Fontenina - ቁም ነገር
1.19K subscribers
71 photos
1 video
6 links
Media Service
Download Telegram
የአሸናፊዎች እና የሰነፎች ልዩነት


ሰነፎች ሁሌም ነገሮችን ለመለወጥ የሆነ ነገር መደረግ አለበት ይላሉ፤ አሸናፊ አይምሮ ያላቸው ደግሞ እኔ ይሄን ማድረግ አለብኝ ይላሉ።

ሰነፎች ሁሌም አስተያየት ሰጪዎች ናቸው ተግባር ላይ የሉበትም፤ አሸናፊዎች ግን የሚያውቁትንና የሚያምኑበትን ተግባራዊ ሳያደርጉ አያርፉም።

ሰነፎች የምክንያትና የሰበብ ሀብታሞች ናቸው፤ አሸናፊዎች ግን የመፍትሄና የለውጥ ባለፀጋ ናቸው።

ሰነፎች ብዙ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ስለ ትናንት እና ስላለፈ ነገር አብዝቶ በማሰብ ነው፤ አሸናፊዎች ግን ከትናንት ተምረው ዛሬን ያጣጥማሉ ነገን አስቀድመው ያቅዳሉ።

እነዚህ ፀባዮች በተፈጥሮ የተሰጡን አይደሉም፤ በጊዜ ሂደት እያዳበርን የመጣናቸው ናቸው። ስለዚህ ምርጫችን አሸናፊ መሆን ከሆነ ከላይ ያሉትን አመለካከቶች ፀባያችን እንዲሆኑ ዋጋ መክፈል አለብን።