5killo Jem'a official Channel
1.16K subscribers
1.43K photos
285 videos
75 files
674 links
This is the official channel of AAiT jem'a where we provide info abt
👉Jem'a Tutors
👉Trainings and Da'ewa programs
👉Weekly lunches and halaqas(circles)
👉qira'ts (Qur'an and other Kitabs)
👉Weekly Q&A sessions

Group: https://t.me/+cw97UaRUF1YzMTg0
Download Telegram
ወደ ዩኒቨርስቲዎች በተለይም ጂማ እና ሐረማያ ለመግባት ላሰባችሁ በዘንድሮ ኢንትራንስ ላለፋችሁ ተማሪዎች፦

ዩኒቨርስቲዎቹ ምን ይመስላሉ? ምን ምን አይነት ዲፓርትመንቶቹ አሉ? በየትኞቹ ዘርፎችስ የተሻሉ ናቸው? ከእኛስ ምን ይጠበቃል በሚሉ እና በሌሎች ነጥቦች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘናል። ስለ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ጠቅለል ያለ መረጃ ይሰጣል።

ተጋባዥ እንግዶች፦

፨ Muhammaddin Muhidin (በጅማ ዩኒቨርስቲ የ5ተኛ አመት ሜዲስን ተማሪ እና የጀመዓው ምክትል አሚር)

፨ Faris Mustefa (የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ምክትል አሚር)

የፕሮግራሙ አስተባባሪ፦ ሚፍታህ ኢብራሒም ነው።

ፕሮግራሙ፦ ነገ ማለትም እሁድ ጷጉሜ 1 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ @MohammadamminKassaw ይሰጣል። በፕሮግራሙ ላይ መመለስ አለባቸው የምትሏቸውን ጥያቄዎች @MOHAMMADAMMINM ላኩልን። መረጃውን ለሁሉም ይደርስ ዘንድም Share አድርጉት።

@aaumsu
3
1_UAT_Test_Taker_Schedule_–_AAU_Test_Site_–_September_7–8,_2026.xlsx
574.7 KB
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና ጷጉሜ 2 እና 3 ይሰጣል። የተፈተኞች ዝርዝር እና የመፈተኛ ቦታ፣ እንዲሁም የፈተና ሰዓት ከላይ ተያይዟል።

©aaumsu

@fivekjemaa
👍1
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑

ክፍል 4

ነጃሺ ኢስላምን መቀበሉን ግልጽ አድርጎ ለነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ዳብዳቤ ጻፈ::
ደብዳቤው የሚከተለው ነበር ፡-

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነውይድረስ ለሙሐመድ-የአላህ መልዕክተኛ-ከነጃሺ አስሐማ፡፡

“ከአላህ የሆነ ሰላምታ በእርስዎ ላይ ይሁን-የአላህ ነቢይ፤እዝነቱና በረከቱም ይሁንብዎ፤ ወደ ኢስላም ከመራኝ አላህ በቀር ሌላ ሊገዙት የሚገባ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ::
ከዚህም በመቀጠል የአላህ መልዕክተኛ ደብዳቤዎ ደርሶኛል። በሰማይና በምድር ጌታ እምላለሁ፡፡ ስለማርያም ልጅ ዒሳ (ኢየሱስ) የጠቀሱልኝን በተመለከተ ራሱ ዒሳም ቢሆን እርስዎ ካሉት የጨመረው ነገር የለም:: ወደኛ የተላኩበትን ምክንያት አውቀናል፡፡ እርስዎም የአላህ መልዕክተኛ መሆንዎን፣ እውነተኛ እና በሐቅ መስካሪ (ሊተማመኑብዎት የሚገባዎ) መሆንዎን ተገንዝበናል፡፡ ለዚህም ቃል ኪዳን ገብቻለሁ:: የአጎትዎን ልጅ ቃል ኪዳን ፈጽሜለታለሁ:: የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህም እጅ ሰጥቻለሁ።”

ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ኡሙ ሐቢባን (ረምላ ቢንት አቢ ሱፍያንን) ለማግባት በሁለተኛው ደብዳቤያቸው ነጃሺን ጠየቁ፡፡ ነጃሺም ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ)ወክሎ ኒካሁን አስፈጽሟል፡፡
ለኢስላም ስትል ወደ ሐበሻ ከነባሏ የተሰደደችው ኡሙ ሐቢባ ቢንት አቢ ሱፍያን ባሏ እምነቱን በመቀየሩና በመሞቱ ነቢዩ እጅግ አዘኑ፡፡
ልቧ ክፉኛ የተሰበረውን ኡሙ ሐቢባን ራሳቸው ለማግባት ወሰኑ፡፡ ለዚህም ነበር በዐምር ኢብኑ ዑመያ አል-ደሚሪይ አማካኝነት መልዕክት ወደ ነጃሺ የላኩት:: ነጃሺም መልዕክቱ ሲደርሰው ለኡሙ ሐቢባ ቢንት አቢ ሱፍያን በቤተ መንግሥቱ አገልጋይ በነበረችው አብረኸት መልዕክት ላከባት:: ልቧ ተሰብሮ የነበረው ኡሙ ሐቢባ ዜናው በአብረኸት አማካኝነት ሲደርሳት እጅግ ተደሰተች፡፡ ጋብቻው ይፈጸም ዘንድ ኻሊድ ቢን ሰዒድን ወከለች:: እጅግ ከመደሰቷ የተነሳም የምሥራቹን ለነገረቻት አብረኸት የተለያዩ የብር ጌጣጌጦችን ሰጠቻት::
ይህ ውቡ ታሪካችን ነው ከራስ አልፎ ለሌላው አለም መትረፍን የምንማርበት ፤ንጉስ ነጃሺም ከራሳቸው አልፈው ሌሎች በሃቅ ጎዳና ላይ እንዲገኙ ሚናቸውን በሚገባ ተወጥተዋል።

ነገር ግን የነጃሺ መስለም ዛሬም ድረስ ሲተረክ ለመቀበል የማይፈልጉ አካላት አሉ::
በእርግጥ እነኚህ ወገኖች አንድ የክርስቲያን ንጉሥ ሊሰልም የማይችልበትን ሁኔታ ማሳየት አልቻሉም።

ያለ መረጃ እንዲሁ ማጣጣልን መርጠዋል::
ነጃሺ ኢስላምን መቀበሉ ብቻ ሳይሆን ዳዕዋ በማድረግ ያስለማቸው ግለሰቦችም ነበሩ።

ከነዚህ መካከል ዐምር ኢብኑል ዓስ ይገኝበታል። ዐምር ሶሓቦችን
ወደ መካ ለማስመለስ ተልኮ ሳይሳካለት ከተመለሰው የቁረይሽ ልዑክ አንዱ እንደነበር ይታወሳል።
በበርካታ ጥንታዊ ኢስላማዊ መዛግብት ላይ እንደተዘገበው ዐምር ኢብኑል ዓስ ኢስላምን የተቀበለው በንጉሥ ነጃሺ እጅ ነበር።
ይህ ሊሆን የቻለው ዳግም ወደ አክሱም በተመለሰበት ጊዜ ነበር፡፡ ዐምር ኢብኑል ዓስ እንዲህ ይተርክልናል፡-
ከኸንደቅ ጦርነት በኋላ ከቁረይሽ ጎሳ መካከል ንግግሬን የሚሰሙኝንና የሚያከብሩኝን ሰዎች ሰበሰብኩ፡፡
“እንደምታዩት የሙሐመድ ነገር (ለኛ) ከቀን ወደ ቀን በሚያስጠላ ሁኔታ እያየለና እየበረታ ሄደ። እኔ አንድ ሐሳብ አለኝ::
በርሱ ላይ ምን ትላላችሁ? ስል ጠየቅኳቸው:: ‹‹ምን አሰብክ?›› አሉኝ፡፡
‹‹ወደ ነጃሺ እንሂድና ከእርሱ ዘንድ እንሁን፡፡ ሕዝባችንን ሙሐመድ ካሸነፈ በነጃሺ ግዛት ስር ሆንን ማለት ነው፡፡ ከርሱ ዘንድ መሆናችን በሙሐመድ ሥር ከመሆን ይልቅ ለኛ የተወደደ ነው:: ሕዝቦቻችን ካሸነፉ ደግሞ በእርግጥ በነርሱ ዘንድ ስለምንታወቅ መልካም ሁኔታ እንጂ አይገጥመንም›› አልኳቸው::
‹‹መልካም ነው› በማለት ከኔ ሐሳብ ጋር ተስማሙ:: ለነጃሺ የሚሰጡትን ስጦታዎች እንዲያሰባስቡ ነግሬያቸው ወደርሱ አገር ተጓዝን::

የነቢዩ መልዕክተኛ ዐምር ኢብኑ ዑመያ አል ደሚሪይ በነ ጃዕፈርና በሶሓባዎች ጉዳይ ከነጃሺ ዘንድ ገብቶ ሲወጣ አየነው::

ለወዳጆቼ “ይህ ዐምር ኢብኑ ዑመያ አል-ደሚሪይ ነው:: ከነጃሺ ዘንድ ገብቼ ስጦታዎችን ሰጥቼው የዚህን ሰው አንገት እንድቆርጥ (እንድገድለው) ጠይቄ ቢፈቅድልኝና ይህን ባደርግ የሙሐመድን መልዕክተኛ በመግደሌ ቁረይሾች ትልቅ ውለታ እንደዋልኩላቸው (ምንዳ እንደከፈልኳቸው) ይቆጥሩ ነበር›› አልኳቸው:: ነጃሺ ዘንድ ገባሁ:: ከዚህ በፊት እንደማደርገው ለርሱ (ለሰላምታ) አጎነበስኩ፡፡

ነጃሺም ‹እንኳን ደህና መጣህ ወዳጄ›› አለኝ:: በርካታ ስጦታም ሰጠሁት:: (በኋላ ላይም) ዐምር ‹‹የጠላታችን ሙሐመድ መልዕክተኛ ከአንተ ዘንድ ገብቶ ሲወጣ አየሁት:: (ከቁረይሽ) ታላላቆቹና ምርጦቹ ተገደሉ፡፡
ስጠኝና ይህን ሰው ልግደለው›› ስል ጠየቅሁት::
ነጃሺ በጥያቄው ክፉኛ ተናደደ።
ዐምርም በነጃሺ አኳኋን ተደናገጠ፡፡
‹‹ምናለ መሬት ተቀዳ በዋጠችኝ!›› እስኪል ድረስ የቁጭት ስሜት ተሰማው፡፡

‹‹ንጉሥ ሆይ! ይህ ጉዳይ እንዲህ የሚያናድድዎ መሆኑን ባውቅ አልጠይቆትም ነበር›› ሲል ተናገረ፡፡

ነጃሺም ‹‹ለሙሴ ይመጣ የነበረው መልአኩ ገብርኤል (ጂብሪል) የሚመጣለትን ሰው መልዕክተኛ ልትገድል ትጠይቀኛለህን?›› ሲል በቁጣ ተናገረ፤ገሰጸው፡፡
ዐምርም ‹‹ንጉሥ ሆይ! እንደዚያ ነው እንዴ?›› ሲል ጠየቀ።
ነጃሺም ‹‹ወየውልህ ዐምር! እኔን ታዘዘኝና እርሳቸውን (ነቢዩ ሙሐመድን) ተከተላቸው፡፡ በአላህ እምላለሁ! ሙሴ በፊርዓውንና ሠራዊቱ ላይ ድል እንዳደረገ ሁሉ
ሙሐመድም በእውነት በተቃዋሚዎቹ ላይ ድል ማድረጉ የማይቀር ነው› አለ፡፡

ዐምር ‹‹በኢስላም ላይ ቃል ኪዳን ተጋባኝ›› ሲል ነጃሺን ጠየቀ። ነጃሺም “መልካም›› በማለት እጁን ዘርግቶ ከዐምር ኢብኑል ዓስ ጋር በኢስላም ላይ ቃል ኪዳን ተጋባ። በነጃሺ ግሳጼና ዳዕዋ የተማረከው ዐምርም ኢስላምን በነጃሺ እጅ ተቀበለ።

ዐምር ትረካውን ይቀጥላል፡- “እጄን ዘርግቼ በኢስላም ላይ ቃል ኪዳን ተጋባሁ:: ከርሱ ዘንድ ስወጣ መስለሜን ከወዳጆቼ ደበቅሁ:: ወደ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ተጓዝኩ:: ጊዜው ከፈትህ (hመካ በድል መከፈት) በፊት ነበር፤ወደ መዲና ስሄድ በመንገድ ላይ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን አገኘሁት::

የሱለይማን አባት ወዴት ነው?› ስል ጠየቅኩት:: ሊሰልም እንደሚሄድ ነገረኝ። «በአላህ ይሁንብኝ! እኔም ለእስልምና ስል ነው የመጣሁት› ስል ገለጽኩለት::
መንገድ ላይም ዑስማን ቢን ጠልሀን አግኝተው ተያይዘው ሄዱ፡፡
ዐምርም ሙስሊምነቱን ይፋ አድርጎ ከነቢዩ ጋር ቃል ተጋባ፡፡
ነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) አገኛቸውና ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኔ ያለፈው ወንጀሌ እንዲማርልኝ  መስፈርት በማድረግ ከርስዎ ጋር ቃል ኪዳን ልጋባ›› አላቸው፡፡ ነቢዩም (ሶ.ዐ.ወ) ‹‹ዐምር ሆይ! ቃል ኪዳን ተጋባኝ! ኢስላም ከርሱ በፊት የነበረውን ኃጢአት ያብሳል:: ስደትም ከርሱ በፊት የነበረውን ያብሳልና›› አሉ::

በነጃሺ እጅ የሰለመው ዐምር ኢብኑል ዓስ ያለፈው ወንጀሉና ጥፋቱ እንዲማርለት ከነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር ቃል ኪዳን ተጋባ፡፡
በዚህም ሐበሻዊው ሙስሊም ንጉሥ ነጃሺ ዐምርን ማስለም ቻለ፤
ዐምርም በ640 ግብጽን በመክፈት ከእስላማዊው የኸሊፋ ግዛት ጋር የቀላቀለ ታላቅ ሳሃባ ነበር።
በእርግጥም ኋላችን ትግል ያዋዛው፣ መማሪያ፣ መገሰጫ እና መንቂያ ደዉል መሆን በሚችል መልኩ ሰፍሯል።
እኛስ?ለወደፊቱ ትውልድ መቅረቡ ግድ የሆነውን ታሪካችንን በምን መልኩ እየጻፍነው ይሁን?

የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል…

@aaumsu
1
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑

የመጨረሻው ክፍል

ከዚህ ሁሉ በኋላ ሶሓቦች ወደ መዲና ተጓዙ፡፡
ጃዕፈርንና ኡሙ ሐቢባን ጨምሮ በሐበሻ የቀሩት ሶሓቦች ወደ መዲና የተመለሱት በሰባተኛው ዓ.ሂ. በኸይበር ዘመቻ ጊዜ ነበር፡፡

ነቢዩም የነጃዕፈርን መምጣት ባዩ ጊዜ ‹‹በኸይበር ዘመቻ ድል ወይስ በጃዕፈር መምጣት ልደሰት?›› ሲሉ ተናግረዋል::ቁጥራቸው ወደ ሃያ የሚጠጉ ሶሓቦች ደግሞ በሐበሻ እያሉ በማረፋቸው በስደት አገራቸው (ኢትዮጵያ) ተቀብረዋል::

ኢማሙ ጦበሪ እንደዘገቡት ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) በኸይበር ዘመቻ ላይ ሳሉ እነ ኡሙ ሐቢባ መዲና ደረሱ፡፡

ኡሙ ሐቢባ ሁኔታዉን እንዲህ ትተርክልናለች፡- ‹‹ወደ ነቢዩ ገባሁ። ስለ ነጃሺ ይጠይቁኝ ነበር፤እኔም የአብረኸትን ሰላምታ አደረስኩኝ፤ነቢዩም ለሰላምታው ምላሽ ሰጡ::
እነጃዕፈር ወደ መዲና ከተመለሱ በኋላ ነጃሺ ወደ አላህ መልዕክተኛ ልጁን አዝሂያ (አርማ) ከስልሳ ሐበሻውያን ጋር  “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በእርግጥ እርስዎ የአላህ መልዕክተኛ መሆንዎን እመሰክራለሁ፡፡ ….ልጄን አርማ አስሐማን ወደ እርስዎ ልኬያለሁ:: ከራሴ በቀር ሌላ የለኝም፤መምጣቴን የሚሹ ከሆነ እመጣለሁ›› የሚል መልዕክት የሠፈረበት ደብዳቤ ላከ፡፡
ይህን መልእክት ይዘው በመርከብ በመጓዝ ላይ ሳሉ በባህር ላይ በተነሳ ማዕበል ሞቱ::

የነቢዩ መሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) አስተምህሮት እዚያው በአካል ተገኝተው እንዲያደምጡ በማለትም ነጃሺ የተመረጡ ሰባት ቀሳውስትና አምስት (ባህታውያን) መነኩሴዎችን ያቀፈ ልዑክ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ልኳል፡፡ እነርሱም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ዘንድ ደርሰው ቁርኣንን ሰሙ፡፡ያሏቸውን ጥያቄዎች ነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) ጠየቁ:: አስተምህሮታቸውን አደመጡ፡፡ በዚህ ጊዜ ከአላህ የተላኩ ነብይ መሆናቸውን አመኑ። ይጠበቅ የነበረውን ነብይ አግኝተው ከአንደበቱ እውነትን በመስማታቸው የሲቃ ለቅሶ አለቀሱ፡፡ ኢስላምንም ተቀበሉ። እምነታቸውንም ለነቢዩ ግልጽ አደረጉ::

አላህ (ሱ.ወ) ለእውነተኛ አማኝነታቸው እውቅና ሰጣቸው:: የነዚህን ሐበሻውያን የሃይማኖት አባቶችን መስለም አስመልክቶ አላህ እንዲህ ሲል ቁርኣን አወረደ፡-

{ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَى أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ (83) وَمَا لَنَا لا نُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا جَاءَنَا مِنَ الْحَقِّ وَنَطْمَعُ أَنْ يُدْخِلَنَا رَبُّنَا مَعَ الْقَوْمِ الصَّالِحِينَ (84) فَأَثَابَهُمُ اللَّهُ بِمَا قَالُوا جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَذَلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ (85) وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ (86) }


ወደ መልክተኛውም የተወረደውን (ቁርኣን) በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፤ ጌታችን ሆይ! አመንን፤ ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን ይላሉ፡፡
በአላህና ከእውነትም በመጣልን ነገር የማናምን፣ ጌታችንም ከመልካም ሰዎች ጋር ሊያስገባን የማንከጅል ለኛ ምን አለን?› (ይላሉ)፡፡
ባሉትም ምክንያት አላህ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ መነዳቸው፤ ይህም የበጎ ሠሪዎች ዋጋ ነው:: እነዚያም የካዱና በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው::



ይህ የቁርኣን ጥቅስ የወረደው ኢስላምን በተቀበሉ ሐበሻውያን ምክንያት ነበር።ታላቁ የቁርኣን ተንታኝ ኢማም ኢብኑ ከሲር ‹‹ተፍሲር አል-ቁርአኑል ዓዚም›› በተሰኘው የቁርኣን ማብራሪያ መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ኢስላምን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ነጃሺ ተመልሰዋል፡፡ ስለ ነቢዩም (ሶ.ዐ.ወ) ለነጃሺ ነግረዋል፡፡ ነጃሺ ኢስላምን ቀድሞ ቢቀበልም ከእነርሱ ከሰማ በኋላ ወደ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ለመሄድ ጉዞ ጀምሮ ነበር። ግና ከአክሱም ከወጣ በኋላ በስደት (በጉዞ ላይ) በመንገድ ላይ ሞቷል::

በሐበሻ ነጃሺ መሞቱን በእለቱ ጂብሪል ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ነገራቸው፤
አስሐማ የሞተው በ630 ነበር፡፡ እርሱ በሞተ እለት ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ወደ በቂእ የሶሓቦች ቀብር ስፍራ ሄደው ሶላተል ጋኢብ ሰግደውበታል፤  በሐበሻ የሞተውን የነጃሺን ቀብር አላህ እያሳያቸው ከአጠገባቸው እንዳለ አስክሬን በአደባባይ ሶላት ሰግደውበታል::
በሶላቱ ተካፋይ ከነበሩት ሶሓቦች መካከል ጃቢር፣ አነስ ኢብኑ ማሊክና ዐብደላህ ኢብኑ አባስ ስለክስተቱ አስተላልፈውልናል፡፡

ተከታዮቻቸውን ለሶላት ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሲጣሩ አንዳንድ መናፍቃን እርስ በርሳቸው ‹‹ሙስሊም ባልሆነ ሰው ላይ እንስገድን?›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ እንዲህም አሉ፡-

انظروا إلى هذا يصلي على علج حبشي نصراني لم يره قط وليس على دينه

‹‹ይህን ሰው ተመልከቱ፡፡ በጭራሽ አይቶት በማያውቀውና የሃይማኖቱ ተከታይ ባልሆነ ሐበሻዊ ክርስቲያን ላይ ይሰግዳል ደግሞ!›› ሲሉ ተናገሩ፡፡

አላህም የሐበሻዊው ንጉሥ ነጃሺ ኢስላምን መቀበሉን በማረጋገጥ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ አወረደ:-

وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَنْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا أُولَئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِنْدَ رَبِّهِمْ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

(سورة : آل عمران آية 199)

ከመጽሐፉ ሰዎች መካከል አላህን ፈሪዎች፣ በአላህ አናቅጽትም ጥቂትን ዋጋ የማይሸምቱ ሆነው በአላህ የሚያምኑ፣ ወደእናንተ የተወረደውንም ወደነርሱ የተወረደውንም (እውነት የሚቀበሉ) ወገኖች በእርግጥ ይገኛሉ:: እነርሱ ከጌታቸው ዘንድ (የላቀ) ምንዳ ተዘጋጅቶላቸዋል:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡


እንግዲህ ይህ የእውነት እምነትና ጽናት ተምሳሌት የሆነው ውዱ ንጉሳችን ነጃሺ ታሪክ ነው።

በርግጥም ይህንን የተገነዘበ ማንኛውም ሙስሊም ያለፈው ታሪኩ በዚህ ልክ መስዋእትነት የተከፈለበት፣ የኢስላም ባንዲራን ከፍ ለማድረግ ለአላህ ተብሎ ዝቅ የተባለበት መሆኑን በመረዳት

እኔስ ? ዛሬ ምን ልስራ ማለት ይኖርበታል

ተፈጸመ።

ሃሳቦቻችሁን በ @Niqab_issueBot ያጋሩን

@aaumsu
1🥰1
በአባጅፋሯ ጅማ የተገፈፈ ክብር፤ የተከለከለ ሒጃብ ... በአባጅፋር ልጆች የተደረገ ትግል፤ የተከፈለ መስዋዕትነት፤ የተረጋገጠ ክብር --- በጅማ ዩኒቨርስቲ !

ሕያው ምስክር - 2

አባጅፋር (ረህመቱላሂ ዐለይሂ) ከጅማ መምለካ ተሻግረው፤ ሐበሻንም አቋርጠው ስለሙስሊሞች መብት የሚብሰለሰሉ፤ የሚታገሉ፤ መስዋዕትነት የከፈሉ ታላቅ እና ፍትሐዊ ንጉስ ነበሩ። ሆኖም ግን ከአመታት ቡሃላ፤ በጅማ ከተማ፤ በጅማ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ባይተዋር ሆኑ። ሙስሊም ስለሆኑ ሊለብሱት ግዴታ የሆነውን ሒጃብ (ኒቃብ) ከመልበስ ተከለከሉ። ለተከታታይ አስር አመታት ያክል በተለያየ ጊዜ፤ በተለያዩ ሰዎች ክብራቸው ተደፈረ።

ይህ እየሆነ ባለበት በ2017 ዓ.ል የአባጅፋር ልጆች መብታቸውን ያስከብሩ ዘንድ የአላህ ፍቃድ ሆነ። በወርሐ ረመዷን ከተራዊህ መልስ ኒቃቢስት ተማሪዎች ወደ ግቢ ካልገቡ እኛም አንገባም በማለት ለተከታታይ አራት ቀናት ታገሉ። መሪዎቻቸው ቢታሰሩም ፀንተው ቆሙ። በአላህ ፈቃድም በፍትሐዊው ንጉስ ሐገር የተነፈገው ነፃነት ተከብሮ ፍትሕ ፀና።

የነበረውን ሂደት፤ የተፈጠሩትን ክስተቶች፤ የመጣውን ውጤት በሕያው ምስክር - 2 የምንዳስስ ይሆናል።

መስከረም - 1
ጁምዓ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ !

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share ያድርጉ።

@aaumsu
3
Ok
AAU - Muslim Students Union
የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ

ሀገራዊ ምክክር ምንድን ነው? ሂደቱ እንዴት ነበር? ከውጤቱስ ምን እንጠብቅ? ከእኛስ ምን ይጠበቃል?

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት ከሆነው ሙሐመድአሚን ካሳው ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

ያዳምጡ፤ ለሌሎችም share አድርጉ።

@aaumsu
Entering The Tech World
ሙሐመድ ተሾመ ተጋባዥ እንግዳችን ነው

የቴክኖሎጂው አለም በግስጋሴ ላይ ነው። እንዴት መግባት እና መዝለቅ እንዳለባቸው ያላወቁትም ወደሗላ እየቀሩ ነው። ይህንን ክፍተት ለመድፈን አጠቃላይ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ያስፈልጋል። እኛም ሁሉንም ሊያማክል በሚችል ርዕሰ ጉዳይ በዘርፉ ልምድ ያለውን እንግዳ ጋብዘናል። ተማሪዎች፤ ምሩቃን፤ በስራው አለም ውስጥ ያላችሁ ሰዎች፤ ሀላችሁም ተጋባዥ ናችሁና በሰዓቱ ተገኝታችሁ ታደሙ።

ተጋባዥ እንግዳችን፦

ሙሐመድ ተሾመ፦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የSoftware engineer ምሩቅ፤ የ Immersive Learning መስራች (በYoutube ብቻ ከ200 በላይ ቪድዮዎችን የሰራ ሲሆን ከ30K በላይ Subscribers አሉት) እንዲሁም በሌሎች ቴክኖሎጂ ነክ የሚንቀሳቀስ ሲሆን Senior Software and Ai Engineer ነው።

ሚፍታህ ኢብራሒም መድረክ መሪያችን ነው። መነሳት አለባቸው ብላችሁ የምታስቧቸውን ነጥቦች @Mohammadamminm ከወዲሁ ይላኩ።

@MohammadamminKassaw
👍52🔥1
እውነትም፣ እስልምና ሰላምን የሚያስተምር፣ በጽናት ለእውነትና ለፍትሕ መቆምን የሚያስተምር እምነት ነው!!

