«በትግራይ ክልል የሚገኙ አብዛኞቹ ሆስፒታሎች ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለጸ»
በትግራይ ክልል ከነበረው ግጭት እና ከሕክምና አቅርቦት እጥረት ጋር ተያይዞ ተዘግተው የቆዩት አብዛኞቹ ሆስፒታሎች አሁን ወደ ሥራ መመለሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ።
የጤና ተቋማቱን አቅም ለማጠናከር እና አገልግሎቱን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተጨማሪ መድኃኒቶች ወደ ክልሉ በሂደት ላይ መሆናቸውን የተመድ ዋና ጸሐፊ ምክትል ቃል አቀባይ ፋርሃን ሃቅ ገልጸዋል።
በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ ክልሎች አሁንም ድረስ የሚታዩ የጸጥታ አለመረጋጋቶች በሲቪሎች እና በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆናቸውን የተገለጸ ሲሆን፣ የተመድ እና አጋር ድርጅቶች ግን ድጋፍ የማድረስ ሥራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተመላክቷል።
@FM_mereja

❤3
💔 ላመነበት ፍቅር ኖሮ አለፈ!
ለብዙ ዓመታት በማትመጣው ፍቅረኛው ናፍቆትና ጽናት፣ በከተማዋ መንገድ ዳር ቆሞ ሲጠብቅ የነበረውና ለታማኝ ፍቅር ምሳሌ የሆነው አቶ ለማ አረፈ።
ፀሐይ ሳይበግረው፣ ዝናብ ሳይበግረው ፣ ያለ ድካም ፍቅሩን በመጠበቅ የጽናት አርማ የነበረው አቶ ለማ፤ የታሪኩ አሳዛኝነት የብዙዎቻችንን ልብ ነክቷል።
ታማኝነቱና ፍቅሩ በብዙዎች ዘንድ ሲታወስ የሚኖር ሲሆን፣ የበርካታ ሰዎችን ልብ የነካው ታሪኩም ለዘላለም ሲነገር ይኖራል።

😭5❤2
2 ነጥቦች‼
📌"ምፅዋ ባዶዋን ቀርታለች አሰብም ሰው አልባ ሆናለች" ፡ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በትግርኛ የተናገሩት
📌 ''አብይ ከኤርትራ ጋር ያለውን ጉዳይ አሁን ካልጨረሰ እሱን ይጨርሰዋል ጉዳዩ'' ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ከሰሞኑ የሰጠው አስተያየት

አራት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በመቀሌ እንዳሉ ለጸጥታ ኃይሎች ሪፖርት አድርገዋል።
እነዚህም:-
1) ተክላይ ገ/መድህን - የህወሓት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፣
2) ሊያ ካሳ - የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል፣
3) ዶ/ር ጸጋዬ በሪሁ - የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የጤና ቢሮ ኃላፊ፣
4) ገብረ ኢሮብ - የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀመንበር መሆናቸው ታውቋል።

ትግራይ ለህውሃት ታጣቂዎች DDR ምዝገባ ማዕከላት ይፋ ሆነዋል።
ማዕከላቱ:-
📌 መቀሌ / እንደርታ
📌 እዳጋ ሐሙስ / አጋመ
📌 ዓቢይ ዓዲ / ተምቤን
📌 ዓዲ በራክ / ዓድዋ
📌 ሽሬ እንዳሥላሴ / ሽሬ መሆናቸውን የትግራይ ሰላም ኃይል አሳውቋል።

❤1🤣1
የድሮን ጥቃት
በማዕከላዊ ትግራይ ናዕዴር ወረዳ ሰማ ከተማ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም ከአምስት ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ በርካታ የህወሓት ታጣቂዎች መጎዳታቸው ታውቋል።
በትግራይ ክልል ተንቤን ጨምሮ በአንዳንድ አከባቢዎች በሚገኙ የህወሓት ታጣቂዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም አካባቢዎች ዘመቻ መጀመሩ ተሰምቷል።

❤2🤣1
ለአገራት እዳ የመክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ ተቋም ፊች፣ ኢትዮጵያ በዶላር የውጭ እዳዋን ለመክፈል ላላት አቅም "ሪስትሪክትድ ዲፎልት" የተባለውን ደረጃ ሠጠ።
ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ይህን ደረጃ የሠጣት፣ በዋናነት አገሪቱ የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ እዳዋን እስካሁን መክፈል ባለመቻሏ መኾኑን ገልጧል።
ኢትዮጵያ ከአብዛኞቹ የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎቿ ጋር ግንኙነቷ መስተካከሉን የጠቀሠው ፊች፣ ዓለማቀፍ ቦንድ ያዦች የዩሮ ቦንድ እዳዋን መልሠው እንዲያዋቅሩላት የጀመረችው ሂደት ሲጠናቀቅ የተሻለ የብድር ከፋይነት ደረጃ እንደሚሠጣት ጠቁሟል።
በትግራይ የተቀሠቀሠው ጦርነት፣ አገሪቱ ኢኮኖሚዋ እንዲያገግም በምታደርገው ጥረት ላይ ስጋት ሊደቅን ይችላል በማለት ድርጅቱ አስጠንቅቋል። 'ሪስትሪክትድ ዲፎልት'፣ ከፊል እዳቸውን ሳይከፍሉ ለቀሩና ከፊሉን በመክፈል ላይ ለሚገኙ አገራት የሚሠጥ ደረጃ ነው።

❤2
ኔታንያሁ ትናንት ምሽት የእስራኤልን አዲስ የጸጥታ መርህ ባብራሩበት ንግግራቸው ወቅት ይህንን ካርታ አሳይተዋል።
ካርታው በመካከለኛው ምስራቅ እየታየ ያለውን አዲስ የጂኦፖለቲካ ዳግም አሰላለፍ የሚያሳይ ሲሆን፣ ቀጣናውን በ3 ተፎካካሪ ጎራዎች ይከፍለዋል።
📌ቱርክን፣ ሳውዲ አረቢያን፣ ግብፅን እና ፓኪስታንን ማዕከል ያደረገ የሱኒ አሰላለፍ፤እና ኤርትራ፣ሱዳን፣የመንን የሱኒ ወዳጆች አድርጎ ገልጿል።
📌በኢራቅ፣ ሊባኖስ እና የመን በኩል የሚዘረጋ የኢራን ዘንግ፤
📌እንዲሁም ሰፊ የቀጣናው አጋሮች መረብ ያለው የእስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ኢትዮጵያን፣ RSF፣ሱማሊላንድ፣ፑንትላንድ አጠቃሎ የያዘ።
እነዚህ የግድ መደበኛ የወታደራዊ ጥምረቶች አይደሉም፤ ነገር ግን የቀጣናው ኃያላን አገራት ራሳቸውን እንዴት እያሰለፉ እንደሚገኙ የሚያሳይ ማሳያ ነው።

«ለቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች የመሬት ይዞታ መብት እና ጥቅማጥቅሞች መመቻቸታቸው ተገለጸ»
በየትግራይ ክልል አዲስ የወጣ ደንብ ለቀድሞ ተዋጊዎች እንደየተቀላቀሉበት ጊዜ የተወሰነ የመሬት መብት እና የተለያዩ ነፃ ጥቅማጥቅሞችን የሚሰጥ መሆኑ ተሰማ።
በደንቡ መሠረት በ2013 ዓ.ም. የተቀላቀለ 200 ካሬ ሜትር፣ ከሰኔ 22/2013 እስከ ታኅሣሥ 30/2014 ዓ.ም. የተቀላቀለ 175 ካሬ ሜትር፣ እንዲሁም ከጥር 1/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ደንቡ መጽደቅ ጊዜ የነበረ ተዋጊ 140 ካሬ ሜትር የመሬት መብት ያገኛሉ።
ለሠራዊቱ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በየደረጃው ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በመንግሥት የሚሸፈን የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ፣ ጫማ፣ ቲሸርት፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ምንጣፍ አቅርቦት ይደረግላቸዋል።
አባላቱ እነዚህን መብቶች የሚያገኙት «የትግራይ ሕዝብ ሰላም ዋስትና ለመሆን በተልዕኮ በመቆየት ሲቀጥሉ» ብቻ መሆኑ መደንገጉ፤ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር ከማቀላቀል እና ትጥቅ ከማስፈታት የፕሪቶሪያ ስምምነት ጋር የሚቃረን እና በወታደራዊ መስመር ለማቆየት የተሰራ ስሌት መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከጌታቸው ረዳ እና ከደብረጽዮን አንጃዎች ጋር በነበራቸው ተለዋዋጭ አቋም እና የውስጥ ፖለቲካዊ ውዝግቦች ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎች መውጣታቸው ተመላክቷል።

ህወሓት ሸሽጎት የነበረው አጥፍቶ ጠፊ የሆኑ በርካታ ድሮን በህዝብ ጥቆማ ተይዛል።
የመከላከያ ተወርዋሪ ከኮብ ኮር በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ቤተ ገበዝ በተባለ አካባቢ ከህውሃት ሃይሎች የተማረኩ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን ያመለክታል።
1. የካዛስኪ (Kazasky) ረጅም ርቀት ድሮን = 01
2. ትልቁ አጥፍቶ ጠፊ ድሮን = 49
3. ትንሹ አጥፍቶ ጠፊ ድሮን = 48
4. የድሮን ቅምቡላ = 61
5. የድሮን ራዳር/ጃም ማድረጊያ 01
6. የድሮን ላፕቶፕ = 04

እጅ የሚሰጡ ታጣቂዎችን ፎቶ አትለጥፉ ተብሏል‼
የህውሃት ታጣቂዎች ተቆርጠው በቀሩባቸው የትግራይ አካባቢዎች ልዩ የተባለው ኦፕሬሽን ለውጥ ማሳየቱ ታውቋል።
ከዛና እስከ ዓዴት ባሉት ቀጠናዎች በተካሄደው ኦፕሬሽን፦
📌ለጊዜው ስማቸው ያልተገለፀ 2 ከፍተኛ የህውሃት የፖለቲካ አመራሮችና እጅ ለመስጠት ያልፈቀዱ የተወሰኑ ተጣቂዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነግሯል።
📌ከ3,400 በላይ ታጣቂዎች በሰላም እጃቸውን ሰጥተዋል።
ቆላ ተንበን ጨምሮ በመከላከያና የትግራይ የሰላም ሃይል ኦፕሬሽኑ እየተካሄደ ነው ተብሏል።
አስተያየት ሰጭዎች እጅ የሚሰጡ ታጣቂዎችን ፎቶ መለጠፍ ሌሎችን ስለሚያስቀር አትለጥፉ ሲሉ መልዕክት አጋርተዋል።

❤4
በፈረንሳይ የተቀሰቀሰው አመጽ ለመግታት የሀገሪቱ ፖሊስ ድክመት በማሳየቱ ወታደሮች ሊሰማሩ መሆኑ ተነገረ
የፈረንሳይ መንግሥት በመላው ሀገሪቱ እየተቀጣጠለ በሚገኘው ሰፊ ሕዝባዊ አመጽን ወቅት ለመቆጣጠር እና የተቋማትን ደኀንነት ከመጠበቅ አኳያ ፖሊስ ጉድለቶችና ድክመቶች እንደነበሩበት በማመን በቀጣይ ለሚደረጉ ተቃውሞዎች ምላሽ ሀገሪቱ ወታደሮቿን ልታሰማራ መሆኑን አስታወቀች።
የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በፓሪስ እና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች በተከሰቱት ሁከቶች፣ ውድመቶችና ዝርፊያዎች ወቅት የጸጥታ ኃይሎች በቂና ፈጣን ምላሽ አለመስጠታቸው ስህተት እንደነበር ማመናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፈረንሳይ ወደፊት ከዚህ የከፉ ሁከት እና ወድመት ሊከሰት እንደሚችል በመገመት የመንግሥትና የሕዝብ ተቋማትን ለመጠበቅ እንዲሁም የፖሊስ ኃይልን ለማጠናከር በዋና ዋና ቦታዎች ላይ የታጠቁ ወታደሮችን ታሰማራለች። ፈረንሳይን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ሰራዊታቸውን በጸጥታ ስራ ላይ የሚያሰማሩት ከፖሊስ አቅም በላይ ከሆነ ብቻ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ በየአካባቢው የከተሞችን ሁኔታዎች ያገናዘበ የተወሰነ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ ምሽት ላይ ረብሻዎችን ለመቀነስና ሰላም ለማስፈን አጋዥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የአካባቢው አስተዳደሮች እንደየሁኔታው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ የሰዓት እላፊና የጸጥታ ቁጥጥሮችን የመጫን ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ፈረንሳይ ከዚህ ቀደም የታዩትን ሕዝባዊ አመጽ እና የሁከት ክስተቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነም ተገልጿል።

❤6
ኤል ሳልቫዶር የታገቱ ወታደሮቿን ለማስለቀቅ የሄይቲ የወንበዴ ቡድኖችን አስጠነቀቀች
በሄይቲ የወንበዴ ቡድኖች የታገቱትን አራት የኤል ሳልቫዶር ወታደሮች ለማስለቀቅ ሀገራቸው ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯን የኤል ሳልቫዶሩ ፕሬዝዳንት ናዪብ ቡኬሌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ወታደሮቻቸው በሕይወትና በጤና ካልተለቀቁ ጠንካራ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
እገታውን ፈጽመዋል የተባሉትን ቡድኖች በማስመልከት “ተግሳጻችንን እንደ ባዶ ዛቻ አትቁጠሩት፤ በኤል ሳልቫዶር የሚገኙትን የወንበዴ ቡድኖች እንደደመሰስን ሁሉ እናንተንም መደምሰስ እንችላለን” ብለዋል።
የወንበዴ ቡድኑ ከሶስት ቀናት በፊት የወታደሮች መኪና ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን፣ ይህም ባለፈው ዓመት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደግፈው ዓለም አቀፍ የፀረ-ወንበዴ ኃይል በሀገሪቱ ስራ ከጀመረ ወዲህ የተሰነዘረ የመጀመሪያው ትልቅ ጥቃት ሆኗል።
የሄይቲ መንግስት ረቡዕ ምሽት ባወጣው መግለጫ የታገቱትን ወታደሮች ማስለቀቅ “ቀዳሚ እና አጣዳፊ ተግባር” መሆኑን አስታውቋል።
የሄይቲ ባለስልጣናት የኤል ሳልቫዶር ወታደሮች በህይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ መስጠት ያልቻሉ ሲሆን፣ የዓለም አቀፉ የፀረ-ወንበዴ ኃይል ቃል አቀባይ ስለ ሁኔታው ለቀረበላቸው ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጡም።

በ1 ቢሊዮን ብር የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ክስ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (ELMIS) ፕሮጀክት ላይ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ 13 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ አጠናቆ ክስ ማስመሥረቱን አስታወቀ።
በዋና ተጠርጣሪው የቀድሞ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አለቃ አስገዶም እና ግብረ-አበሮቻቸው ላይ በተደረገው ምርመራ፦
📌 81,236 ዜጎች ያለሥልጠና ሕገ-ወጥ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) እንዲያገኙ ተደርጓል።
📌 64,500 ዜጎች በሐሰተኛ ቪዛ ወደ ውጭ ሀገር እንዲላኩ ተደርጓል።
📌በሕገ-ወጥ መንገድ የተሰበሰበ 1 ቢሊዮን 13 ሚሊዮን ብር፣ በባንክ የታገደ 249 ሚሊዮን ብር እና ወደ ክሪፕቶከረንሲ ተቀይሮ የነበረ 965,500 ዶላር በቁጥጥር ሥር ውሏል።
📌በቢሊዮኖች የሚገመቱ መኖሪያ ቤቶች እና የቅንጦት ተሽከርካሪዎች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።
ፖሊስ የወንጀሉን ምርመራ አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል። መረጃ ያላቸው ዜጎች በነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም በፌደራል ፖሊስ መተግበሪያ (EFPApp) ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

❤1
የፈረንሳይ ጤና ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም እንደ በጎች፣ ፍየሎችና ፈረሶች ባሉ የቤት እንስሳት ላይ ብቻ ይታይ የነበረው "ሻሞንዳ" የተሰኘው ቫይረስ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ መገኘቱን አስታውቋል።
በዋናነት በነፍሳት ንክሻ ወደ እንስሳት እንደሚተላለፍ የሚነገርለት ይህ ቫይረስ የተገኘበት ግለሰብ፣ አስቀድሞም የበሽታ መከላከል አቅሙ እጅግ ደካማ የነበረ መሆኑ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት በተደረገለት የህክምና ክትትል ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ማረፉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
ይህንን ያልተለመደ ክስተት ተከትሎ፣ የፈረንሳይ የጤና ባለስልጣናት ቫይረሱ ወደ ሰው የመተላለፍ አቅም ማዳበሩን እና በማህበረሰብ ጤና ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት በጥልቀት እየመረመሩ ይገኛሉ።
ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለተገኘበት ግለሰብ እና አጠቃላይ ሁኔታው ከፈረንሳይ መንግስት ጋር መረጃዎችን በቅርበት እየተለዋወጠ መሆኑን ገልጸዋል።
የጤና ባለሙያዎች ክስተቱ ገና በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ ማህበረሰቡ አላስፈላጊ ድንጋጤ ውስጥ ሳይገባ፣ ከትክክለኛ እና ይፋዊ የጤና ተቋማት የሚወጡ መረጃዎችን ብቻ እንዲከታተል ይመክራሉ።

🙏2❤1
ማህሙድ አህመድ በሕይወት አለ
"ምን ቢያረጋችሁ ነው? አባቴ በሕይወት እያለ ሞተ እያላችሁ የምታወሩት?" የድምጻዊ ማሕሙድ ልጅ ሀብቱ
የአንጋፋው ድምፃዊ ማሕሙድ አሕመድ ልጅ ሀብቱ ማሕሙድ ፤ "ማሕመድ አህመድ አረፈ" በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ ገጾች በዛሬው ዕለት ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሐሰት መሆኑን አስታወቀ።
ኤቨንት አዲስ ሚዲያ እንደተመለከተው ሀብቱ ማህሙድ ባስተላለፈው መልዕክት "አንዳንድ የፌስቡኩ ፔጆች እና ቲክቶከሮች አባቴን ከዚህ አለም ተለየ እያሉ በውሸት እየዘገቡ ነው ያሉት። እና ይሄ በጣም በጣም አስነዋሪ ድርጊት ነው። ምን ቢያረጋችሁ ነው አባቴ በህይወት እያለ ሞተ እያላችሁ የምታወሩት? አባቴ በህይወት አለ" ብሏል።
አባቱ ድምፃዊ ማህሙድ አሕመድ በሕይወት የሚገኝና በሙሉ ጤንነት ላይ ያለ መሆኑን አረጋግጦ፣ መሰል የሐሰት ወሬዎችን የሚያሰራጩ አካላትን ድርጊት "አስነዋሪ" ሲል ኮንኖታል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአንጋፋው ድምፃዊ ያለውን ፍቅርና አክብሮት ያወሳው ሀብቱ፤ ህብረተሰቡ ያልተረጋገጡና ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ገጾችን ሪፖርት በማድረግ የሐሰት መረጃ ስርጭትን እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።
አንጋፋው ድምፃዊ ማሕሙድ አሕመድ ትላንት ረቡዕ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባሕል ማዕከል በተካሄደውና ለታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ በተዘጋጀው ጥበባዊ መርሃ-ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝቶ እንደነበር ይታወሳል።

የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር በሞያሌ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ
የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር ባወጣው ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በድንበር አካባቢ በተቀሰቀሰው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከኢትዮጵያ ወገን ተፈናቅለው ወደ ኬንያ ማርሳቢት ካውንቲ ሞያሌ ከተማ በመግባት ላይ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርገውን ሰብአዊ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታውቋል።
ማኅበሩ ከካውንቲው መንግሥት አካላትና አጋሮች ጋር በመቀናጀት ጊዜያዊ መጠለያዎችን፣ ድንኳኖችንና እንደ ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ፣ ጄሪካን እና የወጥ ቤት ዕቃዎች ያሉ መሠረታዊ ቁሳቁሶችን ማሰራጨት ጀምሯል።