🙏በጾም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን በሌላ ጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን
✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እነርሱም፡-
✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን
✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Telegram
AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት
ይህ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ main ካምፓስ ግቢ ጉባዔ የቤተ-መፃህፍት ጥያቄ ና መልስ እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎች የሚተላለፍበት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው
ማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ በዚህ @AMUlibrary_bot ያድርሱን።

🙏4👍1
🔏ሰላም ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ የዚህ ሳምንት የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብራችን
ጋር የተያያዘ ስለሚሆን ሁላችሁም ተዘጋጁ!
📍በተጨማሪ በቻናሉ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንዲለቀቅ የምትፈልጉትን @AMUlibrary_bot ላይ ፃፉልን::
መልካም ፆመ ፍልሰታ 🙏
ከፆመ ፍልሰታ እና ውዳሴ ማርያም
ጋር የተያያዘ ስለሚሆን ሁላችሁም ተዘጋጁ!
📍በተጨማሪ በቻናሉ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንዲለቀቅ የምትፈልጉትን @AMUlibrary_bot ላይ ፃፉልን::
መልካም ፆመ ፍልሰታ 🙏
❤2🙏2
ድንግል ማርያም የሊባኖስዋ ድልድይ
በቤሩት በክርስትያኖች እና ሙስሊሞች መካከል እጅግ ልዩነቶች አሉ።
ከየትኛውም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ህግ በላይ ግን ሙስሊሞችንና ክርስቲያኖቹን አንድ የሚያደርግ የጋራ ጉዳይ አለ። ክርስትያኖች ከሙስሊሞች ጋር እየተጋፉ ሰልፍ ይዘው የሚውሉበትና የሚጐበኙበት ታላቅ ስፍራም አለ። አንድ ስም ከአፋቸው በፍቅር ሲጠራ የሚውልበት ቀን አብረው የሚያከብሩት በአል አለ።
ይህች ሁለቱን ታላላቅ ወገኖች የምታስተሳስር ድልድይ ማን ናት?
ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ይህች ማን ናት?
ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መፅሀፍ 📕: ከሞት ባሻገር ገፅ 167

ቅድስት ድንግል ማርያም!!!
ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መፅሀፍ 📕: ከሞት ባሻገር ገፅ 167
❤3
🎲 Quiz 'የፍልሰታ እና ውዳሴ ማርያም ጥያቄዎች'
🖊 10 questions · ⏱ 30 sec
🖊 10 questions · ⏱ 30 sec
የዛሬ አሸናፊዎች እና ተሸላሚዎች
1.@Yisakora_16
2.@Yohannan16
3, Y M
ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር @AMUlibrary_bot በዚህ ላኩልን
ዛሬ መሳተፍ ያልቻላችሁ ጥያቄውን በማንኛውም ሰዓት መመለስ እና ራሳችሁን መፈተሽ ትችላላችሁ።
🔏የሚቀጥለውን ሳምንት የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብር በአቅማቹ ስፖንሰር ማድረግየምትፈልጉ @AMUlibrary_bot ወይም +251901234850 ማናገር ትችላላችሁ ።
አስተያየት እና ጥያቄ ካላችሁ በ @AMUlibrary_bot አድርሱን
የያዕቆብ ለሊት ይሁንላችሁ።

❤1
ነሐሴ ፮ /6/
በዚችም ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች መግደላዊት ማርያም አረፈች። ከዘህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ አገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ አለች እስከ ቀበሩትም ድረስ አልተለየችም።
በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች ። መልአኩም እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል አላቸው።
ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው አላት ። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው።
ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋርተቀበለችው።
ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው ። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት።
ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም በፍቅር አረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏🙏🙏
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
🙏4❤3
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ?
እንኳን ለፍልሰታ ጾም አደረሰን አደረሳችሁ!!!
ክረምት አንዴት እያሳለፍን ነው? ከቤቱ አንዳንርቅ፤በቸርነቱ ሁላችንንም በቤቱ ያኑረን።
አባታችን ቀሲስ መኳንንት አንድ የቤት ስራ ሰጠውኛል።አርሱም ጾመ ፍልሰታ አንዳለቀ የእመቤታችንን ዓመታዊ የእርገት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ከሚያገለግሉት አባቶች ጋር ዓመታዊ ዝግጅት አላቸው። እንደሚታወቀው ከአባታችን ጋር መልካም የሆነ ቆይታ ነበረን😊 ይኽን መልካም ግንኙነት ለማስቀጠል ከአባታችን ጎን መሆን አለብን።እግዚአብሔር በሚያውቀው በ2016ዓ.ም ሁላችንንም በሚባል ሁኔታ ለንሰሃ እንዴሁም ሳይገባን ተገብቶን ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ አብቅተውናል።
እግዚአብሔር ይመስገን።
ከዚህ በፊት ይኽን ዝግጅት በየዓመቱ የሚያከብሩት ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ነበር። አሁንም እኛ ልጆቻቸውን ተስፋ አርገው እየጠበቁን ስለሆነ በእግዚአብሔር ሰም አቅማችን የፈቀደውን ከ50ብር ጀምሮም ቢሆን እናግዛቸው🙏🙏።
1000421521305
Samrawit Girma
ማሳሰቢያ፦ የላካችሁትን ብር screenshot አድርጋችሁ እዚሁ group ጋ መላክ እንዳይረሳ።

🎲 Quiz 'የደብረታቦር ጥያቄዎች'
🖊 10 questions · ⏱ 45 sec
🖊 10 questions · ⏱ 45 sec
❤1
የዛሬ አሸናፊዎች እና ተሸላሚዎች
1, @Abi_Dev_27
2, @Geme1216
3, @kassiealemu
ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር @AMUlibrary_bot በዚህ ላኩልን
ዛሬ መሳተፍ ያልቻላችሁ ጥያቄውን በማንኛውም ሰዓት መመለስ እና ራሳችሁን መፈተሽ ትችላላችሁ።
🔏የሚቀጥለውን ሳምንት የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብር በአቅማቹ ስፖንሰር ማድረግየምትፈልጉ @AMUlibrary_bot ወይም +251901234850 ማናገር ትችላላችሁ ።
አስተያየት እና ጥያቄ ካላችሁ በ @AMUlibrary_bot አድርሱን
የያዕቆብ ለሊት ይሁንላችሁ።
1, @Abi_Dev_27
2, @Geme1216
3, @kassiealemu
ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር @AMUlibrary_bot በዚህ ላኩልን
ዛሬ መሳተፍ ያልቻላችሁ ጥያቄውን በማንኛውም ሰዓት መመለስ እና ራሳችሁን መፈተሽ ትችላላችሁ።
🔏የሚቀጥለውን ሳምንት የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብር በአቅማቹ ስፖንሰር ማድረግየምትፈልጉ @AMUlibrary_bot ወይም +251901234850 ማናገር ትችላላችሁ ።
አስተያየት እና ጥያቄ ካላችሁ በ @AMUlibrary_bot አድርሱን
የያዕቆብ ለሊት ይሁንላችሁ።
ደብረ_ታቦር
ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።
በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።
ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።
በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።
ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።
የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት።
ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም።
ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።
ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ።
ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
(ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ)

❤2🙏1