ግዕዝ ሙላት / ግጥሞቹ/
392 subscribers
34 photos
11 links
አነ ግዕዝ

'
Download Telegram
ኢትዬጲያ 👋
ሩጠን ሳንጨርስ ድካም እንዳይመጣ
በጣም ተጣልተን ሰላም ሚባል ይምጣ

በጣም እንጋደል በጣም እንማታ
ብርሃን ብቻ አደለም የተስፋችን ቦታ
ቀን ቀንን አንጠብቅ እንታረቅ ማታ

ተዉ እንታረቅ ተዉ እምነት ስጡ
ይበልጥ አታስፋፉት የገደሉን ምጡ

ተዉ እባካችሁ ሀገር ነው የያዝነው
ተዉ ስለማሪያም እውነት ነው የያዝነው
ትንሽ ሲጨልም ነው
ድንቢጥ በሌሊቱ ሲጥ ብላ ምትጮኸው

ወዶ ላልተገባ ወዶ እንዳይወጣ
በጣም ተጋድለን ሰላም ሚባል ይምጣ


08/01/2017
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
በወጋሽኝ እጅሽ
ኑሮሽ መክረም ነበር
ሀሳብ ከሚበጅሽ
ሞትም ትዳር ነበር

አስበሽኝ  ይሆናል
ብየስ እያሰብኩት
አላውቅም ባውቅማ
ያንቺን ኑሮ በከረምኩት

በከረምኩት በነፃነት
ብኖረውስ ተንደፍድፌ
ልብ ጭምትር ኩርኩም ቢሆን
አልጠቀመም ባንቺ ልፌ

ጀግና ሆነሽ የደም ስም
መተቃቀፍ ሀዘን ያስረሳል
ትንሽ ስሜሽ አመት እርሽኝ
ካዘንሽበት ቀን ያስወጣል

አንቺ መሳም በጣም ሀዘን
አንቺን ማኖር በጣም ክፋት
ህልም ብቻ የጌሾ ሀሳብ
ላያድሩብሽ እንዲው መልፋት

በጠጉርሽ ላይ ፋኖ መሳይ
ጫካ አዳሪ ያለ ሲሳይ

ሳቅሽም ጥርስሽ ጥሩ ውበት
ሀዘን አለው ስትስቂበት

ነፃነትሽ ለደቂቃ
ስምሽም ትንሽ ስሜት
ድቅን ሲልም ያንቺ ሀዘን
ጥፊ ነው ያንቺ እሬት

ድቅን ድቅን እንደጨለማ
በለስላሳ የሚያለፋሽ
ደርሶ ከቶ ሚለውጥሽ
ሀዘን ነበር የሚገፋሽ ?

እስቲ ንገሪኝ የኔ ዓለም
በነፃነት ነፃ እንዳትሆኝ
ያደረገሽ የኔ አደለም ?

አደለሁም እኔ እጂ
አደለሁም አጠርጣሪ
እንዴት ፍቅር አይዋስም
ደፋር ልብ ከፈሪ

እንዴት አታውሽም
እንዴት አትዋሽም
እንዴት አትረሽም
እንዴት ለሀዘንሽ
እኔን አትረሽም

ባልፎክር ባላውቀው
ባልተኩስ ጥይቱን
አልነፈገኝም እጂ
በትዕግስት ማለፋን
ወንድነት ቢረሳኝ
አውቃለሁ ማቀፋን


ለነፃነት

@geez_mulat
አንቺን መቅረብ ቀላል ነበር ?

እኔን መቅረብ እንዴት ነበር ?

@geez_mulat
ረክሶ ነው እንጂ
እግዜር ሚባል አልማዝ
ይሻማበት ነበር
ፍጡር እንደቁስ ጓዝ

ረክሳ ነው እንጂ
ማሪያም ሚሏት ሀምሎ
ቤት አያጣም ነበር
ልብ 'ሚባል ኪሎ

ቀንሶ ነው እንጂ
ሰው ሚባል ሳጥናኤል
ወንበሩን ባልሸጠው
ለእነ ሊቅ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤልስ
ይጠብቃል ሰውን
ቅዱስ ገብርኤልስ
ያወጣል እሳትን
እግዜር ግን ዝም ነው
ያቺን ቀን ያላትን

ሀገር ሚባል ዕዳ
ቃል ሚያክል ሚካኤል
ሸጦታል አሉ ሰውን ለሳጥናኤል

እግዜሩ ቢረክስ ገነት ይወደዳል
ሳጥናኤል ቢረክስ ሲኦል ሰውን ያጣል
ሰው ሰውን ካጣ ሰው ከየት ይገባል ?

ጨለማው ላይ ሆነሽ
ስሜንም አትጥሪ
ጊዜ ሚጠብቅ ሰው
አይባልም ፈሪ
እባክሽን ዓለም
ባይሆን ሰይጣን ፍሪ


@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
ደሞ እዛ ማዶ ፥ መንግስቱ ይታያል ፣
ደሞ እዚህ ሰፈር ፥ ሸሌ ቦንብ  አሲይዟል፣

ከፍቷት ከፈነዳች ፥ ውስጥ ውስጡን አንድዷት፣
አጥፊ ዝም ካለ ፥ ይሆናል ቁልፍ  ጠፍቷት ፣"

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
የድሮው አምላክ
'
'
አዲሱ አምላክ ገና አልመጣም
የቀድሞ አምላክ አገናኜን ፣
ቢያንስ ቢያንስ ባያድሰን ፥
ለትዝታ እስኪፈጥረን ፥
አዲሱ አምላክ እስኪ ተወን ፣
'
'
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

" ዛሬ ጠዋት አያቴ  ከድሮ ጓደኛዋ ጋር ተገናኝታ
የድሮ አምላክ አገናኜን ስትል ሰማዃት "
ዕድሜ ለጠገበው ሰው ደረት ይደቃል
ያልተበላ ዕድሜ በሞት መሃል ቆሞ ፣
ሰው ሲያረጅ ያለቅሳል ወጣት ሞትን ስሞ ፣

@geez_mulat
'
'
ፋኖ ትለኛለች ቤቴን ከውስጥ ዘግታ
የድሮ ባሏ የኑሮ ኪሷ መሆኔን ረስታ

ፀጉሬ እንኳ ያደገው ፋኖ ሆኜ አደለም
ፀጉር ያለው ሁሉ
ልብ ካልመረረው ሞትን አልገደለም

በሩን ክፈችልኝ
ያነኛው ወንድሜ ከፍቶኝ ነው አረሳም፣
በሌት መምጣቴ
ጫካ ማደሬ ቤቴን አያስረሳም፣

ፊቴ ከሰል ሆኖ መለየት ቢያቅትሽ
ፀጉሬ ተጨንጨብርሮ አይኔን ቢጋርድሽ
ወደውስጥ ስገባ እኔ እንድታወቅሽ
ያኔ ታቅፊኛለሽ....
ቀዝቃዛው ግድግዳ አውርቶ ሲነግርሽ

@geez_mulat
ሀገር እና እምነት
እውነት እና ሀቅ
ባንድ ላይ ሲኖሩ ፣
ሞት እና ፍርስራሽ
በህዝብ አደሩ ፣

@geez_mulat
ቤታችን ላይ ካለው ማዶ
ይታየኛል ፊላ ዛፍ
አልጋ ሰርተን ደጅ እንተኛ
ጨረቃዋን ለማትረፍ
በዛው እንኳ ለማቀፍ

በዛው እንኳ እንዲሞቅሽ
እልም ካለ ቀዝቃዛ ሀገር
ስንት ሌት ደጅ አደርኩኝ
ለመሳም ያንቺን ከንፈር

ልትኖሪ ነው የመጣሽው
ልትከርሚ ነው ያፈቀርሽው

ነፃነት ናት የኔ ሀገር
ልብ አይገድም ላሳብ ደንበር

አግብቻት እንድኖር
ስመኝ ስመኝ በቀለበት
ሀገር ሚያክል ትክሻዋ
አጎበጣት እንደ እመት

ልጆች ሚያክል ስትወልድልኝ
የነፃነት ንፁህ ዘርን
ልብ መች እኩል ሊወድ
ባል እና ሀገርን

ስብከነከን በየጫካው
ሳስብ ደሞ በገጠሩ
ፋጨት ሁሉ ወፍ ሲጠራ
ቤቴ ሆነ ያንቺ ዱሩ

ፀጉርሽ እንኳ ጎፈሬ ነው
ጉንጉን እንኳ አትሰሪም
መስመር የለው የዱር ጫካ
ታይተሽ እንኳ አትጠሪም
ደሞም እኮ አታስፈሪም

የዱር ወይን በለስ ፍሬ
አጋም እሾህ ብታገቢም
አፍቃሪ እግር ቢወጋበት
ቢደማ እንኳ አያምም

እጠራጠራለሁ ያንቺን ደረት
እጠረጥራለሁ ያንቺን እሸት
አብረሽኝ እውነት ነሽ
ወይስ የቀን ውሸት

ፀጉር ሰሪዋ ሞታለች
ማነው ከቶ የሚሰራሽ
ጉንጉን ከራስሽ መንገድ ባገኝ
ገባኝ ኑሮ እንዳስፈራሽ

ቤታችን ላይ ካለው ማዶ
ይታየኛል ፊላ ዛፍ
አልጋ ሰርተን ደጅ እንተኛ
ጨረቃዋን ለማትረፍ
በዛው እንኳ ለማቀፍ

በዛው እንኳ እንዲሞቅሽ
እልም ካለ ቀዝቃዛ ሀገር
ስንት ሌት ደጅ አደርኩኝ
ለመሳም ያንቺን ከንፈር

አትገኝም እንደልብ
ቢራቢሮ መንገደኛ
በዛው ቀንቶሽ ከመጣሽስ
ባልሽ ነኝ ነይ እንተኛ

ደረትሽ ላይ እስኪ ስጭኝ
ሀገር ጠፋቶኝ ደክሜለሁ
ማረፊያ እንድትሆኝኝ
ወታደር ሴት አፍቅሬለሁ

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

"የአንዲት ወታደር ሴት መንገድ "
ያልሆንኩትን ሆኜ ሳልኩት
የሆንኩትን ስሆን ስኖር
አላውቃትም ላውቃት ስሻ
አትቆይም ትንሽ ብትኖር

ቀደሰች እያወቀች
ደም ቀምሳ ለምትለምደው
ምን ያደርጋል ከተነቃ
ነቄ ብለን ከለመድነው

ከሰማንስ ማንን ሰምተሽ
ተስመሽ ለምታልቂው
ከረሜላ የምላስ ልብ
ተደባብሰሽ ለምትነቂው

በምላስሽ ጀርባ ደሞ
ጥርስ አበቀልሽ ትንሽ ትንሽ
ከመቁሰሌ በላይ በላይ
መሳሜን ነው የምነግርሽ

አለ አይድል...
እንደ ሮማ ጅራፍ እሾህ እንዳቀለጠው
አፍቅሮ ላጠፋ ንግስት ለተመኜው
ባደባባይ መሃል ወቴ እንደሚገርፈው

አንዴ ጅራፉ ከጀርባው ላይ ሲያርፍ
ስጋን አንስቶ አጥንቱን ሲተርፍ
ልብ እስኪጨንቃት እስኪንሰፈሰፍ

ያን ያህል ነው
የምላስሽ ጅራፍ የቃላትሽ ለምድ
ትንሽ እየሳመ ህመም ሚያስለምድ

አንዴ ይፈታ እንጂ ጀርባ ስጋ በፍርድ
ንግስት ካዘነች ይሄዳል ተስቦ ከተፈታ በግድ

@geez_mulat
አንቺን ነበር የፈለኩት
ላንቺ ነበር የተሳልኩት

ወይ አለችኝ ህልም ብላ
ጋኔል አለች ጨለም ብላ
መቼ ሰማች ወይብላ

የጠራናት ከአመት ቁስል
ሞተን ቆየን መጣሁ ስትል

ደከምኩኝ እስካለሽ
ተብከነከንኩ በየአፍ
ይቅናህ በይኝ እንዳገኝሽ
አልደረስኩም ስንቱን ባልፍ

ደሜን ማነው ያባከነው
ሞቴን ብቻ ሚመነዝር
አንቺን ከእኔ እያራቁ
ቃሉን ደግመው የሚያሰምር
ማነው አንቺን የሚያፈቅር ?
ማነው አንቺን አምኖ ሚያድር
ማነው ላንቺ የሚሰክር ?

