Fontenina - ቁም ነገር
1.19K subscribers
71 photos
1 video
6 links
Media Service
Download Telegram
ምግቦች ለመፈጨት የሚወስዱት ጊዜ
---------------------------------
(ሌሎምችም ይወቁት ሼር አድርጉት)
1. የወተት ውጤቶች 120 ደቂቃ
2. የበሬ ስጋ 180 ደቂቃ
3. የዶሮ ስጋ ከ90-120 ደቂቃ
4. አሳ ከ45-60 ደቂቃ
5. ድንች ከ90-120 ደቂቃ
6. ፍራፍሬ ከ15-20 ደቂቃ
7. አትክልት ከ30-40 ደቂቃ
8. የተቀቀለ አትክልት 45 ደቂቃ
9. ለውዝ/ ኦቾሎኒ 180 ደቂቃ
---
Channel name was changed to «Fast Info - ፈጣን መረጃ»
የመረጃ ማፈላለጊያዎችን #browsers ስንጠቀም ማድረግ ያለብን የጥንቃቄ ርምጃዎች

• የመረጃ ማፈላለጊያዉን ታሪክ(browsing history) ማጥፋት

• ደረ-ገፆችን በኤችቲቲፒኤስ #HTTPS ማገናኘት

• የመረጃ ማፈላለጊያዉን በየጊዜው ማደስ #update

• የተለያዩ የይለፍ-ቃሎችን በብሮዉዘሩ ላይ አለማስቀመጥ

• ዶክመንት ከማውረዳችን በፊት ጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መጫንና አባሪዎችን መቃኘት #scan ማድረግ

• ለተለያዩ አካውንቶች ተመሳሳይ የይለፍ-ቃል አለመጠቀም

• የህዝብ ወይም ነፃ ዋይፋይ አለመጠቀም

• የመረጃ ማፈላለጊያውን ፖፕአፕ #pop up ብሎከር ማብራት/መክፈት

• የመልእክት ማንቂያዎች ላይ መመዝገብ #register on alerts

Ethio ICT
ሶፍትዌር ዳውንሎድ ሲያደርጉ serial key ለማግኘት 5 ቅደም ተከተሎችን ይተግብሩ።
============================
step1. ወደ www.google.com እንሄዳለን።

step2. የምንፈለገውን ሶፍትዌር ስም ሰርች ቦክስ ውስጥ እንፅፋለን።

step3. ከዚያም በማስከተል ሰርች ከማድረጋችን በፊት ከፃፍነው የሶፍትዌር ስም አጠገብ 94FBR ብለን እንፅፋለን። ለምሳሌ፡- IDM 94FBR

step4. ከዚያም Search በተንን ይጫኑ።

step5. በመጨረሻም serial key የያዙ ብዙ ዌብ ሳይቶችን እንደምርጫ ይመጣሎታል ከዚያም የፈለግነው ሳይት ውስጥ በመግባት የፈለግነውን serial keys ማግኘት እንችላሉ፡፡
መልካም ቀን ይሁንልዎ
የትምህርት ፍቅር…

የ53 ዓመቱ አባ ዘውገ በቀለ ሙላቴ አዲስ አበባ በቃሊቲ ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በማታው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሲከታተሉ የቆዩና የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የወሰዱ ናቸው።

የ65 ዓመቷ ወይዘሮ ወርቅነሽ ወንበራ በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ኔሪ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማታው ክፍለ ጊዜ የ8ኛ ክፍል ተማሪና ተፈታኝ ናቸው።

@fontenina2018
ዝንጀሮው፤አንቃቂ ንግግር ከሰማ በኋላ...
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
<<ለዚህ የደረስነው ኢትዮጵያ ኖራ ስላስተማረችን ነው ሃገራችን ኖራ ስላስተማረችን ነው። እየተሸከሙ ያስተማሩ እናቶች ነው ያሉን እየታገሉ ያስተማሩ እናቶች ነው ያሉን ዛሬ እንዲህ አምሮብን ዛሬ አጊጠን ዛሬ ለብሰን ስንታይ ብርቱዎች ሆነን ሳይሆን ብርቱ የሆኑ እናቶች ስላሉን ነው!>>

የዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ
“የዕድሜዬ መግፋት ከትምህርት ፍላጎቴ አላስቀረኝም” የ70 ዓመቱ አዛውንት ተመራቂ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ካስመረቃቸው ተመራቂዎች መካከል የ70 ዓመቱ ተመራቂ አዛውን የበርካቶችን ቀልብ የሳበ መሆኑ ተነግሯል።
የ70 ዓመቱ አዛውንት አቶ ዓሊ ሳፋ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲው የ9ኛ ዙር ተመራቂዎች ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከ35 ዓመት በፊት እንዳገኙ ያስታወሱት አዛውንቱ፣ ለትምህርት ባላቸው ፍቅር የተነሣ የዕድሜያቸው መግፋት ሳይገድባቸው በ70 ዓመታቸው ዛሬ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ለመቀበል መብቃታቸውን ገልጸዋል።
“የዕድሜዬ መግፋት ከትምህርት ፍላጎቴ አላስቀረኝም” ያሉት አቶ ዓሊ ሳፋ፣ ስምንት ልጆች እና አራት የልጅ ልጆች አያት መሆናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከባለሥልጣን ቤት ንብረት የዘረፈችው የቤት ሠራተኛ ጠንቋይ ቤት ተያዘች!! ቢቢሲ

የኬንያ ፖሊስ እንዳለው በስርቆት ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር የዋለችው ሚሪያም ሙዌሉ የተባለችው ይህች የቤት ሠራተኛ “ታዋቂ ከሆነው” ጠንቋይ ቤት “ከእስር ያስመልጣል” የተባለለትን መተት ለማግኘት ተፍተፍ ስትል እጅ ከፍንጅ ይዣታለሁ ብሏል።

ተጠርጣሪዋ ግምቱ ከ33 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጣ ጥሬ ገንዘብ እና ውድ ጌጣ ጌጦችን ከዘረፈች በኋላ ለሦስት ሳምንታት ብትሰወርም መርማሪ ፖሊስ ሴቲቱን በጠንቋዩ ቤት በስርቆት ወንጀሉ ከተባበራት ግብረ አበሯ ጋር በቁጥጥር ሥር እንዳዋላት አሳውቋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክር፣ በእድሜ የገፉት ጠንቋይ የፖሊስ አባላቶቹ ለማሸሽ ይረዳል ያሉትን የመተት ቃላት ቢደረድሩም፤ ሕግ አስከባሪዎች ግን ተልዕኳቸውን ከመወጣት አላገዳቸውም ብሏል በመግለጫው።

የኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት በሕግ የሚፈለጉ ሰዎች ጥንቆላ ከሕግ ተጠያቂነት ስለማያስመልጣቸው ጊዜያቸውን እንዳያባክኑ አሳስቧል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል