የሆሄያት ህብር📝📝
855 subscribers
427 photos
57 videos
122 files
240 links
ውድ የሆሄያት ህብር ቻናል ቤተሰቦች ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።👍👍
ቻናላችን፦
👉በግጥም 📔📰📼📼
👉በድርሰት📚📚
👉በትረካ📀🎼
👉በስዕል🃏🃏
👉ወጎች📜📜
👉በአጫጭር ልብ ወለዶች ወደ እናንተ እንደርሳለን።
ለሀሳብ እና አስተያየት
፦ሊዮ ማክ፦ @Leoyri
፦ዮሲ ማን፦ @yosikeman
፦የሪ፦ @yerijo
ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል 👉 @gGetem
Download Telegram
ስርና መሬት
""""""""""""""
ወጣ ወጣና እንደሸንበቆ
ከፍ ከፍ አለ ቁልቁሉን ንቆ
አልያዘም ነበር
ስሩ ከአፈር እጅጉን ጠልቆ
መሬት ቆንጥጦ

ሄደ ሄደና ከበላይ በላይ
ወጣ ወጣና ከሰማይ ሰማይ
ንፋስ ሽው ሲል አካል ተንጫጫ
የሰማይ ህልሙ አንሶበት ጫጫ
መሬት ና አለችው ተንከባለለ እንደሙቀጫ።



@gGetem
@gGetem
@gGetem
🥰3
እንዳገር
የሀሳብ ጎጠኞች...
ከጉድጓዱ አፍ ላይ ለምለም ሳር ጎዝጉዘው
እስከመች እንውደቅ ሳናይ ስንረግጠው።
ያስቀመጥነው ድንበር በጥላቻ ከፍሎን
ከአንድነት በላይ ልዩነት አንግሰን
መኖርን ወደናል ከሰውነት ወጥተን።
ደግሞ በዚህ ዘመን ባለንበት ዛሬ
ከተማው ዱር ሆኗል ሰዉ ሆኖ አውሬ።
ሁሉ ተናካሽ ነው ከራሱ ማይስማማ
ከላዩ ደርቦ የጥላቻ አክራማ
እንደያኔው ልማድ መተሳሰብ ቀርቷል
ሁሉ በርጋጊ ነው ካምላኩ ተጣልቷል።
ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ዘርጋለት
ልባሽህን ቢመኝ እጀጠባብህን በእምነት ጨምርለት፤
ንዋይ ቢጠይቅህ ለመስጠት አትሰስት።
ይህ ሁሉ የወንጌል ቃል ጠቅላላ ተረስቷል፤
በነጣቂ ተኩላ ልቦናው ተበልቷል።
በየሰፈረበት ጥጋጥጉ ቆሞ
ሁሉ አቃሳች ነው ተውጧል በታሞ።
መንደር እየሰፋ ሀገር በመጥበቡ
እንዳገር ለመኖር አልፈቀደም ልቡ።
ግና የሚያስፈራው በትውልዶች ሒደት
ሀገር ስሟ እንዳይቀር ከቆይታ ብዛት፤
በታሪክ ድርሳን ላይ ነበረች በማለት።
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ
ባሌ-ጎባ
ተፃፈ፦01/02/2015ዓ.ም
@gGetem
@gGetem
የለሙላ ትግል
(ሊዮ ማ.)
ሲፈስ ሳለ የደም ወዝ
ካለመውደቅ የመሸሽ ጥርዝ
ቢታገሉ ለመንፋቀቅ
ሲታገሉ ለመጠንቀቅ
መልስ አልባ ነው
የሚደበቅ።
ነገን በመፍራት ጦስ
ህሊና ሲቃወስ
መቅናት ባለመቅናት
መሆን ባለመሆን
ተስፋ መቁረጥ ሲነግስ
እንደዚህ ሲሆን ነው
እንባ የሚታፈስ።
t.me/gGetem
comments. .. @leoyri
2👏1
የሀገሬ ሰው ሲተርት ህልም እንደ ፈቺው ነው ይላል።
አይገርማችሁም....!!
ጨካኝ ነህ ይሉኛል
ከክፉዎች ጋርም ያመሰስሉኛል
ፍቅር የማይገባህ ....
ብለው ካሻቸው ጓራ ይመድቡኛል
በፊት......
ሆዴ የኔ አባት
ያ'ንተን ሀዘን የኔ ያርጋት
ሆዴ የኔ ጌታ
አንተ እኮ ነህ የእኔ ፈገግታ
የኔ ሁሉ ነገር .....
አልፍን ቀናት አብረን እንሻገር
ብላኝ እንዳልነበር....
        እኔ
ከእኔ በፊት የእርሷን
አያነባው ሳቋን
የማስቀድም የእርሷን ደስታ
ትኑርልኝ ብዬ በፈገግታ