ከእኔ ብቻ ዕንባ ዕንባ
ከእኔ ሌላ ህመም አለ?
ወይ'ብላም አጠራኝም
ኮሶ ብቻ መድን ካለ

ኑሮሽን እንድሸከም
ወንድሞቼን ፈለኳቸው
ተከዜ ላይ ጎርፉን ሆነው
ወድቀው ነው ያየኋቸው

ሶስት አይን ጥቁር ያላት
ሀዘን ጫንቃ የበዛባት
ይቺ ሀገር ሀገር ሳትሆን
የሲኦል በር ማለፊያ ናት !

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
ሐሙስ ማታ ....አቃቅፌሽ
ስሞቅ አደርኩ እቅፍሽን፥
እንኳ ሳምኩሽ አይቆጨኝም
ሳታስቢው ከንፈርሽን ፣
አንዴ ልድገም አንዴ ብቻ
እችላለሁ ጥፊሽን ፣
....እያልኩ.....ነጋና.....

አርብ ማታ ሳምኩሽ ድጌ
ቅዳሜ ጧት አመመኝ፣
ሐሙስ እስከ አርብ
ህልም መሆኑ ነው...እኔን.. ያናደደኝ፣

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
እ ግ ዜ ር...አትቆጣን
እ ኛ ን.......እንዳታጣን
'
'
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
ሁሉም በዘመኑ ዕዳ አለበትና
በል የኔ ትውልድ ሀገር ትበል ቀና

@geez_mulat
እግዜር ግን ታያለህ
እውነት አይን አለህ

እግዜር ታደምጣለህ
እውነት ጆሮ አለህ

እስኪ አይን ካለህ...
ተመልከት ተመልከት ያለብንን ዕዳ
እውነት ካደመጥክስ የለቅሶውን ፍዳ
እንዴት አታዝንም ወይ?
......ሀገር...... እንዲ ታርዳ ?

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
ማሰብ ከሌለበት ፥
ዓለም እስኪበተን ፣
መሰብሰብ እስኪገባን፥
በደንብ እንበተን ፣

@geez_mulat
ላገባሽ ነው እንዳታገቢኝ
'
'

አመጣጤ እንዳየሽው
ሚያምር መስሎሽ አትሸወጅ
ምላስ ስንት ያሳልማል
ወንድ እስኪዝ በእጅ

አልጋየ ላይ እትት ስልሽ
ስታለፊኝ ከሌት አዳር
የሴት ልብ ሞኝ ነው
ከተወራ ስለትዳር

ላግባሽ ግን አታግቢኝ
ላግባሽስ አልፈልግም
ካልጋ ቤት ካልሆን በቀር
በቀለበት አንሰርግም

/ ላገባሽ ግን አልፈልግም.../

የሴት ጫካ ገብቼ
ሳድን ሳካልል
አንቺን ድንግል ህፃን
ጣለሽ ከመሃል

እንደው ላልጋ አስቤሽ
ላግባሽ ላግባሽ ስልሽ
ጠዋት ልፈታሽ ነው
አትመኝኝ ባክሽ

አግባኝ አግባኝ አትበይ
አፈቀርኩህ ፍቅር
ምናምንቴ ትዳር ፥
ኩችኩች ሆታሄ
ምናምንቴ ቁማር ፣
እኔ አልታመንም
እሽ ካልሽ ግን
ላግባሽ ከአንሶላየ ጋር ፥