ጂማ ዩኒቨርሲቲ ብዙ የመስዋትነትን ታሪኮችን ከጀርባው ያዘለውን ውዱን የሙስሊም ሴት ሂጃብ ለተማሪዎቹ አጀንዳ ካደረገ ረጅም ጊዜን አስቆጥሯል። በነዚህ ሁሉ ጊዜያት ሰላምን መንገዳቸው ጽናትን መለያቸው ያደረጉ የግቢው ሙስሊም ተማሪዎች እስልምና የሰላም እምነት መሆኑ በ ተግባር ከኖሩት ውስጥ ተጠቃሾቹ ናቸው••

የአባጂፋር ሀገር ጂማ ስትጠራ፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በስፋት የሚኖርባት አካባቢ መሆኗ ከሚገልጿት ቀዳሚ መገለጫዎቿ አንዱ ነው። ታዲያ ሂጃብን አንዱ የ ሂወቱ ክፍል አድርጎ ሚኖር ማህበረሰብ ውስጥ
🎯ሂጃብ ለ ትምርት ስኬታማነት እንቅፋት
🎯ሂጃብ ለ ግቢውና ለማህበረሰቡ የ ደህንነት ስጋት ሆኖ ሊቀርብ የቻለው በምን አግባብ ነው ?
!

እንዴትስ ሂጃብን የ ሕይወት መርህ ብሎ ልጁን ያስያዘ ማህበረሰብ ውስጥ በሂጃብ ጥያቄ ምክንያት ተማሪዎችን ማግለል፣ ማንከራተት፣ ማሰር አልፎም ከግቢው ማባረር ጋር መድረስ ተቻለ ?!

ሕያው ምስክር ~2~ የጂማ ዩኒቨርሲቲ የ ነጻነት ጉዞ!

ተጋባዥ እንግዶች
አብዲ ኮርማ ~ በጊዜው የጂማ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አግሪ ካምፓስ አሚር
ሱደይሲ አብዱረሕማን~ የጂማ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር


🗓መስከረም-1 የፊታችን ጁምዐ!
🕞ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ!

@aaumsu
21
ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ
በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!

ጁምዓ (መስከረም 1) ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !

የአባ ጅፋር ልጆች የሰሩትን ትግል፤ የከፈሉትን መስዕዋትነትን ሕያው ምስክር ሆኖ እንቃኛለን። በደልን አንቀበልም ብለው እስር ቤት እስከማደር ስለደረሱት የጁማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል እንቃኛለን።

ቻለንጁን እንቀላቀል !

@aaumsu
👍1🔥1
🔥ከሙተነቂቦች መንደር ~ 1
ጂማ ዩኒቨርሲቲ!🔥


“...ከዚህ በላይ ስማቸው የተጠቀሱ ተማሪዎች የሃይማኖት መግለጫ በሆነው አለባበስ፣ ከሚከለከሉት አንዱ ጀለቢያ፣ ጥምጣም እና ማንነታቸውን በማይገልጽ አለባበስ ኢቃም ፊታቸውን ሸፍነው ግቢ ውስጥ በመንቀሳቀስ፣ እንዲሁም የተማሪዎች መመገቢያ ካፌ ለመመገብ ሲሄዱ መያዛቸውን አሳውቀውናል። ስለዚህ ሦስቱ ተማሪዎች የአለባበስ የዲሲፕሊን መመሪያ ጥሰው ስለተገኙ፣ የተከለከሉ ተግባራትን ለሚያከናውኑ ተማሪዎች መማሪያ ይሆን ዘንድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመሪያ ቁጥር 002/012 መሠረት በተማሪዎች ዲሲፕሊን ታይቶ እንዲቀጡ…”


🍂ኒቃብ የለበስኩት የግቢ ተማሪ እያለው ነበር በሰዓቱ ግቢው ኒቃብ ካለመፍቀዱም በላይ ማስክ ለብሰው ያገኟቸውን ልጆች እንኳ ID በመቀማት የሚያስተጓጉሉበት ወቅት ነበር።

ከኒቃብ ጋር ተያይዞ ብዙ አይነት ፈተናዎች ይኖራሉ እኔም ጋር ከነበሩት ውስጥ አንዱ በክፍል ውስጥ ከ አስተማሪ ጋር የነበረ የ እለተእለት ማስጠንቀቂያ ነበር••• አስተማሪው attendance ለመሙላት የሁሉንም ስም በሚጠራበት ጊዜ ሁሌም ስሜን ከጠራ ቡሃላ ጠቋሚ ጣቱን እያወዛወዘ "ይሄ ነገርሽን ዝቅ አድርጊ ብያለው " ይል ነበር ወደ ለበስኩት ማስክ እያመላከተ... አንዳንዴም ብቻዬን እየጠራኝ አለባበሴን እንዳስተካክል ይነግረኝ ነበር

ከሁሉም በላይ ግን እኔ ዘንድ ላይረሳ በደማቁ የተፃፈው "ኒቃብ ለብሳችሁ በመገኘት" ተብሎ ከ 2 ጓደኞቼ ጋር ከ ዲስፕሊን ቢሮ ቀርቦብን የነበረው ክስ ነው!! መጀመርያ ID ሲቀሙን እንደሌላ ጊዜው በነጋታው ይመልሱልናል ብለን ስንጠብቅ ነገሩ ከሮ ከጥበቃና የደህንነት ክፍል ለጂማ technology institute ተማሪዎች discipline ኮሚቴ ለሌሎች ተማሪዎች መማርያ በሚሆን መልኩ እንድንታረም ሚጠይቅ የክስ ደብዳቤ ገባ..


🗓መስከረም - 1 ከምሽቱ 3:00! ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ቴሌግራም ገጽ እንገናኝ!"

@aaumsu
👍3
💫ልዩ የዳእዋ ፕሮግራም ለእህቶች💫

ሂጃብ እና የዘመኑ ፈተና

አላህ ሱ.ወ ሴትን ልጅ ካላቀበት እና ካከበረበት ነገሮች ውስጥ ሂጃብ አንዱ እና ትልቁ ነገር ነው።የተስተካከለ አለባበስ የአንዲት ሙስሊም ሴት ጥብቅነት መገለጫም ጭምር እንደሆነ ተቀምጦልናል። ታድያ አለባበሳችን ምን መምሰል አለበት...ምንድነው ሂጃብ መስፈርቶቹ እንዲሁም ምንድነው የተፈለገበት .....እሚለውን እና ሌሎችንም ለማውራት ቀጠሯችንን የፊታችን ቅዳሜ በታላቁ ሁዘይፋ መስጂድ አድርገናል።

ምን እሱ ብቻ ..

ከሂጃብ ጋር እየመጡ ያሉ ትምህርት ላይ እንቅፋት የሆኑ ክልከላዎች እና ዘመን አመጣሽ ውጣውረዶች ምንድናቸው ? በምን መልክ ማለፍ እንችላለን ? ለሚመጣውስ ትውልድ ምን ማበርከት እንችላለን ? የሚለውንም የምናነሳ ይሆናል።

ቦታ፡- ሁዘይፋ መስጂድ (የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ)
ቀን ፡- የፊታችን ቅዳሜ
ሰአት ፡-3፡00-6፡00
ተጋባዥ ፡- ሁሏም እህት ሁሏም እናት ሁሏም ተማሪ (አዲስ ግቢ የምትገቡ ተማሪዎች ብትመጡ በደንብ ትጠቀማላቹ)

@aaumsu
👌5
ጥቂት ሰዓታት ብቻ ይቀሩታል!

ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ

በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!

ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !

@aaumsu
Forwarded from 5K Muslim Developers Circle(MDC)
💎የውመል ጁሙአ(ተወዳጁ ቀን)💎

💎 { ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ }

      ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ 


🌸የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

" የውመል ጁሙአ ቀኑንም ማታውን እኔ ላይ ሰለዋት ማድረግን አብዙ፡ እኔ ላይ አንድን ሰለዋትን ያወረደ አሏህ በሱ ላይ አስር ሰለዋት
ያወርድለታል........

🌸"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشراً"

ሰለዋት ልብን ያረጋጋል፣
ሰለዋት  ጭንቀትን ይቀንሳል፣
ሰለዋት ከአላህ ዘንድ በረካ እና ምህረትን ያመጣል፣

ዛሬ ጁሙአ ነው በረሱል ﷺ ላይ ሰለዋት አውርደናል
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد ﷺ
ብዙ ያልተነኩና የልተዳሰሱ አሻራዎች ያሉበት መንገድ!

ሕያው ምስክር ~ 2 ~ ጅማ ዩኒቨርስቲ የነፃነት ትግል!!

🗓 ዛሬ ከ ምሽቱ 3:00 እንገናኝ!


@aaumsu
ሕያው ምስክር - 2 - 3:00 ላይ ይጀመራል!

ከ2 ሰዓት ያነሰ ጊዜ ቀረን ማለት ነው። ስለ አባጅፋሯ ጅማ፤ ስለአባጅፋር ልጆች የመብት ጥያቄ ሂደት ከሕያው ምስክሮች ጋር ልዩ ቆይታ ይኖራል። መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ። ሰከንድ ሳያልፍ በሰዓቱ እንገኝ።

የጥያቄ አለን ትውልድ የሚዘነጋው ትግል የለም!

@aaumsu
1 ሰዓት ብቻ ቀረው!

ዝግጁ?

@aaumsu
"የጀመዓ ትልቁ ኃላፊነት የተማሪዎችn መብት እና ደህንነት ማስጠበቅ ነው።"

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
ችግሩን እንፈታለን ብለው ቃል የገቡ አካላት መጨረሻ ላይ ፈሩ፤ ችግሩን መፍታት አልቻሉም።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu