሸሽጌ የምፈልጋት
እየወደድኩ የምሰጋት
ገነቴ
የልጅነቴ
የምታሳደኝ ልክፍቴ
የሆነ 'ለት
አንድ ጠዋት
ካለች ብዬ
እንደ ሁልጊዜዬ
( ሳላንኳኳ )
በሩን ከፈትኩ - የቤቷን
አየሁት - ጡቷን ክፍተቷን
ደንግጬ ሮጥኩኝ ወደ ቤቴ ...
ከዚያማ ...
ከዚያ ኋላማ ገነቴ
ገነቴ የልጅነቴ
እንደ ምትሃት
እንደ አስማት
ሐኪም የማያውቃት
ቃልቻ ዱዓ ያላስለቀቃት
ሳልወድ የግዴን የምታመናት
የሌት አድባሬ ፥ የህልሜ ዛር ናት ።

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@paappii
👍309🤩9🎉1