ኤምሬትስ ግሎባል አልሙኒየም በ ኢራን ጥቃት ምክንያት ‘ከፍተኛ ጉዳት’ እንደደረሰበት አስታወቀ
በኢራን የሚሰነዘሩ የሚሳይል እና የድሮን ጥቃቶች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚገኘው የ‘አል ታዊላህ’ የማምረቻ ማዕከል ላይ “ከፍተኛ ጉዳት” ማድረሳቸውን ኤምሬትስ ግሎባል አልሙኒየም ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. አስታወቀ።
ኩባንያው ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በአቡ ዳቢ ‘ከሊፋ ኢኮኖሚ ዞን’ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የኤምሬትስ ግሎባል አልሙኒየም (ኢጂኤ) ሠራተኞች ለጉዳት ተዳርገዋል። ሆኖም የደረሰው ጉዳት ለሕይወት አስጊ እንዳልሆነ ኩባንያው አክሎ ገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አብዱልናስር ቢን ካልባን በመግለጫው ላይ እንዳሉት፦ “በኢጂኤ በማንኛውም ጊዜ ለሠራተኞቻችን ደህንነት እና ጥበቃ ቀዳሚ ትኩረት እንሰጣለን። በደረሰው ጥቃት በጥልቅ አዝነናል፤ በአሁኑ ወቅትም በማምረቻ ተቋሞቻችን ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን በመገምገም ላይ እንገኛለን።”
የዓለምን 9 በመቶ የአልሙኒየም አቅርቦት የሚሸፍኑት የባህረ ሰላጤው ሀገራት አምራቾች፣ በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ምርቶቻቸውን በተለመደው የንግድ መስመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻሉም። ይህ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ (Strait of Hormuz) የንግድ እንቅስቃሴ በመታገዱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
ሮይተርስ የኩባንያውን መግለጫ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ የኢጂኤ ‘አል ታዊላህ’ የአልሙኒየም ማቅለጫ ጣቢያ በ2017 ዓ.ም. 1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የቀለጠ ብረት አምርቶ ነበር።
@Freshmerejaet

❤2
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተደለደለውን ነፃ የአየር ሰዓት ድልድልን ይፋ አደረገ።
ቦርዱ ይህንን የሚመራ ኮሚቴ ማዋቀሩ የሚታወስ ሲሆን ድልድሉን ለማውጣት ለረዥም ጊዜ የተሰራበት መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላት ወርቅ ሀይሉ ተናግረዋል።
ይህ የአየር ሰዓት ድልድል የምርጫ ቦርድን “ገለልተኝነት የሚያረጋግጥ” ነው ተብሏል።
የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀይማኖት ዘለቀ እንደተናገሩት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ምደባ ስራን በማጠናቀቅ የተመደበውን የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ዕጣው የሚወጣ ይሆናል።
ይህ የአየር ሰዓት ክፍፍልን በተመለከተም 40 % እኩል የሚካፈሉ ሲሆን 25 % ደግሞ ባቀረቧቸው እጩዎች፣ 15 % በአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ቀሪው ደግሞ 15 % በሴት እጩዎች እና 5 % በሴት አካል ጉዳተኞች መሠረት ድልድል የሚደረግ ይሆናል።
ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የድልድል ቀመር መሰረት ለ47 የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚሆን በሬዲዮ 782.5 ሰዓት፣ በቴሌቪዥን 513.45 ሰዓት፣ በጋዜጣ 576 አምድ ያዘጋጀ ሲሆን ይህን አገልግሎት እንዲሰጡም 50 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን ዝግጁ እንዳደረገ አሳውቋል።
እነዚህ መገናኛ ብዙሃን 12 የግል እና 12 የህዝብ እንዲሁም በቴሌቪዥን በኩል ደግሞ 12 የህዝብ እና 8 የንግድ የቀረበ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ስድስት የህዝብ ጋዜጦችን አዘጋጅቻለሁ ብሏል።

❤7
ሁለት መረጃዎች‼️
📌የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) F-16 የአሜሪካ ተዋጊ ጄት መቶ መጣሉን አልጀዚራ ዘግቧል። አንድ F-16 ተዋጊ ጀት አሁን ባለው ወቅታዊ ገበያ ከ30 እስከ 60 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል።
📌ኢራን ሁለት የቻይና መንግስት ኮንቴይነር መርከቦችን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ውስጥ እንዳያልፉ ከለከለች።
ቴህራን አሁን ለኢራን የቤት እቃዎችን፣ መኪናዎችን፣ ልብሶችን እና መድሃኒቶችን የያዙ መርከቦች ብቻ እንዲያልፉ ፈቃድ እንደምትሰጥ ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።
ኢራን በሆርሙዝ ላይ ቁጥጥሯን አጠናክራ ቀጥላለች።

❤7👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰበር መረጃ‼️ ትራምፕ ያልጠበቁት ገጠማቸው❗❗👇
በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን የነገስታት አገዛዝ አንፈልግም (No kings) በሚል መፈክር በዶናልድ ትራምፕ አስተዳዳር ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
ትራምፕ በበኩላቸው "እኔ አሁን ላይ የንጉሥ(king) ስሜት የለኝም፣እየሰራሁ ያለሁት አሜሪካን ታላቅ ለማድረግ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
በአሜሪካ ዘመናዊ ታሪክ በአንድ ቀን ከተካሄዱት ግዙፍ የሰልፍ ንቅናቄዎች አንዱ ሊሆን ይችላል የተባለለት ይህ ተቃውሞ፣ በዋናነት ያነጣጠረው የትራምፕ አስተዳደር በሚያራምዳቸው የኢሚግሬሽን ህጎች፣ በኢራን ላይ በተከፈተው ጦርነት እና በሲቪል መብቶች ጥሰት ላይ ነው።
ይህንን ያልተጠበቀ ድንገተኛ ሰልፍ ማን እንዳቀነባበረው የአሜሪካ መንግሥት ወደ ማጣራት ገብቷል።

🥰15❤7👏7
Fresh መረጃ | FreshNews
Photo
ለጨረቃ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ‼️
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለ”ጨረቃ ቤቶች” የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊሰጥ ነው‼️
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በክልሉ ያሉ ሕገወጥ ወይም በተለምዶ “ጨረቃ ቤት” ተብለው የሚታወቁ ካርታ እና ፕላን የሌላቸውን ቤቶች ባሉበት ሕጋዊ ሊያደርግ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ሊሰጥ መሆኑ ተሰማ።
የክልሉ መንግሥት ምክር ቤት ወይም ጨፌ ኦሮሚያ፣ ባሳለፍነው መጋቢት 10፣ 2018 ዓ፣ም ባካሄደው 6ኛ የሥራ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው፣ መመሪያውን አቅድቆ ለክልሉ መሬት አሥተዳደር ቢሮ መላኩ ታውቋል።
እነዚህን ሕገ ወጥ ቤቶች ሕጋዊ የማድረጉ አሰራር ከከተሞች ፕላን እና መሠረት ልማት ጋር ፈጽሞ ሊጻረር በማይችል መልኩ ብቻ እንደሚከወን የሚያትተው መመሪያው፣ በክልሉ ከተሞች የመሬት ሊዝ አዋጅ መሰረት አስፈላጊው ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ሂደቱ እንደሚጀመር ያመለክታል።
ይህን አሰራር የሚከታተሉትና የሚያስፈጽሙት በከተማ አስተዳደሮች ያሉ የመሬት አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች መሆናቸውን የሚደነግገው የኽው መመሪያ፣ አመልካቾች ማመልከቻቸውን የሚያስገቡበትን ቀንም በይፋዊ ማስታወቂያ እንደሚገለጽ ያብራራል።
የከተማ መሬት አሥተዳደር ጽሕፈት ቤቶች በማመልከቻው መሠረት ያዋቀሯቸውን ባለሙያዎች ወደ ስፍራው በመላክ ቤቱ ያለበት ቦታ ከከተማው ፕላን ጋር የሚጣጣም መሆኑን ከተጣራ በኋላ ቤቱን ሕጋዊ የማድረግ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ የመስክር ወረቀት የመስጠት ሂደቱ እንደሚጀመር መመሪያው ያዛል።
ሕጋዊ የሚደረገው የመኖሪያ ቤት ቦታ በካሬ ሜትር ተለክቶ ከከተማው የመሬት ሽንሻና ደረጃ ወይም ስታንዳርድ የሚተርፍ ከሆነ፣ መሬቱ ወደ መሬት ባንክ ተመላሽ እንደሚደረግ መመሪያው አትቷል።
እነዚህን ሕገ ወጥ ቤቶች ሕጋዊ የማድረግ ሥራ ሸገር፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞችን አያካትትም።
ክፍያን በተመለከተ በሊዝ ስርዓት በሚተዳደሩ ከተሞች በከተማው የመሬት ደረጃ መሰረት የከተማ መሬት ሊዝ አዋጅ ከጸደቀበት ከጥር 24፣ 2005 ዓ፣ም ጀምሮ ያለውን የሊዝ ውዝፍ ክፍያ እንዲሁም፣ የጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያ አመልካች መክፈል እንደሚኖርበት መመሪያው ይደነግጋል።
በመሬት ሊዝ ስርዓት ስር ባልገቡ ከተሞች የሚገኙ ቤቶች ደግሞ፣ ከጥር 24፣ 2005 ዓ፣ም ጀምሮ በከተማው ደረጃ ተሰልቶ የመሬቱን ኪራይ እንዲሁም የጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ክፍያ፣ በተጨማሪም የክፍያውን 30 በመቶ ቅጣት መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
ክፍያውን በአንድ ጊዜ ከፍለው ማጠናቀቅ ለማይችሉ ሰዎች፣ በሁለት ዓመታት ውስጥ በአራት ጊዜ ክፍያ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የፈቀደው መመሪያው፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ክፍያውን ከፍሎ ያላጠናቀቀ አመልካች ግን መሬቱ ሕጋዊ እንደማይደረግለትና የከፈለውንም ክፍያ መልሱ ብሎ መጠየቅ እንደማይችል አስጠንቅቋል።
መመሪያዎችን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያልፈጸመ አካል፣ በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት ፈርሶ መሬቱ ወደ መንግሥት የመሬት ባንክ ተመላሽ እንደሚሆን የጠቀሰው መመሪያው፣ መንግሥት ቤቱን በማፍረሱ የሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ካለ ቤቱ ሳይፈርስ ባለበት እንደሚወርሰው ደንግጓል።
በየትም ቦታ በስሙም ይሁን በሌላ ሰው ስም ከአንድ በላይ ሕጋዊ ያልሆነ መሬት ያለው ግለሰብ መሬቱን ሕጋዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ እንደማይስተናገድ የጠቀሰው መመሪያ፣ ይልቁንም መሬቱ በመንግሥት ይወረሳል ብሏል።
በተጨማሪም ከከተማ ፕላን እና መሰረተ ልማት ጋር የማይጣጣሙ ሕጋዊ ያልሆኑ ቤቶችን ማፍረስ እንደሚቀጥል የጠቀሰው ዋዜማ የተመለከተችው መመሪያ፣ ቤቱ የፈረሰባቸው ግለሰቦች የክልሉ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርገው መሬት ሸንሽኖ የመስጠት ሂደት ውስጥ እንደሚካተቱ ደንግጓል።
እነዚህን ሕገወጥ የመኖሪያ ቤቶች ወደ ሕጋዊ መንገደ የመመለስ ሂደቱ በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ መመሪያው የሚያዝ ሲሆን፣ ለሚፈጠረው ማንኛውም መዘግየትና መጓተት የወረዳ አሥተዳዳሪዎች፣ የከተማ ከንቲቦች፣ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የመሬት አሥተዳደር መዋቅሮች ተጠያቂ ይሆናሉ ሲል ያስጠነቅቃል።
የኦሮሚያ ክልል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በበኩሉ፣ ከክልሉ መሬት አሥተዳደር ቢሮ ጋር ለሥራው መሳካት በቅንጅት እንዲሰራ ያሳሰበው መመሪያው፣ መመሪያው በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል አለመዋሉን እንዲቆጣጠር ጭምር አዟል።
ይህን ሥራ በዋናነት ኃላፊነት ወስደው የሚሰሩት የክልሉ የመሬት አሥተዳደር ቢሮ፣ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ እንዲሁም የክልሉ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት መሆናቸውም ተመላክቷል።
መመሪያውን በየጊዜው በመከታተል ኦዲት የሚያደርጉ የክልሉ የመንግሥት መዋቅሮች በመመሪያው ውስጥ የተዘረዘሩ ሲሆን እነርሱም፣ የፕሬዝዳት ጽሕፈት ቤት፣ የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ፣ የክልሉ የገንዘብ ቢሮ፣ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ እንዲሁም የክልሉ እቅድ እና ልማት ኮሚሽን ናቸው።
ለአንድ ሰው ከአንድ መሬት በላይ ሕጋዊ ማድረግ፣ ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ አስፈላጊው ማጣራት ሳይደረግና አመልካች የሚጠበቅበትን ክፍያ ሳይፈጽም ሕጋዊ ላልሆኑ ቤቶች የመሬት ባለቤትነት የምስክር ወረቀት መስጠት ከባድ አሥተዳደራዊ እርምጃ እንደሚያስወስድ ተገልጿል።
Via_ዋዜማ

❤7👍1
የኢራን ሚሳይል ገና አልተነካም‼️
የአሜሪካ የስለላ መረጃ እስካሁን አረጋገጥኩት ባለው መረጃ በአሜሪካ እና እስራኤል በተደረገው ጥቃት የኢራን ሚሳኤል አንድ ሶስተኛውን ብቻ መውደሙን ሮይተርስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
የዩናይትድ ስቴትስ እና የእስራኤል የአየር ጥቃቶች የቀጠሉ ቢሆንም፣ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ኢራን ከጦርነቱ በፊት ከነበራት የባሊስቲክ ሚሳኤል እና ድሮን የጦር መሳሪያዎች ውስጥ እስካሁን አንድ ሶስተኛው ብቻ መውደሙን በቅርብ ጊዜ ባደረጋቸው ግምገማዎች ላይ ማረጋገጡን ዘገባው ጠቅሷል።
ባለስልጣናቱ ብዙ ሚሳኤሎች እና ድሮኖች በደረቅ የመሬት ውስጥ ዋሻዎች እና ታንከሮች ውስጥ ጠልቀው የተቀበሩ እንደሆኑ ያምናሉ።
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርኮ ሩቢዮ የኢራን ጦርነት ቢያንስ ለተጨማሪ አንድ ወር እንደሚቀጥል ትናንት ለዲፕሎማቶች አሳውቀዋል።

👍8❤2
የጥራት ችግር ያለበትን ፌኒቶይን (Phenytoin) መድኃኒት በአስቸኳይ እንዲመለስ ታዘዘ።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ፣ ሜዲካመን ባዮቴክ ሊሚትድ (Medicamen Biotech limited) በተባለ ኩባንያ የተመረተ የፌኒቶይን 100 ሚሊ ግራም (Phenytoin 100 mg) ታብሌት መድኃኒት የጥራት ችግር ስላለበት ከጤና ተቋማት በአስቸኳይ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱ ለሁሉም የጤና ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው፣ በአምራቹ የተመረቱት የዚህ መድኃኒት ባቾች (batches) በሙሉ የጥራት ጉድለት የታየባቸው በመሆኑ ተመላሽ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ አንዳንድ የጤና ተቋማት መድኃኒቱን የመለሱ ቢሆንም፣ አንዳንድ ተቋማት ግን እስካሁን አለመመለሳቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።
በመሆኑም መድኃኒቱን ያልመለሱ ተቋማት ያላቸውን ቀሪ መጠን በደብዳቤ ገልጸው እስከ ትላንት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎቱ አክሎም፣ ይህንን ትዕዛዝ ተላልፈው መድኃኒቱን ተመላሽ የማያደርጉ ተቋማት ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ አስጠንቅቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እንዳረጋገጠው በተጠቀሰው ባች የተመረተው ምርት የጥራት ችግር ያለበት በመሆኑ ከ 19 ኙም የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሰበሰቡ ትዕዛዝ መተላለፉን አረጋግጧል።
የፌኒቶይን (Phenytoin) መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ የሚጥል በሽታን (Epilepsy) ለመቆጣጠርና የሚያገለግል መሆኑ ይታወቃል።

❤6
አሜሪካ በኢራን ለሳምንታት የሚቆይ የምድር ዘመቻ ለማካሄድ እያጤነች መሆኑ ተነገረ
የአሜሪካው መከላከያ ሰራዊት በኢራን ልዩ ኃይል እና መደበኛ ወታደሮችን በማሳትፍ ለሳምንታት ሊቆይ የሚችል የምድር ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀ መሆኑን ዋሽንግተን ፖስት ነው የዘገበው።
ይህ መረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ቀጣናው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት የመጣ ነው።
እቅዱ ወታደሮቹን ለኢራን ድሮኖች፣ ሚሳኤሎች እና ለምድር ተኩስ ተጋላጭ በማድረግ የግጭቱን ወደ አደገኛ ምዕራፍ መሸጋገር እንደሚያመለክት ዘገባው ጠቁሟል።
ሆኖም ዶናልድ ትራምፕ እቅዱን ያጸድቁ እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም።
ዘገባው ትራምፕ ቀደም ሲል "የትም ቦታ ወታደሮችን አላሰማራም"፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው አሜሪካ "ያለ ምድር ጦር ሁሉንም ግቦቿን ማሳካት ትችላለች" ማለታቸውን አስታውሶ፤ ከዋሽንግተን የተጣረሱ መልዕክቶች እንደሚወጡ አመልክቷል።

የተሳፈሩበት ዶልፊን ተሽከርካሪ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት ሴኖትራክ ላይ የተሳፈሩ 8 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ
በቄለም ወለጋ ዞን ሰዮ ደንታ ወረዳ አሸዋ የጫነ ገልባጭ ሴኖ ትራክ ላይ የተሳፈሩ ተጓዦች በደረሰባቸው የተሽከርካሪ መገልበጥ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታወቋል።
የዞኑ ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሞቲ ጉዲሳ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓም 3:30 ከ20 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች ከደንቢ ዶሎ ከተማ ወደ አሺ ሙጌ ወረዳ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲጓዙ ተሽከርካሪዎ መንገድ ላይ ነዳጅ በመጨረሱ የተነሳ ተሳፋሪዎቹ አሸዋ የጫነ ሴኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ለመሳፈር ተገደዋል።
የተሳፈሩበት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-35460 ኢቲ የሆነው አሸዋ የጫነ ሴኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ፣ ነዳጅ ጨርሶ ከቆመው የሕዝብ ማመላለሻው ዶልፊን የወረዱትን ከሃያ በላይ ተጓዦች በጫነው አሸዋው ላይ አሳፍሮ ወደ ሙጊ ከተማ ሲጓዝ ደንታ ቀበሌ፣ አባ ጃራ ቀረብቾ፣ የተባለ ስፍራ ሲደርስ በመገልበጡ ወዲያውኑ የስምንት ሰዎች ህይወት አልፋል።
በአደጋው 6 ወንዶች እና 2 ሴቶች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ ሁለቱ ሕፃናት ናቸው።በ 12 ሰዎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰ ሲሆን ከዚያ ውስጥ 7ወንዶች እና 5 ሴቶች እንደሆኑ ምክትል ኢንስፔክተር ሞቲ ጉዲሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
አደጋውን ያደረሰው የሴኖ ትራኩ የጭነት አሽከርካሪ ለግዜው ከህግ ቢሰወርም ክትትል እየተደረገበት ይገኛል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ደንቢ ዶሎ ከተማ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

❤8🕊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ደብረ ማርቆስ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ
አየር መንገዱ በሳምንት ሦስት ቀናት ማለትም በየሳምንቱ ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ የአማራ ክልሏን ደብረ ማርቆስ ከተማ ከአዲስ አበባ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ይሆናል።
ይህ አዲስ የበረራ መስመር ለደብረ ማርቆስና አካባቢው ማኅበረሰብ ፈጣን የትራንስፖርት አማራጭ ከመፍጠሩም በላይ ለንግድ፣ ለጤና አገልግሎት እና ለቅርስ ቱሪዝም ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።
ደብረ ማርቆስን ጨምሮ አየር መንገዱ በቅርቡ ይፋ ያደረጋቸው የነገሌ ቦረና እና የጎሬ መቱ በረራዎች ሲታከሉ፤ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹ ወደ 27 ከፍ እንደሚሉ ተመላክቷል።

❤22😁1
ኢራን ሳይጠበቅ ኬንያን አስጠነቀቀች
ናይሮቢ ኬንያ የሚገኘው የኢራን ኤምባሲ፣ ኬንያ ከአሜሪካና ከእስራኤል ጋር በምታደርገው ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንድታደርግና በኢራን ላይ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች ላይ ተባባሪ እንዳትሆን የሚል ጠጠር ያለ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ አውጥቷል።
ኤምባሲው መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው በዚህ መግለጫ የሆርሙዝ የባህር መተላለፊያ መስመር ለሁሉም ዝግ እንዳልሆነ ገልጿል።
ይሁን እንጂ መተላለፊያው በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለሚሰነዝሩት አሜሪካና እስራኤል፣ እንዲሁም ለጥቃቱ ድጋፍ ለሚሰጡ ማናቸውም ወገኖች ዝግ መሆኑን በይፋ በማስታወስ፤ ኬንያም በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት ተባባሪ የምትሆን ከሆነ ለኬንያ መርከቦች ዝግ እንደሚሆን በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ገልጿል።
ኤምባሲው አክሎም፣ የኬንያ መርከቦችም ሆኑ የሌሎች አገራት የንግድ መርከቦች በመስመሩ በሰላም ማለፍ የሚችሉት የሚከተሉትን ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟሉ ብቻ እንደሆነ ገልጿል፦
1. በኢራን ላይ እየተካሄደ ባለው "ሕገ-ወጥ ጥቃት" ላይ አለመተባበር፤
2. የኢራን ባለሥልጣናት ያወጧቸውን የደህንነት ደንቦች ማክበር፤
3. ከመጓዛቸው በፊት አስቀድሞ ከኢራን የሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት መፍጠር የሚሉ ናቸው።
በመሆኑም ኬንያ ከጥቃት ፈጻሚዎቹ ጋር የምትተባበር ከሆነ መርከቦቿ "ሰላማዊ" ተብለው ስለማይቆጠሩ በመስመሩ እንዳይተላለፉ እገዳ ሊጣልባቸው እንደሚችል ኤምባሲው አስጠንቅቋል።
በተጨማሪም፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት በኬንያ የኑሮ ውድነት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ "የአሜሪካና የእስራኤል የፕሮፓጋንዳ ውጤት ነው" ሲል አስተባብሏል።

❤6😁1🤪1
ሩሲሲያ የአሜሪካን ምስጢራዊ መረጃ ለኢራን አሳልፋ መስጠቷ ተገለጸ፡፡
የዩክሬን የስለላ ተቋማት ባወጡት አዲስ መረጃ መሠረት፤ ሩሲያ በሳውዲ አረቢያ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎችን ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ለኢራን አሳልፋ ሰጥታለች።
የዓለምን ትኩረት በሳበው በዚህ መረጃ መሠረት፤ ሞስኮ ለቴህራን የሰጠችው መረጃ የጦር ሰፈሩን ቁልፍ ስፍራዎች በትክክል ለይቶ የሚያሳይ ሲሆን፤ ይህም ኢራን ለሰነዘረችው ጥቃት እንደ ትልቅ ግብዓት ጥቅም ላይ ውሏል ተብሏል።
ይህ ድርጊት በሩሲያ እና በምዕራባውያን መካከል ያለውን ፍጥጫ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገምቷል።
በተለይም በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የፔንታጎን መሥሪያ ቤት በኢራን ላይ የየብስ ወታደራዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ፍንጮች እየታዩ ባሉበት በዚህ ወቅት የሩሲያ ጣልቃ ገብነት ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።
የዩክሬን የስለላ ድርጅት ይፋ ያደረገው ይህ ምስጢራዊ ሰነድ በሳውዲ አረቢያ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር እንዴት ኢላማ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ግልጽ ማብራሪያ የሚሰጥ ነው።

❤10👏3
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛውን ወታደራዊ በጀት በመመደብ ቀዳሚነቱን ያዘች
በ2026 የፈረንጆቹ ዓመት፣ ጎረቤት ሀገራት ትኩረታቸውን በመንገድና በንግድ ልውውጥ ላይ ሲያደርጉ፣ ኢትዮጵያ ግን የመከላከያ አቅሟን ለማጠናከር ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰች መሆኑን ግሬት አፍሪካ ዲጂታል ሚዲያ ዘግቧል። ሀገሪቱ በዘርፉ ካላት ግዙፍ በጀት በተጨማሪ፣ ሰራዊቷን በዘመናዊ ድሮኖች፣ በረቀቁ የጦር አውሮፕላኖችና በቴክኖሎጂ የታገዙ ትጥቆች በማስታጠቅ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከ0.9 እስከ 3.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የተገመተ ሲሆን፣ ይህም ቀጠናዊና ውስጣዊ የጸጥታ ስጋቶችን ለመቋቋም የሚያስችል ዝግጁነትን ለመፍጠር የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ከመከላከያ ግንባታ ጎን ለጎን በከተሞች ዘመናዊነት ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ዘገባው አክሎ አመልክቷል። በተለይም አዲስ አበባን በአፍሪካ ካሉ እጅግ ዘመናዊ ከተሞች ተርታ ለማሰለፍ የሚከናወኑት የልማት ስራዎች ሀገሪቱ ለጥበቃም ሆነ ለብልጽግና ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው። ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሰረተ ልማት ላይ ሲያተኩሩ፣ ኢትዮጵያ ግን ወታደራዊ ሀይልንና ዘመናዊነትን በማጣመር ቀጠናዊ ተሰሚነቷን እያሳደገች ትገኛለች።

😁13👏10❤2🍌1