Fontenina - ቁም ነገር
1.19K subscribers
71 photos
1 video
6 links
Media Service
Download Telegram
ልብ ብለዉ ያንብቡት

3 ዛፎች ነበሩ ። 2ቱ የቆሙ ሲሆኑ አንዱ ግን
ወድቋል። ከእለታት አንድ ቀን እኚህ ዛፎች
የህይወት ህልማቸውን ይነጋገሩ ጀመር ።
አንደኛው ዛፍ " እኔ ሳጥን ሆኜ የአለም ውድ
እቃዎች እንዲቀመጡብኝ ጥልቅ ምኞቴ ነው " አለ፣
ሁለተኛውም ቀበል አድርጎ " እኔ መርከብ ሆኜ
የአለም ነገስታት እንዲጓጓዙብኝ እንዲፈንጩብኝ
እፈልጋለው" አለ ፣ ሶስተኛው ደግሞ " እኔ
መድሀኒት ሆኜ ብዙዎችን ማዳን ከቻልኩ ከዛ በላይ
ምንም ኣልፈልግም" አለ ።
ሶስቱም ህልማቸውን አውርተው ሲጨርሱ ዛፍ ቆራጮች
መጡ፡ የወደቀውን ይዘውት ሄዱ ።
እሱም ሳጥን መሆን የህይወት ፍላጎቱ ቢሆንም
ጠርበው የከብቶች መመገቢያ አድርገው ሰሩት።
ሁለተኛውንም መጥተው ቆረጡት ለጀልባነትም
አዋሉት፡ መርከብ የመሆን ምኞቱም ባክኖ ቀረ።
ሁለቱም ዛፎች ተናደዱ ህልማቸው የተጨናገፈም
መሰላቸው። ሶስተኛው ዛፍም ለምንም አገልግሎት
ባለመዋሉ እጅጉኑ አስከፋው።
ከአመታት በኋላ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አለም መጣ።
እነሆ በ ቤተልሄም ቦታ ስላልነበር በከብቶች በረት
ተወለደ። እናቱ ማርያምም በከብቶች መመገቢያ
ውስጥ ጠቅልላ አስቀመጠችዉ። የአለም ውድ ነገሮች
ማስቀመጫ መሆን የፈለገው ዛፍም የውዶች
ውድ የእንቁዎች አንቁ የሆነው ክርስቶስ
ተቀመጠበት።
ጌታም ሊያስተምር ሲሄድ በታንኳ ተጓዘ ፡ ያም
ታንኳ ያ የአለም ነገስታት እንዲጓዝብኝ እፈልጋለው
ያለው ነበር፡ የነገስታት ንጉስም ተጓጓዘበት። ጌታችን
እንዲሰቀል ሲፈረድበት የቀረውን ዛፍ
ቆርጠው አመጡ በሱም ሰቀሉት። ለብዙዎች
መድሀኒት መሆን የፈለገው ዛፍ መስቀል ሆኖ አለም
ሁሉ ዳነበት።
ሶስቱም ዛፎች ህልማቸው የተጨናገፈ ሲመስላቸው
ፈጣሪ ግን ካሰቡት በላይ አደረገላቸው። ወዳጆቼ ለእኛም
ከራሳችን በላይ የሚያስብልን
አምላክ አለን። ስለዚህ ህልማችን የተጨናገፈ
ቢመስለን አምላክ አብዝቶ ሊሰጠን ስለሆነ ሁሌም በ
ትዕግስት እንጠብቀው።
ለጓደኞቻችሁ share share በማድረግ አድርሱ
==========================
ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን ነገሮች
=================================
በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮችን ማጥፋት (Airplane Mode ላይ ማድረግ) (ምክንያቱም ራዲየሽኑ መብረቅ ይስባል) | off wi-fi | Bluetooth | Main Network

FM(ኤፍ.ኤም) በEarphone አለማዳመጥ | ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደ አንቴና ነው የሚጠቀሙት - ስለዚህ በኢርፎን ስናዳማጥ Eectromagnetic ራዲየሽኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል።

ስልክን Charge እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይም | አለመደዋወል - Calling | Wifi አለመጠቀም | Gaming - ጌም አለመጫወት።

በEarphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ (ምክንያቱም በNormal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል - የHz አለመጣጣም።

ትልልቅ Magnet (Magnetic field) ያላቸው ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁን አታስቀምጡ።

⚠️ የስልክ ስክሪን Blue Light የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን Brightness መቀነስ / Blue Light Filter App መጠቀም።

የባትሪ ቻርጅ በጣም Low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ | ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል።

ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ | ቢያንስ ከ5 Centimetre በላይ ራቅ ማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡

የሞባይል ስልኮን ታቅፈው አይተኙ | በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 metre በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው Electromagnetic ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ፡፡

ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ | የጽንሱ ሕዋሳት ለElectromagnetic radiation እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው | ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን | አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለበዎት፡፡

ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል አይጠቀሙ | ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል | ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ | የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡

በተለይ!!! በተለይ!!! ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል | ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡

በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው | ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው | ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡

ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት፡፡

Smartphone አብዝተን ስንጠቀም የሚመጣው በሽታ
-Premature Death
-Diabetes
-Heart disease
-የተለያዩ የCancer በሽታዎች
-Discomfort
-Musculoskeletal Symptoms

ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የራሱም የሆነ ከፍተኛ ጉዳት አለው ስለዚህ በተቻለን መጠን የSmartphone አጠቃቀማችንን እንቀንስ የዛሬው መልዕክታችን ነው።

Join our telegram channel here it is(የተለግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ)
https://t.me/fontenina2018
የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል
=====================
0. - አልቦ
1. ፩ አሐዱ
2. ፪ ክልኤቱ
3. ፫ ሠለስቱ
4. ፬ አርባዕቱ
5. ፭ ሐምስቱ
6. ፮ ስድስቱ
7. ፯ ስብዓቱ
8. ፰ ስመንቱ
9. ፱ ተሰዓቱ
10. ፲ አሠርቱ
11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ
12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ
13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ
14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ
15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ
16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ
17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ
18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ
19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ
20. ፳ እስራ
21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ
22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ
23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ
24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ
25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ
26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ
27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ
28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ
29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ
30. ፴ ሠላሳ
31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ
32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ
33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ
34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ
35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ
36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ
37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ
38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ
39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ
40. ፵ አርብዓ
50. ፶ ሃምሳ
60. ፷ ስድሳ
70. ፸ ሰብዓ
80. ፹ ሰማንያ
90. ፺ ተሰዓ
100. ፻ ምዕት
101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ
102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ
103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ
104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ
105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ
106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ
107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ
108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ
109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ
110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ
111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ
114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ
115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ
119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
120. ፻፳ ምዕት ወእስራ
130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ
140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ
150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ
160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ
170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ
180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ
190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ
200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት
201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ
202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ
203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ
204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ
205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ
206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ
207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ
208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ
209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ
210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ
211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ
214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ
215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ
230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ
240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ
250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ
260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ
270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ
280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ
290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ
300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት
400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት
500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት
600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት
700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት
800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት
900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት
1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት
2000. ፳፻ እስራ ምዕት
#Share
Join ☞t.me/fontenina2018
ስለ እርግዝና ያልተሰሙ አስደናቂ እውነታዎች

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ #share በማድረግ ይተባበሩን!

1. የጠዋት ሕመም (morning sickness) የሚባለው ሁሌ ጠዋት የሚከሰት አይደለም፡፡ ብዙ ሴቶች ቀኑን ሙሉ አንዳንዶች ድግሞ ጠዋት፣ግማሽ ቀን ወይም ማታ ስሜቱ ሊታያቸው ይችላል፡፡

2. እረጃጅምና ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች መንታ ልጅ የመውለድ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ከቤተሰብ ውስጥ መንታ የወለደ ሰው ካለና ዕድሜዎት ከ35 በላይና ረጅም ከሆኑ መንታ ልጅ የመውለድ ዕድል አልዎት፡፡

3. የደም መጠኖ ይጨምራል፡፡ በልብዎ የሚሰራጨው የደም መጠን ከ40 እስከ 50 በመቶ ይጨምራል፡፡

4. የልብዎ መጠን በእርዝመትም በወርድም ይጨምራል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተጨማሪ ደም ለመርጨስ ሲል ይለጣጣል፡፡

5. እርግዝና ከተከሰተበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ጡት ወተት ለማምረት ይዘጋጃል::

6. ልጅዎ ይሰማዎታል፡፡ ጆሮ ቀደም ተብለው ከሚሰሩት የህፃኑ አካለት አንዱ ሲሆን ልጅዎም የእለት ተዕለት ንግግሮን ይሰማል፡፡ በተለይ ከ6 ወራት ጀምሮ ብቻዎን ስላልሆኑ ልጅዎን ያናግሩ፡፡

7. ልጆ ከእርስዎ ቀድሞ ይበላል፡፡ ማንኛውም የሚመገቡት ቫይታሚንና ማእድናት ልጆ ከተጠቀመ በኃላ ነው የቀረው ወደ እርሶ የሚደርሰው፡፡ ለዚህም ነው በእርግዝና ጊዜ ጥሩ ጥሩ ነገር መመገብ ለልጆ ጤንነት ወሳኝ ነው የሚባለው፡፡

8. በእርግዝና ጊዜ ምግብ ቀስ ብሎ ወደ ትንሹ አንጀት ስለሚሄድ ሆድ በጋዝ ሊሞላ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአይነምድር ድርቀት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ስለሆነም ለብ ያለ ውሃ በብዛት መጠጣት ሊያስታግሰው ይችላል፡፡

9. የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል፡፡ይሕ ማለት ዕርግዝናው ጤናማ እስከሆነ ብቻ ነው፡፡፡ ውስብስብ የሆነ እርግዝና ከሆነ ግን ሐኪም ማማክር ግድ ይላል፡፡ ህፃኑ በእንሽርት ውሃ ውስጥ ስከለሚሆን ከመራቢያ አካል ጋር ግንኙነት ስለማይኖረው ወሲብ መፈፀም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. ጫማሽ ላይበቃሽ ይችላል፡፡ እግርሽ በሆርሞን ምክንያት ስለሚጨምርና ስለሚያብጥ ጨማዎችሽ ላይበቁሽ ይችላሉ፡፡

11. ሴት ልጅ ካረገሽ በህፃኗ ማህፀን ውስጥ እንቁላል ከዚህ ወቅት ጀምሮ መፈጠር ይጀምራል፡፡ ስለሆም የልጅ ልጅሽን እንደተሸከምሽ ልታስቢ ይገባል፡፡ ወንድ ልጅ ከሆነ ግን ስፐርም አይኖረውም፡፡ ስፐርም የሚፈጠረው በረአፍላ ዕድሜው ላይ ሲደርስ ነው፡፡

12. የእንግዴ ልጅ ከእናቱ ወደ ልጁ ምግብ ለማስተላለፍ ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ልጁን ከባክቴሪያና ከኢንፌክሽን ይጠብቃል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ #share በማድረግ ይተባበሩን!
ምግቦች ለመፈጨት የሚወስዱት ጊዜ
---------------------------------
(ሌሎምችም ይወቁት ሼር አድርጉት)
1. የወተት ውጤቶች 120 ደቂቃ
2. የበሬ ስጋ 180 ደቂቃ
3. የዶሮ ስጋ ከ90-120 ደቂቃ
4. አሳ ከ45-60 ደቂቃ
5. ድንች ከ90-120 ደቂቃ
6. ፍራፍሬ ከ15-20 ደቂቃ
7. አትክልት ከ30-40 ደቂቃ
8. የተቀቀለ አትክልት 45 ደቂቃ
9. ለውዝ/ ኦቾሎኒ 180 ደቂቃ
---
Channel name was changed to «Fast Info - ፈጣን መረጃ»