Fontenina - ቁም ነገር
1.19K subscribers
71 photos
1 video
6 links
Media Service
Download Telegram
ተአምረኛው ዲማ ...

በኢትዮጵያ፣ ነገሌ ቦረና፣ ጎብቻ ቀበሌ ውስጥ ከ32 ዓመት በፊት ሞቷል ተብሎ ወዳጅ ዘመድ እርሙን ያወጣለት ሰው፣ 'አለሁ' ብሎ የቤተሰቦቹን ደጃፍ አንኳክቷል።

ዲማ ዶዮ ቦሩ ይባላል በነገሌ ቦረና ነው ነዋሪነቱ በ1982 ዓ.ም. በወቅቱ አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት ለብሔራዊ ውትድርና በግዳጅ አብረውት ከ100 የማያንሱ ወጣቶች ለጦርነት ይወሰዳል።

ከዘመተ በኋላ ቤተሰቦቹ የሰሙት ወሬ በሐዘን ማቅ እንዲለብሱ አደረጋቸው፤ ወላጆቹ በነበረው ጦርነት ላይ ጓደኞቹ መሞታቸውን፣ ዲማ ደግሞ መቁሰሉን ነበር የሰሙት፤ በእርግጥ ልጃቸው ስለመሞቱ ከማንም ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አላገኙም።

ዲማ በወታደርነት በግዳጅ እንዲዘምት ሲደረግ አላገባም፤አልወለደም ነበር። ለዓመታት ድምፁ የጠፋው ዲማ ያፈራቸውን ንብረቶች፣ ከብቶች ቤተሰቡ ተከፋፈለ።ታዲያ ይህ ሁሉ ከሆነ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ነበር ዲማ ቤተሰቦቹን ፈልጎ የመጣው።

በብዙዎች ዘንድ እንደ ተዓምር የሆነው ዲማ ብዙዎች ቤተሰቦቹ ዘንድ እየመጡ የቤተሰቡን ደስታ ከመጋራት ባሻገር ጥያቄም አላቸው።

ከ32 ዓመት በፊት አብረውት ዘምተው የነበሩ የአካባቢው ወጣቶች፣ዛሬም በሕይወት ካሉ ለማረጋገጥ የሚፈልጉ መኖራቸውን የዲማ የወንድም ልጅ ይናገራል።

ዲማ ሞቶ አፈር ያላለበሱትን ልጅ ሞቷል ብለው እርማቸውን ለማውጣት የተቸገሩት እናት፥ሞቷል እርሺው ሲሉኝ እሺ አላልኩም ነበር፤ እንደ ሞተ አይሰማኝም ነበር፤ ይመጣል ብዬ አስብ ነበር ይላሉ።

ስንት ዓመቱ እንደነበር አላስታውስም የሚሉት እናት አብረን እየሄድን እያለ ነው መጥተው በጉልበት ነጥቀውኝ የወሰዱት እርሱ የመጣ ዕለት በደስታ ራሴን ስቼ ነበር፤እንደ ዐይናችን ብሌን የምንሳሳለት ልጅ ነበር በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።
እንኳን አደረሳችሁ