  በመታመን የኖርኩላት
በጌታ ፊት ቃልን ገባሁለት
ከነፍሴ ከእስትንፋሴ የወደድኳት
እያፈቀርኩ ያፈቀርኳት
እያወራን የማልጠግባት
ትሁት ሆኜ ያከበርኳት
  
   ጥላኝ ሄዳ ተጎዳሁኝ
ከማንነት ተጣለሁኝ
አንዴ ሳይሆን ስስቴ ሞትኩኝ
በቃላት ጦር ተወግቼ
በዝምታ ተገፍቼ
ባመንኩት ሰው ተከድቼ
ልብን አልባ በድን ሆንኩኝ
እንባን ሳይሆን ግጥም ፃፍኩኝ
በስንኜ አለቀስኩኝ
መጨረሻም እንዲህ ሆንኩኝ
እንዳሻቸው የሚገልፁት
በተረዱት የሚፅፉት
ህልምን ሆኜ ተቀመጥኩት
======//========
በገጣሚ:ጆሲ
@Joyefull
@gGetem
2👌2
(በላይ በቀለ ወያ)

በሰው አእምሮ ልክ
በሰው እውቀት መጠን፤ ያለሁ ተወስኜ
የአሁንን ብቻ ነው...
ልነግርሽ ምችለው ፤ እርግጠኛ ሆኜ
በኋላ ምን ቢሆን ፤ ነገ ምን ቢፈጠር
መገመት ነው እንጂ ፣
ተስፋ መድረግ እንጂ ፣
እርግጠኛ ሆኜ አልችልም በናገር፡፡
እናም አሁን ላይ ነው !
ከራስ አስበልጦ ፣
የኔ አንቺን መውደድ ፣ የኔ አንቺን ማፍቀር፡፡
።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በኋላ ብርቅሽ ፣
ነገ ላይ ብጠላሽ ፣
‹‹አይወደኝም ነበር›› ዋሽቷል እንዳትይኝ
የአሁን እውነቴን ፤ ዘላለም እመኚኝ፡፡
ምክንያቱም የኔ ውድ
በኋላን ያለፈ ፤ ነገን የሚሻገር
አሁን ነው ሰው መጥላት፤ አሁን ነው ሰው ማፍቀር
ቅፅበት ነው መለየት ፤ ቅፅበት ነው መጣመር፡፡
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
እናም አሁኔ ላይ…..
ከራሴ አስበልጬ ፣ አንቺን ያፈቀርኩሽ
እናም አሁኔ ላይ…..
የዘልዓለሜ ነሽ ፣ ብዬ እንደነገርኩሽ
ቀናቶች ወራቶች ፥ አመታቶች ሁሉ
እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ
የእድሜ ዘመናቶች ፣ አሁኔ ላይ አሉ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በኋላ ብርቅሽ
ነገ ላይ ብጠላሽ
"አይወደኝም ነበር " ፣ዋሽቷል እንዳትይኝ
የአሁን እውነቴን ፤ ዘላለም እመኚኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

@gGetem
@gGetem
@gGetem
3👏1
ታምናለህ?
:
“ውስኪን ከብርጭቆ
መጎንጨት አንስቶ
ጭኗን ከገለጠች…
ማውራት እንቶፈንቶ ፤
አያድርስ በደሉ !
የሀብታም ሰው ግፉ
ተናግሯል መጽሐፉ”
ብሎ የሚታዘብ…
አረቄ ቤት ያለ …
የዛ ድሀ ምኞት ፤
:
በሴቶች ታጅቦ...
ውስኪ መጠጣት ነው
እ’ሱም ገንዘብ ኖሮት።

(ሚካኤል አ)
@gGetem
2👏1
የግራ ጎን አጥንት
"""""""""""""""""""""
ከቀደምት ፍጥረቱ፥
ከአደም ከጥንቱ፥
ከአዳም ከብርቱ!
ከአንድ እርምጃ ኃላ ፥ተከተለች ሃዋ፤
የአደምን ብርታት ፥እርጋ መመኪያዋ!
ከአንድ እርምጃ ኃላ ፥ሄዋን ተከተለች፤
ከአዳም ከግራ አጥንት
ፍልቀቷን አድርጋ፥ ከጀርባው ዋለለች!

