ግጥም ብቻ 📘
68.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
172 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የስሌት #ጋብቻ
#አንቺ
ሽማግሌ አዘጋጅ ብለሽ ተናግረሻል
ምን አለው ይሉኛል ብለሽ ተጨንቀሻል
#እኔ
ከቀየው መርጬ
በቂ ሽማግሌ አዘጋጅቻለሁ
የሌለኝ ነገር
ለራሴ አለኝ ብዬ በቃል ሸምድጃለሁ
#እነሱ
ቤተዘመድ መጥቶ
ምን አለው ለማለት ማልዶ ይሰለፋል
ሽማግሌ ከቦ
ምን አለው ለሚባል
የወላጅ ጥያቄ የሐሰት መልስ ይፅፋል
#ውዴ #አትጨነቂ
ያንቺ ብቻ አይደለም የሀገር ነው ችግሩ
እኛም ቤት ብትመጪ ይሔው ነው ነገሩ
#አምና
የታናሽ እህቴ
የልጅነት ፍቅሯ አመት በአል አስታኮ
በፍቅር መርቀን
ፈቅደን እንድንሰጠው ሽማግሌ ልኮ
#መልስ #ሲጠባበቅ
በዚህ ወገን ሆኜ እኔም ጠይቄያለሁ
ማይደርስብኝ መስሎኝ ምን አለው ብያለሁ
በሴት ወገን ስንሆን የወንዱን ባናውቅም
ምን አለው ተብሎ ሰው አይጠየቅም
ሀቅ ተዟዙሮ
ቦታ ተቀያይሮ
የትናንት ተቀባይ ከነገ ወዲያ ይልካል
በሴቷ ጠይቆ በወንድ ይጠየቃል
ሸፋፍነነው እንጂ
ደፍረን ከጠራነው ነገሩ ያሳስባል
በንግድ አጠያየቅ
ምን አለው አይደለም ስንት አለው ነው ሚባል
ባንክ ቤት ስንት አለው በጥሬው ያኖረው
ስንት መኪና አለው የሚያሽከረክረው
ስንት ካሬ መሬት ካርታ የወጣለት
ስንት ክፍል ቪላ የተንጣለለለት
በልጅ የደም ቀለም የሌለንን ስንስል
ልጅ የምንድር ሳይሆን ገዢ ነው ምንመስል
የመመኘት ቀመር
የማዟዟር ብዜት በዘመን ሲጣፋ
ምን አለው ነው እንጂ
ከዬት አመጣው የሚል ሽማግሌ ጠፋ
#እኔ #ምለው ?
የማካፈል ስሌት ዞሮ የመጣ ‘ለት
ምን ያህል ይዘናል ምን አለው ለማለት
#ይልቅ
እግዚአብሔር አድሎት
በጥላቻ ዘመን የሰው ልጅ ሲፋቀር
አፍቃሪ ልብና
ሁሉም ነገር አለው ከሀብት በስተቀር
ሀቁን እያወቅነው ውጠን ከማባበል
ምን አለውን ትተን ምን የለውም እንበል
=====||=====
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@beppa_19