ግጥም ብቻ 📘
64.6K subscribers
1.55K photos
31 videos
61 files
177 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እነዚህን ሁለት ግጥሞች የዛሬ ሁለት ዓመት ከምናምን ነበር ጣና በእንቦጭ አረም የተወረረ ጊዜ እዚሁ የቴሌግራም ቻናል ግርግዳ ላይ በፅሁፍ ለቅቄው ነበር እናም አሁንም ግን የጣና ሀይቅ ጉዳይ መፍትሔ ስላልተገኘለት ህዝቡም ሆነ መንግስት ችላ ስላሉት በአንዳንድ በጎ ሰዎች እንደ አዲስ ተነስቶ መንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር እና ጣና ሀይቅ ሙሉ ለሙሉ ሳይጠፋ እዳውም ለአባይ ሳይተርፍ አሁንም እየጮኹ ይገኛሉ እና እኛም ጩኸቱን ተቀብለን ማስተጋባት ይዘናል ...#ለዛሬ ለምሽታችን ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በፅሁፍ የለቀኳትን ዛሬ ቢነሽጠኝ ጊዜ በድምፅ ለምን አልሞክራትም ብዬ ሁለት ግጥሞችን ጀባ ብያለው ተጋበዙልኝ.....

ሸጋ ምሽት !💚 "ናካይታ"💚

@getem
@getem
@Nagayta
ሰኔ እና ሰኞ!!!!


ሃበሻ ብልህ ነው፣ዘመን ይሞሽራል፣
እሮብ ባሙስ ሽሮ፣በአርብ ይጀረጅራል።
ታዲያ ዛሬም ድረስ፣በቀን ቅኔ ቋጥሮ፣
በቀንና ባመት፣ፊክሮ ፈክሮ፣
ሊቀናው ነው መሰል፣ ዘመንና ኑሮ፣
ሰኔ እና ሰኞ ቀን፣ ገጠመ ዘንድሮ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@Nagayta
የምኞት ጫፍ!
(ዳግም ህይወት)
.
.
አትሰማኝም እንጂ፥
ስጠራህ ስጠራህ፥ ከጀማው ለይቼ
አታየኝም እንጂ፥
እንቅፋት ሲመታኝ ፥
ከተራማጅ መሃል ፥ አንተን ብቻ አይቼ
ስንቴ እንደወደቅሁ ፥ ስንቴ እንደተሰበርኩ
ባልሰጠኸኝ ግዛት ፥
ርስትህን ላስከብር ፥ ጎንህ እንደነበርኩ
አንተ ስትገረፍ ፥ እኔ… እንደደማሁ
ጠላት ሲያሴርብህ… ቀድሜ እንደሰማሁ
አታውቅም አውቃለሁ
ለሚወዱት ዓለም ፥ ተላልፎ መሸጥን!
በሚያፈቅሩት ህይወት ፥ ሞትን መለወጥን!።
እንደ ጋሻጃግሬ!
በጠላትህ በኩል ፥ በመከራህ በኩል
በነፍሴ እያቀለምኩ ፥ የሞት መልኬን ስኩል
ስንቴ ተላልፌ ፥ ቀራኒዮ ወጣሁ
አንተን እየፈለኩ ፥ ራሴን ስንቴ አጣሁ።
የሚገርመው ነገር!
ዛሬም በ'ንቅልፍ ዓለም ፥ ዐይኖችህ ወድቀዋል
ከመቃብር አፋፍ ፥
ከውድቀት ተራራ ፥ አናት ላይ ከትመዋል።
ላይገለጡ ነው ፥
ላያዩ ነው መሰል ፥ እስከ ጌታ ምፃት
የመገፋቴ ስፍር ፥ ነፍሴን እንዲያነጻት።
እኔእንደሁ አልሳል
(አይሞረድ ቀልቤ)
የወርቅ ዣንጥላ
እጣንና ከርቤ፥ ወስጄ እንዳስገባ
"ማህሪ ተብዬ፥
"ይቅር ባይ" ተብዬ ፥ ገነት እንድገባ።
ቀሚሴን አልቀድም'
ክብሯ እንደፈረሰ ፥ የቤት ጋለሞታ
እናዳነባች እናት፥
ሀዘን እንደጎዳት ፥ መሰል ልጇ ሞታ።
ግን አንድ እውነት አለ!
ከዚህ በባሰ ቀን ፥
የመሪር ሀዘን ግንድ ፥ አውጥቶ ቅርንጫፍ
ሞትህን ከሰማሁ ፥ ወድቃለሁ ህይወት ጫፍ።
እናም …
ጣርህ እና ጣሬ ፥ እኩል ተጠራርተው
ሞትህና ሞቴ ፥ በልሳን አውርተው
ሳልሰማ ሳትሰማ ፥
ክፉህም ክፉዬን ፥ ሰከንዶች ሳይቀድሙት
አንድ ሌሊት ታመን ፥ አንድ ቀን እንሙት ።
አሜን ወአሜን
.
.
@getem
@getem
"...
ወይሁኝ ለጣና፣
ወየሁ ለአብያታ ... ወየሁኝ ለጫሞ
ፊት ሰው ሞቶለታል ... ባሕር ይሙት ደሞ?? "
/
(# አበባው_መላኩ ፣ "ወዮ አለማያ")

@getem
@getem
#bernabas
........../// አሳባቂ ብርሃን \\.........
°°°°°°©ሲራክ
አሳባቂ ብርሃን ማሰብ ማይከለክል
ልቦናን አብርቶ ከራስ የሚነጥል
እንደሚሻ ፈረስ እንደሚንቀለቀል
እንደክረምት ጎርፍ እንደሚጥመለመል
ይመጣል አንዳንዴ ራሱን ሳይከልል
ገሳ ሳይጠለል
-------- #አሳባቂ_ብርሃን ____
_°°°°°°°°°°°°___
@getem
@getem
@getem
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

<< አባ >>

ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
አባትነትህ ልዩ ነው
ከነውጠኞች የሚበልጥ
ለኔ ለልጅህማ
አለምን ሁሉ ሚገለብጥ

.. ዛሬ ግን..........
አባ ፈራሁ ተጨነኩኝ
ስሷ ልቤ ተቀየመች....
ካልጠበኩህ ቦታ ተገኝተህ
ምስኪን ልቤ አለቀሰች...
አዎን አባ ተቀየምኩህ
አምርሬ አነባሁኝ...
እጅህ ቀሚሴን ሲገልብ
ከባትነትህ ጠፍቶ
የአውሬ ፊትህን አየሁኝ.....

.......ግን ያልገባኝ የኔ አባት......
ምን የማታውቀው ውበት
የቱ የተደበቀ ደም ግባት
ከእኔ አልጅህ ዘንድ አየህ...
ልብህ ለሴሰኝነት ተገዝቶ
ከአባትነትህ አስበልጦ
እርካታህን ያስመረጠህ
እስኪ ተናገር ካለ
ያላየኸው የደበኩህ ልጅነቴን
ስታቅፈኝ እኮ ታውቀዋለህ
ስትኮረኩር
ስትደባብስ ሰውነቴን

አባዬ.....
አሁንም አባቴ ነህ
ስምህን የምጠራበት
ያሳደገኝ ነውና
አንገቴን ሳልደፋ በፊት
ምጠራ' የኮራሁበት

* * * * * *
ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
* * * * * *

አዎን አባዬ...
ትዝ ይልሀል...አፌን ስፈታ ገና
አባዬ ነበር ያልኩኝ
የማነሽ ሲሉኝ እንኳን
ያባቴ ልጅ ነበር ያልኩትኝ

ዛሬ ግን....
ሴሰኝነትህ በለጠ~ ከትውስታችን አለፈና
ከእናቴ ያጣኸውን ከኔ ከልጅህ ፈለክና
እናቴ ስታልፍ እንኳን
አንተ ነበርክ እናቴ
ሰው በራበኝ ግዜ እራሱ
ሆነሀልም ጓደኛዬ....
ከዛ ሚበልጠው ግን
አባቴ ብዬህ ነበር
እኔነቴን የሚገልፅ
ክብር መከታዬ እንደ ነበር

አሁንማ....
አንተው በፈጠርከው ገላ ላይ
ተረማምደህ አረከስከው
የወደፊት እኔነቴን
በአውሬነት ደመሰስከው

አዎን የኔ....... ጀግና አባት
እውትትም ወንድ ወጥቶሀል
ሴት የሆንክ መስሎኝ ነበር
እኔን ለማሳደግ፣
ስመለከት ከሴት መሀል
ብዬ ነበር የኔ አባት
እውነትም እናት ሆኗል

ስሷ ልቤን አስከፋሀት
አዎን አባ ተቀየምኩህ
እንድተኛ
ተረት በነገርከኝ ቦታ ላይ
ዛሬ ግን
ከጭኖቼ መሀል አገኘሁህ.....

📩ይድረስ📩
<< በከባቷ ህይወቷን ለተቀማችው ህፃን>>

ተፃፈ በ @Mak_bale
ሰኔ,2,2012

@getem
@getem
@getem
1
እሳት
""""""
አይቶና ተልሞ
እሳትን ለመፍታት፥ አይገኝም ውሉ፤
ደግም ክፉም አይሉት
ለመፈረጅ ከባድ፥ ብዙ ነው ተግባሩ፤
ለቅል ነው አመሉ!

እሳትነት ሲታይ
አላቀቀን ስንል
ከጨለመ ደዌ ፥ብርሃን አቀናጀ፤
ሲያስለቅሰን ያድራል
የነካነው እንደው ፥ብርሃኑ እየፈጀ!
መገበንም ስንል
ለአፍ የቸገረ ፥ጥሬውን አብስሎ፤
ከችግር ይጥላል
ጎጆውን፣ ንብረቱን ፣ንዋዩን አቃጥሎ!

አይሆን ተናግረውት
እሳትን አንቋሾ
............ ማጥላላት አይቀና
ደግሞም አሞግሶ
............አይሆን ለምስጋና
የእሳትነት ግብር
............ጥንድ አመል ነውና!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@paappii
Audio
*ለየቅል*
.
እኔ የሻማ ዕንባ
ብርሃንን ለግሼ ቁልቁል ምወረወር
አንተ የ'ሣት ጌታ
ለዕምነቱ ያደረን አካል ምታቃጥል
ግብራችን ለየቅል ነዳጅና አንዳጅ
እስኪ በል ንገረኝ ለማን ነው የምንበጅ?
.............//...........
በሔለን ፋንታሁን

@getem
@getem
@getem
ሥዕል ለማሳል
በ +251934039346
ወይም @cher46 ላይ ፎቶ በመላክ ማዘዝ ይቻላል።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ

@seiloch
@seiloch
.........///.እንደ ወረደ.///....
ገና በትኩሱ እንደ ተወለደ
ጉልበት ሳይጠነክር ልቡ ተራመደ
ኣይኑ ሌላ ሳያይ እሱዋኑ ወደደ
እናቱን በ ፍቅር ገና እንደ ወረደ።

( ቴዉድሮስ)

@getem
@getem
🖤🖤🖤🖤
.... ፈራጁ ከጠፋ ....
.
.
.
በሴትነት ገላ ህፃን ተፈትኖ ልጅነት ጨከነ፣
ከአባትነት ይልቅ የወንድነት ስሜት፣ በአካል ገነነ፣
ዘመን እረከሰ ትውልድም ቆሽሾ ጭካኔ ሰፈነ።
.
.
.
.......... እውነት እልሀለሁ
ለዝች ምስኪን እንጭጭ ፈራጁ ከጠፋ፣
ጥበብ እንዳትጮህ ማስተዋልም ይክፋ፣
እውነት ሀገር ይጣ ፍትህም ይገፋ።
.
.
.
የእንቡጧን ሲቃ ሚሰማው ከጠፋ.....
.
.
.
ፍቅርም ቤቱን አጥቶ መንገድ ዳር ይዳፋ፣
ለምስኪኗ ጨቅላ ድምፃችን ከጠፋ፣
የማስተዋል ጥጉ ዳር ላይ ከከረፋ፣
ችሎት ያጣው ስሜት በእብለት ከገፋ፣
የህጻን ሴት ገላ ስሜት ማርክያ ሆኖ ትርጉሙ ከጠፋ፣
ፅድቅ ትርጉም አጥቶ መኖር መሮ ይክፋ።
.
.
.
ወላጅነት እና የወንድነት ጥጉ በዉል ሳይታወቅ፣
የብዙዎች እንስት ልባቸው ሲጨነቅ፣
ፈራጁ ይጠበቅ ዳኛዉ አይበል ፈቀቅ።
.
.
.
ልንገርህ ወገኔ-----------
በሀሰት ማሳ ላይ ተስፋችን አትደግ፣
መብት እየተሰጠን መብትን አንነፈግ፣
በጭንቅላት ሰበብ ቅል ለተሸከመ ህሊናን አንፈልግ።
.
.
.
በጭን ነብስ አግኝቶ ለጭን ነብሱን ለገደለ፣
የሀሳቡ ዝቅጠት እረግቶ ለጠለለ፣
መኖርን አልሞ መሞትን ለቻለ፣
.
.
.
ለአብራኩ ክፋይ ክንድን ላበረታ፣
አባዬ ለሚል ድምፅ ፍፁም ላልሰጠ አፍታ።
መጨከን ተጨንቆ ክፋትን ላስከፋ፣
ሰይጣን አስቀንቶ ስራውን ላስከረፋ።

.... ፈራጁ ከጠፋ....
.
.
.
መሬት አትዋጠው ፍትህ ሀገሯ ይራቀው፣
መኖርን አልሞ መሞትን ይቅመሰው፣
..... የምን ትንሳኤ ነው፣
ኑሮ ትርክት ሆኖ ሞቱን ሞት ይዋጠው።
.
.
.

ማስታዎሻነቱ በአባትዋ ለተደፈረችው ህፃን......................
1/10/2012
መክሊት የ 16ቷ
ለአስተያየት @Yuliyana16

@getem
@getem
1
#እልፍኟ

ባለፈው አመት ላይ ና ብለኸኝ ነበር
ብዙ ጊዜ ነግረህ ከእልፍኙ እንዳልቀር
ይኸው በአመቱ
ቃልህን አክብሬ ከእልፍኝህ ብገባ
ስም ዝርዝር ውስጥ
የለው ከእልፍኙ እንዳልገባ
ማንም ማይቀርበት
ቤቴ የሁሉም ነው ሲለን የነበረ
ዛሬ በስም ሆኗል የሁሉ እንዳልነበረ
ጥሩ የሚለብሱ ከውስጡ ቢገቡ
ልባሰቸው ነው እንጂ ክፋትን ሚያስቡ
ሚያውደው ሚቀቡት የልብሳቸው ሽቶ
ግብራቸው ሲያጠፋው ስራቸው ከርፍቶ
እልፍኟም የለችም ያቺ የፍቅር ቤት
ዛሬ ተቃርማዋት አድርገዋታል
የግብዞች መሬት

ብላቴናው

@getem
@getem
@getem
እድሜዬን ንገረኝ

ለሀጢያቴ ቅጣት ማስተሰርያ..
ለክብርህ ዙፋን ስል ለመንበርከኪያ፣
ጉልበት እንዳትንሳኘ ፣
ወዳንተ እመጣ ዘንድ መልክት እንዲደርስኝ ፤
የምሞትበትን እድሜዬን ንገረኝ።
አ.ግ

@getem
@getem
<የሰው ልጅ>

ወዶ ምን ሊጠቅም ~
ጠልቶ ምን ሊገታ
ይጠብቀን እንጅ የ ፈጠረን ጌታ ።
@getem
@getem
🤩1
#ሙሉ ጌታ (የልቤ) ለማንም ማስታወቂያ መስራት አልወድም ለሙሉ ጌታ ስለ ምሉእ ጌታ ግን ማንም የጥበብ ወዳጅ ፣ ማንም የግጥም ወዳጅ ፣ ማንም የቅኔ ወዳጅ ፣ ሰው የሆነ ሁሉ አማርኛ የሚችል ሁሉ እንደ ቁርኣን እና መፅሐፍ ቅዱስ እቤቱ አስገብቶት እንዲያነበው ባያነበው እንኳን ለእቤት ግርማ ሞገስ ነውና እንዲያስቀምጠው እሻለው ስለሱ በደንብ አልተወራም እንዲወራለት ፈልጋለው ......#ፀሐይ ሆኖ አብርቶ የኩራዝ ያህል ክብር አልተሰጠውም አሁን ግን ያቺ የሙሉ ጌታ ፀሐይ እየወጣች ነው እሱ ይሄን ለማየት ባይታደልም....(እቺህ ሀገር ስንቱን አበባ ቀጥፋ ለስንቱ አበባ አስቀመጠች?)ለማንኛውም ከላይ የምታዩት መፅሐፍ የባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ስራዎችንን እና ማብራሪያዎችን አጠናክሮ የያዘው " ኢትዮጵያዊነት እምነት " በሚል ርዕስ ዳጎስ ተደርጎ ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉ በፋሲካ ከበደ ተዘጋጅቷል :: ፋሲካ ከበደ ከዚህ ቀደም " የባለቅኔው ኑዛዜ " በተሰኘው መጽሐፉ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬን ዘክሮበታል ::

" ኢትዮጵያዊነት እምነት " መጽሐፉ ስለ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ሕይወት ዙሪያ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቡ በደንብ የታየበት ቅኔዎቹ የተፍታቱበት ያለተነገሩና ያልተሰሙ ዐዳዲስ ነገሮች የተካተቱበት ዳጎስ ያለ ድርሳን ነው ::

#እባካቹ ነው የምለው አንብቡት መርምሩት ይሄን የከተማ ባህታዊ ፣ ይሄ ሀበሻዊው ካህሊል ፣ ይሄ ንጉስ ፣ ይሄ ቅዱስ ፣ ይሄ ፍቅር ስጋ ለብሶ ፣ ይሄ ምሉእ ...ይሄ ...ይሄ..ይሄ....

#እሱን ለማወቅ የአበበ ተካ ሙዚቃዎች ስሙት (በተለይ ወፍዬን )

#እሱን ለማወቅ የታምራት ደስታን "ሀኪሜነሽ " ስሙት

#እሱን ለማወቅ የብፅአት "አደራን ልጄን " ስሙት

#ከምንም በላይ እሱን ለማወቅ "የባለቅኔው ምህላ እና የነብያት ኑዛዜን አንብቡት "


በፍቅሩ ትወድቃላቹ ፣ በስራው ትደመማላቹ ፣ በድርጊቱ ትወዛገባላቹ ፣ በህይወቱ እውነት እንደዚህ አይነት ሰው ነበር ትላላችሁ .....እውነት ትላላችሁ .....

"ናካይታ"💚 ሰላም አምሹልኝ!

@getem
@getem
@Nagayta
156,500 አባላት ያሉት ቻነል መግዛት ምትፈልጉ
@atsuperior ላይ ልታናግሩን ትችላላችሁ፡፡
"ነገ መቼ ነው? "
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።
ጥበቃን በናቀ፥
መጪን በማይናፍቅ ፥ ዝም ባለ መንገድ
የዛሬን የነገን፥
እስር ፈቶ ለቆ ፥ ትዝታን ነው ማገድ።
ይለኛል መንፈሴ……
ስለልጅነቱ አጢኖ እያሰበ ፥
የማይመለስን ሐቅነት አፍቅሮ ፥
ዛሬውን አኩርፎ ፥ ትላንቱን ይስቃል
አለሁ ማለት ውሸት!
ነገ 'ሚባል ቀንስ ፥ እንዳለ ማን ያውቃል ?

@getem
@getem