እና በዚህ አለም፥ በፍጥረታት ሚስጥር፤
ሃዋ ከአደም ፊት
ሄዋን ከአዳም ፊት ፥ቀድማው ብትፈጠር!
ከእልፍ አመት በኃላ ፥ነገር ይጣረሳል፤
የፈጣሪ ስራ
የእሽክርክሮሽ ሂደት፥ ከህይወት ይፋረሳል፥
የአንዱ የጎን አጥንት
የሌላውን ሃዋ
የሌላውን ሄዋን፥ የሱ አድርጎ ያፍሳል!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
3
ሐምሌት___ በሊዮ.m4a
4 MB
ሐምሌት
#ዝግጅት_ሊዮ ማክ
🎧🎤🎼🎹🎬🎨
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
🦋🦋🦋🦋
@gGetem
@leoyri
@leoyri
😘
🥰1
እንደምትወዳት ንገራት,

(በእውቀቱ ስዩም)
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

@gGetem
@gGetem
🥰2
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን

@gGetem
@gGetem
@gGetem
4
አደራ እንዳታምኚ
።።።።።።።።።።።።።
አንድ የጨነቀው ሰው
ብዙ ቃል ወርውሮ ወድሻለሁ ቢልሽ
ውሸታም ነው አፉ እንዳያምነው ልብሽ

ካላንች አልኖርም በሀሴት በደስታ
ካላንች አይመታም የልቤ ትርታ
ነፍሴ ጥሟ አይረካም ካንች ተለይታ
እትት ብትት የሚለሽ ከበዛ
ውሸታም በይ እና
              ወርውሪው ወደዛ
የመውደድን ግጥም
                 ድንገት ከፃፈልሽ በወረቀት ሞልቶ
ይወደኛል አትበይ
                    ልብሽ አይከፈል አትመኝው ከቶ
የመውደዱን ጥልቀት
                  በጥላሁን ዜማ ሊነግርሽ ከለፋ
እውነቱን ነው እንዴ?
              ልብሽን አትበይው እንዳትሰጭው ተስፋ
ፍቅርን በወረቀት መሳል ከሞከረ
ውሸታም ነው እርሡ በሀሰት የሰከረ
           ም
             ክ
               ን
                 ያ
                   ቱ
                     ም
የእውነት ካፈቀረሽ የእውነት ከወደደሽ
በተግባር ነው እንጅ
በየትኛውም ቃል አይችልም ሊያስረዳሽ
(ታግሎ የተሸነፈ በፍቅር ሜዳ ላይ በፍቅር ጦርነት
  ደካማ ነው ቀልቡ
                  ስሜቱን አውጥቶ አይችልም ማስረዳት)
  ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በፍቅር የተጠፈረ ልብ ስሜትን ለአፍ እና ለእጅ የመንገር አቅም የለውም!!!!!!


