ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እልፍ ስትል እልፍ አበሳ ሄድ ስትል ጉድ ጭካኔ በመንገድህ ለሚነጉደው
ምን ለማትረፍ ምን ለማግኘት እርምጃህን 'ምትቀጥለው
ወዴት ይሆን ህይወቴ ሆይ የምትሄደው
የብቻነት የስቃይ ቤት ምን ይሆን ‘ምትፈልገው
እዚህ የእንባ ጎርፍ ውስጥ አለምን ከሰራት
ብትሰምጥ ብትሞት እርሷን እንደው ይቸግራት?
ደስታ ፍለጋ ‘ምትባዝን ህይወቴ ሆይ
ከንቱነት ነው አንተን ‘ሚቆይ
አንተ አበባው በሜዳህ ላይ የምትስቀው
አንቺም ወፏ ከዛፍሽ ስር ተደብቀሽ 'ምታለቅሺው
ፍፃሜያቹ ለካ አንድ ነው
ለማይዘገን ጥቂት ደስታ ዞሮ እንደ ጉም ለሚበነው
በስለቱ በጫፉ ላይ አየዘለልክ 'ምትጨፍረው
.....አንተ እኮ ነህ የምትደንቀው


Translated from "hymen of death " the movie

By yodan

@getem
@getem
@getem
👍339🔥1😢1
ተራራ የሆነብንን የዳህንበትን አቀበት
እየናጠጡ እየፈረጠጡ ተንደረደሩበት

መስከኛ  ያለውን    ለም መሬት
ፎሮሹ   ፈጩበት
ወቁ ሰለቁበት


አደራ  አማን ብለን ሳለ
አልተዘገረ
አልተመተረ
ከተባለ
አኑር ጠብቀን   ብለን ሳለ
ከሆነ የሞት ሹም
አይሳሉ ስለት   ለሞታችን የተሳለ

ተመርቆለትም ከኪሎው ካለየ
ወደ ተመዛኙ ካላዘነበለ 

አይጠረጥርም ወይ
ምንም ያልጠየቀ   ?

ክሳት ገፅ የለውም 
አጥንት ካልገለጠ ?


ነገር  ነገሩን ቢለይም
ምኑን ከምኑ
ውል ያልያዘ ሰው
ቢመሽበትም  አይነጋለትም

ዘንድሮም ዘንድሮ ተባለ
ሹም ሽረቱ ፍርዱም ተሻረ
ውሸቱ ሲፍም  እውነት ከሰመ

ጊዜ ለሁሉ መልስ ቢያኖርም    
ምኑን ከምኑ
ውል የተሳተው
ቢመሽበትም   አይነጋለትም

By mik

@getem
@getem
@paappii
👍329🔥1
ስምን መሄድ ጥሎ
ከታሪክ ተካፍሎ
አሸብርቆ መኖር
በወርቅ ተጠቅልሎ ፤
ዘርን በመተካት …
ወዳጅን በማፍራት
የምድር መናዋን
ብዙውን በመብላት
ሸጋውን በመልበስ
ፋሽን በመጫማት
ማርሴዲስ መኺና
ሸምቶ በመንዳት
ነው እያልን ስንኖር
መለኪያ ፣ ሚዛኑ
ሁሌ በየቀኑ…
ከልብ መሳቅ ኖሯል
የስኬት ተመኑ !

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
27👍20🔥6🤩2
ጭጋጉ ሲያከትም በክረምቱ ማብቂያ፤
ፀሐይ ስትፈነጥቅ በመሬት መድረቂያ፤
የፀደይ አበባ ማበብ ስትጀምር ፤
አደይዋ ለሰዎች ተስፋን ስታበስር፤
በወርሐ ጥቅምት በመጀመሪያው ቀን፤
ዛሬን ነዉ የወጣሁ ከእናቴ ማኅፀን።

ያቺ እናቴ በጭንቋ ቀን ምጧ ደርሶ፤
እያነባች ላብ አጥምቋት ፊቷ ርሶ፤
ማርያም ማርያም እያለች፤
ምጧ ቀለለላት ስሟን እየጠራች።

በልደቷ ቀን መታሰቢያ.........
ሰምታ ጸሎት ስዕለቷን፤
ማርያም ማረቻት እናቴን።
በዚያች ሴኮንድ በዚያች ቅፅበት........
ከልቤ ታትሞ ማርያም የሚለው ስም፤
ለዛሬ ደረስኩኝ በፍቅሯ ስሸለም።

የእቅፏን መዓዛ እየመገበችኝ፤
የትህትናን ዋጋ እያስተማረችኝ፤
የልጇን ጌትነት በልቤ ሰሌዳ፤
የእርሷን ትሁትነት በፍቅር አዋድዳ፤
የንስሐ እድሜን ፈጥና አሰጠችኝ፤
አዲስ ቀንን እንዳይ ድንግል ባረከችኝ።
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎊🎊🎊🎊
ዔደን_ታደሰ @ediwub
ጥቅምት ፩/፳፻፲፯
መልካም ልደት ለእኔ🎂🎂🎊🎊🎊
@getem
@getem
@getem
70🎉27👍24🤩4
Forwarded from TIZITA21
💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
23👍8🔥7
ቀጥቅጬ የገደልኩት~እባብ የትናንቱ
ሳይተነፍስብኝ~ሳይነካኝ መሞቱ
ተረሳው መሰለኝ...
ዛሬ እንደነደፈኝ~በዛ መጠዝጠዙ
በቃ እንደፈራሁት~ያንተ ነበር መርዙ

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem
21👍15😁3
...ትዝታ

ትዝታ ገዳዩ ናፍቆትን ያብሳል
በጥላቻ መሀል ፍቅርን ይሰብካል
እንባን አሳብሶ በምናብ ይወስዳል
ትዝታ ከባዱ ቫይረስ ነው ይገላል

By
@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem
👍373👎2🔥1😱1😢1🤩1
Forwarded from TIZITA21
💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
29👍5🔥5👎1
ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
37👍14🔥4
44👍10🔥4
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
ችግር ውስጧን ሚረዳላት
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
የአይኗን እንባ ሚያብስላት

ለጠየኳት ጥያቄዎች
ምንም ነበር መልሰ ቃሏ
ብዙ እንደሆነች ግን
ይናገራል ፊት አካሏ

ብቻ...ዝም ብላለች

ታስታውቃለች ሆድ ብሷታል
ታስታውቃለች እንደከፋት
ቆንጆ መልኳን ተመልክቶ
ማን ይሆን ሰው ደርሶ የገፋት
ደረቅ ብሏል ውብ ከንፈሯ
አላገኘም አንዳች እህል
ቀዝቀዝ ብሏል የእጇ መዳፍ
ምን ሁናለች እቺ ጉብል

ቀና ብላ እያየችኝ
ዘረገፈች የአይኗን እንባ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
ነጠላ እጇን ተከናንባ

እንዲህ ነው እያለች መናገር ባትችልም የውስጧን አውጥታ
ብዙ አውርታኛለች ከኔ ጋራ ሳለች ቃሏን በዝምታ
ይገርማል አንዳንዴ
ቃላት ሳይደረደር ምስክር ሳይጠራ ሀቀኛ ሳይለካ
ብዙ ሳንናገር በዝምታ ብቻ ቃል ይወጣል ለካ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍9151🔥9🎉3😁1😢1🤩1
ጥያቄ

ሊሰጠኝ ከሚችል ከብዙ ስጦታው ሞልቶ የተረፈኝ
ከሰው ከሀብት ከፍቅር ሁሉ የተሰጠኝ
ባልጎደለ ኑሮ እኝ እኝ የሚያስብለኝ
ምን ይሆን የጎደለኝ
ምን ይሆን የመረረኝ

