ግጥም ብቻ 📘
64.6K subscribers
1.55K photos
31 videos
61 files
177 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
~~~~ ምኞት ~~~~

አንዱ ሲገኝ አንዱ ሲጎል
ሲስተካከል ሲስተጓጎል
ወና ሲሆን ባዶ ቅርጫት
ድገሞ ሲጥር ለመሙላት
መች ያልቃል የሰው ምኞት
፣ የሰው ልፋት ፣
ሁሌ ፍጋት ሁሌ ድካም እስከሚሞት።

(የእንጀራ ስርቅ) አንድነት

@getem
@getem
...... እየሳቁ ማልቀስ.....
ዳግም ደጀኔ (ሄራን)
በቅርቡ በአዲስ መፅሀፍ ይመጣል!!
#ሰው_ፍቅር_ናፍቆት
በቅርብ ቀን !!
@getem
@getem
@getem
#የጠፍ_ትውልድ_ልሳን
-
"ሀገራችንን - ኢ ት ዮ ጵ ያ ን
ዳሯን እሳት
መሃሏን ገነት ____ አድርግልን!"
-
ብለን የጸለይነው
ሽቅብ የረጨነው፣...
እንባችንን ቆጥሯል።
ስዕለታችን ሰምሯል።
-
ይኸው በዳር ዳሯ - እሳት እናያለን
ምስክር ይሆን ዘንድ - በገነት እንዳለን¡¡
___________
[ በርናባስ ከበደ ]

@getem
@getem
👍2
እንዳላጣሽ

(ዶ/ር #በድሉ ዋቅጅራ)
.
.

በመኖርሽ
ማለዳ ወፎች ሲዘምሩ፣
ዜማቸው
ይገባኛል፤
በመኖርሽ
ምሽት ጉጉት ሲያሟርት፣
ሰቀቀኑ
ያስፈራኛል፤
በመኖርሽ
ጨረቃን አድማስ ላይ ሳያት፣
ውበት
ድምቀቷ
ያጓጓኛል፡፡
.
ብቻዬን
የለኝም ቅኝት፣
ብቻዬን
የለኝም ስስት፣
ብቻዬን
የለኝም ጉጉት፣
እንዳላጣሽ፡፡
----------------
ታህሳስ፣ 2013
@getem
@getem
#ጊዜ #ሚዛን

ባክኖ እያባከነ ~ ዘመኑን በከንቱ
ሲወለድ ቢሞትም ~ የኔ ቢጤ ገልቱ
ህያው ስራ ሰርተው ~ ስም ተክለው ‘ሚሄዱ
የቀብራቸው ቀን ነው ~ ጀግኖች ‘ሚወለዱ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@getem
ግጥሜን አንብቢ..

#ቅልልቦሽ በከዋክት ተጫወትኩ

ፀሀይን እንደኮፍያ ከራሴ ላይ አረኩ

በግማሽ ጨረቃ ሽንኩርት ከትፌያለሁ

መስታወት አድርጌያት

በሙሉ ጨረካ መልኬን አይቻለሁ።

እውነቴን ነው ምልሽ!

ተራምጄ ነበር ደመና ላይ ቀሎኝ

ዛሬ ነው የቀለልኩ ክፉ ጊዜ ጥሎኝ

ካላመንሽ ጠይቂ

እታጀብ ነበረ በአንበሳ በነብሩ 

ብሮጥ አይቀድሙኝም ጥልቸልም አነሩ

ያኔ በዛ ዓመት ወቅቱ ነበር ጥሩ

እንዲህ እንደዛሬው ወርጄ ሳልገኝ

በባህር ዋኝቼ ጥልያን ነው 'ምገኝ

መንደሩን ጠይቂ

ዘንዶ ውጦኝ ያውቃል ቀድጄው ነው የወጣሁ

ዝሆን ልፊያ ገጥሞኝ በክርኔ ነው የጣልሁ

ንጉስ ነው ግርማዬ አክሊል ነው የኔ ዘውድ

ወርቅን ነው የማለብስ ... እኔ ሰውን ስወድ።

ደግሞ የሚገርምሽ ...

ዱር መሀል ስዝናና ሳምንት ይቆጠራል

በቀልድ ጨዋታዬ አራዊቱ ሁሉ ተገርሞ ይስቃል

በጣም ይገርምሻል

በአውሎ ንፋስ አውታር ሰይጣን ገርፌያለሁ

ከመልዐክቱ ጋር ዝማሬያቸው ስቦኝ አመስግኜ አውቃለሁ 

ካላመንሽ ጠይቂ

ሁሉም ይነግሩሻል.. .

የተኛሁኝ ጊዜ ህልሜ ያስገርማል።

ዛሬ ጊዜ ጥሎኝ.. . አዙሮብኝ ፊቱን

አንቺን ነው ማልመው ዘወትር ለሊቱን

ካላማንሽ ጠይቂ ...

አንቺን ስወድ ነው ህልሜን የተነጠቅኩ

ግርማ ክብሬ ሸሽቶኝ ለፍቅርሽ ነው ያደርኩ።

ዛሬ በዚህ ሰዓት ...

ጨረቃም ኮከቤም ፀሀዬንም ትቼ

ላንቺ ነው የምቀኝ ቃላትን ከሽኜ

ካላመንሽ አንብቢ የአሁኑን ግጥም

ፍቅርሽ እኮ ሲጥም! 

(ሚካኤል አስጨናቂ)

@getem
@getem
@getem
👍4
⛺️Camping Trip to #Ankober with #Sunsethiking!

📅camping Date :- Jan 23 - 24, 2021(tir 15 - 16, 2013)

🛫Departure:- - Piassa Tayitu Hotel

Departure Time - 2:00Am Local time 🚩

💵 contribution per person:- 1350 💰

🎉🎊Package 🎋🎊

🔵🚍 - Transportation
🔴⛺️- Tent, campfire &tea
⚫️🍝 - Traditional Roasted meat ( 🐏), Lunch and snaks🍟🍤
⚪️ Bottled water
🔵 Park entrance with Guide
🔴photograph 📷

NB.
🚫 Sanitizer & facemask mandatory!


for more join the
🔸channel @sunsethiking🍁
🔻📷 @sunsetphotography🍁

🎫 tickets available at
@Paappii ( +251922303747 )
እህህ...
እህህ
አንቺ አለሽ በጤና
አውቃለሁ... አውቃለሁ
የኔ ነው የጠፋኝ
ኧረ እንደምን አለሁ?
ንገሪኝ ስለኔ
እንዴት ያልፋል ቀኔ?
አውቃለሁ ያንቺንስ
አውቃለሁ ናፍቀሻል
እኔስ ናፍቆት ራቀኝ?
በምን በኩል ናፈቅኹ?
ፀፀቱስ ለቀቀኝ?
ኧረ እንደምን አለሁ?
የቅድማያትሽ ቤት
አርሲ ያለው dheራ
ዘመም ጎበጥ ያለው
የኋለኛው አጥር
እንዳዲስ ተሰራ።
የተሰራ ለታ
አጥር ሊመርቁ
የመጡት ጎረቤት
ሰክረው ደጅ ወደቁ።
ሰምቻለሁ እሱን
ንገሪኝ ይልቁን
መርጬ እንዳልበላ
ብስልና ጥሬ
የሚከከክለኝ
የሚጠዘጥዘኝ
ተሻለኝ አልሰሬ?
ወለም ብሎኝ ስወድቅ
ተጣሞ አልነበር?
አሁን እንዴት ሆነ?
ይራመዳል እግሬ?
ሳውቅሽ ደህና ነበርኩ
ስትሄጅ ያመኝ ነበር
ተሻለኝ ወይ ዛሬ?
ኧረ እንደምን አለሁ?
አያትሽ ካዛንችሽ
ካንድ ቱጃር ጋራ
የመሬት ክርክር
የነበረባቸው
በየመንግስት ቢሮ
በጠራራ ፀሐይ
በእግር ሲኳትኑ
ቱጃሩ ሌ'ት መጥቶ
በእጁ ቀደማቸው።
ሰምቻለሁ እሱን
ንገሪኝ ይልቁን
ትምሕርት ብጤ
ጀምሬ አልነበር?
ተመረቅኩ ወይ ተውኩት?
ስራዬስ እንዴት ነው?
ያኔ የተቀጠርኩት?
አዲስ ሰፈሬንስ
ጠላሁት ወደድኩት?
ልክ እንደቀድሞዬ
እስቃለሁ እቱ?
የሳቄ ታቦትስ
ደስታ ነው ጽላቱ?
ወይስ እንደ ሄድሽው
ከንቱ ነው ውእቱ?
ኧረ እንደምን አለሁ?
አባትሽ ለቮልሱ
አዲስ ጎማ ገዝቷል
ወንድምሽም ጠብሶ
ጫት መቃሙን ትቷል
እናትሽ ቀኝ እግሯን
ይጠዘጥዛታል
አጎትሽ ቀን በቀን
የታክሲ ረዳት ላይ
ሹፌር ላይ ይዝታል
ያ ቦቢ ውሻችሁ
አንገቱ ስር ቆስሏል
ምናለ ትያለሽ!
ሰሞኑን ይሞታል።
አየሁ ያንቺንማ
የኔን ልወቅማ
ንገሪኝ እስኪ የኔን
ይዣለሁ ፍቅረኛ?
አጨሁ ወይ እጮኛ?
ወለድኩ ወይ አግብቼ ?
አደጉ ልጆቼ?
ኑሮ
እሚሉት
ቁልቋል፡
ፀድቋል
ወይስ ደርቋል?
እልህ አሜኬላ
ያቆጠቆጠብኝ
ቆንጥር ነኝ ከድሮም
አልቆረጠልኝም?
እሾህ ነኝ ዘንድሮም?
ኧረ እንደምን አለሁ?
ውበት ፈሶብሻል
አምረሽ ሞት መስለሻል
አየሁሽ በቀደም
ጉንጭሽ የእንጆሪ ደም
ያለፍሽባት ምድር
በጣዝማ ተነክራ
የተራመድሽበት
እንደፃ'ይ ሲያበራ
ግርማሽ አኮስሶኝ
የማማትብበት
ቢጠፋብኝ ቀኜ
«በስመ አብ!» በግራ።
እንኳን ሄደች አልኩኝ
በምልክት ልሳን
አፌን ትንፋሽ ርቆት
ኪሩብ እንኳ አይደለሁ
ስጋዬ እንዴት ችሎ
ሊታቀፍ መለኮት?
ካንቺ እሚተሳሰር
ግሱን ግሳንግሱን
ከደጃፍ ከጓሮሽ
ማን ሳር መበጠሱን
ምን ንፋስ መንፈሱን
የማን ቤት መፍረሱን
የማን መታደሱን
ተይው ሰምቻለሁ
ይልቅ እኔ ጠፋኝ
ንገሪኝ በሞቴ
እኔ እንደምን አለሁ?
ህያው ነኝ ሞቻለሁ?

@getem
@getem
@paappii

#rediet aseffa
*ላንተው*

ስንት ዘመን ዕንባ ሁኖኝ ላይኔ ስር ኩል ፤
በምን ጥበብ ልቤ ሳቀ ባንተ በኩል ?!

@getem
@getem
@paappii

#Helen Fantahun
"የመረጨት ስምረት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
****************
በባሕረ ቡራኬው
በጥባሌ ጥማቄው
ሕዝበ አዳም ፍጥረቱ
በንጋት ጉዞ ፍሰቱ

ምራቄውን ሰንቆ
እርኩስናውን አርቆ
በእግዚኦታው ተማጽኖ
ዕምንተ ክሩን ጎንጉኖ

ሲተም በትማሜ ዥረት
ለይቅርታ ለበረከት
ለጉዳሌው ጉድል ሙሌት
ከተራውን ሊከትርበት
በዓለ ክብሩን ሊነግስበት

የእመቤቴን ቸርነቷን
የምልጃዋን ተአምራቷን
ሊነፍስበት ደግነቷን
ሊጸናበት መሠረቷን

አደግድጎ በነጠላ
በጧፍ ከርቤ በዣንጥላ
ስዕለቱን ለምህላ
መባ ሲሰጥ ፍጡር ሁላ ።

ሻማ ዘቢብ ውብ ካባውን
የምስጋና በረካውን
ዕጹብ ሊያደርግ መከራውን።

በቀኑ ስምር ቀኑን ሰርቶ
ከእጦት ይልቅ አግኚ ሞልቶ
በአንድነት ግምድ ግፍፊ ዓለም
አንዱ ባንዱ ሲተራረም

ሕብር ሸማ ፍቅርን ሲቀልም
ድምጻችን ላይነጥፍ ተሰማ
ከሰማየ ሰማያት ከዘለዓለሙ ከራማ
አዬ ጥምቀት የነፍስ አርማ ።
............

(እንኳን ለ2013 በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ : አደረሰን)
@poem_with_mela
@poem_with_mela
@getem
@getem
🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
........... ©ሲራክ ......
በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣
አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣
ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣
ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ......
ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ።
በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣
እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣
ማጨብጨብ ተስኖኝ ...
እልልታ ጠፍቶብኝ...
ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ።
ይኸውልሽ ውዴ ....
አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ ..
እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ..
ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣
ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣
ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥
ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ።
እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣
ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣
እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣
አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ።
አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣
ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ።
እስከዛ ግን አንቺ .....
ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ
ሂጂልኝ ግድ የለም፣
ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ...
ፈርቼስ አይደለም።
ወርውር ያለኝ ልቤ .....
ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣
እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ።

🍋🍋🍋🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋🍋🍋
--------- ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@getem
@getem
@getem
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ እኔ እና ክርስቶስ “ የግጥም መድብል ::

//

ንፋስ ወእስትንፋስ

አገር እንዳንላት ካ'ለም አይደለችም፣
ገነት እንዳትባል ካፈር አልራቀችም፤
ቅጽበት ናት ኢትዮጵያ!
በስተምስራቅ በኩል የምትመጣ ንፋስ፣
በጥልቅ ዕንቅልፍ መሃል እንዳለች እስትንፋስ።
@getem
@getem
@getem
👍1
አጥንቴ በደም ተሞላ ፣
ምላሴም በጉሮሮዬ ታነቀ
ጨረቃ ግርማ ሞገሷ ፣
ፀሀይም ብርሃኗ ጠፋ
መላዕክት ሰይፍ መዘዙ ፣
የመለከት ድምፅ ተነፋ
መብረቅ ህዋውን ሲያነጋ ፣
ማዕበል ክዋክብትን ጠረገ
ተራራው እንደ አፈር በኖ ፣
ውቅያኖስ ወደ ውስጥ ሰረገ
መቼ እንደሆነ ታውቂያለሽ ፣
የተሰማኝ ይህ አባዜ
ከብቸኝነት ሰገነት ፣
አውጥተሽ የሳምሽኝ ጊዜ።

@getem
@getem
@paappii

#Kura Gebra
Audio
አሌክስ አብርሀም


@getem
@getem
@Abrham_teklu
#አይከፋም
አውደምህረት መሀል ተቀምጠሽ መማር
ከጋዜጣ አምዶች
ከገፃቸው ደረት ማንበብ አንዲት ጦማር
ሙዚቃን ማዳመጥ መመሰጥ በዜማ
ቁምነገር አይጠፋም ከሰማሽውማ።
አይከፋም
ሰርግ ቤት ተገኝቶ ሀሴትን መሸመት
ከጃምቦ ብርጭቆ ስሩ ላይ መገኘት
ዕፀ ሰመመኑ ሲጃራው ጭሰቱ
ሁሉን መሞካከር ደግ ነው በውነቱ ።
.
ከጉብል መሳሳም ገሳ ተጀቡኖ
መዓዛውን መሳብ አንገቱ ስር ሆኖ
ተራራ ላይ መውጣት ሀይቅ ዳር መዝናናት
ሁሉም መልካም ናቸው ለደስታሽ ግብዐት።
አይከፋም.. .
መታወቅ በሀገሬው ፥ የገነነ ዝና
የአሸርጋጅ አጀብ ፥ ስልጣንና ጤና
ውበትም ድንቅ ነው ማማር መሽሞንሞኑ
በሰው ልጅ ፍካት ነው የሚደምቅ ቀኑ።
አይከፋም ...
የጀበና ቡና ጥቂት ማክያቶ
መዋሉ ሸጋ ነው ጨዋታን ተጋርቶ
ጥሬ ስጋ መቁረጥ.. .ጠጁንም ማንደቅደቅ
በተድላ በትር ነው.. . ድባትሽ የሚደቅ ።
አይከፋም ...
ከህላዌ መዝገብ አኗኗርን መግለጥ
በቀለም ፍሰቶች የዕውቀት ጥምን መቁረጥ
ሁሉም ደግ ናቸው
አይከፉም በውነቱ ...
ሆኖም አያክሉም የአዳምን ሞቱ ።
ይኸውልሽ ዓለሜ...
መፅሀፍ ከመግለጥ ከመዞር ጉባኤ
ሰርግ ቤት ተገኝተሽ ዳንኪራ ከመርገጥ
በጉብል ልጅ ቃና ደርሶ ከመመሰጥ
ከንዋይ ከክብሩ ከዓለሙ ዝና
ከዚህ ሁሉ ገና ...
መቃብር የሚሏት የፍፃሜ እውነት
እርሷ ትበቃለች እውቀትን ለማግኘት
መማርስ ከሟች ነው አፈር ከቀመሰ
ፅልመት ከተዋሰ
ማየት ሀላፊን ነው ድንቁን አስተማሪ
አትቅሪ በህይወት በአንዲቷ ድግሪ
ሌላ ድግሪን ደግሞ ከሞት ላይ ጨምሪ።
፤፤፤
.... (ሚካኤል አስጨናቂ)...

@getem
@getem
@getem
👍1
የንጋት ጸጋ
ለካስ
ወድቀን ነበር በውድቅት
ተሸንፈን ደክመን በጽልመት
ጠፍተን ተሸሽገን በጨለማ
በምስራቅ ባይልኮስ የብርሃን ሻማ
ለካስ
ባትወጣ የጥዋቷ የንጋቷ የፍካቷ ጀምበር
እምነት ክህደታችን
ሃሰት እውነታችን ተሸፍኖ ይቀር ነበር፡፡
ሜሎስ
@getem
@getem
~~~~~~~~~~~~~~~~~~


#የመነነ_ቅኝት
.
.
ባ'ለካኸው ስንዝር፤
~ባልሰራኸው ወንጀል፣
ካልሞካት ፀሃይ ስር፤
~ባልበደልከው በደል፣
ልጄ አንተን ከራበህ ሆድህ ካልጠረቃ፣
በመናኝ ቅኝትህ፤
አንጀቴና ልቤን ወስደህ ብላው በቃ፡፡!!!!


@abiye12

@getem
@getem
የምታምኚው መልክሽ ተከታይ አብዝቶ
እኔ አለው ቢልሽም
ምሽቱ ሲቃረብ ቀን የፈካ ፀሐይ ማታ
አይኖርልሽም!

@getem
@getem
@getem

ካሊድ አቅሉ
"ራስ ንጉሥ"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
.
.
ከድብት ኩሬ ከኃሴት ጣራ
በመለሳ ስፍራ

በሕላዌ ታድሞ
በግብሩ ግርፍ ተደሞ

ከሞጣህት ሰጥሞ
ከክብሩ ሽል ገጥሞ

ተንተርሶ
ተርመስምሶ
ተድበስብሶ
ተዳብሶ

ከስል ትልም ተጋድሞ
በእድሞ ተደምድሞ

በተስፋ ማጣት አርግዶ
ርግፍ ዕርዮት አግዶ

ለነገ ትልሙ
ለዛሬ ስሙ
ጥብቅና ቆሞ
እራሱን ስሞ

ለእራስ ሲቆርሱ አያሳንሱን ፈሊጡን ለብሶ
ሰው ኖረ ዘለዓለም በእራሱ ላይ ራሱን አንግሶ።
......
@poem_with_mela
@poem_with_mela
@getem
@getem
#የድሀ ትሩፋት!

.

ሀብታም ሆኜ ሳለው ...

ጨብራራ ጎረምሳ ፥ ኑሮ ያሸመደው

ሸራውን ወድሮ ፥ ቀለሙን ሲያፈሰው

እብድ እየመሰለ ፥ ገርሞ እየታየኝ

አብስትራክት ብሎ ፥ ስዕሉን ቢያሳየኝ

ይበልጡን ደበረኝ!

አሁን ይሄ ራስታ ... 

የሀሳብ ከርታታ...

በቀላም ጭቃዎች ፥ ተለውሶ ቆሞ

ብሩሽ እያነሳ.. . የሚለቀልቀው 

አብስትራክት ያለው ስዕሉ ምንድነው?

እኔን የሚገባኝ አብስትራክት ማለት 

ነው ስራ ፈትነት !

ዓላማ ቢስነት !

በውስኪዎች ፈንታ ቀለማትን መርጨት

ከሴት ጋር ተቀምጦ እንደመጉረስ ከንፈር 

በወጣኒ እድሜ ... በግዑዝ መደበር 

ካልጠፋ መዋቢያ ... መፈሸንን ንቆ

በዝተት አልባሳት.. . ገላውን አላሽቆ

ሳየው ይገርመኛል..

ስዕል እየሳለ ስዕል ይመስለኛል ።

...

ሀብታም ሆኜ ሳለው ...

በጫት ቅጠል ነፍዞ ...በሲጃራ ጥንባት

እድፋሟን ስከርቭ.. . አንገቱ ላይ ጥሏት

ውዴ ፍቅሬ ግና.. . ጨረቃና ፀሀይ

የደመናው ንጣት.. .ደግሞም ይሄ ሰማይ

ምናምን እያለ የሚፈላሰፈው 

ያ ምስኪን ገጣሚ እውነት ጤነኛ ነው ?

እያልኩ አስባለሁ ።

አሁን ለዚህ ወጣት ... 

ድህነቱ ገዝፎ ... ፊቱን ላገረጣት

ሰማይ ፀሀይ ብሎ ስንኝ ከሚቋጥር

ምናል ስራ ሰርቶ እህል በልቶ ቢያድር?

እያልሁኝ ኖሬያለሁ ብዙ ዓመታትን

እኔም ድሀ ሆኜ እስካያት ጥበብን።

..

አሁን የሚገርመኝ.. .

በመፅሀፍት ፈንታ ዳሌ የሚያነበው

ቀለም እንደመርጨት ውስኪ የሚያፈሰው

መኪና ሲቀይር ... ሀሳብ ያልቀየረው

ከግጥም ተጋብቶ እንደመኖር አብሯት

ይህችን ብርቅ ዓለም ከሴት ጋር ጨርሷት

የሚኮፈሰው ነው ያ ከርታታ ሀብታም

የጥበብ ስስታም.. .

አብስትራክት ስሎ.. . ስዕል ሳይደረድር

ዓለምን መስጥሮ ... መፅሀፍትን ሳይጭር 

ለሙዚቃው ቅኝት.. . ክራሩን ሳይወድር

ነፍስያን መበደል ... ገንዘብ ብቻ መርጦ

አያስጠላውም ወይ ... መኖር ከሀሳብ ዘቅጦ?

እያልሁ አስባለሁ.. .

የድህነት ትርፉ.. .ጥበብ ነው አውቃለሁ።
....

@getem
@getem
@paappii

#ሚካኤል አስጨናቂ....
👍3