@gGetem
@gGetem
                            
1🥰1
አንቺዬ
````
እኔ ሸክላ መሳይ
አንቺ የንጥር ወርቅ
ማን አስቦት ነበር
የእኛን በፍቅር መውደቅ!?
by-Leo Mak
@leoyri
@gGetem
@gGetem
1
[ረድኤት አሰፋ]
.
¹የሌት ዝናብ ክፉ
አይተነበይም
'ካፊያ' ሲሉት አይቆም
'ዶፍ' ሲሉት አይቆይም።
.
²የሌት ዝናብ ግፉ
የምቾት እንቅልፉ።
³ፍሳሴው ቅላፄው
ከሕልም ሥራፄው
⁴የጣራ ላይ ምቱ
ለጋድሚያ ምቾቱ
⁵በመንቂያችን ሰዓት፣ የ'ተኙ' ስብከቱ...
ክፋቱ።
.
⁶ቀን ቢዘንብ አንተኛም... ሕጻናት ነንና
ገና ሲከብድ አየር... ሲጠቁር ደመና
⁷ጭንቅላቶቻችን፣
እየተራቆቱ ...እንኳን ሊሸፈኑ
እየበሰበስን፣
"ዝናብ አሳድገኝ"፣ ይቀልጣል ዘፈኑ።
.
⁸እንኳን ልንተኛ፣
አይርገበገብም፣ ዐይናችን ይፈጣል
ወትሮስ ያፈጠጠ...መች እድሉን ያጣል?
⁹እንደቀኑ አልሆነም...የሌት ዝናብ ከፋ
ነብይ ቸገረ፣
ዶፍና ካፊያውን፣ የሚለየው ጠፋ...
¹⁰ዝንጋዔ ዳመጠው፣
'ምቾቱ' ለጠጠው...እንቅልፋችን ሰፋ
¹¹የዝናቡ ጠጉሮች...
ውሃ እየነከሩ... ጣራውን ሲያቀልሙ
ለቆርቆሮው ደረት... ምት ሲሸልሙ
ጠፋ "እንንቃ ባይ" ... ሁሉም ጣመው ሕልሙ።
.
¹²ዘመኑ ከነፈ...
ጊዜው ገሰገሰ
ከሌታት ባንዱ ሌት፣ እንደታቀደለት፣ ጣራው አፈሰሰ።
ከተኛነው መሃል...
¹³ጠፈጠፍ መርሯችቸው፣ ቁሩን ያልታገሱ
አራት ነፍሶች ነቁ፣ እንደበሰበሱ።
¹⁴አንዱ ተጠልሎ...እንቅልፉን ሊቀጥል፣ ቤቱን ጥሎ ሄደ
¹⁵ሁለተኛው ሊሞቅ... አልባሳቱን ሊያደርቅ፣ እሳት አነደደ
¹⁶ሶስተኛው ራራ... የተኙትን ሁለ፣እየቀሰቀሰ፣ ሊያነቃ ወደደ
¹⁷አራተኛው ባንቂው...በሶስተኛው ቀስቃሽ፣ ሀሳብ ተናደደ።
እርምጃውን ገትቶ፣ተግሳጽ አወረደ።
¹⁸"ተዋቸው ይተኙ...
ስለነቃን አይደል ማፍሰሱን ያወቅን?
ከነቃን በኋላ፣
ካወቅን በኋላ፣ላንዴ`ንኳ መች ሳቅን?
መሳቁስ ቅንጦት ነው፣
ከነቃነው መሃል፣
ማናችን ተረፍን? ማናችን ጸደቅን?
¹⁹ተዋቸው እነሱን
ተዋቸው ይተኙ ነቅተው ላይፈይዱ
መበስበሳቸውን፣
ላለማዳመጥ ነው፣ኩርፊያቸው መክበዱ።
.
²⁰ሶስተኛው ተረታ፣ ተወው መቀስቀሱን
²¹ሁለተኛው ይዟል፣ እስኪሞቀው ድረስ፣ እሳት መቆስቆሱን
²²አንደኛውም ሄዷል፣ እንቅልፉን ሊቀጥል፣ እንጃ መመለሱን
²³አራተኛው አለ፣
በመካከላችን
ከኩርፊያችን ሰርቆ፣ ሊቀምር ሙዚቃ
²⁴ጣራችን አፍስሶም
ልብሳችንን በስብሶም
ካልተቀሰቀስን... እኛ አንነቃም በቃ?
በቃ????
.
@getem
@getem
@getem
2😁1
ፍቅር ነው አውቃለሁ
።።።።።።።።።።።።።።
መራር ፅዋ በመንገዴ፣
አንቺ ነሽ ወይ የኔ ገዴ።
እንደእንቅፋት እየመታሽ፣
ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ወጣሽ።
ዝብርቅርቋ አንቺ አለሜ
አለሽ ስልሽ የሌለሽው፣
ቢታየኝም ባይታየኝ
ፍቅርሽ እኮ አለ እላለው።

መች መሰለሽ፣

እንደ እሳት፣
ሲያደምቀኝ ወይ ሲያሞቀኝ ፣
ሌላ ጊዜ ስታስከፊኝ፣
ንዴት ሆኖ በግለት መልክ ሲያተኩሰኝ።

ፍቅሬ ሙሉ
ከልብሽ ውስጥ የጎደለለው፣

እንዳልተውሽ፣
ተዋት የሚል ዝግ ሀሳቤን
አይምሮዬ እየተወው፣
እራኩሽ ስል፣
ሸፋፋ እግሬ
እየዞረ ካንቺ ስር ነው፣
ልቤን ካንቺ
ፍቅርሽ ካልኩት እንዳስጥለው፣
ሳሰላስል
ካንድ ሀሳብ ጋር ተገናኘሁ፣

ሀሳቡ፣

አምላክ ወዶን
ፍቅርን በሞት ከገለፀው፣

ለምን ታዲያ፣
በሞት ማግስት በፍርድ ወንበር
ወደሲኦል የምንወርደ፣
ገባኝ፣ ለካ ፍቅር ትርጓሜው
መያዝም ነው መልቀቅም ነው።

ፍቅር ይዤ ባትመረጪኝም