By Yodan

@getem
@getem
@paappii
24👍12😢6🔥4
ረክሶ ነው እንጂ
እግዜር ሚባል አልማዝ
ይሻማበት ነበር
ፍጡር እንደቁስ ጓዝ

ረክሳ ነው እንጂ
ማሪያም ሚሏት ሀምሎ
ቤት አያጣም ነበር
ልብ 'ሚባል ኪሎ

ቀንሶ ነው እንጂ
ሰው ሚባል ሳጥናኤል
ወንበሩን ባልሸጠው
ለእነ ሊቅ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤልስ
ይጠብቃል ሰውን
ቅዱስ ገብርኤልስ
ያወጣል እሳትን
እግዜር ግን ዝም ነው
ያቺን ቀን ያላትን

ሀገር ሚባል ዕዳ
ቃል ሚያክል ሚካኤል
ሸጦታል አሉ ሰውን ለሳጥናኤል

እግዜሩ ቢረክስ ገነት ይወደዳል
ሳጥናኤል ቢረክስ ሲኦል ሰውን ያጣል
ሰው ሰውን ካጣ ሰው ከየት ይገባል ?

ጨለማው ላይ ሆነሽ
ስሜንም አትጥሪ
ጊዜ ሚጠብቅ ሰው
አይባልም ፈሪ
እባክሽን ዓለም
ባይሆን አምላክ ፍሪ


@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii
28👍19👎16🔥4😱1
ልሳነ አፍቅሮት

ለቃል
   ለትዕዛዙ
      ብርሀንም
      ጨለማም
       ተገዝቷል ።
      
    ለበጋ
          ወቅቱ በጋ
     ሆኗል።
ለማበብ
      አበባ ፈክቶ
               ደምቆ
              አሸብርቋል ...።
  .......
.....
ኩሉ አላፊ
       ወፈላሲ
    ሆኖ ሳለ



ከማስበው
     ስሩ
            ስሩ
ከውስጥ
          ከውስጥ
ከልቤ ላይ
እሷን መጥራት
መጥቀስ አለ
ቃል የሆነ
አልፋ ኦሜጋ
ልሁን ያለ
     
                  ምክያስ አለምሰገድ(mik)

@getem
@getem
@paappii
👍249🔥6🎉4🤩2
እስቲ ልመርቅሽ
        እስቲ ደሞ ልጣሽ
የልብሽን አይቶ እግዜር ከኔ ያውጣሽ
.


ዮኒ
      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
29👍17🤩7👎3
የድሮው አምላክ
'
'
አዲሱ አምላክ ገና አልመጣም
የቀድሞ አምላክ አገናኜን ፣
ቢያንስ ቢያንስ ባያድሰን ፥
ለትዝታ እስኪፈጥረን ፥
አዲሱ አምላክ እስኪ ተወን ፣
'
'
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii
👍188👎3🤩3🎉2😁1
ሀ እና ለ

የቀመስኩት ሁሉ
የሰማሁት ሁሉ
     ጣዕሙ ቢመሳሰል
     ጀመርኩኝ መብሰልሰል ።

    እሰልፉ የለለ ሆነና እድሉ
     ከራስ መጠማጠም ...

ጀመርኩ
           ከምላስ ጋር ቁሮሾ
         ከጆሮ አምባጓሮ....

  መብሰልሰል   ሀ

       ኑረንም መልካም ነው
       ጠፍተንም መልካም ነው
ሆነና ነገሩ  
    የሄደን ላይመልስ
ከንቱ እየፈጠነ
ሰው ማለት የዋሁ
        ከንቱ እየደከመ
የራቀ ሲመስለው
     እልፍ  እየቀረበ
ስንቱ  ተከተተ ?
ሞትም  መንገድ ይሆን ?
ስንቱን አስከተለ ?



