. ➕➕➕
ሁለቱ የምግብ ዘር
ባቄላና አተር
ካለ ባህል ልምዱ
አሻፈረኝ ቢሉ
ዱቄት እየሆኑ በአንድ መዋሀዱ
ከቤት ከመንገዱ
ጠፋ ክሽን ሽሮ
ድፍኑ ባቄላ ከድፍኑ አተር
አብሮ ተደምሮ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
ሁለቱ የምግብ ዘር
ባቄላና አተር
ካለ ባህል ልምዱ
አሻፈረኝ ቢሉ
ዱቄት እየሆኑ በአንድ መዋሀዱ
ከቤት ከመንገዱ
ጠፋ ክሽን ሽሮ
ድፍኑ ባቄላ ከድፍኑ አተር
አብሮ ተደምሮ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
👍22❤5🤩4
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ይኸውልህ...........
ከጅማሮው መንገዳችን ሆኖ ለቅል
ከኔ ሆነህ ከኔ ህይወት ላትበቅል
ማር ቢያዘንቡህ ከንፈሮችህ.....
....ሁሉ አካሌን ብትገዛ
ብትወድም ከኔ መዋል.......
.....ቢማርክህ የአፌ ለዛ
ብንባልም ክርስቲያኖች ቢመሳሰል መጠሪያችን
አንድ አይደለም የዕምነት ልኬት መንገዳችን
ያንተ አስተምሮ.....ያንተ ድህነት-ዕምነት ብቻ
የኔ አስተምሮ-አምኖ ማድረግ...ጎዳናችን ለየብቻ
እኔ በእተ አፍ "ጌታን ከሃጂ"መጠሪያዬ
ያንተም ለኔ"ምንፍቅና"የምትባል በአስተምሮዬ
ያንተ መዳን በአለማዊ ስደድ መጣል
የኔ መሻት በመቅደሱ ተንበርክኮ ማረኝ ሲሉ ሰርክ መዋል
ለኔም ለአንተም ቢሞትልን አንድ ጌታ
ስብከታችን ለየቅል ነው ማይዛመድ በየትም ቦታ
ሆኖም ብለን....
በፍቅር ቃል ብንስማማ አንድ ጎጆ ብንቀልስ
ባንተ ሃዘን ላልደማ በኔ ህመም ላታለቅስ
ደጁ ላትደርስ ላትጠመቅ...ከኔ አምባ መቅደስ ላትቆም
ታቦት ሲያልፍ ላታጅበው...በርከክ ብለህ ላትሳለም
አንድ መሆን አይቻልም በአቅጣጫው ባጋምድም
አንተ ሆዬ.....
የሚታይህ የኔ ተግባር በአንተ ዓይን ጌታን መካድ
እኔ ደሞ ማርያም ማለት እሷን መውደድ
የኔ ኢየሱስ ማያቅ ምልጃ የአን ኢየሱስ የሚያማልድ
ማርያም ማለት ላንተ ሚከብድ እኔ ደሞ ስሟን ስወድ(...ማርያምን ስልህ...)
ምን አለፋህ....
ባጣምርህ ከኔ ምዕራፍ ወደህ ፈቅደህ ላትጋመድ
ጅምሮአችን ለየቅል ነው አንድ አይሆንም የኛ መንገድ
ከኔ አይደለም መቀመጫው ወንጌልህን ይኸው ውሰድ.....
"""""""""""""""""""""""""""""""""
✍ጦቢያ
@getem
@getem
@getem
ይኸውልህ...........
ከጅማሮው መንገዳችን ሆኖ ለቅል
ከኔ ሆነህ ከኔ ህይወት ላትበቅል
ማር ቢያዘንቡህ ከንፈሮችህ.....
....ሁሉ አካሌን ብትገዛ
ብትወድም ከኔ መዋል.......
.....ቢማርክህ የአፌ ለዛ
ብንባልም ክርስቲያኖች ቢመሳሰል መጠሪያችን
አንድ አይደለም የዕምነት ልኬት መንገዳችን
ያንተ አስተምሮ.....ያንተ ድህነት-ዕምነት ብቻ
የኔ አስተምሮ-አምኖ ማድረግ...ጎዳናችን ለየብቻ
እኔ በእተ አፍ "ጌታን ከሃጂ"መጠሪያዬ
ያንተም ለኔ"ምንፍቅና"የምትባል በአስተምሮዬ
ያንተ መዳን በአለማዊ ስደድ መጣል
የኔ መሻት በመቅደሱ ተንበርክኮ ማረኝ ሲሉ ሰርክ መዋል
ለኔም ለአንተም ቢሞትልን አንድ ጌታ
ስብከታችን ለየቅል ነው ማይዛመድ በየትም ቦታ
ሆኖም ብለን....
በፍቅር ቃል ብንስማማ አንድ ጎጆ ብንቀልስ
ባንተ ሃዘን ላልደማ በኔ ህመም ላታለቅስ
ደጁ ላትደርስ ላትጠመቅ...ከኔ አምባ መቅደስ ላትቆም
ታቦት ሲያልፍ ላታጅበው...በርከክ ብለህ ላትሳለም
አንድ መሆን አይቻልም በአቅጣጫው ባጋምድም
አንተ ሆዬ.....
የሚታይህ የኔ ተግባር በአንተ ዓይን ጌታን መካድ
እኔ ደሞ ማርያም ማለት እሷን መውደድ
የኔ ኢየሱስ ማያቅ ምልጃ የአን ኢየሱስ የሚያማልድ
ማርያም ማለት ላንተ ሚከብድ እኔ ደሞ ስሟን ስወድ(...ማርያምን ስልህ...)
ምን አለፋህ....
ባጣምርህ ከኔ ምዕራፍ ወደህ ፈቅደህ ላትጋመድ
ጅምሮአችን ለየቅል ነው አንድ አይሆንም የኛ መንገድ
ከኔ አይደለም መቀመጫው ወንጌልህን ይኸው ውሰድ.....
"""""""""""""""""""""""""""""""""
✍ጦቢያ
@getem
@getem
@getem
👍40❤19👎3🔥2
እርጉም ድብርት ልቤን ሰርጾ፣
በእልፍ ዱካክ ሐዘን ሊግት ...
ንቁ ጅስሜን በ'ሾህ ቀርጾ፤
ጭምት! ፍዝዝ!
ቁዝም! ትክዝ!
አርጎ ሚጥል አካል ነፍሴን ...
በእንባ ለበቅ በአመል ቁጣ፣
ፊትሽ ዳምኖ ያየ ዐይኔ ...
እንደ ሶምሶን ኃይሉን ሲያጣ።
ንጥር ሀሴት ደሜን ሞልቶ፣
በሳቅ ጀንበር ፌሽታ ሊያጭድ ...
ድድር ጥርሴን ፍካት ቀብቶ፤
ፍንትው! ፍንክንክ!
ፍግግ! ፍልቅልቅ!
አርጎ ሚሰድ ጽልመት በሬን ...
በልዝብ ቀልድ በልጅ እብደት፣
ፊትሽ ፈክቶ ያየ ልቤ ...
እንደ ዳንኤል ሲቸር እምነት።
ሀሴት ጎራሽ መፍለቅለቄ
የሚቀየር ... በአዛኝ ፊትሽ!
ድብርት አዛይ መከፋቴ
የሚለወጥ ... በድንቅ ሳቅሽ!
ቢገርምሽ...
ቢደንቅሽ...
ኑረት እርሳስ ፈተና ኩል፣
እንደራሱ ልቤን ሊኩል ...
ጣቱን ቢያረግ ሰበር ሰካ፣
ህይወቴ መልክ የላትም
ባንቺ ገጽ ነው የምትዳምን ...
ባንቺ ገጽ ነው የምትፈካ።
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@paappii
በእልፍ ዱካክ ሐዘን ሊግት ...
ንቁ ጅስሜን በ'ሾህ ቀርጾ፤
ጭምት! ፍዝዝ!
ቁዝም! ትክዝ!
አርጎ ሚጥል አካል ነፍሴን ...
በእንባ ለበቅ በአመል ቁጣ፣
ፊትሽ ዳምኖ ያየ ዐይኔ ...
እንደ ሶምሶን ኃይሉን ሲያጣ።
ንጥር ሀሴት ደሜን ሞልቶ፣
በሳቅ ጀንበር ፌሽታ ሊያጭድ ...
ድድር ጥርሴን ፍካት ቀብቶ፤
ፍንትው! ፍንክንክ!
ፍግግ! ፍልቅልቅ!
አርጎ ሚሰድ ጽልመት በሬን ...
በልዝብ ቀልድ በልጅ እብደት፣
ፊትሽ ፈክቶ ያየ ልቤ ...
እንደ ዳንኤል ሲቸር እምነት።
ሀሴት ጎራሽ መፍለቅለቄ
የሚቀየር ... በአዛኝ ፊትሽ!
ድብርት አዛይ መከፋቴ
የሚለወጥ ... በድንቅ ሳቅሽ!
ቢገርምሽ...
ቢደንቅሽ...
ኑረት እርሳስ ፈተና ኩል፣
እንደራሱ ልቤን ሊኩል ...
ጣቱን ቢያረግ ሰበር ሰካ፣
ህይወቴ መልክ የላትም
ባንቺ ገጽ ነው የምትዳምን ...
ባንቺ ገጽ ነው የምትፈካ።
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@paappii
👍30❤10
አይኔን ሁሉ ከመንደሩ
ቅላት ንጣት አማረረው
ጠይም ሴት ግን እንደ ታሪክ
ደብዝዛ ነው የምታምረው
ምን አሳቃት እስቲ አሁን
መሽኮርመምን ምን አመጣው
ጥቁር ፀጉር ጥቁር አይን
ጥርሷ ብቻ ለሚነጣው
ጠይም ገላ እያሳየች
ልስልስ ቆዳ እያስነካች
ለሚያስተውል ንፅህናን
በአካኋኗ እየለካች
እየቀባች ስትደልል
አመንኩላት ቀኗ ይፍካ
ወዟ ከሩቅ ቢታይ እንጂ
እንደ ግዑዝ አይነካ
ባይዳሰስ ገፀ መልኳ
ፊቷ ታጥቦ ሰው ይሰራል
አይ እውነቴን የማቀው ግን
የጠይም ልጅ ሳቋ ያምራል!
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
ቅላት ንጣት አማረረው
ጠይም ሴት ግን እንደ ታሪክ
ደብዝዛ ነው የምታምረው
ምን አሳቃት እስቲ አሁን
መሽኮርመምን ምን አመጣው
ጥቁር ፀጉር ጥቁር አይን
ጥርሷ ብቻ ለሚነጣው
ጠይም ገላ እያሳየች
ልስልስ ቆዳ እያስነካች
ለሚያስተውል ንፅህናን
በአካኋኗ እየለካች
እየቀባች ስትደልል
አመንኩላት ቀኗ ይፍካ
ወዟ ከሩቅ ቢታይ እንጂ
እንደ ግዑዝ አይነካ
ባይዳሰስ ገፀ መልኳ
ፊቷ ታጥቦ ሰው ይሰራል
አይ እውነቴን የማቀው ግን
የጠይም ልጅ ሳቋ ያምራል!
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
❤50👍27🔥6😢2🤩2
🤷አንቺ እንደፈለግሽ🤷
አቋሜ አያምርም አንቺን አይስብሽም
ብዙ ብር የለኝም ደሀ ነኝ አልዋሽም
መኪናና ቤትን ችዬ አልሰጥሽም
ግን እንደምትይው ለሰው እንዳወራሸው
እውነተኛ ፍቅርን የእውነት ከፈለክሽው
እሱ እኔጋ አለ መቼም እንዳትረሺው::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
አቋሜ አያምርም አንቺን አይስብሽም
ብዙ ብር የለኝም ደሀ ነኝ አልዋሽም
መኪናና ቤትን ችዬ አልሰጥሽም
ግን እንደምትይው ለሰው እንዳወራሸው
እውነተኛ ፍቅርን የእውነት ከፈለክሽው
እሱ እኔጋ አለ መቼም እንዳትረሺው::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
👍52❤19👎3🤩1
ውበት —.•: በመሥፈሪያ
ከጤፍ ማዳበሪያ
ሀሴት — .•: በላይ በላይ
ከእንጀራ ምጣድ ላይ
ስታስስ ይመሻል — .•: የሚያሳዝን ቀኗ
ጨረቃ
ሙዚቃ
ሥነ-ጥበብ — .•ኮከብ — .•: አይማትርም ዓይኗ
•••
ተአምሯ — .•: ማጀቷ
ትንግርቷ — .•: ሽንኩርቷ
ሲምፎኒዋ — .•: ሳንቲም
ግጥሟ — .•: ቲማቲም
የልቧ ሥራ — .•: ኩርማን እንጀራ
የቀኗ ትጋት —.•: ጉሮሮዋን መዝጋት
•••
ለመሰንበት መኖር — • እንደ ሁሉ ወጣት
ፍልስፍና
የቅኔ ጥፍጥና
የመጽሐፍ ምዕራፍ
አሪፍ ፎቶግራፍ — • ብዙም ግድ አይሰጣት
•••
የመልስህን ዓለም
በ’ሷ ጥያቄ ውስጥ — .•: ከምትፈልገው
የቄሳርን ዲናር —.•: ለቄሳር አድርገው
•••
ዳኛት በራሷ ሕግ
ሆዷን —.•
ጌታዋን — .•
መቅደሷን አትናቀው
ኩሽናዋን ስትረግጥ ጫማህን አውልቀው::
@getem
@getem
@paappii
By henok bekele
ከጤፍ ማዳበሪያ
ሀሴት — .•: በላይ በላይ
ከእንጀራ ምጣድ ላይ
ስታስስ ይመሻል — .•: የሚያሳዝን ቀኗ
ጨረቃ
ሙዚቃ
ሥነ-ጥበብ — .•ኮከብ — .•: አይማትርም ዓይኗ
•••
ተአምሯ — .•: ማጀቷ
ትንግርቷ — .•: ሽንኩርቷ
ሲምፎኒዋ — .•: ሳንቲም
ግጥሟ — .•: ቲማቲም
የልቧ ሥራ — .•: ኩርማን እንጀራ
የቀኗ ትጋት —.•: ጉሮሮዋን መዝጋት
•••
ለመሰንበት መኖር — • እንደ ሁሉ ወጣት
ፍልስፍና
የቅኔ ጥፍጥና
የመጽሐፍ ምዕራፍ
አሪፍ ፎቶግራፍ — • ብዙም ግድ አይሰጣት
•••
የመልስህን ዓለም
በ’ሷ ጥያቄ ውስጥ — .•: ከምትፈልገው
የቄሳርን ዲናር —.•: ለቄሳር አድርገው
•••
ዳኛት በራሷ ሕግ
ሆዷን —.•
ጌታዋን — .•
መቅደሷን አትናቀው
ኩሽናዋን ስትረግጥ ጫማህን አውልቀው::
@getem
@getem
@paappii
By henok bekele
🔥35👍21❤7😁3👎1
▪️▪️የውሸት ብርሀን🔸🔸
ዙሪያክ ገደል ቢሆን መሄጃው መንገዱ
ያመንካቸው ሰዎች አንተኑ ቢከዱ
ተንዶ ቢከስም የነበረክ ተስፋ
ያካበትከው ሀብትህ በሙሉ ቢጠፋ
አዝነህ እየተከፋ
ድቅድቁ ጨለማ ዙሪያህን ሲከበው
መውጫ ቀዳዳህን ጨንቆህ ስትፈልገው
ድንገት ምታያቸው
ብርሀኖች ሁሉ
እንዳያታልሉክ ተስፋ እየመሰሉ: :
ምክኒያቱም
ካላየኸው በቀር በጥሩ እይታ
የጅቦችም አይን ያበራል በማታ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
ዙሪያክ ገደል ቢሆን መሄጃው መንገዱ
ያመንካቸው ሰዎች አንተኑ ቢከዱ
ተንዶ ቢከስም የነበረክ ተስፋ
ያካበትከው ሀብትህ በሙሉ ቢጠፋ
አዝነህ እየተከፋ
ድቅድቁ ጨለማ ዙሪያህን ሲከበው
መውጫ ቀዳዳህን ጨንቆህ ስትፈልገው
ድንገት ምታያቸው
ብርሀኖች ሁሉ
እንዳያታልሉክ ተስፋ እየመሰሉ: :
ምክኒያቱም
ካላየኸው በቀር በጥሩ እይታ
የጅቦችም አይን ያበራል በማታ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
👍70❤16🔥10
🔸🔸🔸🔸እስከመቼ🔹🔹🔹🔹
አንዱ መርጦ...እንዲበላ..የስንቱ አንጀት..
....ሲታጠፍ
ወንበር ማሞቅ..ለናፈቀው..ህይወት ሁሌ
....እሚረግፍ
ቦታ ሰፍቶት...እንዲቀመጥ..ሌላው ቤቱን
....እየለቀቀ
የደላቸው እየተባሉ.......ምስኪን ደሀ.....
....ብዙ አለቀ
ቀጣይ ትውልድ...የሚመርዝ......
....ሀገር አፍራሽ...ሀሳብ በዝቶ
እስከመቼ ይቀጥላል...የሰው ህይወት
.....ክብር አቶ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
አንዱ መርጦ...እንዲበላ..የስንቱ አንጀት..
....ሲታጠፍ
ወንበር ማሞቅ..ለናፈቀው..ህይወት ሁሌ
....እሚረግፍ
ቦታ ሰፍቶት...እንዲቀመጥ..ሌላው ቤቱን
....እየለቀቀ
የደላቸው እየተባሉ.......ምስኪን ደሀ.....
....ብዙ አለቀ
ቀጣይ ትውልድ...የሚመርዝ......
....ሀገር አፍራሽ...ሀሳብ በዝቶ
እስከመቼ ይቀጥላል...የሰው ህይወት
.....ክብር አቶ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
👍66❤32😢15😁2🔥1
------------------------------------------------------------
ህልም አየሽ ወይ፤ ደግሞ እንደትናንቱ?
ፀባይሽ ተቀየረ፤ ብላሽ ሆነ ከንቱ
ምን ሲሰራ አለሽ ፤አቃጣሪዉ ህልምሽ
ጥሩ ስሰራማ ፤መቼም አያሳይሽ።
✍ ኒቆዲሞስ
@niko_nikodimos1
------------------------------------------------------------
@getem
@getem
@getem
ህልም አየሽ ወይ፤ ደግሞ እንደትናንቱ?
ፀባይሽ ተቀየረ፤ ብላሽ ሆነ ከንቱ
ምን ሲሰራ አለሽ ፤አቃጣሪዉ ህልምሽ
ጥሩ ስሰራማ ፤መቼም አያሳይሽ።
✍ ኒቆዲሞስ
@niko_nikodimos1
------------------------------------------------------------
@getem
@getem
@getem
😁36👍19❤18🤩5😱1🎉1
❤️❤️ሰበበኛው ልቤ❤️❤️
ለስንት አመት ኖሮ ሆኖ ኩሩ ላጤ
ዛሬ ቢነካካው ትንሽ ፍቅር ቢጤ
ያ ልቤ ከውስጤ ሳይወጣ አምልጦ
ያስጨንቀኝ ጀመር ካምሮዬ በልጦ::
:
:
ባፅኖት ነግሬው ሰላም እንዲሰጠኝ
በስድብ በቁጣ
ጭራሹን ባሰበት እሷ ስትመጣ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
ለስንት አመት ኖሮ ሆኖ ኩሩ ላጤ
ዛሬ ቢነካካው ትንሽ ፍቅር ቢጤ
ያ ልቤ ከውስጤ ሳይወጣ አምልጦ
ያስጨንቀኝ ጀመር ካምሮዬ በልጦ::
:
:
ባፅኖት ነግሬው ሰላም እንዲሰጠኝ
በስድብ በቁጣ
ጭራሹን ባሰበት እሷ ስትመጣ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
👍45❤24
#ለፈገግታ😁
🙅♀እሺ አትበይ አሁን🙅♀
አፈቀርኩሽ ብልሽ
ሁሌ ብከተልሽ
እያልኩኝ ብነግርሽ
ካላንቺ አልኖርም
ሳላይሽ ከዋልኩኝ እህል ባፌ አይዞርም
የተጎዳው መስሎሽ እየተሰማሽ ሀዘን
እባክሽ ቸኩለሽ እሺ አትበይ አሁን::
:
:
እንዴት ካልሽኝ ለምን?
ግራ እንዳትጋቢ ልንገርሽ ምክኒያቴን::
:
:
በዚ እሳት ዘመን በዚ ከባድ ኑሮ
ምግብ ስለዘጋኝ ብር ቆጠብኩ ዛሬ
ታሪክ ተቀይሮ
:
:
እና እሺ ብለሽ ሆዴ ከሚከፈት
መልስሸ ይቆይና ለትንሽ ጊዜያት
ዘግቶኝ ልኑርበት::🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
🙅♀እሺ አትበይ አሁን🙅♀
አፈቀርኩሽ ብልሽ
ሁሌ ብከተልሽ
እያልኩኝ ብነግርሽ
ካላንቺ አልኖርም
ሳላይሽ ከዋልኩኝ እህል ባፌ አይዞርም
የተጎዳው መስሎሽ እየተሰማሽ ሀዘን
እባክሽ ቸኩለሽ እሺ አትበይ አሁን::
:
:
እንዴት ካልሽኝ ለምን?
ግራ እንዳትጋቢ ልንገርሽ ምክኒያቴን::
:
:
በዚ እሳት ዘመን በዚ ከባድ ኑሮ
ምግብ ስለዘጋኝ ብር ቆጠብኩ ዛሬ
ታሪክ ተቀይሮ
:
:
እና እሺ ብለሽ ሆዴ ከሚከፈት
መልስሸ ይቆይና ለትንሽ ጊዜያት
ዘግቶኝ ልኑርበት::🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
😁107👍41❤10😱6🔥2🤩2
(አልነበርሽኝም..)
============
ያልሄደ ... ፈፅሞ አይመጣም
ያልመጣም... ለካ አይሸኝም
ያጣሁሽ መስሎኝ ስጸጸት
ለካ አንቺ አልነበርሽኝም
#Da_kiyorna
@getem
@getem
@paappii
============
ያልሄደ ... ፈፅሞ አይመጣም
ያልመጣም... ለካ አይሸኝም
ያጣሁሽ መስሎኝ ስጸጸት
ለካ አንቺ አልነበርሽኝም
#Da_kiyorna
@getem
@getem
@paappii
❤67👍31🔥9
....የውስጤን ልናገር...
❤️❤️❤️❤️💗💗💗💗
አ--አፌ ለመናገር
ፈ-ፈራ ተባ ቢልም
ቅ--ቅንጣት ታክል ድፍረት
ር--ርቆኝ ብቸገርም
ሻ--ሻካራ አይደለም ውስጤ አንቺን አልረሳም
ለ--ለመናገር ባልችል ቃሉን ባላወጣም
ው--ውዴ አፈቅርሻለው ወድሻለው በጣም::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
❤️❤️❤️❤️💗💗💗💗
አ--አፌ ለመናገር
ፈ-ፈራ ተባ ቢልም
ቅ--ቅንጣት ታክል ድፍረት
ር--ርቆኝ ብቸገርም
ሻ--ሻካራ አይደለም ውስጤ አንቺን አልረሳም
ለ--ለመናገር ባልችል ቃሉን ባላወጣም
ው--ውዴ አፈቅርሻለው ወድሻለው በጣም::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
❤83👍33🎉10🤩10
🚖🚖የመኪናው ጉዞ🚖🚖
መኪናው ሲበላሽ ሲያቆም መንቀሳቀስ
ለጠጋኝ ተሰጠ ዳግም እንዲታደስ
ታድሶም ባይሆንም ልክ እንደ በፊቱ
ይመስል ነበረ ሚሄድ በስርዓቱ
ስራውን ጀምሮ ጊዜው እየነጎደ
ከባድ ሚመስለውን--ያን ትልቁን ዳገት
ወቶ አንደወረደ
መሪው ተጠማዞ ወደ ገደል ሄደ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
መኪናው ሲበላሽ ሲያቆም መንቀሳቀስ
ለጠጋኝ ተሰጠ ዳግም እንዲታደስ
ታድሶም ባይሆንም ልክ እንደ በፊቱ
ይመስል ነበረ ሚሄድ በስርዓቱ
ስራውን ጀምሮ ጊዜው እየነጎደ
ከባድ ሚመስለውን--ያን ትልቁን ዳገት
ወቶ አንደወረደ
መሪው ተጠማዞ ወደ ገደል ሄደ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
😁43👍18😱8❤3👎2🔥1😢1
#አልገባሽም
:
:
:
ስንለያይ ጊዜ
የየብቻው ጉዞ ገና ሲጠነሰስ፤
አብረን የገራነው የጋራችን ፈረስ፤
ትዝታን ሸክፎ ቤትሽ እንደመጣ፤
ከዛም ከደጃፍሽ አራግፎ እንደወጣ፤
የኋሊት ጎትቶ ሆዴን ሊያላውሰው፤
በሰመመን ስትሄጅ ነግሮኛል ያየሽ ሰው።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ህይወት በኛ ስትከር፤
እንዲው እንደ ዘበት ፍቅራችን ሲሰበር፤
የሀዘን ድንኳን ጥለሽ፤
እንዴት ሆነ ብለሽ፤
እንባሽን ስትዘሪ፤
ደግሞም ከራስሽ ጋር ስትከራከሪ፤
ባላይ እንኳን ባይኔ፤
ያየሽ አርድቶኛል ሁሉን ክንዋኔ።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ያቆራኘን ገመድ እንደተበጠሰ፤
የትካዜው ሾተል ስለቱን አስሎ ካንቺ እንደደረሰ፤
ከዚያም አልፎ ተርፎ እንዶነብሽ እዳ፤
ሁሉን ሰምቻለው ያንቺን ሳሎን ጓዳ።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ደስታ ሚባል ነገር ጥሎሽ እንደሄደ፤
የቀለለሽ ሁሉ ደርሶ እንደከበደ፤
እንኳን እኔን ቀርቶ ዘር አዳም ሚረታ፤
የተከዘን ሚያስቅ ያ ምጥን ፈገግታ፤
ፅልመት መደረቡን፤
ድንገት መለዘቡን፤
አንቺ ባታወሪኝ ያየሽ ሰው ነግሮኛል፤
በሰማውኝ ጊዜም በጣሙን ከፍቶኛል፤
ደግሞም አስቆኛል።
:
:
እውነት ነው አንቺ ሴት፤
እየው ተሰምቶኛል ሁለት አይነት ስሜት።
እያዘኑ መሳቅ እየሳቁ ማዘን፤
ከራሴ ጋር ማውጋት እራሴን መመዘን።
:
:
እያዘንኩኝ ስቄ እየሳቅኩኝ ሳዝን፤
በህሊና ሚዛን ላይ እራሴን ስመዝን፤
የሳቅኩት ባንቺ ነው
እውነቱን መርምረሽ ገልጠሽ ላላወቅሽው፤
መቦረቅ ሲገባሽ በእምባ ለታጠብሽው፤
ገራገር ለሆንሽው።
ያዘንኩት ለራሴ ይብላኝ ያልኩት ለኔው፤
ወርቁ ላልበራልኝ የመዋደድ ቅኔው፤
ለሰጠሺኝ ፍቅር ለጠፋኝ ምጣኔው።
:
:
ሀቅ ነው አንቺ ሴት ...
ያንቺ አይነት ነው እንጂ
ሚገኝ ከስንት አንዴ እሱም ለታደለ፤
የኔ አይነት ሰውማ
የትም በሄድሽበት በየቦታው አለ።
:
:
አልገባሽም እንጂ
የእኔ 'ና አንቺ ቅኔ ወርቁ ቢበረበር፤
ፍቅርን ከቃል በስቲያ ሆኖት ማያቅን ሰው
አጥቻለው ብለሽ አታለቅሺም ነበር።
አልተረዳሽ እንጂ እውነቱን ብታውቂ፤
እንኳን ልተክዢ
ካንጀትሽ ነበር ሰርክ ምትስቂ።
ሽፍንፍኑን ገልጠሽ ብትረጂ ኖሮ፤
በደስታ ነበረ
ጥለሺኝ ምትሄጂው ገና ያኔ ድሮ።
:
:
እናልሽ አንቺ ሴት...
ዋጋሽ የከበረ ገራገር ቀይ ዕንቁ፤
የተለባበሰው ሲገለጥ ድብቁ፤
የኔ ፋንታ ማልቀስ ያንቺም ነው መሳቁ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
:
:
:
ስንለያይ ጊዜ
የየብቻው ጉዞ ገና ሲጠነሰስ፤
አብረን የገራነው የጋራችን ፈረስ፤
ትዝታን ሸክፎ ቤትሽ እንደመጣ፤
ከዛም ከደጃፍሽ አራግፎ እንደወጣ፤
የኋሊት ጎትቶ ሆዴን ሊያላውሰው፤
በሰመመን ስትሄጅ ነግሮኛል ያየሽ ሰው።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ህይወት በኛ ስትከር፤
እንዲው እንደ ዘበት ፍቅራችን ሲሰበር፤
የሀዘን ድንኳን ጥለሽ፤
እንዴት ሆነ ብለሽ፤
እንባሽን ስትዘሪ፤
ደግሞም ከራስሽ ጋር ስትከራከሪ፤
ባላይ እንኳን ባይኔ፤
ያየሽ አርድቶኛል ሁሉን ክንዋኔ።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ያቆራኘን ገመድ እንደተበጠሰ፤
የትካዜው ሾተል ስለቱን አስሎ ካንቺ እንደደረሰ፤
ከዚያም አልፎ ተርፎ እንዶነብሽ እዳ፤
ሁሉን ሰምቻለው ያንቺን ሳሎን ጓዳ።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ደስታ ሚባል ነገር ጥሎሽ እንደሄደ፤
የቀለለሽ ሁሉ ደርሶ እንደከበደ፤
እንኳን እኔን ቀርቶ ዘር አዳም ሚረታ፤
የተከዘን ሚያስቅ ያ ምጥን ፈገግታ፤
ፅልመት መደረቡን፤
ድንገት መለዘቡን፤
አንቺ ባታወሪኝ ያየሽ ሰው ነግሮኛል፤
በሰማውኝ ጊዜም በጣሙን ከፍቶኛል፤
ደግሞም አስቆኛል።
:
:
እውነት ነው አንቺ ሴት፤
እየው ተሰምቶኛል ሁለት አይነት ስሜት።
እያዘኑ መሳቅ እየሳቁ ማዘን፤
ከራሴ ጋር ማውጋት እራሴን መመዘን።
:
:
እያዘንኩኝ ስቄ እየሳቅኩኝ ሳዝን፤
በህሊና ሚዛን ላይ እራሴን ስመዝን፤
የሳቅኩት ባንቺ ነው
እውነቱን መርምረሽ ገልጠሽ ላላወቅሽው፤
መቦረቅ ሲገባሽ በእምባ ለታጠብሽው፤
ገራገር ለሆንሽው።
ያዘንኩት ለራሴ ይብላኝ ያልኩት ለኔው፤
ወርቁ ላልበራልኝ የመዋደድ ቅኔው፤
ለሰጠሺኝ ፍቅር ለጠፋኝ ምጣኔው።
:
:
ሀቅ ነው አንቺ ሴት ...
ያንቺ አይነት ነው እንጂ
ሚገኝ ከስንት አንዴ እሱም ለታደለ፤
የኔ አይነት ሰውማ
የትም በሄድሽበት በየቦታው አለ።
:
:
አልገባሽም እንጂ
የእኔ 'ና አንቺ ቅኔ ወርቁ ቢበረበር፤
ፍቅርን ከቃል በስቲያ ሆኖት ማያቅን ሰው
አጥቻለው ብለሽ አታለቅሺም ነበር።
አልተረዳሽ እንጂ እውነቱን ብታውቂ፤
እንኳን ልተክዢ
ካንጀትሽ ነበር ሰርክ ምትስቂ።
ሽፍንፍኑን ገልጠሽ ብትረጂ ኖሮ፤
በደስታ ነበረ
ጥለሺኝ ምትሄጂው ገና ያኔ ድሮ።
:
:
እናልሽ አንቺ ሴት...
ዋጋሽ የከበረ ገራገር ቀይ ዕንቁ፤
የተለባበሰው ሲገለጥ ድብቁ፤
የኔ ፋንታ ማልቀስ ያንቺም ነው መሳቁ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
❤57👍55🤩4😱3😢2🔥1
#የድሃ_ሰው_ፀሎት
.
.
በአየር ሰረገላ ጉም ደመና ጭኖ፣
መብረቅያ ታጠቆ ስግምታ ተክኖ።
"ሀምሌ ነሀሴ መጣ ስሩ ደነደነ፣
የምበላው የለኝ ቤቴ አልተከደነ።"
አንተ ሁሉን ገዢ የተፈጥሮ ጌታ፣
ድዊ የምትፈውስ ታሳሪ የምትፈታ።
ህልሜን እየረታሁ እንድረሳው ቀኔ፣
የማነሳት አካል የምላት ወገኔ።
ላክልኝ አንድ እሷን ልቤን ታሳርፈው፣
ጠራርጎኝ እንዲሄድ ወይ ዶፉን አጉርፈው።
ብዬ ያልኩህ ለታ፤
ለደጅህ ባይደርስም የሌጣ ፀሎቴ፣
እራስ ያህል ሸንፈት ቢያህልም ውድቀቴ።
'ባክህ አትዘንብኝ አይክፋህ እግዜሩ፣
ቢያሳሳኝ ውሽንፍር ቢያደክመኝ ነው ቁሩ።
✍ ዓቢይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
.
.
በአየር ሰረገላ ጉም ደመና ጭኖ፣
መብረቅያ ታጠቆ ስግምታ ተክኖ።
"ሀምሌ ነሀሴ መጣ ስሩ ደነደነ፣
የምበላው የለኝ ቤቴ አልተከደነ።"
አንተ ሁሉን ገዢ የተፈጥሮ ጌታ፣
ድዊ የምትፈውስ ታሳሪ የምትፈታ።
ህልሜን እየረታሁ እንድረሳው ቀኔ፣
የማነሳት አካል የምላት ወገኔ።
ላክልኝ አንድ እሷን ልቤን ታሳርፈው፣
ጠራርጎኝ እንዲሄድ ወይ ዶፉን አጉርፈው።
ብዬ ያልኩህ ለታ፤
ለደጅህ ባይደርስም የሌጣ ፀሎቴ፣
እራስ ያህል ሸንፈት ቢያህልም ውድቀቴ።
'ባክህ አትዘንብኝ አይክፋህ እግዜሩ፣
ቢያሳሳኝ ውሽንፍር ቢያደክመኝ ነው ቁሩ።
✍ ዓቢይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
❤25👍15🔥3😁2👎1🤩1
ነይ ተጠለይ
----------------
ንፋሱ የነጠቀሽ ዣንጥላሽን
እኔ ብይዝልሽ፤
ደግሞ፤ ንፋስ በዣንጥላ
ቢይዘው ፍቅርሽን።
ፍቅርም በዣንጥላ
ዝናብ ተጠልሎ፤
ልቤ ላይ ዘነበ
በረዶ ቀላቅሎ።
ብርዱ ቢጎስመኝ
የማቅፈው ሰው ፈለግኩ፤
ዣንጥላሽን ብለሽ
ስትመጪ ተፋጠጥኩ።
አጋጣሚ አቃጣሪ
አይደል የሚባለው፤
ነይ ከጎጆሽ ግቢ
ፍቅርን ከዘራብኝ፤
ከዝናቡ ሸሽተሽ
በእጆችሽ እቀፊኝ።
በያዝነው ዣንጥላ
አንድ እንሁን ተቃቅፈን፤
ዝናብ እንዳይነካን
እንሂድ ተደጋግፈን።
ጎጆ እስክንቀልስ
ጠጋ አልኩኝ ተጠለይ፤
በዝናብ አሳበን
እንሁን አንድ ላይ።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
----------------
ንፋሱ የነጠቀሽ ዣንጥላሽን
እኔ ብይዝልሽ፤
ደግሞ፤ ንፋስ በዣንጥላ
ቢይዘው ፍቅርሽን።
ፍቅርም በዣንጥላ
ዝናብ ተጠልሎ፤
ልቤ ላይ ዘነበ
በረዶ ቀላቅሎ።
ብርዱ ቢጎስመኝ
የማቅፈው ሰው ፈለግኩ፤
ዣንጥላሽን ብለሽ
ስትመጪ ተፋጠጥኩ።
አጋጣሚ አቃጣሪ
አይደል የሚባለው፤
ነይ ከጎጆሽ ግቢ
ፍቅርን ከዘራብኝ፤
ከዝናቡ ሸሽተሽ
በእጆችሽ እቀፊኝ።
በያዝነው ዣንጥላ
አንድ እንሁን ተቃቅፈን፤
ዝናብ እንዳይነካን
እንሂድ ተደጋግፈን።
ጎጆ እስክንቀልስ
ጠጋ አልኩኝ ተጠለይ፤
በዝናብ አሳበን
እንሁን አንድ ላይ።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤35👍19🤩6🎉2