ምርጫሽ ይሁን ፈቅጃለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለው
ለወደድሽው ትቼሻለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለሁ
እረስቼሻለሁ ይቅር ብዬሻለሁ፣

ፍቅር ነው አውቃለሁ

@gGetem
@gGetem
@gGetem
🥰42
"ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር"


.
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
.
.
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
.
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
.
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
.
2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
.
3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)
.
.
.
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
.
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
# አሁን_ትዝታ_እንጂ .....
# ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
.
.
.
.
.
©ኤፍሬም ስዩም(ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር)
@gGetem
@sirak6
4
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
ጠብቄሽ ነበረ
ሲራክ
#ጠብቄሽ_ነበረ
.
ገጣሚ ደበበ ሰይፉ
አንባቢ ሲራክ
1
"ከሞት ጋር ተቃጥረን
ከሞት ጋር ተቃጥረን፣ የቆራጥ ቀጠሮ
ካምናም ብሶበታል ዘገየ ዘንድሮ::
ወትሮም እንዲህ ነዉ የአበሻ ቀጠሮ !!
ሞት ለካ አበሻ ነዉ ?!
ግና ምን ሆኖ ነዉ ?
እንዴት ቢንቀኝ ነዉ ?
እንዴት ቢፈራኝ ነዉ ?
መንገዱ ረዘመ ወይ መንገዱ ጠፋዉ ?
የህይወትን አጥር፣ ዳር ዳሩን ይዞራል !
ዕድሜን ደጅ ይጠናል::
ሞትም እንደሰዉ ልጅ ቀን ይጐድልበታል ?
በለስ የቀናት ለት
ህይወት እንደዚህ ናት
ሞትን መገነዣ፣ ስዉር ስፌት አላት !!"

ስዉር-ስፌት

እንዳልከው ነው 😭.... የመነጠቅ ቀጠሮ። ።
@leoyri
@gGetem
Leo Mák
2
--------
#የማለዳ_ድባብ
===========

ጎሕ ገሰግሶ
ደርሶ
ጽልመት ቢያባርርም
የማለዳ ድባብ ፥ ህብሩ ገጹ ቢያምርም
ስው ፀሀይን አምኖ ፥ ፍኖሱን አይሰብርም
-----------------------//------------------------
✍🏽© በዕውቀቱ ሥዩም
📔የማለዳ ድባብ
-----------------------//------------------------@gGetem
3
ወራት ያወቀችው
ወዳጅ የከዳትም
የሶስት ወር ጨቅላዋን
እግዜር የለያትም
ያለቅሳሉ እኩል
በተበዳይ እንባ
:
ፍራንክ የጎደለው
ጃምቦ ቤት ሲገባ
ካነደደው ሀዘን
ልቡን እያደባ
እጅ እግር የሌለው
ስንኩል ሆኖ ሽባ
:
ምን ማለት ይችላል
እንባ ከረከሰ ?

(እርሱም ይህን ጊዜ
ጌታውን ከሰሰ !)

"እግዜር ሆይ
ጌታ ሆይ ....

ለመደሰት ሳቅን
እንባን ለመከፋት
አድርገህ ዓለሟን
እንዲህ ወጥነሀት
የሶስት ወር ወዳጇ
በወረት ያላያት…
የሶስት ወር ጨቅላዋም
በሞት የተለያት…
እኩል ካለቀሱ
ባንተው አወቃቀር

ከሀዘን ተላልፈን
እንባ ለማይበቃን
አዲስ ነገር ፍጠር። “

(ሚካኤል አ)
@gGetem
@gGetem
2