አንሶላ ውስጥ ገብተሽ
" ልስጥህ ሴትነቴን "
ጠዋት እንለያይ
መልሽ ቀለበቴን

ቢጃማ አወላልቀሽ
ፊቴ ስትቆሚ
በራቁት ሰመመን
ወንድ ልጅ ዝም ካለ
ይቅርብሽ ማመን

ማፍቀሬን ሳስመስል
አይደለም የሴት
የአጋንንት ልብ ሸውዶ ይገዛል
ተይ አትመኝኝ
ወንድ ልጅ ሲያሸንፍ
ዝምታ ያበዛል

ላገባሽ ነው አልጋዬ ውስጥ
ልጥልሽ ነው ጥሎሽ ዕንባ
ላንድ ቀን ከሆነማ
ለአንድ አዳር እንጋባ

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

"በእውነተኛ የወንድ ታሪክ የተፃፈ 🙏"
እንቅልፌን ላውስሽ
እስከ ጠዋት ተኝ
ለችግርሽ እንደው
እኔ ልብከንከን ፣
ከቀን ባላድንሽ
የሌት ህልሜ ከሆን
ባንቺ ይታለም ፣

ከንፈርሽ ስር ያለች ነጥብ
ማሪያም ስማሽ ከሆነ ግን ፣
እንዴት አየህ አትበይ
ከእግሬ ስር ተኝተሽ
በሌሊት ወጋግን፣

(ነውና ያየሁሽ )

ካይንሽ ስር ላይ ገደል አለ
ግፋኝ ልውደቅ እያነባሽ ፣
እኔ ከታች ልውደቅ ቆይ
የዱር እሾህ እንዳይወጋሽ ፣

ደረቴ ጋር ጥብቅ በይ
ይጠፍሩኝ በልጥ ዛፍ ፣
ጡቶችሽ ጋር ካሳደረኝ
ከተራራው ጎጆ አፍ ፣

ከሰው መንጋ ተገንጥለን
ከጫጩት ድምፅ ተነጥለን ፣
በባዶ እግር ጫካ አልፈን
ተራራው ጫፍ ጎጆ ሰርተን
በጫካ ዛፍ ተከልለን ፣

ከሰሜን ንፋስ ሲ ነ ፍ ስ
ደመናው ሰማይ ሲ ወ ር ስ

በምስራቅ ጎን
የድንቢጥ ድምፅ
በምዕራብ ታች
የአንበሳም...፣
በቀስታ ተቃቅፈን
በዝምታ ስንሳሳም ፣

በጣቶቼ ወገብሽን
ክንዴ ሞልቶት ዞሮ ሲደርስ ፣
ከሰማዬ ነጫጭ ውሃ
ዝናብ ሚሉት ከእኛ ሲፈስ ፣

ተቃቅፈን ከአልጋችን
ዶፉ ሲወርድ ከጎጆ ውጭ ፣
በሳቅሽ እየታጀብኩ
በብልጭታው እያየሁሽ
በነጎድጓድ ስትደነግጭ ፣
በጣቶችሽ ጣቴን
በጭንቀት ስትጨብጭ ፣

ድንግጥ ስትይ አንገቴ ስር
ትንፋሽሽ ላይ ሙቀት ሳገኝ ፣
በግርብታ ያልጠበቀ
በቀ..ስ..ታ..ከንፈርሽ እንደሳመኝ

ከሩቅ ላይም የአራዊት ድምፅ
ከክንዴ ላይ ያንቺ ነፍስ ፣
ከንፈርሽ ስር ባለው ሀይቅ
ዋኝተንበት እንፍሰስ ፣

ከዚህ ጩኸት እንደበቅ
ከጫጫታው እንሰወር
በጨለማው ፍቅር ወበቅ
እንደ ድር እንደወር
ህልም ማለት..?እስኪ እንወቅ...?

የእኛን ኑሮ ካልጠበቁት
ከገፉን ስር ከሚስሙት
አድበስብሰው ከሚቀብሩት
ተራራ ስር ካለው ጎጆ
ዘላለም ነጥለን
ዘላለም ተቃቅፈን
ዘላለም እንሙት

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት