ግጥም ብቻ 📘
65.6K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
176 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እኔም በኔ ቁና
"""""""""""""""""
ልትፈትሽኝ አይተሽ
ገመና ችግሬን፥ በፀሀይ ጠራራ፤
አይኖችሽን ዶለሽ
ልብሽ ልቦናየን፥ ደጋግሞ ቢያጣራ!

በቆምንባት ፀሀይ፥ ሲፈትሸኝ ቢውል፤
እኔም በኔ አይን
አየሁት ልብሽን፥ ፈተሽኩት ያንቺን ውል!

እናማ ስፈትሽ
በራስ ቁና መስፈርት
ልቤ ልቦናሽን ፥በአንክሮ ሲያጣራ፤
የእምነትሽ ገመድ
የተስፋሽ ማሰሪያ ፥ቀጭን ነው ሰላላ፤
ክርክር የበዛበት
የተዘናነፈ ፥ማጥበቂያው የላላ!

ልብሽም ልብ የለውም
ንቀትን ሸክፎ ፥ፍቅርን አይናፍቅም፤
የላይ ላይ ብቻ ነው
ቆንጥጦ አይዝም ስር ሰዶ አይዘልቅም!

ልብሽ ልብ የለውም
አይመራመርም፥ አያስተውል ከቶ፤
የወደደን አያውቅ
የጠላውን አያውቅ ፥አይዝም አጥርቶ፥
ሰባራ ነው እምነትሽ ያለ ተንኮትኩቶ!

ሀሳብሽም ከንቱ
ከፍሬ ገለባው
ከስንዴ እንክርዳዱ፥ እጅጉን መብዛቱ፤
አይንአዋጅ አለበት
ያም የኔ ያም የኔ ያም የኔ ማለቱ፤
መራርጠሽ ስትኖሪ
ሰውን መገመትሽ ፥ይሄ ነው ስህተቱ፤
ምራጭ ነው መውደቂያሽ
በሰፈርሽኝ ቁና ፥ያው ሰፈርኩሽ እቱ!

እናማ አለሜ
ሰፍረሽኝ ከጨረሽ
ተልቆ ከታየሽ ፥ያ ሰባራ ጎኔ፤
ባየሽበት ቅፅበት
ያንቺንም አየሁት ፥እኔም ልክ እንዳይኔ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@paappii
ተጋጋሪ እንጀራ
ዓይኑ እንዲበራለት ይሠማል ምጣዱ፤
ማየቱን ሲጀምር ወደ አፍ ሊሄዱ፤
በምጣድ ጆሮና በእንጀራውም ዓይኖች አፍም ይከፈታል፤
እንደ'መስማት' ጥበብ ትልቅ ምግባር የታል?፤

አጭሬ
(ልዑል ኃይሌ)

@getem
@getem
@getem
የሰካራም ግጥም
_______________

ማን ነው የሰከረው? 🤔

ሰሙ የእኔ መጠጣት ወርቁ የእሷ መስከር
ከመስከሯ በፊት ስትቀዳልኝ ነበር
አልገባኝም እኔ "ለምን ሰከርክ?" ብላ እቃ ስትወረውር
.
.
እኔን ለታዘበኝ አርምሞዬን ላየው
የመነኮስኩ እንጂ የጠጣው አይመስለው

ከሶፊ

@getem
@getem
@paappii
የመጀመሪያው ቀን
ሲራክ
የመጀመሪያው _ቀን
ገጣሚ፦ ገብረ ክርስቶስ ደስታ
አንባቢ፦ ሲራክ @siraaq
@getem
@getem
@getem
#ሁለት_ገፅታ

አይዳንድ ጊዜ : ሰዉ ከራስ ሲስማማ፣
ሲሄድ ሲራመድ : በሀሳብ ማማ፤
አይጣል ነዉ ነገሩ፣
አይፈታ ሚስጢሩ።

ሰዉ . . . .
ከራስ ተስማምቶ : ሲመቸዉ ጊዜያቱ፣
ረጥቦ ሲለመልም : ዉስጠት አንጀቱ፤

ፈጣሪን አይሰማ : ከራሱ ሲጣላ፣
ራሱን ተመክቶ : አያገኝ ከለላ።

ሀሴት ሲጎናፀፍ፣
በቀሽም ሀሳብ : ከጎን ሲደጋገፍ፤

ያገኘ ሲመስለዉ : ኪሱ ሲሞላ፣
ጠግቦ ስለዋለ : ሲሞላ(ሞ) በተድላ፤

ሚስጢር ነዉ ነገሩ፣
አይጣል ነዉ ሚስጢሩ።

ደግሞም . . . . .
ሲከፋዉ . . .ተድላ ሲከዳዉ፣
ሆድ ሲብሰዉ : ባዶነት ሲሰማዉ(ሰ)፤

ከራሱ አይስማማ፣
ከቶ አይራመድ : በሀሳብ ማማ።

. . . . .
ደግሞም ደግሞም፣
ሰዉ ከራስ ተጣልቶና ከርሞም፤

ሲናከስ ከሀሳቡ፣
ሲኮፈስ ከልቡ፤

ሲራቆት ሲናቆር፣
ሲፋጅ ሲሸናቆር፤

ሲከፋዉ በሆዱ ሲከዳ፣
የልቅሶ እንባ ከልቡ ሲቀዳ፤

ማልቀስ፣
ከሁሉ መናከስ፣
ከህይወት መፋለስ፤

ስራዉ ሆኖ በየጊዜው፣
ፈጣሪን ያማራል: ሆዱ ሲጎለዉ።

ደግሞም . . . . .
ከራስ ተስማምቶ : ሲመቸዉ ጊዜያቱ፣
ረጥቦ ሲለመልም : ዉስጠት አንጀቱ፤

ይኖራል ፈጣሪን ረስቶ፣
ነፍስ እያለዉ ሞቶ።

ይኖራል ረስቶ አስራቱን፣
ደሀዉን መቀለቡን፣
እጅ መዘርጋቱን።

ይኖራል ረስቶ : የእዉነትን አምላክ፣
ያቺን የፈጣሪ እናት : ያቺን ወላዲተ አምላክ።


እንግዲህ . . . .
የዚህ አለም ኑሮ : እንዲህ ነዉ በየአይነት፣
ሲያጡ ፈጣሪን መፈለግ : ሳይነጋ ለማግኘት።
ሲያገኙም አምላክን መሸሽ : ሲመሽ ላለመገኘት።

በቃ ይህ አለም : እንዲህ ነዉ ሀቁ : የሞላዉ ልዩነት፣
ማግኘት ማጣት ሰፍቶ : ጠፍቶ አንድነት፣
ያገኙትን ማጣት : ያጡትን መግኘት።

18 / 10 / 2010

@getem
@getem
@getem
👍1
ቁመው ተቀደሙ!!!!!!!!


እጅ በሞላበት፣
እግር በበዛበት፣
አይተው ካልሄዱበት፣
ሰርተው ካልበሉበት፣
እጅም ዋዘኛ ነው፣ እግርም አባ ልግመት።


ታዲያ በኛ ቀዬ፣
አንድ ራሳቸውን፣
መሄድ አቅቷቸው፣
መሄጃው ጠፍቷቸው፣
መሃል መንገዱ ላይ፣
በሚያምር ባታቸው፣ ሞንደልደል እያሉ፣
ወይ አይራመዱ፣
ወይ አያራምዱ፣
ወዲህና ወዲያ፣ ሰርክ እንደዋለሉ፣
ማን ይሂድ?? ማን ይምጣ????
ግራ እንደገባቸው፣ ቁመው ሲደመሙ፣
የልብ እግር ባለው፣
ባንድ ጎበዝ ጀግና፣ ሁሉም ተቀደሙ።

((( ጃ ኖ )))

@getem
@getem
@balmbaras

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁና ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ !💚
"ሲጓዙ መጠበቅ"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*********
ቀለም ያናከረው ብልቃጥ ልቅላቂ
መስለሽኝ ታየሺኝ ድንገት ስትስቂ።
እኔ ፍቅፋቂ
አንቺኑን ናፋቂ።
.
.
.
ተጻፈ:-፰/፲፪/፳፻፲፩ ዓ.ም
@getem
@getem
@poem_with_mela
የጥላቻ ንግግርን በጋራ እንከላከል።

Oromiffa Version:

https://forms.gle/AWq3CWKwKQqvpNoV9

Amharic Version :

https://forms.gle/oMa2WHCrENvFdL3R9

English Version:

https://forms.gle/ZzJ3Kmzafu1S7o479

Thank you for your support!
ግጣምና ግጥም
""""""""""""""""""""
አንቺን ፍቅሬን ብዬ
ሀሳብ አውጠንጥኜ ፥የምፅፈው ግጥም፤
ከኔ ይሁን ከእውነታው
ቤት አይመታ አይደፋ ፥ምቱም አይጣጣም!
ስንኞች ያንሳሉ፥
ቃሎች ይጠፋሉ፥
ብዕሩም አይታዘዝ ፥ቀለሙን አይሰጥም፤
ለካ ልፃፍ ሲሉ
ሀቅን ይፈልጋል፥ እውነት ይሻል ግጥም!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@paappii
በ +251934039346
ወይም @cher46 ላይ ፎቶ በመላክ ሦዕል ማሳል ይቻላል።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ

@seiloch
@seiloch
[እሪ በይ]
.
እሪ በይ ኡኡ በይ ብዕሬ
የእውነት ምሥክሬ
ፈላጬ ቆራጬ
የሥትንፋስ ፍላጬ
ሐቅን ተናገሪ
እውነትን መሥክሪ
እሪ በይ ብዕሬ
ተናገሪ ዛሬ
አድምጦ የሚመልሥ
አቋድሶ የማያቃምሥ
እሥከምታገኚ
እሪ በይ አትቦዝኚ
ብዕሬ ተንፍሺ
ዋጪ እንጂ አታቀርሺ
ካላየሽ ዝም በይ ካየሽ ግን ተንፍሺ
እሪ በይ ብዕሬ ቁሚ እንጂ እንዳትሸሺ
.
#zeku
.
@getem
@getem
@getem
ረመዳን
❤️
ረመዳን የተከበረው ወር ስያሜ መሆኑ ይታወቃል። ለመሆኑ ረመዳን ማለት ምን ማለት
ነው?

ረመዳን የሚለውን ስያሜ የቋንቋው ሊቃውንቶች በተለያየ መልኩ አብራርተውታል።
ከፊሎች ረመዳን (ረመደ ወይም ረምዳእ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ።
ይህ ማለት ደግሞ ጥማትና ረሀብን የሚያመጣ እጅጉን የበረታ ሀሩር (ሙቀት) ማለት
እንደሆነ አያይዘው ይገልፃሉ።
ሌሎችም ከዚህ ጋር ተቀራራቢ ባለው መልኩ አብራርተውታል።


ለምሳሌ ታላቁ ሙፈሲር ኢማሙል ቁርጡብይ :—
"ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎችን
በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ ስለሚያደርጋቸው ነው።" በማለት አብራርተውታል።
ቁም ነገሩ:—
ማነው በዚህ በተከበረ ወር መልካም ስራዎችን አብዝቶ በመስራት አመቱን ሙሉ
ያከማቸውን ወንጀል አቃጥሎ አመድ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ!?

❤️ረመዳን ቁርአን የወረደበት ወር
❤️ረመዳን የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ️የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት
❤️ረመዳን ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር
❤️ረመዳን ከሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት የያዘ ወር
❤️ረመዳን ከምንጊዜውም በበለጠ ዒባዳ የሚደረግበት ወር
❤️ረመዳን ፈርድ ስራዎቻችን በ 70 የሚባዙበት ሱናዎቻችን የፈርድን ዋጋ የሚያገኙልን ትልቁ
የረመዳን ወር ነው።




ረመዳን መጣ!!!!!!


እንግዲህ ጓዴ ሆይ፤
ሾይጣን ሊታሰር ነው፤ ረመዳን መጣ፤
መቼስ ሰው ነኝና፤
የበደልኩህ ካለ፤
አኡፉ በሉኝና!!!!!
እኔም ሸክሜ ይቅለል፤ አንተም ነጃ ውጣ።

((( ጃ ኖ )))

#እዚህ ቻናል ላይ ባለማወቅ ያስቀየምኳቹ ፣ በምፅፈው ነገር ቅር የተሰኛቹ ወንድምና እህቶቼም ካላቹ ያው ካለማወቅ ካለመብሰል ሊሆን ስለሚችን አውፍ (ይቅርታ ) አድርጉልኝ ከልባቹ!!

ለመላው የእስልምና ተከታዮች እንኳን ለታላቁና ለተከበረው ለረመዳን ፆም አደረሳቹ!!!

# አላህ ከፈቀደ 36 ቀናቶች ቦኋላ የምንገናኝ ይሆናል !

ጦማችሁ ይመርበት!!❤️

@getem
@getem
@Nagayta
👍1
እውነትን ስቀሏት!!

ስቀሏት! ስቀሏት! እውነትን ስቀሏት!
እሷ ስለሆነች የሰው ልጆች ጠላት
ምድር አትፈልግም የሀቅን ውለታ
ስቀሏት! ስቀሏት! በርባን ግን ይፈታ !
ካለችበት አገር እጇን የሚያስይዘን
ማነው አሳልፎ ስሞ የሚሰጠን?
ስቀሏት! ስቀሏት!
እውነትን ስቀሏት!!
በርባንን ፍቱልን
መቃብር ተከፍቶ ሂትለር ይነሳልን
አቦይ ሞሶሎኒን ሂዱ ቀስቅሱልን
ቦካሳና ስታሊን ተቃቅፈው ይምጡልን
ከሲኦል ደጃፍ ላይ ጋኔልን ጥሩልን
ልጅ ግራዝያኒ በቶሎ ይምጣልን
ውቡ ገጽታዋ መልኳም እንዲጠፋ
ደጋግመን “አክ!” እንበል ፊቷ ላይ እንትፋ
እውነትን ለመግደል እንጩህ አጥብቀን
ግን እንዳትነሣ በሶስተኛው ቀን!
ትውልድ እየመራች የምታባልገው
እሷ ስለሆነች ስሟ የገነነው
ወዳጅ ዘመዶቿን ፊት ለፊት ተጋፍጠን
በሆታ ተባብረን ፣ ጮኸን - ተጨጩኸን
በጎለጎታ ላይ መስቀል አሸክመን
ኣዋርደን - አዋርደን - እውነትን አዋርደን
ወዳጅ - ዘመዶቿን አሳደን - አሳደን
በገዛ ልብሶቿ እጣ ተጣጥለን
በጭንቅላቷ ላይ የእሾህ አክሊል ደፍተን
መራራውን ሃሞት እሬት አጠጥተን
ጎኗን በጦር ወግተን!
እንባዋን አፍስሰን!

ደሟን አንዥቅዥቀን!
ዳግመኛ እንዳትመጣ በሰው ልጆች አምሳል
እውነትን እንስቀል በወንበዴ መሀል!
እውነት ስለሆነች ...
ስንቱን ያዋረደች
ሜዳ ላይ የጣለች
እውነት ስለሆነች
ስንቱን ያጋለጠች
ሚስጥር ያባከነች
ቅሌት የፈጠራች
እሷ ስለሆነች ....
እውነት ስትፀና ኃላ ይቆጭሃል!
ስንት ሰው እንደእኔ ይጨልምብሃል?
የስንቱን ሰው አንጀት በእሷ ተቃጠለ
ኩሩው ተዋረደ - ታላቁ ቀለለ
እውነት ያጠፋችው ስንት ነገር አለ!!
እውነት ነች !እውነት ነች! እሾህ አሜኬላ
ይሄን አዲስ ትውልድ በክላ - በክላ
አምላኪዋ በዝቶ ኋላ ከመቸገር
ዛሬ ነው መስቀል ላይ እጅ - እግሯን መቸንከር!
እውነት ክፉ ናት መራራ ......
ያለ ስጋት ተኝታችሁ በሠላም እንድታነጉ
ሀቅን ማለባበስ አደል ጨርሶ ማጥፋት ነው ደጉ
“ታወቀ-አልታወቀ” ብሎ መፍራት መጨነቅ ምንድነው?
ሀቅን መሸፋፈን ሳይሆን አፏን አፍኖ መግደል ነው!
እውነትን ካላጠፋናት
መልሳ አጥፊያችን እሷ ናት

እውነትን ሲጥ አርገን ገለን
መቃብሯን በወታደር በመቶ አለቃዎች አጥረን
ሰልስቷን አርባዋን በልተን
ነፍሷን አይማረው ብለን
ስሟን ከታሪክ ላይ ፍቀን
ያዘኑላትን አፅናንተን
ደስ ያላቸውን ሸልመን
ያኔ ነው በሰላም እንቅልፍ
“እፎይ!” ብለን እምናርፍ፡፡
የስው ልጆችን ገመና የምታጋልጥ ለዓለም
ከእሷ በላይ የሚያሳድድ፣ የሚያስጨንቅ ጠላት የለም
ስቀሏት ይቺን ጠንቀኛ
በእሷ ሞት እንዳን እኛ!
ተፃፈ:- ፳፻ዓ.ም

ሰለሞን ሞገስ (ፋሲል)

#share

@getem
@getem
@NuEnanbib
👍1
እለፊው!(ልዑል ኃይሌ)

የረገጥሽው እሾህ አብቅሎ
የታቀፍሽው እንጨት ቢከስል፤
የቆላሽው ፍሬ እያረረ
የጣድሽው ሁሉ ባይበስል፤
አትሳዪኝ በክፉ ልብ ውስጥ
አትሳዪኝ በርግማን ምስል፤
ስንወለድ ጀምሮ
ምንም ለኛም ባይገለጥ ዕጣ ፈንታችን ኖሯል፤
በፍፁም ክህደት ሰብሬሽ
'አላውቃትም!' እንደምል ከዕትብቴ ጋር ተቋጥሯል፤
እኔም አደግኩኝ ተነሣሁ
ከልብሽ እልፍኝ ተቀመጥኩ፤
ለተፃፈልኝ ክህደቴ
አመቺውን ጊዜ አማረጥኩ!፤
ሳወጣ ሳወርድ ቆይቼ
ጥዬሽ ሄጃለሁ አውቃለሁ፤
ግን የተፃፈልን ይኸው ነው!
.
.
ስለዚህ...
በሆነው ሁሉ አትዘኝ ፈጣሪሽን አታማርሪው፤
በጠመኔነቴ ተጠቅሞ የፃፈልሽን ተማሪው፤
ሚያዚያ 12,2012

@getem
@getem
@getem
#ለቀን #ተማሪ #ማሟያ #ጽሑፍ
መትረፏን ጠብቀህ ~ በማለዳው ፀሐይ
አህያን ጠይቃት ~ ስለ ጅቦች ፀባይ
ዘርዝሮ እንዲያስረዳሽ ~ ያህያን ባህሪ
በጨረቃ ወ‘ተሽ ~ ጅብን አነጋግሪ
ጊዜና ጉልበቱን
ድካም ፍርሀቱን ~ መቆጠብ የሚሻ
ሳይተኛ ካገኘው
የሁለቱንም አመል ~ ይነግረዋል ውሻ
====||====
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@getem
#ዕድሜ ለ...
:
:
ዕድሜ ለሊፒስቲክ...
ዕድሜ ለዐይን ኩል...
ዕድሜ ለሂውማን ሄር...
ዕድሜ ለፊት ፓውደር...
ደብዝዞ የነበረው ውበትሽ ደመቀ
የሚያሳዝነው ግን ...
ጠግበሽ ሳትበዪ ገንዘብሽ አለቀ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@Henokbirhanu

@getem
@getem
ዱአና ፀሎት
""""""""""""""
በክርስቲያኑ ዘንድ
የአብይ ፆም አልቆ እንደተቃለለ
አሁን በሙስሊሙ
የረመዳን ፆም ወቅት መልሶ ቀጠለ
በዱአና ፀሎት
ሰይጣን መሄጃ አጣ ሲደበደብ ዋለ
በሰንሰለት ታስሮ
በብረቶች ታጥሮ በሩቁ ተጣለ።

አለም ነጃ ትውጣ
አለም ነፃ ትውጣ
ከመጣባት ደዌ ከያዛት በሽታ
በቃ በለን ይብቃ
ከሰቆቃ ወጥተን እንኑር በደስታ!

ነጃ በለን ነጃ
ነፃነት አድለን ሰላም ለዱንያ
ሞቶብን አይለቅ
የሰው ክቡር ህይወት ልክ እንደ ክፍያ!

ነፃ በለን ነፃ
ነፃነት አድለን ሰላም ለምድሩ
ጤና ሁኖ ይደር
ጤና ሁኖ ይዋል አውጋርና አድባሩ!
#አሜን

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ረመዳን ከሪም!
@Mykeyonthestreet