    ሸኛችን ቢለያይ
        ሞታችንስ ያው ነው
           ግን  ምላስ
                 ግን ምላስ.....
   ጆሮ ይታዘበው
   ግጣም ያላደለው
    በቃኝ እማይችለው...

              ምክያስ አለምሰገድ (mik)

@getem
@getem
@getem
👍2615🔥2🤩2
የተሸጡ እውነቶች
____^____


ኧረ ተይ ሀገሬ፣ ኧረ ተይ ኧረ ተይ
ፀሐይሽን ከድተሽ ጨረቃ አትከተይ።
እስኪ ተመልከቺ...
መድኃኒት ውጬ ሞትኩ - መርዝ ወግተውኝ ነቃሁ፣
ስጨርስ ጀመርኩኝ - ስጀምር አበቃሁ፣
ቁልቢ ተገኘ ቋራ ያስቀመጥኩት
አራምባ ላይ ታየ፣ ቆቦ ላይ ነው ያልኩት
ጣዝማ ማር ቀምሼ፣ መረረኝ እንደ ሬት
እንዲህ ነው የሚሆን፣ እውነቶቿን ሽጣ በከበረች መሬት።


___^___

- ደሱ ፍቅርኤል፣
ተይው ፖለቲካን...


@getem
@getem
@paappii
41👍28🤩5🔥4😁1
ደብተራ የዘወረበት
ከጠንቋይ የተዋለበት
ሰንካላ መዉደድ ታቅፎ
ተፈጥሮን ከነፍሱ ፍቆ

አለት ልቤ ያልኩትን ፍቅሩ መቶ ደወረዉ
ሴጣን ለርሱ ሳያስቀር እንዴት በሙሉ ቸረዉ?
ይህን ያህል መዉደድ እሱን ከየት አምጥቶ ተማረዉ?

💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
15👍11🔥7😢3🤩3😱2
የት ልንደርስ?
(ሳሙኤል አለሙ)

[እ--ወ--ድ--ሃ--ለ--ው
እ--ወ--ድ--ሻ--ለ--ው]
ባንዲት መኺና ፥ ሞልተው ሊሳፈሩ
መልዕክት መጣና
ተቀጣጠሩ።

እንደ ደረሱ...
ከአፍ መናኸሪያ ፥ ወደ ልብ ሊጓዙ
ለጉዞኣቸው መዳረሻ
ቆሎውን ኩኪሱን ገዙ።

ሊሞላ...ሊሞላ...ሊሞላ
ሊሞላ ሲል
አንተ ነ-ሃ
አንቺ ነ-ሻ
በመሃል ስንባባል
ለካስ ቃል ይደነግጣል።

ይኸው እያቸው...
የሞላውን ትተው ፥ በኔና ባንቺ ኩርፊያ
ይኸው እያቸው...
ወደ መጡበት ፥ ሊመለሱ በጥድፊያ
ይኸው እያቸው...
የጋራ ቃላችንን
ነጥለን ስናሳፍራቸው።

[እ]--[ወ]--[ድ]--ሻ--[ለ]--[ው]
--- --- --- --- --- --- ---
[እ]--[ወ]--[ድ]--ሃ--[ለ]---[ው]

#ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu


@getem
@getem
👍3510🔥3
እንቆቅልሽ ?
ምን አውቅልሽ
ድንግል ልጅ አገርድ ሁለት ልጆች ያሏት
አንድኛው ሲገላት ሌላው የሚሞትላት
ይቺ ምስኪን እናት መልስልኝ ማናት
ብለሽ ስጠይቂኝ
ምናውቅልሽ ስልሽ ሀገር ስጠኝ ያልሽኝ
ሁሉ በእጄ ብለሽ መልኳን ያጠፋሽው
የዝች እናት ሀገር
ግማሽ ገፅታ ነኝ ገለሽ የቀበርሽው

   By ዮም ብዕር

@getem
@getem
@getem
67👍32🔥14🤩8