🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ16ተኛ ሳምንት የጨዋታ መርሀግብሮች 🔥

📅 ቅዳሜ ታህሳስ 04

⏱️ አመሻሽ 12:00 ላይ
ቼልሲ 🆚 ኤቨርተን
‎ ሊቨርፑል 🆚 ብራይተን

⏱️ ምሽት 02:30 ላይ
በርንሌይ 🆚 ፉልሃም

⏱️ ምሽት 05:00 ላይ
አርሰናል 🆚 ዎልቭስ

📅 እሁድ ታህሳስ 05

⏱️ ቀን 11:00 ላይ
ክርስታል ፓላስ 🆚 ማንቸስተር ሲቲ
‎ ኖቲንግሃም 🆚 ቶተንሃም
‎ ሰንደርላንድ 🆚 ኒዉካስትል
‎ ዌስትሃም 🆚 አስቶንቪላ

⏱️ ምሽት 01:30
ብሬንትፎርድ 🆚 ሊድስ

📅 ሰኞ ታህሳስ 06

⏱️ ምሽት 05:00 ላይ
ማንቸስተር ዩናይትድ 🆚 በርንማዉዝ

@yesport_mereja
👍2
💡ቤተሰብ ዛሬ አንድ መሞከርና መስራት ያለባችሁ ነገር ይዤላችሁ መጥቻለሁ

🔻 የተለያዩ የስፖርት ቪዲዮዎችን ልክ እንደ ቲክቶክ ቪድዮ በመልቀቅና በመመልከት በተጨማሪም ሰው በመጋበዝ የሚከፍል አፕ ነው ይዤላችሁ ከች ብያለሁ

🤑ልክ $10 ሲሞላ ማውጣት ትችላላችሁ

🧲አካውንት ለመክፈት ይህን step ተከተሉ

🔻ይህን ሊንክ ተጭናችሁ አፑን ከplaystore or appstore አውረዱ 👇
https://app.buzzerfan.com/referral-invite/rs4582f1331ad5405e931b2b63595cadb4

🔻በመቀጠል create account ሚለውን ተጭናችሁ email እና የማረሱትን password አስገቡ ከዛ በemail የላከላችሁን ኮድ አስገቡ

🔻በመቀጠል username,first & last name አስገቡ ከዛ gender,age አስገቡ

🔻በመቀጠል referral code የሚል ሲመጣላችሁ 100 bonus point (3 USD) ለማግኘት ይህን ኮድ አስገቡ 👉1332B6

🔻አሁን አካውንት ከፍታችኋል ከዚህ በኋላ ቪዲዮ እየጫናችሁ በ1k view ትከፈላላችሁ በተጨማሪም 1ሰው ስጋብዙ $0.15 ታገኛላችሁ

🔻ከዚህ በኋላ መስራት ነው እድሉን ተጠቀሙ። በዚሁ አጋጣሚ የቡንደስሊጋው ይፋዊ page የኔ ነው። 🇩🇪⚽️😎
👍1
Gashu 🃏 Mika
Photo
ተበልተናል ወገን 😯😂

30 የተለያዩ የስራ ዘርፎች የደበቁን አስገራሚ ሚስጥሮች! 😱
በተለይ 30ኛው🤔

በቅርቡ ባለሙያዎች "ህዝቡ የማያውቃቸው የሙያችን ሚስጥሮች" በሚል በማህበራዊ ሚዲያ አጋርተዋል። አንዳንዶቹ ያስደነግጣሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ያስቃሉ!

1️⃣ የደንበኞች አገልግሎት (Call Center): ስልክ ደውላችሁ "እባክዎ መስመር ላይ ይጠብቁ" ተብሎ ሙዚቃ ሲለቀቅላችሁ፣ ኦፕሬተሩን እያማችሁ ከሆነ ተጠንቀቁ! 😂 እናንተ እነሱን ባትሰሙም፣ እነሱ ግን እናንተ የምታወሩትን ሁሉ ይሰማሉ።

2️⃣ ሆቴል (Housekeeping): ብዙ ግዜ በሆቴል አልጋ ላይ ያሉት ትራስ ልብሶችና አንሶላዎች ከአንድ ተጠቃሚ በኋላ አይታጠቡም።እንዳለ ለሌላ ተጠቃሚ ይዘጋጁለታል።
ለማንኛውም ከነልብሳችሁ ተኙ🤢

3️⃣ አይቲ (IT Support): ኮምፒውተራችሁ ተበላሽቶ ወደ IT ባለሙያ ስትወስዱት፣ 99% የሚያደርጉት ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? "Google ማድረግ" እና "አጥፍቶ ማብራት" (Restart) ብቻ 99% የኮምፒተራችን ችግር የሚፈታው አጥፍቶ በማብራት ነው።! እኛ የማናውቀውን ጉግል ማድረግ ስለቻሉ ነው የሚከፈላቸው። 😂

4️⃣ አየር መንገድ (Baggage Handlers): "Fragile" (ይሰበራል) የሚል ምልክት በሻንጣችሁ ላይ መለጠፍ ዋጋ የለውም። እንዲያውም ሰራተኞቹ ሆን ብለው በሃይል ሊወረውሩት ይችላሉ። ጠንካራ ሻንጣ መግዛት ብቻ ነው መፍትሄው።

5️⃣ የልብስ መሸጫ ሱቆች (Retail): አዲስ የገዛችሁት ልብስ "አዲስ" አይደለም። ከእናንተ በፊት ስንት ሰው እንደለካው እና መልሶ እንደሰቀለው አታውቁም። ከመልበሳችሁ በፊት እጠቡት!

6️⃣ ሲኒማ ቤቶች: በሲኒማ ቤት ውስጥ የምትገዙት ፖፕኮርን (Popcorn)(ፈንዲሻ) ትኩስ ላይሆን ይችላል። ትናንት ማታ የተረፈውን በፕላስቲክ ከረጢት አድርገው አስቀምጠውት፣ ዛሬ አሞቀው ሊሸጡላችሁ ይችላሉ። 🍿

7️⃣ የጥርስ ሳሙና: ማስታወቂያ ላይ እንደምታዩት ብሩሹን ሙሉ ሳሙና ማድረግ አይጠበቅባችሁም። የሽያጭ ስልት ነው። ጥርሳችሁን ለማፅዳት የሚያስፈልጋችሁ የባቄላ ፍሬ የምታክል ሳሙና ብቻ ናት።በጥበብ ተጠቀሙ!

8️⃣ የመኪና ሜካኒክ: መኪናችሁን ሰርቪስ ለማድረግ ስትወስዱ፣ አንዳንዴ ያልተበላሸ እቃ "ተበላሽቷል" ተብላችሁ ልትጠየቁ ትችላላችሁ። በተለይ ስለ መኪና ብዙም የማታውቁ መስላችሁ ከታያችሁ ተበልታችኋል!

9️⃣ የመነጽር ዋጋ: መነጽር ሲያሰሩ የተጋነነ ዋጋ ከከፈሉ ተበልተዋል! በ$10 ዶላር የሚመጣ ፍሬም በ$100 እና ከዚያ በላይ ነው የሚሸጠው። ትርፉ እብድ ነው!

🔟 የመርከብ ጉዞ (Cruise Ships): በመርከብ ላይ የሚፈጠሩ ወንጀሎች እና የሰዎች መጥፋት ብዙ ጊዜ ይድበሰበሳሉ። ምክንያቱም በአለም አቀፍ ውሃ ላይ ስለሆኑ የየትኛው ሀገር ህግ እንደሚሰራ ግልጽ አይደለም።ደመ ከልብ ሆነው ነው ሚቀሩት🤔

11️⃣ የግንባታ ስራ (Construction): ብዙ ህንጻዎች ውስጥ ግድግዳው ውስጥ የሽንት ቤት ቆሻሻ፣ ጠርሙስ እና የሲጋራ መተርኮሻ ተቀብሮ ይገኛል። ሰራተኞቹ ቆሻሻ መጣል ሲደክማቸው ግድግዳው ውስጥ ይደብቁታል። 🏗️

1️⃣2️⃣ የውበት ምርቶች (Cosmetics): የ1000 ብር ክሬም እና የ100 ብር ክሬም ብዙ ጊዜ አንድ አይነት ንጥረ ነገር ነው ያላቸው። ልዩነቱ ማሸጊያው እና ማስታወቂያው ብቻ ነው።

1️⃣3️⃣ የምግብ አሰራር (Chefs): ምግብ ቤት ሄዳችሁ "የዛሬው ልዩ ምግብ" (Today's Special) ስትባሉ፣ ብዙ ጊዜ ያ ምግብ ሊበላሽ የተቃረበ እና ቶሎ መሸጥ ያለበት ምግብ ነው። 🍽️

1️⃣4️⃣ የሆስፒታል ንፅህና: በሆስፒታል ውስጥ የዶክተሮች የነጭ ኮት (White Coat) እና የክራቫት ንፅህና አጠራጣሪ ነው። ብዙ ጊዜ አይታጠብም፣ ባክቴሪያም ሊሸከም ይችላል።

1️⃣5️⃣ የባንክ ብድር: ባንኮች ብድር ሲሰጡ፣ ወለዱን የሚያሰሉት መጀመሪያ ወለዱን ከፍላችሁ እንድትጨርሱ ነው። ዋናው ብድር (Principal) የሚቀንሰው ከብዙ አመት በኋላ ነው።

1️⃣7️⃣ የጋዜጠኝነት ስራ: ብዙ ዜናዎች "ሰበር ዜና" የሚባሉት በእርግጥ አዲስ ስለሆኑ ሳይሆን፣ እናንተን ለማስደንገጥ እና ክሊክ እንድታደርጉ ነው። "ፍርሃት ይሸጣል!"

1️⃣8️⃣ የመድሃኒት ፋብሪካ: አንዳንድ መድሃኒቶች ጊዜያቸው ካለፈ በኋላም ለተወሰነ ጊዜ ይሰራሉ። ነገር ግን ኩባንያዎቹ አዲስ እንድትገዙ "Expiry Date"ን ያሳጥሩታል። (ግን በራስዎ አይሞክሩት በጣም አደገኛ ነገር ሊፈጠር ይችላል!)

1️⃣9️⃣ የስዕል መሸጫ (Art Galleries): የአርቲስቶች ስዕል ዋጋ የሚወሰነው በስዕሉ ጥራት ሳይሆን፣ በጋለሪው ስም እና በገበያ ትስስር ነው። ገንዘብ ማጠቢያ (Money Laundering) ሊሆንም ይችላል። 🎨

2️⃣0️⃣ የወይን ጠጅ (Wine): ውድ ወይን እና ርካሽ ወይን ለይቶ ማወቅ ለባለሙያም ይከብዳል። ብዙ ጊዜ ዋጋው በጠርሙሱ ውበት እና በብራንዱ ስም ይወሰናል። 🍷

2️⃣1️⃣ የሞባይል ስልክ ጥገና: ስልካችሁን ለመጠገን ስትሰጡ፣ የግል ፎቶዎቻችሁን እና ዳታችሁን ሊያዩት እንደሚችሉ እወቁ። ፓስወርድ ቢኖረውም የሚከፍቱበት መንገድ አላቸው።

2️⃣2️⃣ የHR (የሰው ሃይል) ስራ: HR የሚሰራው ለኩባንያው ጥቅም እንጂ ለሰራተኛው አይደለም። ቅሬታ ስታቀርቡ፣ እነሱ የሚያስቡት "ይህ እንዴት ኩባንያውን ይጎዳል?" ብለው ነው።

2️⃣3️⃣ የዩኒቨርሲቲ መጽሐፍት: ፕሮፌሰሮች በየአመቱ የመጽሐፍ "አዲስ እትም" (New Edition) እንዲገዛ የሚያደርጉት፣ ትንሽ ነገር ቀይረው ተማሪው አዲስ መጽሐፍ እንዲገዛ እና ኮሚሽን እንዲያገኙ ነው። 📚

2️⃣4️⃣ የጂም (Gym) አባልነት: ጂሞች ትርፍ የሚያገኙት አባል ሆነው በማይመጡ ሰዎች ነው። ሁሉም አባል በየቀኑ ቢመጣ፣ ጂሙ ይጨናነቅና ይዘጋ ነበር።

2️⃣5️⃣ የመኪና ሽያጭ: መኪና ሻጮች ወርሃዊ ኮታ አላቸው። በወሩ መጨረሻ አካባቢ ከሄዳችሁ፣ ኮታቸውን ለመሙላት ሲሉ ቅናሽ የማድረግ እድላቸው ሰፊ ነው። 🚗

2️⃣6️⃣ የሪሳይክል (Recycling) ውሸት: ለብቻው "ፕላስቲክ"፣ "ወረቀት" እያልን የምንለየው ቆሻሻ፣ መጨረሻ ላይ አንድ ላይ ተቀላቅሎ ከሌላው ቆሻሻ ጋር እንደሚጣል ያውቃሉ? ብዙ ቦታዎች ላይ ለይስሙላ ነው። ♻️

2️⃣7️⃣ የፎቶ ሞዴሎች: ኢንስታግራም ላይ የምታዩት የሞዴሎች ፎቶ፣ በመብራት፣ በሜካፕ እና በPhotoshop የተሰራ ነው። በእውነተኛ ህይወት እንደዛ አይመስሉም። ራሳችሁን ከነሱ ጋር አታወዳድሩ!

2️⃣9️⃣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ (Tech Support): የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች (ISP) ፍጥነታችሁን ሆን ብለው ሊቀንሱት ይችላሉ። ስትደውሉላቸው ብቻ "ሪሴት" አድርገው ያስተካክሉታል።

3️⃣0️⃣ የቀብር ስነስርዓት (Funeral Homes): የሬሳ ሳጥን (Coffin) ዋጋ እጅግ የተጋነነ ነው። እንጨቱ ርካሽ ቢሆንም፣ በስሜታዊነት ስለምትሆኑ ውዱን እንድትገዙ ይገፋፉአችኋል። ⚰️

🤔 ከነዚህ ውስጥ የትኛው ይበልጥ አስገረማችሁ?
የእናንተስ የስራ ቦታ ጉድ ምንድነው? ኮሜንት ላይ ሚስጥር አውጡ! 👇

✍️:- Bilal Mengstie

@gashumika
👍1😱1
Channel photo updated
የህይወት ዓላማዬ ጠፋብኝ ብለህ ተጨንቀሃል? 🤔

ብዙዎቻችን አንድ ወቅት ላይ "ለምን ዓላማ ነው የምኖረው? ግቤስ ምንድን ነው?" ብለን ራሳችንን ጠይቀን እናውቃለን። መልሱ ሲጠፋብን ደግሞ ግራ ይገባናል።

ወዳጄ... ዓላማህ ከሰማይ አይወርድም፤ የሚገኘው ከውስጥህ ነው። የህይወት ዓላማህን ለማግኘትና ጊዜህን ለመጠቀም እነዚህን 3 ወሳኝ ነጥቦች ተመልከት
👇
Gashu 🃏 Mika
የህይወት ዓላማዬ ጠፋብኝ ብለህ ተጨንቀሃል? 🤔 ብዙዎቻችን አንድ ወቅት ላይ "ለምን ዓላማ ነው የምኖረው? ግቤስ ምንድን ነው?" ብለን ራሳችንን ጠይቀን እናውቃለን። መልሱ ሲጠፋብን ደግሞ ግራ ይገባናል። ወዳጄ... ዓላማህ ከሰማይ አይወርድም፤ የሚገኘው ከውስጥህ ነው። የህይወት ዓላማህን ለማግኘትና ጊዜህን ለመጠቀም እነዚህን 3 ወሳኝ ነጥቦች ተመልከት👇
1. ራስህን ጠይቅ (Self-Discovery)
ዓላማህ ያለው አንተ ውስጥ ነው።
ገንዘብ ባይከፈልህም እንኳ ማድረግ የሚያስደስትህ ነገር ምንድን ነው?
ሰዎች "ይሄን ነገር እኮ ጎበዝ ነህ/ነሽ" የሚሉህ ተሰጥኦህ ምንድን ነው?
በአካባቢህ ወይም በዓለም ላይ የሚያናድድህና መፍትሄ ልትሰጠው የምትመኘው ችግር አለ?

👉 የምትወደው፣ የምትችለው እና ዓለም የሚፈልገው ነገር ሲገናኝ ዓላማህ ዓላማህ ተገኘ ማለት ኘው።

2. በተግባር ሞክር (Action)
ዓላማህ ቁጭ ብለህ የምትጠብቀው ነገር አይደለም።
🔹 በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ተሳተፍ ፣ አዳዲስ ነገሮችን ተማር፣ የተለያየ ቦታ ሂድ።
🔹 እንቅስቃሴ ውስጥ ስትሆን መንገዱ እየጠራ ይመጣልሃል።
🔹 በአቅምህ ልክ ጀምር!  በበድንገት ተነስተህ ዓለምን መቀየር ካሰብክ ከባድ ነው፤  ቀስ በቀስ ሀሳብህ እየጠራ፣ ዓላማህን እየተረዳህ ትመጣለህ

3. ጊዜህን አትግደል (Time Management)
ጊዜህ ማለት ህይወትህ ነው።
ቅድሚያ ስጥ: ሁሉንም ነገር ማድረግ አትችልም። ለአንተ "ዋና" ለሆኑ 3 ነገሮች ጊዜ ስጥ።

📱 ትኩረትህን ሰብስብ: ስልክህ ላይ የምታጠፋውን ጊዜ ቀንስ።
"እምቢ ማለትን ልመድ : ከዓላማህ ጋር የማይሄዱ ነገሮችን "አይ" ማለት ተለማመድ።

💡 አስታውስ: ዓላማህን አለማወቅህ ውድቀት አይደለም፤ ለመፈለግ መነሳሳትህ ራሱ ትልቅ ጅምር ነው። ራስህን አትጨናነቅ። ዛሬ ልብህ የሚወደውን መልካም ነገር አድርግ፤ መንገዱ ቀስ በቀስ ይገለጻል።

ይህ ስሜት የተሰማው ጓደኛ አለህ? Share አድርግለት!
አንተስ ምን ማድረግ ያስደስትሃል? ኮመንት ላይ አጋሩን። 👇

✍️:- Bilal Mengstie

@gashumika
👍2
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሰን!

⭐️ መልካም የገና በዓል ⭐️
1
በኦንላይን የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር  ከታች ያሉትን ሊንኮች መጠቀም ትችላላችሁ።
መውረጃው Official የናሽናል መታወቂያ መስሪያቤት የX አካውንት ነው።

ልብ ይበሉ፦ ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር (Harmonization) በነዚህ ሊንኮች ይጠቀሙ።

አቢሲኒያ ባንክ
cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect 

አዋሽ ባንክ
fayda.awashbank.com

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:
my.coopbankoromiasc.com/harmonization 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
cbefayda.cbe.com.et

ኦሮሚያ ባንክ
bfayda.oromiabank.com

ወጋገን ባንክ
fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

ንብ ባንክ
fayda.nibbank.com.et

ፀሀይ ባንክ
fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home

ስንቄ ባንክ :
fayda.siinqeebank.com:7443

ዘምዘም ባንክ
fayda.zamzambank.com.et

አማራ ባንክ :
fayda.amharabank.com.et

@gashumika
👍1
ስክሮል ገንዘብ ነው! (Scroll is Money)

ጓደኛዬ... አንድ ሚስጥር ልንገርህ?
ስክሮል ገንዘብ ነው። አዎ፣ በትክክል ሰምተሃል። ያ ጣትህ የስልኩን ስክሪን ወደ ላይ በገፋ ቁጥር (Scroll ባደረገ ቁጥር)፣ የገንዘብ ቆጣሪ ይንቃቃል። ሳንቲሞች ይንከባለላሉ። ዶላሮች ይቆጠራሉ። ጥያቄው ግን ይህ ነው... ገንዘቡ የሚገባው ወደ ማን ኪስ ነው? ወደ አንተ ወይስ ወደ እነሱ?
👍1
Gashu 🃏 Mika
ስክሮል ገንዘብ ነው! (Scroll is Money) ጓደኛዬ... አንድ ሚስጥር ልንገርህ? ስክሮል ገንዘብ ነው። አዎ፣ በትክክል ሰምተሃል። ያ ጣትህ የስልኩን ስክሪን ወደ ላይ በገፋ ቁጥር (Scroll ባደረገ ቁጥር)፣ የገንዘብ ቆጣሪ ይንቃቃል። ሳንቲሞች ይንከባለላሉ። ዶላሮች ይቆጠራሉ። ጥያቄው ግን ይህ ነው... ገንዘቡ የሚገባው ወደ ማን ኪስ ነው? ወደ አንተ ወይስ ወደ እነሱ?
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ በሶሻል ሚዲያ ዓለም ውስጥ ጨካኝ ህግ አለ። ምርጫው ሁለት ብቻ ነው።
    "ወይ አንተ ትሸጣለህ፣ ወይ ደግሞ በሌሎች ትሸጣለህ።"
መሃል የሚባል ነገር የለም። ምርት ወይም አገልግሎት ይዘህ ወጥተህ እየሸጥክ ካልሆነ፣ እወቀው... ሸቀጡ አንተ ነህ! ትኩረትህ እየተሸጠ ነው። ጊዜህ እየተሸጠ ነው። የአንተ "View"፣ የአንተ "Like"፣ የአንተ "Comment" ለሌሎች የባንክ ሂሳብ ማደለቢያ ነው።
ሶሻል ሚዲያ የተሰራው ለመዝናኛ ብቻ ይመስልሃል? ተሳስተሃል። በዛ ስክሪን በስተጀርባ በሺህ የሚቆጠሩ ኢንጂነሮች እና የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ተቀጥረው የሚሰሩት አንድ ነገር ብቻ ለማሳካት ነው። አንተን ሱሰኛ ለማድረግ!
ስክሮል ማድረግህን እንድታቆም አይፈልጉም። ስልኩን አስቀምጠህ ህይወትህን እንድትቀይር፣ እንድትማር ወይም እንድትሰራ አይፈልጉም። ምክንያቱም አንተ ስልክህን ስታስቀምጥ፣ እነሱ ገንዘብ መስራት ያቆማሉ።
ስለዚህ አንተን እዛው ለማቆየት የማይፈጥሩት ወጥመድ የለም።
    የሚስብ ቪዲዮ ያመጡልሃል።
    የሚያስቅ ምስል ይለቁብሃል።
    በማያገባህ ጉዳይ እንድትከራከር ያደርጉሃል።
አንተ ግን "ትንሽ ልዝናና" ብለህ ገብተህ፣ ሰዓታት በተለኮሱ ቁጥር፣ ከህይወትህ ላይ ውድ ጊዜ እየቆረጠህ ለነሱ እየሸጥክላቸው ነው። ባወጣህው የሞባይል ካርድ ብቻ እየከበርክ አይደለም፤ እድሜህን ነው እየከፈልክ ያለኸው!
ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው? ስልክ እንጣላ? ሶሻል ሚዲያ እንዝጋ?
አይደለም! ጨዋታውን ቀይረው። ከዛሬ ጀምሮ ተራ ተመልካች አትሁን። ተጫዋች ሁን!
    ስክሮል የምታደርገው ለመማር ከሆነ፣ ቀጥልበት።
    ስክሮል የምታደርገው ለራስህ ቢዝነስ ገበያ ለመፈለግ ከሆነ፣ ቀጥልበት።
    ስክሮል የምታደርገው ኔትወርክ ለመፍጠር ከሆነ፣ አሪፍ ነው።
ነገር ግን... ዝም ብለህ የሌሎችን ህይወት እያየህ፣ የሌሎችን ስኬት እያደነቅህ ወይም እየተቹህ የምትውል ከሆነ፣ ንቃ!
ስልክህ የገቢ ምንጭህ እንጂ፣ የጊዜህ መቃብር ሊሆን አይገባም። የሶሻል ሚዲያ ኩባንያዎች አንተን "Product" (ሸቀጥ) አድርገው ከመሸጣቸው በፊት፣ አንተ ራስህን ሻጭ አድርግ።

ስክሮል ገንዘብ ነው። ግን ለማን? ለባለቤቶቹ ወይስ ለአንተ? ምርጫው የአንተ ነው።

ስክሮል ማድረግ አቁም፤ መፍጠር ጀምር!

✍️:- Tariku Mehdi

@gashumika
👍1
ETHIO TELECOM አይሾው ስፒድ የአዲስ አበባ ቆይታውን በፈጣኑ 5ጂ በቀጥታ ስርጭት እንዲያስተላልፍ ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለው ቢሰክሱንም ለLive Stream የረዳው ዋናው ነገር እንዲህ ከታች በዝርዝር ለመፃፍ ሞክርያለሁ።
👍1
Gashu 🃏 Mika
ETHIO TELECOM አይሾው ስፒድ የአዲስ አበባ ቆይታውን በፈጣኑ 5ጂ በቀጥታ ስርጭት እንዲያስተላልፍ ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለው ቢሰክሱንም ለLive Stream የረዳው ዋናው ነገር እንዲህ ከታች በዝርዝር ለመፃፍ ሞክርያለሁ።
በምስሉ ላይ የሚታየው ቦርሳው ውስጥ ያለው መሣሪያ TVU One ይባላል። በብዛት እንደ IShowSpeed ያሉ ታዋቂ የዩቲዩብ (YouTube) ቪዲዮ ሰሪዎች እና የዜና ማሰራጫዎች የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) ለማድረግ ይጠቀሙበታል።

​ስለ መሣሪያው ጥቅምና ዋጋ ዝርዝር መረጃ እነሆ፦

​የመሣሪያው ዋና ጥቅሞች (Functionality)

1, ​ይህ መሣሪያ በዋናነት "Mobile Transmitter" ወይም "IP Video Transmitter" በመባል ይታወቃል።

2, ​ያለ መቆራረጥ የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ መሣሪያው ውስጥ ብዙ የሲም ካርድ (SIM Card) ማስገቢያዎች አሉት። የተለያየ ኔትወርክ ያላቸውን ሲም ካርዶች (ለምሳሌ፦ Safaricom እና Ethio Telecom) በአንድ ላይ በማገናኘት፣ አንዱ ቢዳከም በሌላው በመተካት ስርጭቱ እንዳይቋረጥ ያደርጋል።

3, ​ከፍተኛ ጥራት (High Quality): ባለ 4K ወይም 1080p ጥራት ያለው ቪዲዮ በትንሽ የኢንተርኔት ፍጥነት እንኳን በጥራት ለማስተላለፍ ያስችላል።

4, ​ተንቀሳቃሽነት (Portability): በምስሉ ላይ እንደሚታየው በቦርሳ ታዝሎ የሚሄድ በመሆኑ፣ ስቲሪመሩ (Streamer) በሄደበት ቦታ ሁሉ ካሜራውን ከዚህ መሣሪያ ጋር አገናኝቶ በነፃነት መንቀሳቀስ ይችላል።

5, ​ዝቅተኛ መዘግየት (Low Latency): በቪዲዮው እና በሰዎች አስተያየት (Chat) መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት በጣም አጭር እንዲሆን ያደርጋል።

​ዋጋው ስንት ነው

​ይህ መሣሪያ በጣም ውድ እና ለባለሙያዎች የተሠራ በመሆኑ እንደ ተራ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በቀላሉ በሱቅ አይሸጥም።

​የመግዣ ዋጋ፦ እንደ አዲሱ ሞዴል እና እንደ አቅሙ፣ አዲስ ከሆነ ከ $5,000 እስከ $10,000 (ከ600,000 እስከ 1.2 ሚሊዮን ብር በላይ) ሊያወጣ ይችላል።

​ተጨማሪ ክፍያ፦ መሣሪያውን ለመጠቀም በየወሩ ለኩባንያው (TVU Networks) የዳታ እና የሶፍትዌር አገልግሎት ክፍያ መክፈል ይጠይቃል።

​ኪራይ፦ ብዙዎች ይህንን መሣሪያ ገዝተው ከመጠቀም ይልቅ በቀን ከ $300 - $500 እየከፈሉ ተከራይተው ይጠቀሙታል።

​በአጭሩ፦ IShowSpeed ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው ቆይታ ኢንተርኔት ባልነበረባቸው ቦታዎች ሳይቀር የቀጥታ ስርጭቱ እንዳይቋረጥ ያደረገለት ይህ መሣሪያ ነው።

✍️:- Filary Ozuna

@gashumika
👍1
እንደአጋጣሚ Tik tok ላይ አይቼው ስለወደድኩት ነው ከተመቻችሁ እንዳይረሳ 👍

🪙 ክሪፕቶ ትሬዲንግ፦ ከሀብት ማማ ጀርባ ያለው የሲኦል መንገድ
👍1
Gashu 🃏 Mika
እንደአጋጣሚ Tik tok ላይ አይቼው ስለወደድኩት ነው ከተመቻችሁ እንዳይረሳ 👍 🪙 ክሪፕቶ ትሬዲንግ፦ ከሀብት ማማ ጀርባ ያለው የሲኦል መንገድ
⚡️ብዙ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ የምናየው የትሬዲንግ ገጽታ "በአጭር ጊዜ መበልጸግን"፣ "ውድ መኪናዎችን" እና "የስክሪን ፎቶዎችን" ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከእያንዳንዱ ስኬታማ ትሬደርጀርባ ማንም የማይነግርህ ትልቅ የሥነ-ልቦና እና የኑሮ ፈተና አለ።

⚡️ሰዎች ስለ ትርፉ ይነግሯችኋል፤ እኔ ደግሞ ማንም ስለማይነግራችሁ ስለ እንቅልፍ ማጣት፣ ስለ ብቸኝነት እና ስለ ውስጣዊ ስብራት ልንገራችሁ። ትሬዲንግ በዓለም ላይ ካሉ ስራዎች ሁሉ እጅግ ከባዱ "ቀላል ስራ'' ነው፡፡

1. የ 24 ሰዓት እስር ቤት

የአክሲዮን ገበያ ቅዳሜና እሁድ ይዘጋል፤ ክሪፕቶ ግን አይተኛም፡፡ ይህ ማለት አንተም አትተኛም ማለት ነው፡፡ ስልክህ ከአይንህ አይርቅም፡፡ ከቤተሰብ ጋር ስትሆን፣ ምግብ ስትበላ፣ አልፎ ተርፎም ሽንት ቤት ስትሄድ ስልክህ ላይ ነህ። የገበያው መውረድና መውጣት (Volatility) የልብ ምትህን ይቆጣጠረዋል። እንቅልፍ ወስዶህ ባነንክ ቁጥር መጀመሪያ የምታደርገው የገንዘብህን መጠን ማየት ነው፤ ''ተበላሁ ወይስ ተረፍኩ?" የሚለው ስጋት በህይወትህ ላይ ጥላውን ይጥላል።

2. "ቀይ" ቀለም የመጥላት ስቃይ

ፖርትፎሊዮህ (Portfolio) በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ቀይ ሲቀየርማየት ስቃዩ የገንዘብ ብቻ አይደለም፡፡ የነፍስ ስቃይ ነው፡፡ የለፋህበት፣ የቆጠብከውና ለወደፊት ህልምህ ያልከው ገንዘብ እንደ በረዶ ሲቀልጥ ስታየው በራስህ ላይ የምታሳድረው ጥላቻ ይጀምራል። "ለምን በጊዜ አልወጣሁም?" (Regret) የሚለው ጸጸት እንደ እሳት ይለበልብሃል።

3. የ FOMO እና የውሸት ስኬት ሰለባ መሆን

ሌላው ሰው 1000% ትርፍ አገኘሁ ሲል፣ አንተ የያዝከው ሳንቲም ግን ወደ ታች ሲምዘገዘግ የሚሰማህ የቅናትና የባዶነት ስሜት። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምታያቸው ''የውሸት ጉራዎች" ስኬታቸውን ብቻ ሲለጥፉ፣ አንተ ብቻ የተሸነፍክ ይመስልሃል። ይህ ስሜት ወደ "Revenge Trading" (ለበቀል መነገድ) ይገፋሃል፤ ይህም የጥፋትህ መጀመሪያ ይሆናል።

4. በቤተሰብ ፊት "ቁማርተኛ" መባል

ለአንተ ትሬዲንግ ስራህ ነው፤ ለሌላው ግን ቁማር። ገንዘብህን ስታጣ የሚደርስብህ ወቀሳ፣ በቅርብ ሰዎችህ የምትታይበት የንቀት አይን፣ እና ''ተወው ብለንህ ነበር" የሚለው ቃል ከገንዘብ ማጣቱ በላይ ልብን ይበሳል። የሚያዋይህ ሰው አጥተህ ብቻህን ስትብሰለሰል፣ የክሪፕቶ ስቃይ ምን እንደሆነ ያኔ ይገባሃል።

5. የህልም መርገፍ (The Crash)

ገበያው በከፍተኛ ሁኔታ ሲወድቅ (Market Crash)፣ አንድ ሰሞን የነበሩህ ህልሞች ሁሉ አብረው ይረግፋሉ፡፡ ቤት ለመግራት፣ ትምህርት ለመማር ወይም ቤተሰብ ለመርዳት የነበረህ ተስፋ በአንድ ሻማ (Candle) ሲከሽፍ፣ ያንን ጭንቀት ለመሸከም ትልቅ የውስጥ ጥንካሬ ይጠይቃል።

"ክሪፕቶ ለደካሞች ቦታ የለውም፤ ምክንያቱም እዚህ ግባ የማይባሉ ሰከንዶች የህይወትህን አቅጣጫ ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡ ስኬቱ ጣፋጭ ነው፤ ግን ያንን ጣዕም ለመቅመስ መጀመሪያ መራራውን የጭንቀት ጽዋ መጠጣት አለብህ።"

መደምደሚያ

ወደ ክሪፕቶ የምትገቡት ለትርፉ ብቻ ከሆነ ተሳስታችኋል። ለስቃዩም ጭምር መዘጋጀት አለባችሁ። ትሬዲንግ ማለት ገንዘብ ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ ራስን በጭንቀትና በፈተና እሳት ውስጥ አልፎ ብረት ሆኖ መውጣት ነው፡፡

ያለ ስቃይ ስኬት የለም፡፡ 🥰🥰

@gashumika
👍2
🇧🇷🌟 የአማዞን ወንዝ በውስጡ የያዛቸውን አስፈሪና ብዙም የማይወሩ ምስጢሮችን ልንገራችሁ! 🌟

የአማዞን የዝናብ ደንና ወንዝ የአለማችን ሳምባ ብቻ አይደሉም፤ "The Kingdom of Monsters" (የጭራቆች መንግስት) እንጂ! 💀 ከውሃው ወለል በታች የሚደበቁት ፍጥረታት ከማንኛውም የሆሊውድ አስፈሪ ፊልም በላይ ዘግናኝ ናቸው።  በደንብ፦ተመልከቱ !
Gashu 🃏 Mika
🇧🇷🌟 የአማዞን ወንዝ በውስጡ የያዛቸውን አስፈሪና ብዙም የማይወሩ ምስጢሮችን ልንገራችሁ! 🌟 የአማዞን የዝናብ ደንና ወንዝ የአለማችን ሳምባ ብቻ አይደሉም፤ "The Kingdom of Monsters" (የጭራቆች መንግስት) እንጂ! 💀 ከውሃው ወለል በታች የሚደበቁት ፍጥረታት ከማንኛውም የሆሊውድ አስፈሪ ፊልም በላይ ዘግናኝ ናቸው።  በደንብ፦ተመልከቱ !
1. The Green Anaconda: The Giant Predator 🐍🪵 (ግዙፉ አረንጓዴ ዘንዶ)
ይህ እባብ በአማዞን ወንዝ ውስጥ The Silent Assassin (ዝምተኛው ገዳይ) ነው።
The Power: ርዝመቱ እስከ 30 ጫማ (9 Meters) ይደርሳል፤ ክብደቱ ደግሞ ከ 250 ኪሎ ግራም በላይ ነው!
The Terror: ሰለባውን የሚገድለው በመርዝ ሳይሆን Extreme Constriction (በሃይለኛ መጠቅለል) ነው። አጥንትን የመሰባበር ብቃቱ የሚለካው በካሬ ኢንች 90 ፓውንድ በሚደርስ ግፊት ሲሆን፣ ይህም ልክ በደረትህ ላይ አንድ ትልቅ አውቶብስ እንደቆመብህ ቁጠር! 🦴💥

2. The Black Caiman: The Apex Stalker 🐊🌑 (ጥቁሩ አዞ)
በአማዞን ውስጥ ከሁሉ በላይ ግዙፉ አዳኝ ይህ አዞ ነው።
The Ghost: ጥቁር ቀለሙ በምሽት ጭለማ ውስጥ እንዳይታይ ይረዳዋል። አንዴ በዛ ግዙፍ መንጋጋው ከያዘህ ማምለጥ The Impossible Mission ነው!
The Vision: በምሽት አይኖቹ ልክ እንደ ደም ቀይ ሆነው ያበራሉ (Blood-red eyes)! 🔴🔴

3. The Candiru: The Tiny Nightmare 🐟🩸 (ትልቁ ስጋት - ትንሹ አሳ)
ይህ አሳ ከዘንዶው በላይ ሊያስፈራችሁ ይችላል። መጠኑ ትንሽ ቢሆንም "The Vampire Fish" ተብሎ ይጠራል።
The Shocking Truth: ይህ አሳ በሰውነት ውስጥ ባሉ ቀዳዳዎች (በተለይም በሽንት ትቦ) በኩል ወደ ሰውነት ውስጥ ዘልቆ የመግባት አስደንጋጭ ችሎታ አለው። አንዴ ከገባ ደግሞ ያለ ቀዶ ጥገና በፍጹም አይወጣም! 😱💉 Warning: Never pee in the Amazon river!

4. The Red-Bellied Piranha: The Meat Grinder 🐟🦷 (ስጋ ፈጪው ፒራና)
እነዚህ አሳዎች በሰከንዶች ውስጥ ሥጋን ከአጥንት የመለየት አቅም አላቸው።
The Attack: በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሆነው ስለሚጠቁ፣ ማንኛውንም ትልቅ እንስሳ (ላምን ሳይቀር) በአምስት ደቂቃ ውስጥ ወደ አጥንት ክምር ይቀይሩታል! 🦴🥩

5. The Electric Eel: The 600-Volt Killer 🐟 (ኤሌክትሪኩ አሳ)
እጅና እግር የሌለው ይህ ፍጥረት እስከ 600 ቮልት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።
The Strike: ይህ ሃይል አንድን ሙሉ ፈረስ በድንጋጤ ሊገድል የሚችል አቅም አለው። It’s a Living Power Plant! 💀
አማዞን ውብ ቢሆንም፣ በውስጡ ግን "Survival of the Fittest" (ጉልበተኛው የሚተርፍበት) ዓለም ነው። ተፈጥሮ እንዲህ አይነት አስፈሪ ፊት ይኖራታል ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? 🤯
ታዲያ አሁንም አማዞን ወንዝ ውስጥ ለመዋኘት ድፍረቱ ከየት ይመጣል? 🏊‍♂️  ከተመቻቹ ላይክና  Share አድርግላቸው! አስተያየት ካለም በኮሜንት 🌹👇

#AmazonSecrets #TheUnderworld #GreenAnaconda #RiverMonsters #NatureHorror #TheLivingNightmare #AmazonRainforest #WildlifeFacts #Ethiopia

✍️:- Mhg Mha

@gashumika
2👍1
ጤናችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ 9 መጥፎ ልማዶች! ‎ጤናችን በእጃችን ነው ይባላል።

‎ብዙዎቻችን ባለማወቅ የምናደርጋቸው ቀላል የሚመስሉ ልማዶች፤ ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርጉን ይችላሉ።

‎ዛሬ ለጤናችን እጅግ አደገኛ የሆኑ 9 ልማዶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል፦

‎ለከፋ የጤና እክል የሚዳርጉ ልማዶች!

1️⃣ ሽንትን መያዝ ወይም ሽንት መቋጠር!
‎••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

‎ሽንታችን ሲመጣ ወዲያው ወይም ቶሎ አለመሸናት፤ የሽንት ፊኛችን ከመጠን በላይ እንዲለጠጥ ያደርጋል።

‎ይህም ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ወይም (UTI) የመጋለጥ እድላችንን ከ3 እስከ 4 እጥፍ ይጨምራል።

‎ስለዚህ፤ ሰውነታችን ምልክት ሲሰጠን ሽንታችንን ወዲያውኑ መሽናት አለብን!

2️⃣ ለረጅም ሰዓታት ተቀምጦ መዋል!
‎•••••••••••••••••••••••••••••••••••••

‎በስራ ቦታም ይሁን በቤት ውስጥ ለረጅም ሰዓት መቀመጥ፤ የደም ዝውውርን እና ሰውነታችን ምግብን ወደ ሃይል የመቀየር ሂደትን ወይም (ሜታቦሊዝምን) ይቀንሳል።

‎ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ፤ በተለያዩ በሽታዎች የመጠቃት እና የሞት ተጋላጭነትን ከ20% እስከ 30% ከፍ ያደርጋል።

3️⃣ ፋስት ፉድ (Fast Food) አዘውትሮ መመገብ!
‎••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

‎እነዚህ ምግቦች በሰውነታችን ውስጥ የሚከሰት ኢንፍላሜሽንን እስከ 70% ይጨምራሉ።

‎በደማችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በድንገት እንዲጨምር ስለሚያደርጉ፤ ለከፍተኛ ድካም እና ላልተፈለገ ውፍረት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው።
1
Gashu 🃏 Mika
ጤናችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ 9 መጥፎ ልማዶች! ‎ጤናችን በእጃችን ነው ይባላል። ‎ ‎ብዙዎቻችን ባለማወቅ የምናደርጋቸው ቀላል የሚመስሉ ልማዶች፤ ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርጉን ይችላሉ። ‎ ‎ዛሬ ለጤናችን እጅግ አደገኛ የሆኑ 9 ልማዶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል፦ ‎ ‎ለከፋ የጤና እክል የሚዳርጉ ልማዶች! ‎ ‎1️⃣ ሽንትን መያዝ ወይም ሽንት መቋጠር! ‎••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••…
4️⃣ በአፍ መተንፈስ!
‎•••••••••••••••••••••

‎በአፍ መተንፈስ ሰውነታችን ማግኘት ያለበትን የኦክስጅን መጠን ከ10 - 20 % ሊቀንሰው ይችላል።

‎ይህ ደግሞ ለጭንቀትና ለእንቅልፍ መዛባት ይዳርጋል።

‎አፍን ዘግቶ በአፍንጫ መተንፈስ ለጤና ተመራጭ ነው።

5️⃣ ስልካችንን እና ላፕቶፓችንን አጠገባችን አድርገን መተኛት!
‎•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

‎ከስልክና ከኮምፒውተር ስክሪኖች የሚወጣው ብርሃን፤ እንቅልፍ እንዲወስደን የሚያደርገውን "ሜላቶኒን" የተባለ ሆርሞን ምርትን በግማሽ ወይም እስከ 50 % ይቀንሳል።

‎ይህም ሰውነታችን ቶሎ እንዲያረጅና በቂ እረፍት እንዳያገኝ ያደርጋል።

6️⃣ የጭንቀት ምልክቶችን ችላ ማለት!
‎•••••••••••••••••••••••••••••••••••••

‎ሰውነታችን የጭንቀት ምልክት ሲያሳይ ትኩረት አለመስጠት፤ ኮርቲሶል (Cortisol) የተባለው የጭንቀት ሆርሞን በደማችን ውስጥ እንዲጨምር ያደርጋል።

‎ይህም እንደ ደም ግፊትና የልብ ህመም ላሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።

7️⃣ እስኪጠማን ድረስ ውሃ አለመጠጣት!
‎•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

‎የውሃ ጥም ስሜት ከተሰማን፤ ሰውነታችን ቀድሞውኑ የውሃ እጥረት ወይም (Dehydration) እንዳጋጠመው እያሳወቀን ነው።

‎የውሃ እጥረት የአንጎላችንን መጠን በጊዜያዊነት ከ1 እስከ 2% ሊቀንሰው ወይም ሊያኮማትረው ይችላል።

8️⃣ የፀሐይ ብርሃን አለማግኘት!
‎•••••••••••••••••••••••••••••••

‎የፀሐይ ብርሃን ዋነኛው የቫይታሚን ዲ ምንጭ ነው።

‎ከቤት ወይም ከቢሮ ሳንወጣ መዋል ለቫይታሚን ዲ እጥረት ይዳርገናል።

‎ይህ ችግር በአማካይ 42% በሚሆኑ አዋቂዎች ላይ በስፋት ይታያል።

9️⃣ የእንቅልፍ ሰአትን ማሳለፍ!
‎•••••••••••••••••••••••••••••••

‎"ትንሽ ቆይቼ እተኛለሁ" በማለት የእንቅልፍ ሰዓትን ማሳለፍ፤ ሰውነታችን ራሱን እንዲጠግን የሚረዳውን የእድገት ሆርሞን ወይም (Growth Hormone) ምርትን እስከ 70 % ሊቀንሰው ይችላል።


🔍 ምንጮች | 📚 Sources Websites

‎1.  Sedentary Behavior and Cardiovascular Disease
‎Website: American Heart Association
‎URL: https://www.heart.org/en/healthy-living/fitness/getting-active/sedentary-behavior

‎2.  Blue Light Has a Dark Side
‎Website: Harvard Health Publishing
https://www.health.harvard.edu/staying-healthy/blue-light-has-a-dark-side

‎3.  Sleep and Health
‎Website: Centers for Disease Control and Prevention (CDC)
https://www.cdc.gov/sleep/about_sleep/how_much_sleep.html

‎4.  Vitamin D Fact Sheet for Health Professionals
‎National Institutes of Health (NIH)
https://ods.od.nih.gov/factsheets/VitaminD-HealthProfessional/

‎5.  Chronic Stress and Health
‎American Psychological Association
https://www.apa.org/topics/stress/health
👍2
እነዚህን ሊንኮች በመጠቀም national ID ከባንክ አካዎንታችሁ ጋር አገናኙት በጣም ቀላል ነው

1. CBE ~  https://cbefayda.cbe.com.et/
2. CBO ~ https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization
3. Bank of Abyssinia ~ https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect

4. Awash Bank ~ https://fayda.awashbank.com/en

5. Hijra Bank ~ https://apps.hijradigital.com/fayda/v2/acctVerf

6. Siinqee Bank ~ https://fayda.siinqeebank.com:7443/

7. Oromia Bank ~
https://share.google/GUWsaxoIAESFRp2hM

8. Dashen Bank ~ https://dashensuperapp.com/dashen-fayda

9. Wegagen Bank ~ https://fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

10. Rammis Bank
~ fayda.rammisbank.et https://share.google/plT5HzQvm1tv8UNXv

11. Bunna Bank
~Bunna Bank S.C https://share.google/A0hUwRAMgdnLtlbzo

12. Hibret Bank
~ Hibir KYC https://share.google/i51ZxAdL9Un0akwdQ

13. Zamzam Bank
~ Zamzam Bank Self Care https://share.google/xGGSSeRFdT1CIbhNy

14. Zemen Bank
~ Zemen Bank - Fayda Harmonization Public Portal https://share.google/suZir106gcgnGBmq0

15.Tsehay Bank
~Tsehay Bank - Secure Authentication https://share.google/kth9Jhv6ZUYBkjplw

16. Nib International Bank
~ Nib-Fayda Harmonization https://share.google/L5ZLh3L8fejwRZuwz

17.  Goh Betoch Bank
~ Goh Betoch Bank- National Id https://share.google/ctaQjZ5hn9oM14V8v

18. Enat Bank
~ Link Fayda ID - Bank Account Entry https://share.google/ylkI3uBltBHjEfQDT

19. Development Bank of Ethiopia
~ DBE-National ID https://share.google/rJZuO1Pgr89iRk78y

20. Anbesa Bank
~Fayda Account Harmonization https://share.google/TZRz6F7D1vyh0drad

21. Ahadu Bank
~ Welcome | Ahadu Bank - Ahadu Fayda https://share.google/AWGS37Dz6lBUjnpc9

22. Addis International Bank
~Home - FaydaOnline https://share.google/VvAB1Q3Ptz5BMeHzg

23. Abay Bank
~ Abay Bank KYC Verification https://share.google/w8Vbv2NE8iKEFmaoG

24.  Sidama Bank
~ Sidama Bank – Fayda Harmonization https://share.google/761CzPTAIDMgDZfq7

25. Tsedey Bank
~ Tsedey Bank – Fayda Harmonization https://share.google/sTOqWWmX7Q9mfREKN

26.  Amhara Bank
~ ABa Fayda Integration System https://share.google/Vv4h7sacieT0EIrXA

27. Berhan Bank
~Source: nationalidharmonization.berhanonline.et https://share.google/mmNkJ7YisczE9C6yK

National ID Ethiopia
👍1