ግጥም ብቻ 📘
69.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
170 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ብታምኚም ባታምኚም!
---------------------------------------

ባለሽበት:መንደር
በምታቂው :ሰፈር
ብትለምጂ :ሌላ :ውቧ :ሶልያና
እኔን:የሚተካኝ:መች:ተፈጠረና!

ደሞ!

በማታውቂው:ጠፈር
ሌላ:አለም:ቢፈጠር
እኔን:የመሰለ:በኤልያኖች ሃገር
ነገም;አይሰራ:ነገም:አይቀመር!!

ሙች!!!!!

Dawit tumay#.
¶30/5/14

@getem
@getem
@getem
የኔ ዝናብ
.
.
ወቅቱን ካልጠበቀ ብዙም አትፍረዱ
ሀጅ ሁኖ ነው እንደሰው ወቅቴ በማርፈዱ
.
የኔ ዝናብ
.
ዶፉ
እናትሽን ደበደበ በረዳቸው
አባትሽም አቀፏቸው
ፍቅር ሰሩ
አንቺን ሰሩ
ጎጆቸውን ባንቺ ለቅሶ አሳመሩ
.
[ከእለታት አድገሽ ቀን]

ካፊያው በመንገድሽ አካፋ
ነፋስ ገፋሽ የብርድ ቆፈን
ባላውቅሽም ባታውቂኝም ተቃቀፍን
ፀሀይ ወጣች ምቀኛ ናት
ብርድ አጣምሮን ስትለያየን ተጣላናት
ሄድሽ ሄድኩ
መሸ
ነጋ
የሆነ ቀን
ተሳስቀን
ብንውል ብዬ ያን ተመኘሁ
ዝናብ ብዬ ሳለዛዝን ስም እያለኝ ስም አገኘሁ
ዝናቡ አለኝ የፈጠረሽ
ካይኔ አጠረሽ
.
ቤት ቁጭ ብዬ
የደመነው ሊዘንብ ያለው ማይ ሲያስሮጠኝ
ዝናብ መሐል መንገድ መሐል
ሞኝ መብረቅ አፈረጠኝ
እሳት ይንሳው
ሰው ሲዘንብ ሊጠለል እቤቱ ይገባል
እኔ ግን ወጣለሁ ሚስት ያጣሁ ያንቺ ባል
ይሁን
መኖር ጥሩ
መውጣት ጥሩ
ዝናብ ጥሩ
አንቺም ጥሩ
የእግዜር ስራ አሰራሩ
.
ቢያገናኘን ምልሰት ዳግም
እንዳታልፊኝ
.
ሥሉጥ ይሁን ብዬ ሰርክ 'ፀልያለው
ዝናብ ያጣመረ'ን ፀሀይ እንዳይለየው

ማረሻዬ ከአይንሽ ጋር ተጣብቆ የደስታን እህል አጨድኹ!

©ናታን ኤርሚያስ
@UniqueDy

@getem
@getem
@getem
#የለኝም



ሁለት እግር አለኝ ብዬ ሁለት ዛፍ ላይ አልወጣሁም፣
ከልብሽ ምንጭ ከሚፈሰው ስሜት በቀር አልጠጣሁም።


አንቺም እኔን በይ ምሰዪ ...
ሁለት ዛፍ ላይ ተንጠልጥለሽ በፍቅር ስም አትነግጂ፣
ችሎ የሚያይ ልብ የለኝም ዃላ ወድቀሽ ብትጎጂ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
#እጎዳብሻለሁ
:
:
የሱ ነገር በቃኝ ባፍንጫዬ ይውጣ፣
ፍቅሩን በማለቴ ለምንስ ልቀጣ፣
ብለሽ የላክሺብኝ ወቀሳሽ ደርሶኛል፣
ካጠፋሁት አንፃር እንደውም ያንሰኛል።
ባፍንጫሽም ልውጣ ይበለኝ አምናለሁ፣
ግን ፍቅሬ ...
ከልብሽ ከወጣሁ እጎዳብሻለሁ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
#ለምን_ይሆን?
:
:
ጡት እንዳጣ ዕፃን ልጅ ስነፋረቅ ውዬ፣
ልክ ዐይንሽን ሳየው በደስታ ዘልዬ፣
ማልቀሴን ምረሳው ለምን ይሆን ውዴ፣
አስተናግር ቅጠል አቀመስሺኝ እንዴ?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
ባደግንበት ሀገር መሄጃ ስናጣ
ያባበልነው ንዴት ገንፍሎ ሲወጣ
የገደለን ነግሶ ቅስማችን ሲሰበር
ኡኡ!... ባይኖር ኖሮ
ምን ይውጠን ነበር?

@getem
@getem
@getem

#ሚኪያስ ፈይሣ
ከፊት ተምዘግዝጎ
ጥላዬ ሲጠልፈኝ
ጥላ እንቅፋት ሆኖ
ማየቴ ሲገርመኝ
መውደቄን ሳላውቀው
መነሳት አመመኝ።

@getem
@getem
@paappii

#Barkiling enyew
(አብርሃም ሙሉ ሰው)

አንኳንኪ ይከፈት፣ የልቤ በር የኔ
ታምሬ ሆይ ልይሽ ፣ቅረቢ ለአይኔ
ህልሜ ሆይ ተገለጭ
ገላሽን ልዳሰው
ማሬ ሆይ ልቅሰምሽ፣ ከንፈርሽን ልቅመሰው
...
የናፍቆት ህመሙ
የብቻነት ድካም ፣ አሰለቸኝ እጅግ
እኔ አንችን ስፈልግ...
ምን ያልሆንኩት አለ ፣ ልቤን ያላደማኝ
ወንድ ሆኜ ስጠጋት ፣ ሁሏም ሴት -ሴት መስላኝ
ስንቴ ተሰብሬ ፣ ወድቌ ተነሳሁ
አይታወሰኝም ፣ ስንቷን ጉድ 'ረሳሁ ?
....
አንኳኪ ይከፈት ፣ የልቤ በር የኔ
ታምሬ ሆይ ልይሽ ፣ ቅረቢ ለዓይኔ
(( ሌላ ሌላ ሌላ ))
ማፍቀር ረስቼ
መውደድን ዘንግቼ
በር መስኮት ዘግቼ
ብቻዬን ቁጭ ብዬ
አትቀሪም ብዬ
ስጠብቅሽ ብዙ ፣ ዘገየሽ አልልም
ብቻዬን የሞትኩት፣
አብረን ከምንኖረው፣ በፍጹም አይበልጥም
ሃይማኖቴ ነሻ ፣ ሳላይሽ አምናሁ
እድሜ ላንቺ -እኔ ፣ ብፁዕ ሰው ሆኛለሁ ፡፡

@getem
@getem
@Abrham_Mulu
,,,,,የታለች,,,,,

ሄዋን ወዴት አለች
በተፈጥሮ ውበት
ኮርታ የደመቀች፣
ፀጉሯ አልበቃ ብሏት
ሂውማን ያልቀጠለች፡፡

አምሮ ለመታየት
በሜካፕ ያለወዛች፣
ጣቶቿን ሞርዳ
ጥፍር ያልሰካካች::

ቅርፃዋን ለማሳመር
በስንፖንጅ ያልተመካች፣
በመሰልጠን ሰበብ
እርቃንዋን ያልወጣች::

ክቡሩን ገላዋንን
በወግ የሸፈነች
ማንነትዋን ሳትክድ
እራሳዋን የሆነች፣
ያቺ ልባም ሄዋን
ንገሩኝ የታለች?!

ሰብለወንጌል

@getem
@getem
@getem
ሳቅሽ ብርድ አለበት?
ለምንድነው እንባ
የምትደርቢበት?

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
#ሌላ_አይደለም
:
:
እውነት ልናገር መልክሽ አይደለም፣
ከሴት የሚለይ አንቺ ላይ የለም።
ጌታን ልበልሽ የምር የ‘ውነትህ፣
ቀርቤ አውቃለሁ ብዙ አይነት ሴትህ።
ካንቺ እንድጣበቅ ባንቺ እንዳመርህ፣
ያረገኝ ፈሊጥ ዋናው ታምርህ፣
ያላንዳች ምክንያት በየደቂቃ፣
አንቺን ሚያስርበኝ ፍቅር ነው በቃ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
Watch "ሙና ከመንደሪን መንደሪን የግጥም መፅሐፍ ገጣሚ ምግባር ሲራጅ" on YouTube
https://youtu.be/_fAQcKAvEmI

@getem
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ያለፍኩትን የህመም ድርድር የቅሌት ድግስ ምን ልሁን ይሆን የናፈቀኝ??
ዞሬ ማየው ሰላም ሳገኝ እንደራበኝ ለቅሶ ብሶት እንደ ደና ውለታ እነዛን ቀናት ?
....እነዛን ያንቺን አይኖች የበደለሰሽን ጠንሳሶች....
...ደላይ ምላስሽን ሸንጋይ ጠረንሽን...
....ባጯሪ ጣትሽን የሚቆጠቁጠኝ ባረፉብኝ ቁጥር ....
ቆይ ለምን ናፈቁኝ እንዛ ህመማት ያ የህመም ድርድር?????

....ቆይ አንቺስ ማሳመም ማስለቀስ ማሳዘን ማስቆዘም እንደ ሙያ ይዘሽው የቆየሽባቸው አልናፈቁሽም ወይ???
....
©Ribka Sisay
....
@ribkiphoto
.................. #ሰላሜን_መልሱ....................
.
.
.
ይነጋል ያልኩት ቀን ላይነጋ እየመሸ፣
ትኩስ ልጅነቴ ጥሎኝ እየሸሸ።
ስተለቸገርኩኝ ሰሚ በማጣቴ፣
እስኪበላኝ ድረስ አቅፎኛል ጠላቴ።
.
.
ኧረ በማርያም!
ስሙኝ በከራማው፣
እዩኝ 'ባርባራቱ።
በምታምኑት አምላክ ተለመኑኝ በ'ርሱ፣
ገዳይ ጦር አልሻም፤
የእሳት ጎርፍ አልሻም ሰላሜን መልሱ።
በልጅነቴ እንባ፤
በአይኖቼ አብራክ፤
ስለማመናችሁ "ይሁን" በሉኝ ይብቃ፣
ከመኖር ይግባችሁ ሞት የመጋ'ት ሲቃ።

"ከነገሮች ሁሉ በፊት "ሰው" መሆን ይቅደም!!"

ሰላም ለአለማችን!!
ሰላም ለሀገራችን!!!
💚💛❤️

ዓቢይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
#ይህች የአሁን ጠሀይ
(ሚካኤል .አ)
ቦግ እልም... ቦግ እልም
ቦግ እልም.. .ቦግ እልም
ወዳጄ ሆይ ቆዝም!
መኖሪያን ማበጀት
በንዋይ መደርጀት
ከእንስት ጭኖች ስር መቅጠፍ አንዲት በለስ
በትዝታ ቅኝት ቅኔ ወጉን መድረስ
ማጣጣም ሙዚቃ
መንገስ እንደ አለቃ
የማለዳ ፀሀይ
የደረጀ ንዋይ
የአንገት ሀብል ማሰር.. .
በውድ ወይን መስከር
መኪና ማሽከርከር
መደነስ መጨፈር.. .
አይንን በአይን ማየት
ስንዴን ከእንክርዳድ ለይቶ ማበርየት
ከቤተሰብ ጋራ ጨዋታን መጋራት
ከምቹ አልጋ ላይ ያለ ሀሳብ መተኛት
ደማቅ ታሪክ መፃፍ
የእውቅና በራፍ ...
ሁሉም ደስታ ናቸው
ቦግ እልም... ቦግ እልም
ቦግ እልም.. .ቦግ እልም
ከዚህ ሀሴት ማዶ ወዳጄ ሆይ ቆዝም
ሁሉም ይላል እልም!
ትጠልቃለች ፀሀይ... መድረሻህ ነው አፈር
አሁን ብርሀን ሳለ
ለእግዜር ቀብድ ስጠው ... ከሱ እልፍኝ ለማደር።

@getem
@getem
@paappii
Audio
ሚስቴ ሁኝ?

#በgeni
(አዝማሪ_ነኝ)

@getem
@getem
@getem
የዘንድሮ ሰይጣን ስንፍና አብዝቷል
እሱ ለጥ ብሎ በሠዉ ከብሮ ያድራል።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ትዝታ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizita21
@getem
ለራሴ ምመክረው...

ከአንገት በላይ አንገት ፣ ማለፍ አቀርቅሮ
ፊትን ፈቶ መቅረብ ፣ በልብ ቂም ቋጥሮ
የይምሰል ፈገግታ ፣ የማስመሰል ለቅሶ
የጥላቻን እርቃን ፣ የአፍቃሪ አመል ለብሶ
ተሸፋፍኖ ሆነ ፣ ሀሉ ተደብቆ
(( ብርሃን ነኝ! ይላል ))
ጨለማ ለሚሆን ፣ ቦታ ቀን ጠብቆ
...
ንስሀው ራሱ ፣ ንስሀ የሚሻ
እንባ ማያነጻው ፣ ያ'ጽያት መጨረሻ
ወዳጅ ተብሎ ታምኖ ፣ ጠላት ሁኖ መክዳት
ነገን እያሳዩት ፣ የሚያውር በትላንት
እንትፍ ለ- ጥላቻ
ቱ ለ- ቂም ለ- በቀል
ገዳይ መሆን ሲሻህ ፣ ሟች ሁነህ ተንጠልጠል፡፡

( አብርሃም ሙሉ ሰው)

@getem
@getem
@getem
#ምነው?



በፈጣሪ አምሳል የተበጀን ገላ፣
ህይወቱ እንድታልፍ በቃታ በቢላ፣
ካሰቃዩት ዃላ፣
የመዳንን ምስጢር ፍቅርን ወዲያ ጥለው፣
ቤንዚን አርከፍክፈው በቁም ሳለ አቃጥለው፣
ሞቶ ያሸነፈን ያን መሲሕ ዘንግተው፣
የተሰጣቸውን ህያው ቃሉን ትተው፣
ግዳይ እንደጣሉ ደረት እየነፉ፣
ጎምለል ቀብረር ብለው በአደባባይ ሲያልፉ፣
ከትቢያ ተናንሶ የሰው ሰውነቱ፣
ሀገሬ ላይ ባየው ባይኔ በብረቱ፣
የወገኔ ሲቃ ከአርያም ሲደርስ አድማስ ሲያስተጋባ፣
ወደ ውስጤ አልቅሶ ልቤም የደም ዕምባ፣
እንደዚህ የሚቀኝ መልስ ያጣ ጥያቄ ከነፍሴ ውስጥ ገባ።


እንዲ ይላል ጥያቄው፣
መልሱን ምን አውቄው?


እስኪያስረሳን ድረስ የመቅደሱን እጣን፣
እውን ግን ሚያባላን ስልጣን ነው ወይ ሰይጣን?
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem