ፍሬ ሃይማኖት
1.84K subscribers
3.87K photos
296 videos
160 files
335 links
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡


® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ

@Frehaymanoteebot
Download Telegram
ምንይልክ ወንድ ይፍራው(ወልደ ትንሣኤ)ይህ ነበር።
.
        ዝክረ ወልደ ትንሣኤ
     (ምንይልክ ወንድይፍራው)

     በደረጀ እሸቴ(ወልደ ሥላሴ)

ሰላም ለኩልክሙ ኦ ውሉደ ፍሬሃይማኖት

እንደ ምን ከረማችሁ???

ፍሬ ሃይማኖት የሰንበት ት/ቤታችን ከነበሯት ጠንካራና ታታሪ ልጆች መካከል  ምንይልክ ወንድይፈራው(ወልደ ትንሳኤ)  አንደኛው ነበረ።

ወንድማችን ፍሬ ሃይማኖትን የተቀላቀለው(አባል የሆነው) ቤተ ክርስቲያኑ ተተክሎ  የሰንበት  ት/ቤቱ ተመስርቶ ብዙም ሳይቆይ በ1988ዓ.ም መገባደጅያ ላይ የተሰጠውን መንፈሳዊ ኮርስ በመማር ነበር።

የሰንበት ት/ቤታችን አባል ከሆነበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዕለተ እረፍቱ  ድረስ  የኮሚቴ አባል፣ የክፍሎች ተወካይ(አመራር)፣ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ተወካይ በመሆን ባለመታከት ያገለገለ ጠንካራ ወንድማችን ነበር።

እኔ በበኩሌ ዛሬም ድረስ ምንይልክን ሳስታውስ  ሁለት ነገሮቹ እጅግ በጣም ያስገርሙኛል።እነዚህም፦

፩ኛ) ትክክል  እስከ ሆነ ድረስ ላመነበት ነገር ሟች ( ሐቀኛ ሰው) የነበረ  መሆኑ ነው።በዚህ አስመሳዩና አድር ባዩ በበዛበት ዓለም እንደ ምንይልክ ዓይነት ሰዎችን ማግኘት ከባድ ነው። በየትኛውም ስፍራ የማይቀያየር(እንደ ገበቴ ውሃ የማይዋልል) አንድ ዓይነት አቋም ያለው  እውነተኛ ሰው ነበር።  

፪ኛ) ከአገሩ ከኢትዮጵያ ወጥቶ(ባሕር ማዶ) የመኖር ፍላጎት ፈጽሞ የሌለው ሰው ነበረ።በየዓመቱ ዲቪ ሎተሪ ሲመጣ እኛ ወንድሞቹ ዕድላችንን እንሞክር ብለን ስንሞላ በርሱ በኩል ግን የማይታሰብ ነገር ነበር።ለርሱ ሕይወት ማለት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ብቻ ነው።

በዚች ፈተና በበዛባት ዓለም ለአጭር ጊዜ ቢሆንም የኖረው ያውም  ደልቶት አልነበረም።ሕይወቱ በአብዛኛው በፈተና የተሞላ ሕይወት ነበረ ማለት ይቻላል።በርካታ ደዌያት(በሽታዎች) ነበሩበት።ስኳር፣ግፊት፣ኩላሊት።ሁሉንም ግን በአኮቴት ተቀብሎት ይኖር ነበር እንጂ አንድም ቀን ፈጣሪውን ሲያማርር ተሰምቶ አያውቅም።

ለአብዛኞቻችን የ2002ዓ.ም አዲስ ዓመት ሲብት ለእርሱ ግን ይህቺን ዓለም የሚሰናበትበት የመጨረሻው(አሮጌ) ዓመት ነበር።ብርቱው ሰው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብቶ ሰነበተ።


በስተመጨረሻም ልክ የዛሬ 17 ዓመት

በዛሬዋ ቀን  ማክሰኞ መስከረም አምስት ቀን 2002ዓ.ም  ከዚች  ከንቱ ዓለም  በሞት ድልድይነት ወደ አዲሲቱ ዓለም የተሸጋገረበትና በምድር ያለነውን ወገኖቹን የተሰናበተባት፤ እኛም ጊዜያችን ደርሶ  እስከምንከተለው ድረስ ዘወትር ስናስታውሳት የምትኖር  ዕለት ናት።

የሕይወት ባለቤት አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር የወንድማችንን የወልደ ትንሳኤን ነፍስ ይማርልን።በአጸደ ነፍስ ከቅዱሳኑ  ጋር ይደምርልን።

ኦ እግዚኦ አዕርፍ ለነፍሰ ገብርከ ወልደ
ትንሣኤ።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ፤
ለ2019 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤታችን ውስጥ የየትኛውን ክፍል አገልግሎት መስጠት እንደሚፈልጉ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመግባት ምርጫዎን እንዲያሳውቁን እንጋብዛለን።
https://script.google.com/macros/s/AKfycbz4VKy5rDMHpZV42UXcL2ZXtti9-u7zJAEXSs_Hfg4GVYtf9lklejLkieT5d8hBt-mBtQ/exec
✝✝✝ የተቀጸል ጽጌ በዓል ✝✝✝

‹‹ተቀጸል ጽጌ›› ማለት ‹‹አበባን ተቀዳጅ›› ማለት ሲሆን በዘመነ አክሱም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት በዐፄ ገብረ መስቀል የተጀመረ በዓል ነው፡፡ ይህ የተቀጸል ጽጌ በዓል የክረምቱን መውጣት መሠረት አድርጎ መስከረም ፳፭ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን ሕዝቡ በክረምቱ ምክንያት፣ በዝናቡ ብዛት፣ በወንዙ ሙላት ተለያይቶ ይከርም ነበርና ለንጉሠ ነገሥቱ የአበባ አክሊል/ጉንጉን/ ሠርቶ በማምጣት የሚያበረክትበት በዓል ስለነበረ ‹‹ተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ሐፄጌ፤….ዐፄ ገብረ መስቀል አበባን ተቀዳጅ›› እየተባለ ይዘመር ነበር፡፡

ምንም እንኳን በታሪክ ደምቆ የሚታወቀው በዚህ መልኩ ቢሆንም ቀደም ያለ የታሪክና የትውፊት ውርርስ ያለው በዓል ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤልን በሰባተኛው ወር (ኤታኒም/መስከረም የመጀመሪያው ቀን ከሚከበረው በዓል መጥቅዕ /የመለከት በዓል/ በኋላ በዐሥረኛው ቀን የሥርየት በዓል አድርገው እንዲያከብሩት አዝዟቸው ነበር፡፡ (ዘሌ. ፳፫፥፳፭)

ይህ የመስከረም ወር ዐሥረኛው ቀን የእስራኤላውያን የንስሐ መግቢያ የጾም ቀን አድርገው ሲያከብሩት የነበረና በሕገ ኦሪት ተወርሶ በኢትዮጵያም የሚከበር እንደነበረና በኋላ ግን በዘመነ ሐዲስ የዐፄ መስቀል በዓል እንደተተካበት መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ የዐፄ መስቀል በዓል ሕዝቡ ሁሉ ነገሥታቱን ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› ለማለት ወደ ነጉሥ ከተማ የሚወጣበትና መሪውን የሚያገኝበት በሀገር ላይ ስላለው ሁኔታም የሚወያይበት ቀን ሆኖ ይከበር ነበር፤ በዓሉም የሚከበረው መስከረም ፳፭ ቀን ነበር፡፡ (ክብረ በዓላት ገጽ ፶፬)

ቆይቶ ግን በዐሥረኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጌታችን ግማደ መስቀል በዐፄ ዳዊት አማካኝነት ከአሌክሳንደርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባው መስከረም ዐሥር ቀን ስለነበር የተቀጸል ጽጌ በዓል የዐፄ መስቀል በዓል እየተባለ ቀኑ ከመስከረም ፳፭ ወደ መስከረም ፲ ተዛውሮ ሲከበር ኖሯል፡፡

ምክንያቱም ንጉሡ መስቀሉን መስከረም ፲ ቀን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው ሲገቡ በኢትዮጵያና በአውራጃዎቿ ሁሉ ብርሃን ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት ሴቱም ወንዱም፣ ትንሹም ትልቁም፣ ሕዝቡም አሕዛቡም በፍጹም ደስታ በዓል አደረጉ፤ ዐፄ ዳዊትም መስከረም ፲ ቀን ከሠራዊታቸው ጋር ደስ እያላቸው በዓሉን አከበሩ፤ በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እየረገጡ በሆታ ካህናቱ በዝማሬ ‹‹መስቀል ኃይልነ፣ መስቀል ጽንዕነ›› እያሉ ከፍ ባለ ደስታ በዓሉን አከበሩ፡፡ ይህንንም ልማድ አድርገው በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ሁሉ በዓልን ሲያከብሩት ኖረዋል፡፡ ስሙንም ‹‹ዐፄ መስቀል በዓል›› ብለው ሰይመውታል፡፡ (መጽሐፈ ጤፉት ገጽ ፶-፶፩፣ የመስከረም ፲ ስንክሳር አርኬ)

ስለዚህ ጉዳይ ድርሳነ መስቀልም እንዲህ ይላል፤ ‹‹መስከረም ዐሥር ቀንም በንጉሥ ከተማ መካከል በመስቀል ምልክት ሰንደቅ ዓላማ ተተከለ ስለዚህም ያቺ ዕለት የዐፄ መስቀል ተባለች›› ይላል፡፡ (ድርሳነ መስቀል ገጽ ፪፻፺፬)

ይህ ታላቅ በዓል እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ በቤተ መንግሥት ሲከበር የቆየ ሲሆን በደርግ መንግሥት ምክንያት በዓሉ ተቋርጦ እስከ ፲፱፻፹፫ ዓ.ም ሳይከበር ቆይቷል፡፡ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ በዓሉ በቤተ መንግሥትና በነገሥታት ፊት ባይከበርም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በፓትርያሪኩ ፊት  ለመታሰቢያ ያክል እየተከበረ ይገኛል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ዴንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን።
1, ትምህርትና ሥልጠና ክፍል
በስሩ 4 ንዑስ ክፍላት ሲኖሩት
    ሀ,ተከታታይ ትምህርት ንዑስ ክፍል፦ትምህርቶችን በተቀመጠው መርሐግብር መሰረት ማስጀመርና መከታተል፣በመማር ማስተማሩ ላይ የሥነ ምግባር ችግር ሲኖር ከሚመለከተው ክፍል ጋር መነጋገር፣ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚፈኑ አባላት የልምድ ልውውጥ መርሐግብር ማዘጋጀት፣የዓመቱ የምርቃት መርሐግብር ማዘጋጀት፣የሰ/ት/ቤታችን አባላት አብነት እንዲማሩ አድርጎ የክህነት ማዕረግን ማስጠበቅ፣ወርሃዊ የትምህርት ጉባኤ ማዘጋጀት
    ለ,ሥልጠና ንዑስ ክፍል፦የሥልጠና መመሪያን መከተልና ማስተግበር፣ተተኪ መምህራንን ማፍራት፣ለመምህራን የአቅም ማጎልበቻ መርሐግብር ማዘጋጀት፣አርአያ ክህነትን በተመለከተ ሥልጠና ማዘጋጀት፣ከንስሐ አባቶች ጋር ውይይት ማድረግ፣ሥርዓተ ቅዳሴን ማስተማር፣በ2019 ዓ.ም ጋብቻቸውን የሚፈጽሙ አባላትን ቅድመ ጋብቻ ትምህርት መስጠት፣አባላትን የሚመለከቱ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት፣
    ሐ,መምህራን ምደባና ቤተ መጻሕፍት ንዑስ ክፍል፦መምህራንን መመደብ መገምገምና መከታተል፣መንፈሳዊና አስኳላ መጻሕፍትን ማሟላት፣ የቤተ መጻሕፍት አባላትን ቁጥር ማሳደግና ወርሐዊ ክፍያን መሰብሰብ፣ወርሐዊ የመጻሕፍት ዳሰሳ ማድረግ
    መ,ቅድመ ጊቢ ጉባኤ ንዑስ ክፍል፦ሳምንታዊ ቅድመ ጊቢ ጉባኤ ማዘጋጀት፣ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፣ልምድ ልውውጥ ማዘጋጀት፣የሰሌድ መጽሔት ማዘጋጀት፣በማህበራዊ ሚዲያዎች ትምህርቶችን ማስተላለፍ፣በክፍላት ጥያቄና መልስ ውድድር ማዘጋጀት




  2,መርሐግብርና ጉባኤያት ክፍል
    4 ንዑስ ክፍላት አሉት
ሀ,የውስጥ አመራር አገልግሎት አደረጃጀት ንዑስ ክፍል፦በሰ/ት/ቤቷ ላይ ያሉ ጉባኤያትን መቆጣጠርና ማስተባበር ፣የጋራ የሆኑ መርሐግብራት በአግባቡ እንዲካሄዱ ማድረግና፣መርሐግብር የሚመሩ አባላትን ከትምህርት ክፍል ጋር በመሆን መልምሎ ማሰልጠን 
ለ,ጉባኤያትና ሃይማኖታዊ በዓላትን የመደራጀት ንዑስ ክፍል፦ሃይማኖታዊና የሕዝብ በዓላትን በመጠቀም ጉባኤ ማዘጋጀት፣አጠቃላይ የሚዘጋጁ መርሐግብሮችን የትምህርትና የይዘት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግ፣
ሐ,ስብከተ ወንገልንና የሰ/ት/ቤቷ አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ፦በአስኳላና በማደራጃው ብሔራዊ ፈተና የሚፈተኑ አባላትን የሥነ ልቦናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚረዳ ጉባኤ ማዘጋጀት፣የምርቃት መርሐግብርን ማዘጋጀት፣በሰ/ት/ቤቷ የሚደረጉ የጸሎት መርሐግብሮችን ማዘጋጀትና ማስተባበር
መ,ክትትልና ግምገማ ንዑስ ክፍል፦በክፍሉ የተደራጁ ንዑስ ክፍላት የሚሰሩትን ስራ መገምገምና ሪፖርት ማዘጋጀትና ማጠናከር




3,የሰው ሃብት አስተዳደር ክፍል
3 ንዑስ ክፍላት አሉት
ሀ,የአባላት እንክብካቤ ንዑስ ክፍል፦አዳዲስ አባላትን መመዝገብ፣የአባልነት መታወቂያ ማዘጋጀት፣በየክፍሉ የተመደቡ አባላት በቂ መሆናቸውን መመገምገምና ለሚመለከተው ሰው ማሳወቅ፣የዓመት መርሐግብርን አዘጋጅቶ መስጠት፣የአባላትን መንፈሳዊ ሕይወትን መከታተል፣የንስሐ አባት የሌላቸውን ማስያዝና በተዘጋጀው መርሐግብር መሰረት የጋራ የቁርባን መቀበያ መርሐግብርን ማዘጋጀት፣አባላት የሐዘንና የደስታ ጉዳዮች ሲገጥሟቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣በሠርክ ጉባኤ ላይ ጸሎት ማድረግ፣የሥነ ምግባር ችግር ያለባቸውን አባላት ለይቶ ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ፣በተለያዩ ምክንያቶች ከሰ/ት/ቤት የራቁ አባላትን የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም እንዲመለሱ ማድረግ
ለ,የወላጅችና የወጣቶች ጉባኤ ንዑስ ክፍል፦የወላጆች ጉባኤን ማጠናከርና የልጆች አስተዳደግ ስልጠና መስጠት፣በአካባቢው ያሉ ወጣቶች የተለያየ ጉባኤ በማዘጋጀት ወደ ቤተክርስቲያን ማቅረብና ማጠናከር
ሐ,የውጪ አባላት ንዑስ ክፍል፦በትምህርትና በሥራ ምክንያት የራቁ አባላትን የተለያዩ መንገዶች በመጠቀም አግልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግና በአሉበት ቦታ መከታተል፣ በትምህርት ምክንያት ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሄዱ አባላት ሲመጡ እንዲያገለግሉ ማድረግና ባሉበት መከታተል
 



4,መረጃና የውስጥ ግንኙነት ክፍል
ሀ,መረጃ መዛግብትና ኦዲዮ ቪዝዋል ንዑስ ክፍል፦የአባላት መረጃ ማደራጀት ወደ ዳታ ቤዝ መቀየር፣የሰ/ት/ቤቷን መገናኛ ብዙሃን መቆጣጠርና የሚደረጉ ተግባራቶች በሚዲያ ማስተላለፍ
ለ,የውስጥ ግንኙነት ንዑስ ክፍል፦ክፍላትን ከክፍላት ጋር ያለው ግንኙነት ማጠንከርና እንዲናበቡ ማድረግ፣ክፍላት የሚጠቀሙበትን ተመሳሳይ የሆነ ሶፍትዌርና መረጃ አያያዝ ማዘጋጀት
ሐ,መንፈሳዊ ኩነቶች ንዑስ ክፍል፦አጠቃላይ ላሉ አባላት በእድሜያቸው መሰረት የጉዞ መርሐግብር በማዘጋጀት የእርስበርስ ግንኙነትን ማጠናከር፣ያሉ አባላትና ወላጆችን በየደረጃቸው የሚወያዩበት የተለያዩ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት(panel discussion)፣በዓመቱ መጨረሻ የተለያዩ መንፈሳዊና ስፖርታዊ ውድድሮችን ማድረግ
    




  5,መዝሙርና ሥነጥበብ ክፍል
8 ንዑስ ክፍላት አሉት የሚሰራቸው ሥራዎች፦አባላትን በዝማሬ አገልግሎት በጥራትና በበቂ ሁኔታ ሆነው እንዲያገለግሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት፣የዝማሬ ምሽቶችን ማዘጋጀት ፣ተተኪ አስጠኚዎች ማፍራት ፣ከትምህርት ክፍል ጋር በመሆን ሥርዓተ ቅዳሴ ዜማና ሥርዓት ስልጠና መስጠት፣አባላት ያላቸውን ተሰጥዖ(ግጥም ፣ድርሰት፣ስዕል....)እንዲጠቀሙ በስልጠና መደገፍና የተለያዩ የተውኔት መርሐግብራት ማዘጋጀት
   



6,ምግባረ ሰናይና ልማት ክፍል
4 ንዑስ ክፍላት አሉት
ሀ,የጥናት፣የእቅድና የድጋፍ ንዑስ ክፍል፦የቤት ለቤት ጉብኝት የገላ ማጠብና የተለያዩ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት፣
አቅም የሌላለቸው አባላትንና ምዕመናንን በመለየት ስፖንሰር በመፈለግ መርዳት እንዲሁም የመስራት አቅመ ያላቸውን ሥራ እንዲያገኙ ማድረግ፣የትንሣኤና የገና በዓላት ላይ የምገባ መርሐግብር ማከናወን፣ለነዳያን የቁርስ መርሐግብር በማዘጋጀት ትምህርት መስጠትና ለቅዱስ ቁርባን ማብቃት፣ጉብኝት የሚደረግባቸውን ገዳማትን ፀበልተኞችን እስረኞችን የእርዳታ ድርጅቶችን መጎብኘት
ለ,ቁሳቁስና አልባሳት ንዑስ ክፍል፦የእርዳታ የሚሆኑ እቃዎች አልባሳትና ጫማዎች በመቀበል ለይቶ ከጉብኝት ክፍል ጋር ለተረጂዎች ማድረስ
ሐ,የሂሳብና የግዢ ንዑስ ክፍል፦የቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ከተለያዩ አካላት የሚሰበሰብ ገንዘብን ለበጀትና ንብረት ክፍል ያስገባል፣በክፍሉ ለታቀዱ እቅዶች የሚያገለግሉ እቃዎችን ይገዛል
መ,ስልጠና፣ልምድ ልውውጥና ግንዛቤ ማስጨበጫ ንዑስ ክፍል፦የደም ልገሳ መርሐግብር ማከናወን ፣የጸሎት መጽሐፍ ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች ቦታ መርጦ በማስቀመጥ እንዲጠቀሙ ያደርጋል፣ስለ ክፍሉ ስራዎች አጠቃላይ ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ማዘጋጀትና ለሚረዱ ሰዎችና ተቋማት የምስጋና ሰርተፍኬት መስጠት
   



     7,በጀትና ንብረት ክፍል
4 ንዑስ ክፍላት አሉት
ሀ,ገቢና ወጪ ቁጥጥር ንዑስ ስ
ክፍል፦ከአባላት ወርሐዊ መዋጮ መሰብሰብ፣ከየክፍላቱ የሚገቡ ገቢዎችን መሰብሰብና በሥራ አመራሩ የፀደቁ ወጪዎችን ማውጣት፣አግልግሎቱን የሚያቀላጥፉ የሒሳብ መያዣ ፎርማት ማዘጋጀት፣ክፍላት ወጪን እንዲቀንሱ ማድረግ
ለ,ሒሳብ አያያዝ ንዑስ ክፍል፦ለክፍላት የወጣ ወጪን ማወራረድና ሪፖርት ማቅረብ
ሐ,ንብረት አስተዳደር ንዑስ ክፍል፦ያሉ ንብረቶችን በዓይነት ለይቶ መቁጠርና አጠቃቀምን መከታተል
መ,ግዢ ክፍል፦ለሰ/ት/ቤቷ የሚያገለግሉ እቃዎች ግዢ መፈፀም
የሰንበት ትምህርት ቤታችን የክፍላት ምዝገባ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ይጠናቀቃል። በመሆኑም እስካሁን ያልተመዘገባችሁ በሙሉ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እየገባችሁ ፈጥናችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
👉 https://script.google.com/macros/s/AKfycbz4VKy5rDMHpZV42UXcL2ZXtti9-u7zJAEXSs_Hfg4GVYtf9lklejLkieT5d8hBt-mBtQ/exec
የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት
ፍሬ ሃይማኖት pinned «የሰንበት ትምህርት ቤታችን የክፍላት ምዝገባ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ይጠናቀቃል። በመሆኑም እስካሁን ያልተመዘገባችሁ በሙሉ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እየገባችሁ ፈጥናችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። 👉 https://script.google.com/macros/s/AKfycbz4VKy5rDMHpZV42UXcL2ZXtti9-u7zJAEXSs_Hfg4GVYtf9lklejLkieT5d8hBt-mBtQ/exec የሰንበት ት/ቤቱ…»
.

            ታሪክ በዛሬዋ ዕለት

✝ የመጀመሪያዎቹ የኮርስ ተመራቂዎች✝

           በደረጀ እሸቴ(ወልደ ሥላሴ)

ሰላም ለኩልክሙ ኦ ውሉደ ፍሬሃይማኖት

ተወዳጆች ሆይ!!! እንደ ምን ከረማችሁ?

ፍሬ ሃይማኖት ከተመሠረተችበት ከህዳር ወር  1985ዓ.ም እስከ ነሐሴ ወር 1987 ዓ.ም ድረስ (ከሁለት ዓመታት በላይ መሆኑ ነው) ቅዳሜ እና ዕሁድ  በተለያዩ መምሕራን ከሚሰጡ ልዩ ልዩ የቤተክርስቲያናችን አስተምሕሮዎች በስተቀር  መደበኛ ኮርስ(ትምሕርት) ለአባላቱ ተሰጥቶ አያውቅም ነበር።

በነሐሴ ወር 1987ዓ.ም ግድም  በወቅቱ መምሕራችን በነበሩት በመሪጌታ(በሊቀ ጠበብት) ዘለዓለም መንግሥቱ በኩል አንድ መልካም ኃሳብ ቀረበ።ይኸውም ኃሳብ፦ በሌሎች አቻ የሰንበት ት/ቤቶች እንደሚደረገው ሁሉ ለአባላቱ መሠረታዊ ዕውቀትን የሚያስገኝ ኮርስ  መሰጠት አለበት የሚል ሲሆን፦

በወቅቱ የነበረው የሥራ አመራር ኮሚቴ የመምሕሩን ኃሳብ ቅቡል በማድረግ  ከትምሕርት ክፍሉም ጋር በመነጋገር መምሕራን ተመድበው  ኮርሱ ይሰጥ ዘንድ ተወሰነ።

በተከታታይ ቀናት ለአንድ ወር  የሰንበት ት/ቤቱ ነባር አባላት የሚሰጡትን ትምሕርቶች ተምረው ልክ የዛሬ ሠላሳ አንድ ዓመት  መስከረም 13 ቀን 1988ዓ.ም  በምስክር ወረቀት ተመርቀዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ባለፈው ክረምት(2018 ዓ.ም) ድረስ ላለፉት ሠላሳ አንድ  ዓመታት ባለማቋረጥ በርካታ ደቀ መዛሙርት የሚሰጡትን ኮርሶች ተከታትለው ተመርቀዋል።ወደፊትም በአዲሱ ሥርዓተ ትምሕርት መሠረት ኮርሱ  ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን። 

ተወዳጆች ሆይ!!!

ሶየዕለቱን ታሪክ ለማስታወስ ይህን ያህል ካወጋናችሁ ዘንዳ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለውድ  አንባብያን  በማቅረብ፤  እኛ ኃላፊነት እንደሚሰማው እንደ አንድ የሰንበት ት/ቤት አባል ዕለት ከዕለት የሚያስጨንቀንን ጉዳይ በተመለከተ ጥቆማን በመስጠት እንሰነባበት። 

👉 የመጀመርያውን ኮርስም ሆነ ከዚያ በኋላ  በየጊዜው የተሰጡትን ኮርሶች ተከታትላችሁ የተመረቃችሁ አባላት ስንቶቻችሁ ኮርስ መማራችሁን፣ የተማራችሁበትን ወቅት እና የተመረቃችሁበትን ቀን ታስታውሳላችሁ??? ከሆነ እስኪ ንገሩን።

👉 መማራችሁ  በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወታችሁ ላይ ምን ዓይነት ዕሴት ጨመረላችሁ?
መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ "አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር።ከማን እንደተማርኸው ታውቃለህና  "2ኛ ጢሞ. 3፥14።

👉 እናንተስ ተምራችሁ ያገኛችሁትን መንፈሳዊ ዕውቀት ለሌሎች የቃሉ ጥማት ላለባቸው ወገኖቻችሁ በማካፈል የተጣለባችሁን አደራ ተወጣችሁ???
ወይስ መክሊታችሁን በመቅበር አደራችሁን በልታችሁ ቀራችሁ???

👉 የነፍስ ምግብ  የሆነ ቃሉን  እየመገበች፣ የሕይወት ውኃን እያጠጣች ያሳደገቻችሁን(ሰው ያደረገቻችሁን)  እናት የሰንበት ት/ቤታችሁን(ፍሬ ሃይማኖትን) ስንቶቻችሁ ከአንገት በላይ ሳይሆን ከልብ ታስታውሷታላችሁ??? ስትጠሩ(ስትለመኑ) ሳይሆን  ራሳችሁ አስባችሁና ፈልጋችሁስ ትጠይቋታላችሁ??እየመጣችሁስ በተሰጣችሁ ጸጋ ታገለግላላችሁ???

👉 በደሞዝ እና በልዩ ልዩ ሥጋዊና ምድራዊ ጥቅም ሳይሆን በነጻ ያስተማሯችሁ  መምሕራንንስ ታስታውሷቸዋላችሁ???
መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ።የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በዕምነታቸው ምሰሏቸው"ዕብ. 13፥7።

በስተመጨረሻም በጣም አሳሳቢና አስቸኳይ መፍትሔ የሚያሻውን ጉዳይ ጠቁመናችሁ ነገራችንን እንቋጭ።

ቀደም ብለን ለመግለጽ እንደሞከርነው በሰንበት ት/ቤታችን ኮርስ የተማረው  ቁጥሩ የትየለሌ ቢሆንም ቅሉ በዚህ ወቅት ከህጻናት፣ከአዳጊዎች፣ከኮርሰኞች(ከቀዳማይ፣ከካልአይ ወዘተ) ክፍሎች  በመቀጠል ነባር አገልጋይ አባላትን የሚያካትተው ዋናው ጉባዔ  እጅጉን እየተዳከመ ሄዶ  የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ስንናገር ልባችን በኃዘን ተሰብሮ ነው።

ችግሩ  ከቀደምት አባላት(ከጎልማሶች ጀምሮ) እስካሁኖቹ ድረስ  ሁሉንም የሚያሳስብ ጉዳይ መሆኑ አያጠራጥርም።

ስለሆነም፦ እገሌ ከእገሌ ሳንባባል ሁላችንም የመፍትሔው አካል ልንሆን ይገባል ብለን እናምናለን።በዚህ ከቀጠለ መጻዒው ጊዜ ለሰንበት ት/ቤታችን እጅግ በጣም አስቸጋሪ  ነው የሚሆነው።

አብዝታችሁም ስለ ፍሬ ሃይማኖት ጸልዩ።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
አሜን።

ተጻፈ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ማለዳ  2:00 ሰዓት።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የጊዜ ባለቤት፣  የዘመናት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ  አደረሳችሁ አደረሰን

የመስቀል ደመራ በዓል ታሪክና አከባበር


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከወደቀበት መርገም ያድነው ዘንድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በ33 ዓመቱ በራሱ ፈቃድ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ በመገረፉ ቁስል እኛ ተፈወስን (1ጴጥ 2፥24)::

በስቅለቱም ዲያብሎስን ድል ነስቶ በወህኒ /በሲዖል/ ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው (1ጴጥ 3፥18-19):: የሰው ልጅ በሙሉ ከዲያብሎስ ባርነት ፍጹም ነጻ ወጣ:: ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ ሕዝብና አሕዛብን በአንድ አካል ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ (ኤፌ 2፥16)፡፡

ከፍተኛ ወንጀል የሠሩ ሰዎች ብቻ ይሰቀሉበት የነበረው መስቀል ከጌታ ስቅለት በኋላ የመዳን ምልክት ሆነ::ዳሩ ግን ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ተአምራትን በማድረጉ የታወኩ አይሁድ መስቀሉን ከሰዎች እይታ ለመሠወር ወሰኑ:: ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት::

መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለ300 ዓመታት ያህል የቆሻሻ መጣያና ማከማቻም አደረጉት:: ምንም እንኳን አይሁድ ለጊዜው መስቀሉን ከዐይን ለመሰወር ቢችሉም ከክርስቲያኖች ልቡና ግን ሊያወጡት አልቻሉም:: የመስቀሉ ብርሃን በልቡናቸው የሚያበራ ክርስቲያኖች እየበዙ መጡ:: መስቀሉንም መፈለግ ጀመሩ::

የንግሥት እሌኒ ድካምና ፍሬ

ንግሥት እሌኒ ልጇን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለ ክርስትና ሃይማኖትና ስለ ክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ 

ቆስጠንጢኖስ የሮም ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነች፡፡ ንግሥት እሌኒም የተፈጠረውን አመች ሁኔታ በመጠቀም የጌታችንን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡

ንግሥት እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነፅ ለልዑል እግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ327 ዓ/ም ተጠመቀ፡፡ ቅድስት እሌኒም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች እንደደረሰችም ስለ ክብረ መስቀል መረመረች ጠየቀች፡፡ ቦታውን የሚያስረዳት ግን አላገኘችም፡፡ አይሁድ የተቀበረበትን ቦታ ለማሳየት ባይፈልጉም በኋላ ባደረገችው ጥረት አረጋዊው ኪራኮስ የጎልጎታን ኮረብታ አመላከታት ዳሩ ግን ኪራኮስ ዘመኑ ከመርዘሙ ጋር ተየይዞ በአካባቢው ከነበሩት ከሦስቱ ተራሮች ውስጥ መስቀሉ የሚገኝበት የትኛው እንደሆነ ለይቶ ማወቅ አልቻለም፡፡

ንግሥት እሌኒ ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት በእግዚአብሔር መልአክ እርዳታ ደመራ አስደምራ ብዙ እጣንም በመጨመርና በማቃጠል ጸሎት ተያዘ፡፡ የእጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ተራራ ላይ በማረፍና በመስገድ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ ቅዱስ ያሬድም ጢሱ ሰገደ ብሎታል፡፡

ከዚያም መስከረም 16 ቀን ቁፋሮው እንዲጀመር አዘዘች፡፡ ሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት 10 ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡የክብር ባለቤት ጌታችን የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ተቸገሩ፡: መስቀሎቹንም ወስደው የሞተ ሰው በየተራ ቢያስቀምጡባቸው ጌታችን  በዕለተ ዐርብ ተሰቅሎ የዋለበትና በደሙ መፍሰስ የተቀደሰው መሰቀል የሞተውን ሰው በማስነሣት በሠራው ተአምር ሌሎቹ ሁለቱ ተአምራት ባለማድረጋቸው የጌታን መስቀል ለይቶ ማወቅ ተችሏል።

እሌኒና ክርስቲያኖች ሁሉ ለመስቀሉ ሰገዱለት፡፡ በየሀገሩ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉ የመስቀሉን መገኘት በሰሙ ጊዜ መብራት አብርተው ደስታቸውን በመግለጥ ለዓለም እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ ንግሥት እሌኒ ለመስቀሉ ቤተ መቅደስ ከሠራችለት ጊዜ ጀምሮ በመስከረም 17 ቀን አሁን በኢትዮጵያ እንደሚከበረው በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል ይከበር ነበር።

ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? 

የጌታ መስቀል ለብዙ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከቆየ በኋላ ነገሥታት መስቀሉን ለመውሰድ ጠብ ፈጠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የአንጾኪያ፣ የኤፌሶን፣ የአርማንያ፣ የግሪክ፣የእስክንድርያ፣ የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት:: ከዚያም አያይዘው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስን መስቀል ለዐራት ከፍለው በስምምነት በመካፈል ከሌሎች ታሪካዊ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት:: የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋየ ቅድሳት ጋር በግብፅ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡

፡ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት የግብፅ ክርስቲያኖች በአማሌቃውያን ከሚደርስባቸው ተጽዕኖ ነጻ እንዲወጡ በማድረጋቸው የግብፅ ፓትርያርክ የከበሩ ስጦታዎችን ላኩላቸው:: ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ወርቅ ሳይሆን ጌታ የተሰቀለበት መስቀሉን እንደሆነ ገለጹላቸው:: በመሆኑም የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግማደ መስቀሉን ከሌሎች ንዋየ ቅድሳት ጋር ለኢትዮጵያ ሰጥታለች:: ይህ ግማደ መስቀል በግሸን ማርያም ገዳም በቅዱስ  በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ኢትዮጵያን እየባረከ ይገኛል::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መስቀልን ከሐዋርያት በተማረችው መሠረት የወርና የዓመት በዓል ሠርታ ታከብረዋለች:: መስከረም 16 ቀን ደመራ ደምራ ጸሎትና ምሥጋና ታቀርባለች። ቅዱስ መስቀሉ ከተቀበረበት መሬት በእሌኒ አማካኝነት መገኘቱን ስታስብ በአሁኑ ዘመን ከብዙ ሰዎች ልቡና የተሠወረው መስቀል እንዲገለጥላቸውም ትጸልያለች:: በመስቀል የሚገኘውን በረከት እየተቀበለች በመስቀል የሚመሰለውን መከራ ሁሉ ትታገሣለች:: መስቀል በካህናት፣ በምእመናንና በምእመናት ልቡና ተስሏል:: በአንገታቸውና ልብሳቸውም መስቀል አለ::

ሥራ ሲጀመርና ምግብ ሲቀርብ በመስቀል አምሳያ ይማተባል:: መስቀል ለሁሉም ነገር መጀመሪያና መጨረሻ  ነው:: “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” (ማቴ 16፡24) እንዳለ ጌታችን ቤተ ክርስቲያናችን ዕለት ዕለት መስቀሉን ትሸከማለች።

«የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚብሔር ኃይል ነው» (1ቆሮ 1፥18) እያልን ልናከብረውና ልንጠብቀው ይገባናል።

በረከተ መስቀሉ በሁላችንም ላይ ይደርብን።

መልካም በዓል ይሁንልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር።

አሜን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

📢 ለሰንበት ት/ቤት አባላት እና ወጣቶች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ!
"መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው"
                         (ማቴዎስ 9:37)

የ2019 ዓ.ም የአገልግሎት ማስጀመሪያ ጉባኤ እና የአዲሱ የሰንበት ት/ቤት አስፈጻሚዎች የትውውቅ ጉባኤ ስለተዘጋጀ ሁላችሁም እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በዕለቱ፦
✝️ በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ  የሚሰጥ ቡራኬ
✝️ የአዲሱ አመራር አባላት (አስፈጻሚዎች) ማስተዋወቅ
✝️ ትምህርተ ወንጌል በመምህር አንተነህ አሽናፊ
✝️ መዝሙር በዘማሪት ሰላማዊት መላኩ እና በሰንበት ት/ቤቱ መዘምራን
✝️በዕለቱ ከቀዳማይ የቀን እና የማታ እስከ ሳድሳይ ያላችሁ ተማሪዎች የአመቱ ማጠቃለያ የምርቃት ቀናችሁ ስለሆነ እዛው  እንገናኝ::

📅 መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም
⏰ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ
📍 በደብሩ ደጀ ሰላም


በጋራ ለአገልግሎት እንነሣ! እርስ በርሳችሁ እየተጠራራችሁ ተገኙ።

አምላከ ቅዱሳን አገልግሎታችንን ይባርክልን። አሜን።