5killo Jem'a official Channel
1.16K subscribers
1.43K photos
285 videos
75 files
673 links
This is the official channel of AAiT jem'a where we provide info abt
👉Jem'a Tutors
👉Trainings and Da'ewa programs
👉Weekly lunches and halaqas(circles)
👉qira'ts (Qur'an and other Kitabs)
👉Weekly Q&A sessions

Group: https://t.me/+cw97UaRUF1YzMTg0
Download Telegram
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات

ፕሮግራማችን ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።

የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችን ታሪካዊ የመብት ትግል ላጋሩን፤ ወንድማችን ሱደይስ አብዱረህማን፤ እንዲሁም በኔትዎርክ ምክንያት ሊቀላቀለን ያልቻለውን ወንድም አብዲ ኮርማን ከልብ እናመሰግናለን።

እንዲሁም ፕሮግራሙ እንዲሳካ ለተነቀሳቀሱ እህት እና ወንድሞች ሁሉ ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ ማለት እንወዳለን!

በቀጥታ መከታተል ላልቻላችሁ ሪከርድ የሚለቀቅ ይሆናል።

ህያው ምስክር ፕሮግራማችን በቀጣይም ከሌላ እንግዳና ሌላ አስተማሪ የትግል ታሪክ ጋር የሚመለስ ይሆናል።

@aaumsu
1
በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ልዩ የሆነ የዳዕዋ እና ፓናል ውይይት ተዘጋጅቷል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ከደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመሆን  የተዘጋጀው ይህ ልዩ መድረክ ሊጀምር ደቂቃዎች ብቻ ነው የቀሩት!

@aaumsu
🔥21
አል በያን - ቅ1.pdf
13 MB
🔥 አዲስ ነገር!!! 🔥
በአዲሱ የትምሕርት ዘመን!!
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ኅብረት!


በመነሻችን ላይ «ስለመንገዱ» መክረን ነበር... መንገዱ የሚጠይቀውን ሁሉ አንዳች ሳንሰስት ለመስጠት ቃል ተጋብተንም ጭምር!... እነሆ አሁን ደግሞ በመንገዳችን ላይ የነበሩትን አጠቃላይ ሂደቶች በምንዳስስበት «አል-በያን!» በተሰኘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተዘጋጀ መጽሔት ብቅ ብለናል። ይህ በችሮታው እንጂ በሌላ አልሆነምና፥ ሰዎችን መግለጽ ያስተማረው ጌታ ምሉዕነቱን የሚመጥን ምስጋና የተገባው ይሁን!!!

መጽሔታችን በሚቀጥሉት ጊዜያት በሙስሊም ተማሪዎች ጉዳዮች ላይ በማተኮር የተለያዩ ሀገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ አርዕስቶችን በተከታታይ እየዳሠሠ፥ ለተማሪዎች እንዲሁም ውጪ ላለው ማኅበረሰብ ሰፊ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ይሆናል።

ይህ ከ«ጥያቄ አለን!» ትውልድ ዘላቂ አሻራዎች ውስጥ አንዱ ነው! መንገዳችን ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ... በጊዜ ሐዲድ ላይ ብሩህ መዳረሻን እናኖር ዘንድ... ለትውልድ ነጻነትን እናወርስ ዘንድ... እስክሪብቷችንን አለመጣላችንን ያረጋገጥንበት ሌላ ክስተት።

መጽሔቱን በማዘጋጀት ሂደት ላይ «እኔም ለትውልድ የማወርሰው ብሩህ ነገ አለ!» ብላችሁ ብዕራችሁን የጨበጣችሁ ውድ ተማሪዎቻችን፥ አላህ (ሱ.ወ) መልካም ሥራችሁን ይባርክላችሁ። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!!!

አላህ ለመልካም ለውጥ ሰበብ የምንሆን ያድርገን።

መልካም ንባብ!

©aaumsu

@fivekjemaa
🔥3👏1
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በGovernment Sponsorship መግባት ለሚፈልጉ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብን ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት፦

📌 ለNatural Science፡ 76.17
📌 ለSocial Science: 58.75


ውጤት የሚሰላው 50% Entrance exam፤ 50% UAT በማድረግ ከ100% ይሆናል።

@aaumsu
👍2
ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት

ክፍል 1

ጊዜው ከሙሳ ዐለይሂ ሰላም በኋላ ነው፤ የኢስራኢል ልጆች በሙሳ መንገድ ፀንተው በተወራትም ህግጋት ሲመሩ ነበር። ዘመናት በራቀ ቁጥር ግን ቀልቦቻቸው ደረቁ፤ በዲናቸውም አዳዲስ ነገሮችን አስገቡ፤ ከፊሎቻቸውም ጣኦታትን ማምለክ ጀመሩ። ከክፋታቸው ይመለሱ፣ በመልካም ይታዘዙ፣ ከክፉም ነገር ይታቀቡ ዘንድ እንዲሁም በመካከላቸው በተውራት ህግጋት እንዲፈርዱ አሏህ መልእክተኞችን አከታትሎ መላክን ቀጠለ።

ቀደም ባለ ጊዜ የኢስራኢል ልጆችን የሚዋጋ ሁሉ ይሸነፍ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ከአላህ ጋር በቀጥታ ከተነጋገሩት ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ጀምሮ ከትውልድ ወደ ወደ ትውልድ ሲወራረሱት የነበረ ተውራትና ታቦትን ይዘው ስለነበር ነው። (ይህ ሲባል ታቦቱ /ሳጥኑ ውስጥ የሙሳ እና ሀሩን ቅርስ የነበረ ሲሆን ጦርነት ሲሄዱ ተሸክመውሄደው ከአላህ በሆነ ተአምር በርሱ በረካ ነስርን ያረጋግጥላቸው ነበር)

የኢስራኢል ልጆችም እነዚያን ክፉ ስራዎች መፈጸማቸውን በቀጠሉ ጊዜ አላህ ጠላቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ሾመባቸው። ብዙዎች ጦር ሜዳ ላይ አለቁ፣ ልጆቻቸው እና ሴቶቻቸው ተማረኩ፣ጠላቶቻቸው በሀገራቸው ሰፊ ክፍሎችን ተቆጣጠሩ፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው በቃ የአንድ ህዝብ ልቅናውም ሆነ ውድቀቱ ሚጀምረው ለጌታውን ትእዛዝ ከሚሰጠው ቦታ ነው።አሁን ላለንበት የበታችነትና በካፊሮች እጅ ስር መጨፍደድ አንዱ ምክንያት ከአሏህ መራቅ ነው።ሙስሊሙ ውጥንቅጡ ወጥቷል፤ ከቁርአን ብርሀን፣ ከነብዩም፣ ከሰሀቦቻቸው፣ ከድንቅ ተተኪዎችም በኋላ መርህ እንደሌለው ተራ ሰው ዘቀጥን ዱንያም ዋጠችን...ውጤቱንም እንደምናየው ነው– በየቦታው ችግራችን በዛ ከብዛታችንም ሀይል አጣን ተዳከምን።

የኢስራኢል ልጆች ታቦቱንና ተውራትን በአንድ የጠላት ንጉስ እስኪያስነጥቁ ድረስ በጥመት መቀጠላቸውን አላቆሙም ነበር። ከዚህም በኋላ ከመካከላቸው አንድን ነብይ አሏህ ላከ። ወደ አላህ እርሱን ብቻ እንዲያመልኩ እንዲጠራ አዘዘው። ነብያቸውም የኢስራኢል ልጆችን ወደ አላህ ጠራቸው።እነርሱም በመካከላቸው ንግስና አብቅቶ ነበርና ጠላቶቻቸውን በእርሱ መሪነት በአሏህ መንገድ ለመዋጋት አንድን ንጉስ እንዲሾምላቸው ጠየቁ።
<<أَلَمْ تَرَ إِلَى الْمَلَإِ مِن بَنِي إِسْرَائِيلَ مِن بَعْدِ مُوسَىٰ إِذْ قَالُوا لِنَبِيٍّ لَّهُمُ ابْعَثْ لَنَا مَلِكًا نُّقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ>>

"ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ በኋላ ወደ ነበሩት ጭፍሮች ለነቢያቸው ፡- «ለእኛ ንጉሥን አስነሳልን በአላህ መንገድ እንዋጋለን፤» ባሉ ጊዜ አላየህምን? (አላወቅህምን?)"

ነብያቸውም እንዲህ አላቸው:-
<<قَالَ هَلْ عَسَيْتُمْ إِن كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ أَلَّا تُقَاتِلُوا ۖ>>

"ከአሏህ ዘንድ በግዳጅነት ቢፃፍባችሁ ላለመዋጋት ትሻላችሁን??"

<< قَالُوا وَمَا لَنَا أَلَّا نُقَاتِلَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَقَدْ أُخْرِجْنَا مِن دِيَارِنَا وَأَبْنَائِنَا>>

"ከሀገሮቻችን እና ከልጆቻችን የተባረርን ስንሆን በአላህ መንገድ የማንዋጋ ለእኛ ምን አለን?" በማለትም መልሱ

መሪ እንዲሰጣቸው ጠየቁ.....ነገር ግን ፈተናውን ለመቀበል ዝግጁ ነበሩ ይሆን!?

ይቀጥላል....
1🔥1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ከደሴ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመሆን "የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ከትላንት እስከ ዛሬ!" - በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ታላቅ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ተካሄደ።

በመድረኩ ከሸይኽ ሙሐመድ አንሲ ነፍስን የሚያናግሩ እና ለሕይዎት ስንቅ የሚሆኑ ምክሮች ተላልፈዋል። በወንድም ሙሐመድአሚን ካሳው ስለሙስሊም ተማሪዎች ውጣወረድ እና መፍትሄዎቻቸው ዳሰሳ ቀርቧል።

መድረኩ በደቡብ ወሎ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሐሰን አህመድ የተመራ ሲሆን ከታዳሚዎችም ጋር ገንቢ ውይይቶች እና የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደዋል።

መሰል ፕሮግራሞች በተሻለ አቀራረብ ሌሎች ቦታዎችም በአላህ ፈቃድ የሚቀጥሉ ይሆናል።

@aaumsu
🔥2
የ SBE ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት Architecture department መቀላቀል ለምትፈልጉ አዲስ ተማሪዎች ( 2nd year ) ለ መግቢያ ፈተና consultation እያዘጋጀ ይገኛል። እንዲዘጋጅ ትፈልጋላችሁ?
Anonymous Poll
57%
አዎ ይመቸኛል እመጣለሁ።
43%
አይ ይቅር አያስፈልግም
የኒቃቢስቷ መልዕክት!

ከአል-በያን ገጾች የተወሰደ...

የሰው ልጅ በሚኖርበት ምህዋር ውስጥ ይህቺ የሚኖርባት አለም: አለም ሆና ማንነቷን ይዛ ትቀጥል ዘንድ ሚናቸውን የተወጡ ብዙ ትናንሽ አለሞች አሉ። እምነት በራሱ አለምን አለም ያደረጋት አንዱ ግብአት ነው። ከእምነት ውስጥ ደግሞ እስልምና የአለሞች ሁሉ ውብ አለም ነው። ሰላት፣ ዱአ፣ ኢባዳ፣ ሰደቃ ፣ መሃባ እና ብዙ ደግሞ ኢስላምን ውብ የሆነ አለም አድርገው ያቆሙት የኢስላም የተዋቀሩ ጌጦች አሉ።

እነዚህ የተሰደሩ የሆኑ ጌጦች በጥንቃቄ እየተጠበቁ ካልቀጠልን የአንዱ ጌጥ መውጣት ስርዓተ-ጥለቱን ያጠፋል። የዲናችንን ውበትም ያደበዝዛል። ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ ደግሞ ሌሎች ጌጦቻችንን አውድሞ ከአለሞች ሁሉ ደካማው አለም የሚል ስያሜን ያሰጠናል።

ወዳጄ!! አለም ላይ ያሉ በጣም ውድ ነገሮች በሙሉ ለማንም ክፍት አይደሉም። የተሸፈኑና ከዛም በላይ በጥበቃ ውስጥ ያሉ ናቸው። ኢስላም ሴትን በሂጃባ ወይም በኒቃቧ ሊጠብቃት ኖሯል። ኒቃብ ጨርቅ ቢመስልም ከጨርቅ በላይ ነው። የኢስላም 1 ጌጥ፣ መጠበቂያ፣ መታወቂያ፣ መከበሪያ፣ የሴትነት ክብር መገለጫም ጭምር ነው። አንድን ሰው ኒቃብ ጠል ሆኖ ስታገኘው ጨርቅ ጠል ሆኖ ሳይሆን ጥብቅነትን፣ ስርአትንና ኢስላምን ጠልቶ ነው። እናም ጥላቻውን፣ ግፉንና በደሉን እሰየው ብለህ የተቀበልክ ቀን ሰላትህም፣ ጀማዐህም፣ መስጂድህም፣ ዲንህም ይጎዳ ዘንድ እሰየው ብለህ እንደተቀበልክ ቁጠረው። ስለዚህ ጠላት ኒቃብ አይሆንም ሲል ኢስላማ አይሆንም እንዳለ የተረዳህ ቀን ደግሞ ታጋይ መሆን ትጀምራለህ። ጥልቅ የሆነና እምነትህን የሚገባ የሆነ ቦታው ላይ ሆኖ እስክታየው ድረስ እንቅልፍ የሚነሳህ፣ ያለህበትን ሁኔታ የሚገልጥልህ፣ ያለፈውን አስታውሶ የሚያነቃህ፣ ለዲንህ ደግሞ መስዋእትነትን የሚያስከፍልህ ትግል ማለት ነው።

ወዳጄ!! እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለዲናችን መስዋእት የመሆን፣ ጠላት ፊት ቆሞ ለሞትና ለሸሂድነት ዝግጁ የመሆን ችግር የለብንም። ግን ያ ድሮ ወይ ዘንድሮም ቢሆን ለታጣቂ እንጂ ለእኛ አይሆንም። ምክንያቱም እንደምናየው በደም ትግል ውስጥ የመጡ መብቶቻችን በሙሉ ጊዜያዊ መብት እየሆኑ ተቸግረናል። ስለዚህ ልንነቃ ይገባል። ጊዜያዊ ሳይሆን ቋሚ የሆነ የትግል መስመር ሊኖረን ይገባል። በየትኛውም የህይወት እርከን ላይ ስናልፍ የሀገራችን እና የኢስላማዊ መብታችንን ሁኔታ ሳንዘነጋ ከስራችንም ከላያችንም ካለው ሙስሊም ወገናችን ጋር በየመሳጂዶቻችን፣ ስራዎቻችን እና ትምህርት ቤቶቻችን የተጠና እቅድ እና እምቅ የሆነ ኃይል ኖሮን መሃላችን ላይ ያለውን ክፍተት በሙሉ እየደፈንን ልንጓዝ ይገባል።

መልእክቴ ነቃቤ ተነክቷል፤ መማር አቅቶኛል። እርዱኝ ሳይሆን በኒቃብ ስያሜ ሊያጠቁ ያሰቡት የጋራ እስልምናችንን ነውና እንንቃ!! ነው።

@aaumsu
1
ለ2019 ዓ.ል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመደበኛው መርሃ ግብር  ለመማር ቅበላ ላገኛችሁ የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች መስከረም 06 እና 07 2019 ዓ.ል በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ
1.     የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒ፣
2.     አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
3.     የማደሪያ ምድብ (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ያስታውቃል፡፡
4.     ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል የዩኒቨርሲቲውን የመግቢያ ፈተና በተፈተናችሁበት UGA2019…. ቁጥር በመጠቀም ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ https://portal.aau.edu.et/NewStudents/DormitoryPlacement
5.     በተጠቀሱት ቀናት (መስከረም 06 እና 07) ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡ ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች እንዲሁም በቦሌ የአገር ውስጥ አውሮፕላን ጣቢያ ዩኒቨርስቲው ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ወደሚገኙት ካምፓሶቻችን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
6.     ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ ሆኖ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ል መሆኑን ያሳውቃል፡፡
7.     ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርስቲዉ ገለፃ የሚደረገዉ ዐርብ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ል ይደረጋል፡፡
8.     ዘግይቶ የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ል ሲሆን
9.     የ2019 ዓ.ል የመጀመሪያዉ ሴሚስተር ትምህርት የሚጀመረዉ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ል ይሆናል፡፡
10.      ስለመቁረጫ ነጥብ ስለምዝገባ ሂደቶች በተመለከተ እና ተጨማሪ መረጃ ከታች ካሉት ሊንኮች ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን::
Ø  https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome
Ø www.aau.edu.et
Ø https://t.me/aauGAT
 
   የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር

@aaumsu
👍2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን በ Self sponsorship የተመዘገቡ ተማሪዎች ወደ የትምህርት መስኮች መግቢያ ነጥብን ይፋ አድርጓል።

@aaumsu