#ስለ_ፍቅር (sele fkr)❤️
2.12K subscribers
50 photos
2 videos
3 files
6 links
Download Telegram
በአንድ ወቅት ስሙ የገነነው ታላቁ ፈላስፋ ዲዮጋን አለምን ከሞሏት ሚሊዮኖች ሰዎች ውስጥ ሰው ፈልጎ ቢያጣባት በየገበያውና በየሰርጣ ሰርጡ በቀን በጠራራ ጸሀይ ወጣ።

የቀን ጋኔን፣ የአለምን ማጋነንና ሃሜት ሳይፈራ ፋኖሱን አብርቶ ሰው ፍለጋ ጀመረ። ግን ዲዮጋን የፋኖሱን መብራት በላዩ አብርቶ ራሱን ተመልክቷል? ራሱን ሰው አድርጎ ነው ሰው ፍለጋ የወጣው? በአለም ፈልጌ አንድ ሰወ አጣሁ ያለውስ ራሱም ሰው ሆኖ አልተገኘም ይሆን? በርግጥ በዛን ዘመን በአለም ከነበሩ ሚሊዮኖች አሊያም መቶ ሺዎች አሁን ላይ በራሱ ከቢሊዮኖች ውስጥ ሰውን ማግኘት ከባድ ሆኗል፤ ሰው የሆነን ሰው ከመፈለግ የማያልቀውን ህልቁ መሳፍርት መላው ዩኒቨርስን አርሶና አዳርሶ፤ አረስርሶ መጨረስ ይቀላል።

እያንዳንዳችን ሰው ለመሆን የምንሞክር የሰው ምስል ፎቶ ነን እንጂ 8 ቢሊዮን ህዝብ አለምን አልሞላትም።

በኢየሩሳሌም የነገሰው ንጉሥ "ንጉሥ ዳዊት " ለልጁ ኑዛዜ ሲያስተላልፍለት "ልጄ ሆይ ሰው ሁን!" ነው ያለው።

ወደ ሰውነት ጉዞ መጀመር አለብን ባይ ነኝ። የስታቲስቲክሱን ነገር ለጊዜው ወደጎን ብለነው "በቁጥር አለም ይህን ያህል ሰው ያዘች " ብለን ከመለፈፋችን አስቀድመን ሰው የሆነና ሰው ያልሆነውን እንደ ዲዮጋን ማሿችንን ከራሳችን ጀምረን እያበራን "የሰው ያለህ" ማለት ይገባናል።

የሀይማኖት ተቋማት በእኛ እምነት የሚያምኑ "ሚሊዮኖች " አሉ ብለን ከመደስኮራቸንና ቁመት ከመለካካታችን አስቀድመን " ሰው" የተባለውን ፍጡር ከጥልቁ ጨለማ አስሰን ማግኘትና ሰውነትን ማጎልመስ ይገባናል ከሚሉት ነኝ።
✍️ሀብታሙ ሀደራ

🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

@fker12
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
👍64🔥1🥰1
አሁን ልሸውድህ ነው!እየነገርኩህ እንኳን እሸውድሃለው!‼️ከተሸወድክ ግን ቻናሉን #share ማድረግ ግዴታህ ነው‼️

👉አልሸወድም ካልክ ማንበብ ትችላለህ




















ሽወዳ በየቀኑ በየጊዜው የሚከወን ድርጊት ነው::በተለያዩ ሀገራቶች እንደሚፈጸም የሚታወቅ ቢሆንም በያንዳንዱ ሃገሮች ደግሞ ለየት ይላል

ለምሳሌ በኛ ሃገር በአንዲት ግዛት አንድ ሰው ለጨዋታ በሚልና በአስቂኝ ሁኔታ ሰውን ከሸወደ 1368832789960632 ገደማ ያክል ይሸለማል

አሁን መሸወድህ ላረጋግጥልህ ??

        💥ማረጋገጫ 💥

1)ከላይ ያለውን ቁጥር ሙሉ በሙሉ አላነበብከውም……ማለት ሳታነብ ዘለልከው አይደል??

2)በዚህም ምክንያት "ኦ" የተባለችዋን የእንግሊዘኛ ፊደል እንዳለች አላየህም😳







ባክህ የለችም ተመለስ 😁

አሁን መሸነፍህን ካመንክ
             #Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
👍13😁103🔥2🗿1
በወንዝ ዳር በጫካ ውስጥ የሚኖር ዝንጀሮ ነበር። አንድ ቀን ዝንጀሮው አንድ አሳ በወንዙ ውስጥ ሲዋኝ አሳው እየታገለ እንደሆነ አሰበ። ዝንጀሮው ርኅራኄ ስለተሰማው ዓሣውን ለማዳን ወሰነ። በፍጥነት ከዛፉ ላይ ወረደና እጁን ዘርግቶ ዓሣውን ከውሃ ውስጥ በማውጣት ወደ ላይ ተመልሶ ዓሣውን በዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አስቀመጠ፡፡ ከዚያም ዓሣው በኃይል ተንፈራፈረና ብዙም ሳይቆይ ሞተ። ዝንጀሮው ግራ ገባው እሱ መርዳት ብቻ ነበር የፈለገው።

ይህ ታሪክ የተለያዩ አመለካከቶችና አረዳዶችን ያሳያል። ማለትም ዝንጀሮው በመሬት ላይ የሚኖር ፍጡር በመሆኑ ሁኔታውን ከአካባቢው እና ከልምዱ በመነሳት ስለገመተ የዓሳውን መዋኘት እንደ መታገል ወይም እንደተሰቃየ ይተረጉመዋል። ዓሳዎቹ በውኃ ውስጥ ሲሆኑ አየርን እንደማይተነፍሱ ተመለከተና ዓሣው አደጋ ላይ እንደሆነ ገመተ። ለማገዝ ባደረገው ጥረት አሳውን ከተፈጥሮ አካባቢው አውጥቶ ወደ ራሱ አካባቢ በማስገባቱ ለዓሣው መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

ይህ ታሪክ ለአንድ ሰው ትክክል ወይም ተፈጥሯዊ የሆነው ነገር ማድረግ የግድ ሌሎችን ይመለከታል ብሎ ከማሰብ መጠንቀቅ እንዳለብን ያሳያል። አንዳንዴ ፍላጎታቸውን፣ ተፈጥሮአቸውን ወይም አካባቢያቸውን በትክክል ሳንረዳ የራሳችንን አመለካከቶች እና አኗኗራችንን በሌሎች ላይ መጫን ለአደጋ ይዳርጋል።

ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው በአለም ውስጥ የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ አለውና ሁሉም ሰው እኔን ምሰል ወይም የእኔ ብቻ ተቀበል ማለት የለበትም!

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
👍108
እኔ እና ብዕሬ

አትዘንጋ፤
በዚህ በአለንባት ምድር ምንም ነገር የኔ የምትለው ለዘለቂታ ካንተ ጋር የሚቆይ ነገር የለም።

አንድ ወፍ በህይወት እያለች ጉንዳንን እያጣጣመች ትመገባታለች፤ጉንዳን ደግሞ በተራዋ ወፎ ስትሞት ጠብቆ አጣጥሞ ይስለቅታታል፡፡ ይገርማል፤ጊዜና ሁኔታ ተለዋዋጭ ናቸው፡፡ በህይወት ማንንም አሳንሰህ አትይ ወይም አትጉዳ። ዛሬ አንተ ለራስህ ጥንካሬህ ይታይ ይሆናል ግን አንተ ሳትሆን ጊዜ ከአንተ የላቀ ጠንካራ መሆኑ መዘንጋትህ ይመስለኛል።

በአንድ የዛፍ ግንድ ብዙ የክብሪት እንጨቶች ይመረታል ግን አንድ የክብሪት እንጨት በሚሊዩን የሚቆጠሩ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡

ስለዚህ አንዲት መጥፎ፣መልካም ያልሆነ ሃሳብ(negatuvity thought) ወይም ነገር ለብዙ መልካም ወይም ጥሩ ሃሳቦች (positivity thought) ማጥፊያ እንዳትሆን በህይወትህ አትፍቀድላት። ስለዚህ መልካም ሁን እንዲሁም መልካም አድርግ።
መልካም ዕለተ አርቢት ለዕለት ቅዳሚት አሸጋገረን፡፡

ቤስቶ(besto)


#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
7👍7
[አንድ ግጥም ፃፊ]

ዓይን ያልመረመረው፣
ጆሮ ያልቆጠረው፣
ምላስ ያልነካካው፣
እጅ አልፎ ያልለካው፣
ከቆዳ ዝላይ ሂያጅ፣
አንድ ግጥም ፃፊ፤
ገሎ ማዳን ልመጅ፣
ከእይታ ግዘፊ፣
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ።

ሰጠሁሽ ዋርካውን፣ ለቀለም ውቀጭው
ጥላው አይምሽበት፣ ማልደሽ አስቆርጭው
እጄን በሴት አንገት፣ የቆየ እንዳያየው
ልቤን እንደ በካር፣ ቀይ ደም እለቢው።

ሁለት ቀለም አለሽ፣
የዋርካ ለነጩ፣ የልቤ ቀይ ደማቅ
ሁለት ጀብዱ ሰራሽ፣
ጎንደር እጅ ሰጠሽ፣ ጃንተከል እስኪደርቅ
በቃ አሁን እረፊ፣
እስኪ ግጥም ፃፊ
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ።

አሁን አየ አሞራ፣ ሟቿን ገዳይ አለ
አሁን ዞረ ንስር፣ ግዳይ ተቀበለ
"ዋ ጀግና ዋ ገዳይ
እስኪ አዝልቋት ትታይ
ሽኝቷ እስከነፍሱ፣ ባሩዷ የቀለም"
ይሸለል ይፎከር፣ ይንገሩልሽ 'ላለም።

በቃ አሁን እረፊ፣
አንድ ግጥም ፃፊ
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ
ቃላት ያከንፋሉ፣ ቃላት ይሰብራሉ
ሆሄያት ያናግራሉ፣ሆሄያት ይቀብራሉ
ህመምን አስታመው፣ ፍቅርን እስኪያበቃ
ታምሚያለሁ መሰል፣ ወደቅኩኝ እንደ እቃ
እጄን ትራስ ውሰጅ፣ ወንድነቴ አበቃ።

©ክፍሌ

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
5👍3
#ከመፅሃፍ_ገፆች

ይቺን አስተማሪ ግጥም በቃሉ የሚችላት?

"ሁለቱ መላጦች"

ሁለቱ መላጦች

ሁለት በራ ሠዎች ሲያልፉ በጎዳና
ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል ያዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ።

በኋላም ተማተው በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ
ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ።

እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ፀጉር የለበት
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ?


ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሣይረዱ
ከመጣላት በፊት ከመቀያየም
የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም።

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
7👍6
🕑የቤተሰብ ሰዓት

🌊 አንድ ነገር ልንሞክር ነው ። አይምሯችሁ ላይ የሚፈጠረውን ተዓምር በማየት ፣ እናንተ እራሳችሁ ምን እንደጠቀማችሁ ትነግሩኛላችሁ! The power of Now - approach ነው የምንጠቀመው!

📮ብቻችሁን ብትሆኑ አሪፍ ነው ፣ በመጀመሪያ ዘና ብላችሁ ለመቀመጥ ወይ ደግሞ ጋደም ለማለት ሞክሩ!አይናችሁን ክደኑት ፣ አንደኛው እጃችሁን ልባችሁ ላይ አርጉት! ከዛን በጥልቀት መተንፈስ ጀምሩ ፣ በጆሯችሁ የሚመጡ ነገሮችን በሙሉ ስሙ! ስለምትሰሙት ነገር አታስቡ!ዝም ብላችሁ ስሙት! በጆሯችሁ ከሚመጣው ድምፅ ጋር እንዲሁ ትንፋሽ ወደ አፍንጫችሁ ሲገባ Feel አርጉት ፣ በ አፋችሁ ሲወጣም እንዲሁ የወላፈኑ ግርፋት ይሰማችሁ! በእጃችሁ የልባችሁን ትረታ አዳምጡ! ስለ ፍቅረኛችሁ አታስቡ ፣ ስለ ኑሮ አታስቡ ፣ ምንም አታስቡ ፤ ለዛ ቅፅበት ብቻ ስሜት ይኑራችሁ! በጆሯችሁ ድምፆች ሲገቡ የሰማችሁ ፤ በገላችሁ ላይ አየሩ ሲዳብሳችሁ ይሰማችሁ ፣ የልባችሁ ትርታ በእጃችሁ ይሰማችሁ ፣ ትንፋሻችሁ ሲገባ ሲወጣ ይሰማችሁ! ሌላ ምንም አታስቡ ፣ የነገርኳችሁን ስሜቶች ብቻ አዳምጡ! ይሄን ማረጋችሁ ሞኝነት አደለም ፣ የሚፈጠረውን ተዓምር ታያላችሁ ፣ የሩቅ ምስራቅ መነኩሴም ላረጋችሁ አደለም ፣በሳይንስ የተረጋገጠ Mindfulness State ነው! ለ 5 ደቂቃ ብቻ አድርጉት! ከዛን የተሰማችሁን መታችሁ ከስር Comment ላይ ትነግሩኛላችሁ! ከመጀመራችሁ በፊት ለ5 Minute የሚሆን Alarm ሙሉ ፣ ከዛ ጀምሩ! አሁኑኑ ሞክሩት

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
👍94
በትንሽ መጀመርና ትልቅ ማለም አንዱ ባንዱ ውስጥ የተደበቁ የስኬት ምስጢሮች ናቸው። ትልቅ ህልም ይዘው አንድም ሳይሠሩ የሚሞቱ ሰዎች የውድቀታቸው ምስጢር ብዙ ጊዜ ትልቁን ህልማቸውን በሚመስል ወይም ለዚያ በሚያዘጋጃቸው ነገር ላይ ያጠፉት ጊዜ ስለሌለ ነው። በትንሽ ነገር ላይ ተጣብቀው እንደማቀቁ የሚሞቱም ብዙ ሰዎች ትልልቅ ነገር ሊሠሩ እንደሚችሉና እንደሚገባቸው ማመን ስለሚሳናቸው ነው። ሌላው ቁልፍ ግን ሰዎች ባላቸው ነገር አሁኑኑ ከመጀመር ይልቅ ነገን ሲጠብቁና የተሻለን ቀን ሲናፍቁ ዕድልም ዕድሜም ያመልጣቸዋል። በትንሽ አሁን መጀመርና ለትልቅ ነገር እየተዘጋጁ ለነገ ማቀድ በርግጥም ጥበብ ነው።

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
9👍4
ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ እና ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ በአንድ የሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ላይ ለሜዳልያ ፉክክር እያደረጉ ነበር።

ኬንያዊው አቤል ሙታይ ውድድሩን እየመራ ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ እየተከተለው ትንቅን ላይ ነበሩ።

በድንገት ግን ከውድድሩ ፍጻሜ መስመር ላይ ሊደርሱ በግምት 10 ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ኬንያዊው የውድድሩ መሪ አቤል ሙታይ ውድድሩን ያጠናቀቀ መስሎት በስህተት ውድድሩን አቋርጦ ቆመ:: ይህንን ክስተት የተመለከተው ስፔናዊው ሯጭ አቤል ሙታይ ውድድሩን እንዲቀጥል እና መስመሩን እንዲያቋርጥ ከኃላው ሆኖ ይጮህበት ጀመር

የስፓኒሽ ቋንቋ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማው አቤል ሙታይ ምን እንደተፈጠረ ሊገባው አልቻለም:: በመሆኑም ስፔናዊው ሯጭ ኢቫን መስመሩን አቋርጦ ውድድሩን ከማሸነፍ ይልቅ አቤል ሙታይን በመግፋት ውድድሩን አሸንፎ የወርቅ ሜዳልያውን እንዲያሸንፍ አደረገው።

ውድድሩ መጠናቀቁ ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለኢቫን ጥያቄ አቀረበለት ...

"ለምን እንደዚያ አደረግክ?"

"የእኔ የህይወት ህልም አንዳችን ሌላችንን በመግፋት አሸናፊ እንድንሆን ማገዝ ነው:: ህልሜ እርስ በእርሱ ተደጋግፎ አሸናፊ የሚሆን ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው" ሲል መለሰለት።

"ለምን ኬንያዊው እንዲያሸንፍ አደረግክ ?" ደግሞ ጠየቀው

"እኔ እንዲያሸንፍ አላደረግኩትም:: እሱ መጀመርያም ሊያሸንፍ ነበር"

"ግን እኮ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳልያውን ማጥለቅ ትችል ነበር" ጋዜጠኛው አሁንም ጠየቀው

"ድል የማድረግ መርሁ እና ጣእሙ ምንድነው? እንዲህ ሆኖ የማሸንፈው ሜዳሊያ ክብሩ ምንድነው? እናቴ ይህንን ስታይ ምን ትለኛለች?" ሲል ጋዜጠኛውን አስደመመው

Moral of the story 👉አሸንፍ...ሌሎችም እንዲያሸንፉ #share አድርግ
👍149👏1
ጋሽ ፕሮፌሰሩ

ፕሮፌሰሩ በባቡር ጉዞ እያደረገ ነው። በመንገዱ ተሰላችቶ ስለነበር ጊዜውን ለማሳለፍ የጨዋታ ሀሳብ ለማቅረብ ዳዳውና ከጎኑ ለነበረው ገበሬ ዞር አለና "አንድ ጥያቄ እጠይቅሃለሁ" "መመለስ ካልቻልክ 5 ዶላር ትሰጠኛለህ። ከዚያም አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለህ። መልስ መስጠት ካልቻልኩ 500 ዶላር እሰጥሃለሁ። ምን ትላለህ?" ይለዋል ገበሬውም በመስማማት እሺ ይለዋል።
ፕሮፌሰሩ “በምድር እና በጨረቃ መካከል ያለው ርቀት ምን ያህል ነው?” በማለት ጥያቄውን ይጀምራል። ገበሬው ዝም ብሎ 5 ዶላር አውጥቶ ለፕሮፌሰሩ ሰጠው።

አሁን ተራው የገበሬው ሆነ።
እንዲህም ሲል ጠየቀው “ተራራ ሲወጣ ሶስት እግር ያለው፣ ሲወርድ አራት እግር ያለው የትኛው እንስሳ ነው?” ሲል ጠየቀ።
ፕሮፌሰሩ ከበደው ሆኖም በቻለው መጠን ምክንያታዊ ማብራሪያዎችን ለመፈለግ ሞከረ ማስታወሻ ደብተሩን ገለጠ መልስ ግን ማግኘት አልቻለም። ተበሳጨና 500 ዶላር ለገበሬው አስረከበ። ገበሬው ገንዘቡን በፈገግታ ወስዶ ለማረፍ ወደ ኋላ ሄደ። የማወቅ ጉጉት በእጅጉ ያደረበት ፕሮፌሰሩ ገበሬውን ከእንቅልፉ ቀስቅሰውና “እሺ፣ የትኛው እንስሳ ነው?” ሲል ጠየቀው። ገበሬው ዝም ብሎ 5 ዶላር አውጥቶ ለፕሮፌሰሩ ሰጠውና ተመልሶ ተኛ።

ጌቱ ወንድወሰን

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
👍164😁4
መተው ወይም መልቀቅ ወደ ፈውስ የሚወስድ እርምጃ ነው :: በሕይወታችን ያጋጠሙን መጥፎ ነገሮች አሳምመውን ያለፉ ወይም አሁንም እያሳመሙን ያሉ ይሆናሉ :: ሀዘን ቢሆን ፣ በሚወዱት በሚያምኑት መከዳት ፣ ቢሆን ወይም ኪሳራ ቢሆን ሌሎችም ህመሞች ቢሆኑ በውስጣችን ይዘን በተብሰለሰልን ቁጥር አየበሉን እያሳሱን እየቆረጡን ነው የሚሄዱት ::

መተው ወይም መልቀቅ ማለት የተፈጠረውን ነገር እንዳልተፈጠረ መርሳት አይደለም ነገር ግን ለመርሳት መንገድ መክፈት ፣ ለአዲስ ሀሳብ ለአዲስ Energy ቦታ ማስለቀቅ ፣ ለለውጥ ልብን መክፈት ማለት ነው :: ከአለፈ ነገራችን ጋር ተጋብተን የምንኖር ከሆነ ቁስላችንን መቼም አይሽርም ህክምና ያስፈልገዋል መድሀኒቱም መልቀቅ ወይም መተው ነው ::

Sometimes letting go is the way to heal.


#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
👍126
እድሜህ ምን አስተማረህ ...??

ሁላችንም ባልተመረመርናቸው በሽታዎች የምንሰቃይ ምስኪኖች ነን ፤ እድሜያችን ያስተማረንን እንኳ የማናውቅ ።

ብዙ ያልተጠየቅናቸው ጥያቄዎች አሉብን በግዜ ሂደት ህመም እየሆኑ እኛነታችንን ከእግዜር የነጠሉ

ብንጠየቅም
ደሞ መልስ የማናገኝላቸው ሺህ ጥያቄዎች ...

እኔ እድሜዬ መዳብ የሆነብኝን ወርቅ ከሔደ ደግሜ እንደማላገኝ አስተማረኝ..እናንተስ
👍226
ለምንድነው ከስራ ይልቅ ቢዝነስ ያልመረጥኩት ?😕

በቻይና ውስጥ በጣም ሀብታም ሰው "ሙዝ እና ገንዘብ በዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጡ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ ሊገዛ እንደሚችል ስለማያውቁ ነው. እንዲያውም ሥራ እና ንግድ ለሰዎች ብታቀርቡ, መስራትን ይመርጣሉ ምክንያቱም አብዛኛው ሰው ቢዝነስ ከደመወዝ የበለጠ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ስለማያውቅ ድሆች ከሚሆኑባቸው ምክንያቶች አንዱ የንግድ ሥራ እውቅና ባለማግኘታቸው ነው። እድሎች በትምህርት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ, እና በትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩት ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለደሞዝ መሥራት ነው።
22👍13
አትምጪ

ቀረሽ ወይ እላለሁ ከአንድም ሁለት ጊዜ

አወይ ፍቅር ፍቅር ያሲያዘኝ አባዜ

ግን ተይው አትምጪ ይቅር ትቼሻለሁ
ስታደሚኝ ያኔ ስቄ አይቼሻለሁ.......🤕

®እብዱ ገጣሚ
8🙈5
አወይ
አወይ ሞኝ መሆን አወይ ጅልነቴ
አባቴ ሲመከሰረኝ ተው ባክህ ማለቴ

ትንሽ አንደበቴ እሳት አቃጠለች
ሳልሰማሽ የቀረሁ አወይ ምንአባቴ

ጉድ አለም ጉድ ህይወት ጀምሬ ቁማር
ይሄው ተያዝኩልሽ አንዴ ላልማር ...
✍️

@እብዱ ገጣሚ
👍74
አንድ ቀን
ፍቅርን ወሰዱና ፍቅር ላይ ቀለዱ
ቡሀላ ሳያቸው እነሱው አበዱ

ጊዜን ወሰዱና እስኪያልፍ ሲሻፍዱ
አስሬ እባክህን ማለትን ለመዱ


አስሬ ሲያጠፉ መካሪ ሆኜ እኔ
አጠንክረውኛል ተማርኩ በሰው ስህተት እኔ

የኔን ስህተት ተውት

@እብዱ ገጣሚ✍️
👍114
አትሸወጅ
አይግባሽ ተይ በቃ


ብዙ የደበኩሽ አለኝ ሚስጥር
አንቺም እኔን እኔም አንቺን ስጠረጥር

ሞትን እንጂ አንዴ ኖረን አናቅም

እንለያይ

✍️እብዱ ገጣሚ
👍216🥰4
👍221
እጀግ በሚገርም ሁኔታ የዓለምን የበላይነት ማለትም በእኮኖሚ በጦር ሚዛን እና በመሳሰሉት የበላይነትን ለመቀዳጀት ሲባል የሩሲያ KGB እና የአሜሪካነ CIA በሰው ሃገር ላይ ያገባኛል በማለት ተፋጠዋል ( ማን ይሳካለት ይሆን?

የ KGBው የስለላ መረብ ሃላፊ ላቀደው ታላቅ ሴራ ማስፈፀሚያ የሰውን ልጅ እንደ እንስሳ ከመጠቀሙም በላይ እንደ ቀልድ እያደባ ይህን ታላቅ ሚስጢር የሚፈፅምበት ቀን ተቃርቧል ይፈፅመው ይሆን?

የ CIA ዋ ሰላይ አንድ አስደንጋጭ የ KGBን ሚስጥር ከመስማትም አልፋ ትደርስበታለች ግን አለቆቿ ሚስጢሩን በማጣጣል ሰማ በማጣቷ ራሷ ሕይወቷን አደጋ ላይ በመጣል ትጋፈጠዋለች::ታጋልጠው ይሆን?

KGB ያጠመደው የኒውክለር ቦንብ CIA ሳይደርስበት የመፈንጃው ጊዜ ደግሞ ተቃርቧል ይህ ጓረቤት ሀገርንም ሆነ አካባቢውን የሚያጠድም ታላቅ > የቦንቡ ሚስጢር ከተሰማ በኃላ ሃገሮችን ሽብር ውስጥ ከመክተቱም --- በላይ እልህ አስጨራሽ እርብርብ ይደረጋል :: ይከሽፋ ይሆን?

እሷ ከደረሰባት የእንሰሳዊ ድርጊት እና እሱ ክደረሰበት በደል የተነሳ የመበቀያ ጊዜና ሁኔታ በመድረሱ እንዳረሩት የልባቸውን የበቀል መልስ ለመመለስ ተቃርበዋል ይፈዕሙት ይሆን፡፡

ይህ መፅሐፍ ለፍቅር ሲባል ከአላማ ውጪ የሚደረግ ጉቦን ፤ለገንዘብ ሲባል የጣምራ ሰላይነት ሚናን ፣ ክደረሰባቸው በደል የተነሳ የበቀል ዕዋን የመጐንጨት እና የተጠበቀው እንዳልተጠበቀ የሆኑና ያልሆነ ድርጊቶች እየተፈፀሙ የአንባቢን ቀልብ በመግዛት ከመጀመሪያ ገፅ እንስቶ ሚስጢሩ አስከሚፈታ የመጨረሻው ገፅ ድረስ በጉጉት የሚነበብ መፅሐፍ ነው።
19🥰1
በቀለኛው ሰላይ.pdf
19.2 MB
ይህ መፅሀፍ .. ለፍቅር ሲባል ከአላማ ውጪ የሚደረግ ጉዞን፣ ለገንዘብ ሲባል የጣምራ ሰላይነት ሚናን፣ ከደረሰባቸው በደል የተነሳ የበቀል ፅዋን የመጎንጨት እና የተጠበቀው እንዳልተጠበቀ የሆኑና ያልሆኑ ድርጊቶች እየተፈፀሙ፣ የአከባቢን ቀልብ በመግዛት
ከመጀመርያ ገፅ አንስቶ ሚስጥሩ እስከሚፈታ የመጨረሻው ገፅ ድረስ በጉጉት የሚነበብ መፅሀፍ ነው።
30👍10