5killo Jem'a official Channel
1.16K subscribers
1.43K photos
285 videos
75 files
674 links
This is the official channel of AAiT jem'a where we provide info abt
👉Jem'a Tutors
👉Trainings and Da'ewa programs
👉Weekly lunches and halaqas(circles)
👉qira'ts (Qur'an and other Kitabs)
👉Weekly Q&A sessions

Group: https://t.me/+cw97UaRUF1YzMTg0
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙስሊም ተማሪዎችን የፍትሕ ጥያቄ አስመልክቶ የፋና ምላሽ ምን ነበር። https://vt.tiktok.com/ZSVWUFjV9/ ያዳምጡ። ሪፖስት በማድረግም ተደራሽነቱን ያስፉ።

@aaumsu
😡4❤1
5killo Jem'a official Channel
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑 ክፍል 1 ከዘመናት በኋላ በታሪክ ውስጥ አሻራውን ጥሎ ያለፈ አንድ ታላቅ ሰው ወዳፈራችዉ ምድር እንሻገር………… በዙሪያው ያለው ኃይል ሁሉ በእጁ በነበረበት ጊዜ ✨በምሕረቱ፣ ማንም ሊገዳደረው በማይችልበትና ሊበድል ቢፈልግ አንዲት ስራው በቂ በነበረችበት ሰዓት ደግሞ ✨በፍትሑና በዕኩልነቱ የታወቀ ንጉሥ። ዓለም በሩን የከፈተለት፣ ተግባሩ ምንም ኃይልና አቅም የሌላቸውን…
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑

ክፍል 2


ቅንነት ካለ፣
ሰብአዊነት ካለ ፣
ሰላም የሆነውን እምነታችንን እና ሙስሊሞችን ለመቀበል ልቦች በሮቻቸውን ይከፍታሉ።

ነጃሺም ያደረገው ይህንን ነው። ቅን ነበር፣ለቅኖችም ልቡን ክፍት አደረገ፣አላህም በሂደት የሂዳያን መንገድ አገራለት።

የነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች በሀበሻ የገጠማቸውን እንዲህ ሲሉ መስክረዋል:-

“ሀበሻ ገባን። መልካም ጎረቤቶችንም አገኘን። በሃይማኖታችን ምክንያት የሚደረግብን ተጽእኖ አልነበረም። አላህን በሰላም መገዛት ጀመርን። አንድም ችግርና መከራ አላጋጠመንም። የምንጠላውን ነገር አልሰማንም።”


ይህ ሰላም ፣ ሰላም የነሳቸው ቁረይሾች  ሀበሻን ቀደም ሲል በንግድ የሚያውቋትን ሁለት ግለሰቦች ያቀፈ ልዑክ ለመላክ ወሰኑ::
ዐብደሏህ ቢን አቢ ረቢዓህ እና ዐምር ኢብኑል ዓስ ስጦታዎችን ይዘው ሐበሻ ደረሱ፡፡ በነጃሺ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደርም እርሱን ከማናገራቸው በፊት ለቀሳውስቱ ስጦታዎችን በማበርከት የመጡበትን ዓላማም አስረዷቸው::
ቀሳውስቱም ደገፏቸው:: ከነጃሺ ፊት በቀረቡ ጊዜም ዐምርኢብኑል ዓስ እንዲህ ሲል ተናገረ፡-

“ንጉሥ ሆይ! በአገርዎ የኛ ሕዝብ አካል የሆኑ ቂላቂል ልጆች ይገኛሉ:: የሕዝባቸውን ሃይማኖት ትተዋል:: ወደ እርስዎ ሃይማኖትም አልገቡም:: እኛም ሆንን እርስዎ የማናውቀውን አዲስና መጤ ሃይማኖት አምጥተዋል:: እኛም ከሕዝባቸው መሪዎችና ልዑላን እንዲሁም ከአባቶቻቸው፣ ከአጎቶቻቸውና ከቅርብ ዘመዶቻቸው ነው የተላክነው:: ወደነርሱ ይመልሷቸው ዘንድ እንሻለን:: እነርሱ (ሹማምንቱ) ከነርሱ የላቀ አመለካከት ያላቸው ናቸው:: በእነርሱ ላይ የፈጸሙትንም ነውር በሚገባ ያውቃሉ:: ለዚህም የሚገባቸውንም ቅጣት ይሰጧቸዋል::”

በስፍራው የነበሩት ቀሳውስትም፡-

“ንጉሥ ሆይ! እኝህ ሁለት ሰዎች የሚሉት እውነት ነው:: የራሳቸው ወገኖች ስለስደተኞቹ የሚያቀርቡት ነገር ይበልጥ ተቀባይነት አለው። በእነርሱ ላይ የፈጸሙትንም ነውር የሚያውቁት እነርሱ ናቸው። ስለዚህ አሳልፈው ይስጧቸውና ወደ ሀገራቸው ይመልሷቸው “
አሉ።

ንጉስ አስሃማ ግን ሁለቱንም ወገን ለመስማት ወሰኑ። ከሰሀቦችም መሪ የነበረው ጃዕፈር ኢብኑ አቡ ጧሊብ ከልብ የወጣ ልብ ይገባል እንዲሉ እንዲህ ሲል ተናገረ:-


“ንጉሥ ሆይ! የድንቁርና ሥርዓት ተከታይ ሕዝቦች ነበርን፡፡

ጣዖታትን እንገዛለን፤የበከተ እንበላለን፤ ዝሙት እንፈጽማለን፡፤ዝምድና እንቆርጣለን፡ በጎረቤቶቻችን ላይ እኩይ ተግባርን እንሠራለን::

ጠንካራው የደካማውን ገንዘብ ይበላል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ እያለን ነበር ….ዘሩን፣ እውነተኛነቱን፣ ታማኝነቱንና ጨዋነቱን የምናውቀው መልዕክተኛ አላህ የላከልን፡፡

ይህ ነብይ ወደ አላህ ጠራን፣አላህንም አንድ አድርገን እንድንገዛው፣ እኛም ሆንን አባቶቻችን ስንገዛ የነበረውን ድንጋይና ጣዖት እንድንተው አስተማረን፡፡

እውነት እንድንናገር፣ አደራ እንድንጠብቅ፣ ዝምድናን እንድንቀጥል፣ ለጎረቤቶቻቸን መልካም እንድንውል መከረን፤ እንዲሁም እርም ከሆኑ ነገሮችና ደም (ያለ አግባብ) ከማፍሰስ እንድንቆጠብ አዘዘን፡፡

(በተጨማሪም) ዝሙት ከመፈጸም፣ በሐሰት ከመመስከር፣ የየቲሞችን ገንዘብ ከመብላት፣ ጥብቅና ንጽሕት የሆኑ ሴቶችን ከማነወር እንድንቆጠብ አዘዘን፡፡

አላህን ብቻ እንድናመልክና በርሱ ላይ አንድም ነገር ላናጋራ፣ ሶላትንም ልንሰግድ፣ ዘካንም ልናወጣ፣ ጾምም ልንጾም አሳስበን፡፡

እውነት ብለን ተቀበልነው:: ከአላህ ይዞ በመጣው ነገር ተከተልነው፤ አላህን ብቻ መገዛት ጀመርን ፤ በርሱም ላይ ማጋራትን አቆምን::

አላህ ሐራም ያደረገውን ክልክል አደረግን፤ የፈቀደውን ነገርም መፈጸም ጀመርን::

በዚህ የተነሳ ነው ወገኖቻችን ጠላት አድርገው የያዙንና
ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን የፈጸሙብን:: መከራ ሲበዛብን፣ ከኃይማኖታችን ሊቀለብሱን ሲጫኑን ወደርስዎ አገር መጣን፡፡ ከሌሎች ንጉሶች እርስዎን መርጠን ጥገኝነት ጠየቅን፡፡ ከርስዎ ዘንድም እንደማንበደል እርግጠኞች ነን።”

ዐምር በዚህ ጊዜ ኢስላም ኢየሱስን በመጥፎ እንደሚያወሳ ለንጉሡ ተናገረ። በጃዕፈር ንግግር ልባቸው የተነካው ንጉሥ ከቁርኣን እንዲያሰማቸው ጠየቁ:: ጃዕፈርም ከቁርኣን የመርየምን ምዕራፍ አነበበላቸው፡፡

ንጉሡ እጅግ ጥልቅ በሆነ ስሜት ያደምጡ ነበር፡፡ እንባቸው ጺማቸውን እስኪያርስ ድረስ አለቀሱ

………ይቀጥላል

@aaumsu
❤2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰዓታት ብቻ ይቀሩታል !

የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ ... ምሽት 3:00 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ።

በሰዓቱ መገኘት፤ መልዕክቱን ለሌሎች ማድረስ እንዳይዘነጋ።

@aaumsu
🔥4
ፕሮግራሙ 30 ደቂቃዎች ብቻ ይቀሩታል። ሌሎችን ማስታወስ አይዘንጋ፤ @aaumsu በሰዓቱ እንገኝ። ርዕሳችን የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ ነው።

@aaumsu
"ኒቃብ ቢከለከል ወዴት ልትሸሹ ነው ከቤታችን ወዴት ይሸሻል?!!"

@aaumsu
"የሀይማኖታዊ መብቶቻችንን የመጠበቅ ግዴታ አለብን!!"

"ዩንቨርሲቲዎች የጋራ ሀብቶቻችን ናቸው!"

ወንድም ሙሐመድ አሚን ካሳ ~ የEHEMSU ፕሬዚደንት!

@aaumsu
" ዛሬ ለተደረጉ ነገሮች ወደፊት ለሚደረጉ ነገሮች በጥልቀት መወያየት አለብን !! መንቃት አለብን!! "

"የአዲስ አበባ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሊበረታታ ይገባል በርቱ በዚሁ ቀጥሉ"

ሙሃመድ አሚን ካሳው ~ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚደንት
@aaumsu
የቀድመው የጅግጂጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂ ዲፕርትመንት ሌክቸር ድጋፋችንን ይሻሉ !

ዶክተር አብዱናሲር አሕመድ በአንድ ወቅት ጂግጂጋ ዩኒቨርስቲን በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ አንጋፋ ምሁር ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህር ሲሆን ባደረበት ፅኑ ሕመም ምክንያት በውጭ ሀገር እንዲታከም ስለተወሰነና ከሕክምና እና ከአንዳንድ ወጪዎች ጋር ተያይዞ የገንዘብ እጥረት ስላጋጠመው እርዳታ ይደረግለት ዘንድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጠይቋል።

ነብያችን ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሙስሊም ከሌላኛው ሙስሊም ልክ እንደ አንድ አካል ነው ብለዋልና የዶክተርን ችግር ችግራችን አድርገን እንተባበራቸው ዘንድ ጥሪያችን ነው። የአንድን ሙዕሚን ጭንቀት በዱንያ ላይ ያቃለለ አላህ ከአኼራ ጭንቀቱ ያቃልልለታልና በቻልነው አቅም ከዶክተር ጎን በመቆም ጭንቀታቸውን እናቃል። መልዕክቱን ለሌሎችም በማዳረስ በኸይር ስራው ላይ ተሳታፊ እንሁን።

የንግድ ባንክ አካውንት፦ 1000003646096 (Abdenasir Ahmed Ibrahim). የላካችሁበትን screenshot በማድረግ @Niqab_issueBot ላኩልን።

አላህ ሙሉ አፊያቸውን ይመልስ፤ የመጨረሻም ያድርገው።

@aaumsu
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑

ክፍል 3

“በእርግጥም አላህ የንጉስ ነጃሺን ቀልብ ለሂዳያ መርጧታል”

ይህንን ንግግር ነጃሺ በጥሞና ካዳመጡ በኋላ እውነታው ውልል ብሎ ታያቸው፤ ስደተኞችንም ለልኡካኑ ላለመስጠት ወሰኑ።

እንዲህ ነው እንግዲህ በቅንነት የተሞላው የንጉስ ነጃሺ ማንነት ቀስ በቀስ ወደ እውነት የተመራው።

ዛሬ ላይ የሚፈጠረው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ፣ አንዳንድ ሰዎች እውነትን ፍራቻ፤
አይድረስብኝ፣ አልወቀው ይቅርብኝ፣ ያወቀውም አይቅረበኝ፣ ማንም አይደርስበት ዘንድም ውሸት መስሎ ይቅረብ በማለት አልፎ ተርፎም እኚህ ሰዎች ከዚህ እውነታ ራስን ለማግለል በሚል በአስቀያሚ ጠላትነት ይታወራሉ።

አስተሳሰብ፣ እይታ፣ ልብ እና አእምሮ ደግሞ ሁሉም ቀስ በቀስ አብረው ሲታወሩ ሰብአዊነትም ይጠፋና በድሮ ጊዜ ……….
እየተባለ ይተረክለታል።አለምም ግፍ ሰጪዎችን፣ ተቀባዮችን እና አንቀበልም ያሉ ታጋዮችን አፍርታ ትቀጥላለች።

ወደ ታሪኩ ስንመለስ እውነቱ የተገለጸላቸው ንጉስ ነጃሺ ስደተኞችን አሳልፎ ላለመስጠት በመወሰን
“ይህ እና ኢሳ(እየሱስ )ይዞት የመጣው መልእክት ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ናቸው “አሉ።

ቀጥለውም ለቁረይሽ ልዑካን

‹‹ሂዱ! ለናንተ አሳልፌ አልሰጣቸውም:: ማንም በመጥፎ እንዳይቀርባቸው:: በአምላክ ስም እምላለሁ፡- ይህ ሰው ያነበበው በወንጌል ከተጻፈው የዚህችን ስንጥርያህል እንኳ የተለየ አይደለም›› ሲሉ ተናገሩ::

በአገራቸው ግዛት ያለምንም ችግር በነጻነት እንዲቆዩም ፈቀዱላቸው:: የቁረይሹ ልዑክም ዓላማው ሳይሳካለት ተመለሰ፡፡

የነጃሺን ሁኔታ ያስተዋሉ ክርስቲያኖች ተሰባስበው መጥተው ነጃሺን ‹‹ሃይማኖታችንን ትተሃል›› በማለት ወቀሱት። አመጽ ተቀሰቀስ፡፡ ነጃሺም ወደ ሶሓቦች በመላክ በሁለት ጀልባ ለጉዞ እንዲዘጋጁ አዘዘ:: ይህን ያደረገው ድንገት ከተሸነፈ ወደ አገራቸው መሸሽ እንዲችሉ ነበር፡፡

ነጃሺ አመጹን ለማኮላሸት ወደ አባይ ወንዝ አቅጣጫ ዘመተ:: ነጃሺ ተሸንፎ የሃይማኖት ነጻነታቸውን የማይጠብቅ ንጉሥ እንዳይመጣ ሶሓቦች ሰጉ፡፡

‹‹ማን ወደ ስፍራው ተጉዞ የጦርነቱን ዜና ያምጣልን?›› ሲሉም ተወያዩ። በእድሜ ትንሹ ዙበይር ኢብኑል ዓዋም ተንቀሳቀሰ፤ነጃሺ ዘመቻውን በድል እንዲወጣ ሶሓቦች ዱዓ ማድረግ ቀጠሉ፤ነጃሺ በጠላቱ ላይ ድል አደረገ። 💫

ዜናውን ዙበይር ለሶሓቦች አደረሰ፤እጅግ ተደሰቱ፡፡ የደስታቸውን ወሰን ሲገልጹ ‹‹እንደዚያ ያለ ደስታ አላየንም›› ሲሉ ነበር የተናገሩት::

ሶሓቦች በነጻነት ሃይማኖታቸውን እየተገበሩ በሐበሻ(አክሱም) ሕይወታቸውን ቀጠሉ፣የነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) ወደ መዲና መሰደድ ሲሰሙ 33 ወንዶችና 8 ሴቶች ሆነው ከሐበሻ ወደ መዲና ተመለሱ::

ወደ አክሱም በስደት የመጡትና የኋላ ኋላ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ባልተቤቶች ለመሆን የታደሉት ኡሙ ሰለማና ኡሙ ሐቢባ (ረ.ዐ.) የአክሱም ማርያም (ጽዮን) ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝተዋል።

በሶሂህ አል-ቡኻሪ የሐዲስ ጥራዝ ላይ በተዘገበው መሠረት በጉብኝታቸው ወቅት በቤተ ክርስቲያኒቱ የተመለከቱትን ‹‹የጻድቃን›› ምስሎች ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ነግረው ነበር።

ነቢዩም (ሶ.ዐ.ወ) ‹‹ከመካከላቸው ጻድቅ ሰው ሲሞት በመቃብሩ ስፍራ ላይ የአምልኮ ቤት ይገነባሉ:: እነዚያንም ምስሎች ከውስጡ ያደርጋሉ፡፡ እነርሱ (ይህን የሚያደርጉት) በአላህ ዘንድ ይበልጥ መጥፎ ፍጥረታት ናቸው›› ሲሉ መልሰውላቸዋል::

ንጉሥ ነጃሺ ቀደም ብሎ ከነጃዕፈር ጋር ባደረገው ውይይት ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ነብይ እንደሆኑ ተረድቶ ነበር።
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ለነጃሺ ከላኩት ሁለት ደብዳቤዎች የመጀመሪያው እንዲህ ይላል፡-


በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩኅሩኅ በሆነው

“ይድረስ ከሙሐመድ (የአላህ መልዕክተኛ) ወደ ነጃሺ አስሐማ የሐበሻ ንጉሥ። ከዚህ በመቀጠል በቅድሚያ አላህን አመሰግናለሁ::

አላህ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ (ጌታ) ነው፡፡ ንጉሥ ነው፡፡ ፍጹም ነው፡፡ ሰላምና የሚታመንበት፣ አሸናፊ ነው::

ዒሳ የማርያም ልጅ ራሷን የጠበቀችና ጻድቅ በሆነችው ማርያም ላይ የተጣለ የአላህ መንፈስና ቃል መሆኑን እመስክራለሁ፡፡ እርሷም በአላህ መንፈስና እስትንፋስ ዒሳን አረገዘች:: አላህ አደምን በእጁና በእስትንፋሱ እንደፈጠረ ሁሉ፡፡

እኔ ወደ አላህ እጠራሃለሁ፡፡ አንድ ነው:: አጋር የለውም:: በእርሱ ትእዛዝም ሥር እንድትውል አሳስብሃለሁ።
እኔንም እንድትከተለኝ፣ እንድታምንብኝና ወደኔም የወረደውን (ቁርኣን) እንድታምንበት እጠይቅሃለሁ፡፡ እኔም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ፤ አንተንም ሆነ ሠራዊትህን ወደ አላህ እጠራችኋለሁ፤
መልዕክቴን አድርሻለሁ። ተቀበሉኝ: ሰላም ቀናውን ጎዳና በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን።”

ደብዳቤውን ለነጃሺ ሲሰጥ ዐምር ኢብን ዑመያ እንዲህ ሲል ተናገረ፡-

“ንጉሥ ሆይ! እኔ የምነግርህ ጉዳይ አለ:: በጽሞና ታደምጠኝ ዘንድ እጠይቅኃለሁ:: አንተ ለኛ አዛኝ ሰው በመሆንህ የኛው አካል ነህ::

እኛም ባንተ የጠበቅነውን በጎ ነገር ሁሉ አግኝተናል፡፡ እንዳይደርስብን የሠጋነው መጥፎ ነገርም በኛ ላይ አልተፈጸመም። ከዚህ በፊትም ያንተን ማንነት አረጋግጠናል፡፡

በኛና ባንተ መካከል ወንጌል የማይሻር ምስክር ነው:: የማያዳላ ዳኛም ነው። አይሁድ ዒሳን (ኢየሱስን) እንደካዱ ሁሉ ይህን ነቢይ አንተም እንዳታስተባብል::

ነቢዩ አንተንና ሕዝብህን ሌሎችን ላላጩበት ተግባር ሊያጩህ ይፈልጋሉ:: ይህም ካንተ ባየነው መልካም መስተንግዶ ሳቢያ ነው፤የላቀ ምንዳ እንድታገኝ እንመኛለን።”

ንጉስ ነጃሺም በነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ማመኑን ግልጽ አደረገ፡፡እንዲህም ሲል ተናገረ:-

“በአምላክ ስም እመሰክራለሁ:: እርሱ የመጽሐፍት ባለቤቶች (አህለል ኪታብ) የሚጠባበቁት ነቢይ ነው::
ሙሴ —አህያ ላይ ተቀምጦ ይመጣል ሲል የኢየሱስን መከሰት እንዳበሰረ ሁሉ ዒሳም (ኢየሱስም) በግመል ላይ ተቀማጭ የሆነ ነቢይ እንደሚመጣ አብስሯል::

የመልዕክት ልውውጥ እንደማየት አይደለምና (መልዕክተኛውን) ካሉበት ቦታ ድረስ ሄጄ ላያቸው ብችል እወድ ነበር፡፡ ነገር ግን የሐበሻ ረዳቶቼ ጥቂት ናቸው:: ስለዚህ የሰዎችን ልብ እስካለዝብና ረዳቶቼን እስከማበረክት ድረስ ጊዜ ስጡኝ።”

ነጃሺ ኢስላምን መቀበሉን ግልጽ አድርጎ ለነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ዳብዳቤ ጻፈ::

ደብዳቤው የሚከተለው ነበር ፡-

……….ይቀጥላል

@aaumsu
❤2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ለዩኒቨርሲቲው የUAT ፈተና፣ መመዝገቢያ እና ትራንስፖርት ወጪ ሽፋን በለቀቀው ፎርም መሰረት በቂ አመልካቾችን አጊኝተናል።

በአሁኑ ሰዓት የተላኩልንን መረጃዎች የማጣራት እና የማረጋገጥ ስራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፤ መረጃቸውን አጣርተን ላፀደቅናቸው ተማሪዎች ነገ ኢንሻአላህ የምናሳውቅ ይሆናል።

በተጨማሪም የሌሎች ተማሪዎችን ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል ተጨማሪ ቦታ ካገኘን በቀጣይ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ!

@aaumsu
👍2
AASTU / ASTU መግባት ለምትፈልጉ፦
ነገ ሐሙስ ከምሽቱ 2:50 ጀምሮ

የመግቢያ ፈተናው ምን ይመስላል፤ አጠቃላይ ማድረግ ያለብኝ ዝግጅት ምንድን ነው፤ የዩኒቨርስቲዎቹ ሁኔታ እንዴት ነው፤ ምን ምን ዲፓርትመንቶች አሉ፤ ምንስ ይጠብቀኛል በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘናል።

ተጋባዥ እንግዶች፦

፨ ኢብራሒም ኸዲር፦ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አካዳሚክ ሴክተር አሚር

፨ መስዑድ ሙስጠፋ፦ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ

ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ BAIS ተማሪ በሆነው ሚፍታሕ ኢብራሒም የሚመራ ይሆናል። እንዲነሳ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ @MOHAMMADAMMINM ላኩ።

ፕሮግራሙ ነገ ሐሙስ ነሐሴ 28 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 2:50 ጀምሮ @MohammadamminKassaw Live ይካሄዳል። ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share አድርጉት።

@MohammadamminKassaw
❤2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ለዩኒቨርሲቲው የUAT ፈተና፣ መመዝገቢያ እና ትራንስፖርት ወጪ መሸፈን የማይችሉ ልጆችን ለመደገፍ በለቀቀው ፎርም ተመዝግባችሁ እስካሁን ያልተደወለላችሁ ወንድም እና እህቶች፤ ስልካችሁን ማግኘት ስላልቻለን በ @Aaumuslimstudentsunion1 እንድታናግሩን እንጠይቃለን።

@aaumsu
#ሕያው_ምስክር_2

✨በ ቅርብ ቀን ይጠብቁን!

@aaumsu
🔥6❤1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ለዩኒቨርሲቲው የUAT ፈተና፣ መመዝገቢያ እና ትራንስፖርት ወጪ መሸፈን የማይችሉ ልጆችን ለመደገፍ በለቀቀው ፎርም ተመዝግባችሁ እስካሁን ያልተደወለላችሁ ወንድም እና እህቶች፤ ስልካችሁን ማግኘት ስላልቻለን በ @Aaumuslimstudentsunion1 እንድታናግሩን እንጠይቃለን።

@aaumsu
👍1
በአባጂፋሯ ጅማ የተገፈፈ ክብር፤ የተከለከለ ሒጃብ ... በአባጂፋር ልጆች የተደረገ ትግል፤ የተከፈለ መስዋዕትነት፤ የተረጋገጠ ክብር --- በጅማ ዩኒቨርስቲ !

ሕያው ምስክር - 2

አባጂፋር (ረህመቱላሂ ዐለይሂ) ከጅማ መምለካ ተሻግረው፤ ሐበሻንም አቋርጠው ስለሙስሊሞች መብት የሚብሰለሰሉ፤ የሚታገሉ፤ መስዋዕትነት የከፈሉ ታላቅ እና ፍትሐዊ ንጉስ ነበሩ። ሆኖም ግን ከአመታት ቡሃላ፤ በጅማ ከተማ፤ በጅማ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ባይተዋር ሆኑ። ሙስሊም ስለሆኑ ሊለብሱት ግዴታ የሆነውን ሒጃብ (ኒቃብ) ከመልበስ ተከለከሉ። ለተከታታይ አስር አመታት ያክል በተለያየ ጊዜ፤ በተለያዩ ሰዎች ክብራቸው ተደፈረ።

ይህ እየሆነ ባለበት በ2017 ዓ.ል የአባጂፋር ልጆች መብታቸውን ያስከብሩ ዘንድ የአላህ ፍቃድ ሆነ። በወርሐ ረመዷን ከተራዊህ መልስ ኒቃቢስት ተማሪዎች ወደ ግቢ ካልገቡ እኛም አንገባም በማለት ለተከታታይ አራት ቀናት ታገሉ። መሪዎቻቸው ቢታሰሩም ፀንተው ቆሙ። በአላህ ፈቃድም በፍትሐዊው ንጉስ ሐገር የተነፈገው ነፃነት ተከብሮ ፍትሕ ፀና።

የነበረውን ሂደት፤ የተፈጠሩትን ክስተቶች፤ የመጣውን ውጤት በሕያው ምስክር - 2 የምንዳስስ ይሆናል።

መስከረም - 1
ጁምዓ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ !


በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share ያድርጉ።

@aaumsu
🔥2
"የተማሪዎችን እርካታ አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊስ ምርምር፤ የአመራር ልማት መርሐግብር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2018 አፈፃፀም ዙሪያ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የቀረበው ጥናት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሁኔታ በግልፅ ያሳየ ነው።" - የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት

ሸገር FM ባወጣው ዘገባ እንዳስቀመጠው የተማሪዎች እርካታን አስመልክቶ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ 47 ዩኒቨርስቲዎች በመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ይህ ውጤት ባለፉት ሁለት አመታት ዩኒቨርስቲው የተማሪዎችን ሐይማኖታዊ እኔ ሰብዓዊ መብቶች የሚጥሱ መመሪያዎችን በማውጣት፤ በሐይማኖታቸው ጣልቃ ገብቶ ሒጃብ መልበስን በመከልከል፤ ተማሪዎች ትኩረታቸውን ወደ መብት ጥያቄ እንዲያደርጉ በማድረግ የፈፀመውን የአመራር ውድቀት በግልፅ ያሳያል። የተፈጠሩ ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ለተማሪዎች ምላሽን በመንፈግ ውጪ እንዲያድሩ በማድረግ፤ በምርቃት ቀናቸው ከእስር ቤት እንዲውሉ በማድረግ፤ ከተመረቁም ቡሃላ መብታቸውን የጠየቁ ተማሪዎችን ዲግሪ በመከልከል የፈፀማቸው አንጋፋ የመብት ጥሰቶች ተጠቃሽ ናቸው።

መሠል ስህተቶች እንደ ሀገር አርዓያ ሊሆን የሚገባው ተቋም ሀገር ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት ጭራ እንዲሆን ከማድረጋቸው ባሻገር የመጪውን ትውልድ ተስፋ የሚያቀጭጩ በመሆናቸው ውጤቱን ከመገምገም ባሻገር መሬት ላይ ያለውን ችግር በመፍታት እና ይህንን አንጋፋ ቅሌት ያመጡ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲረባረብ እንጠይቃለን።

@aaumsu
😁2🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የሐሩን ሚዲያ ምላሽ ምንድን ነበር? https://vt.tiktok.com/ZSq85g9u5/ ያዳምጡ፤ ሪፖስትም ያድርጉ።

Šaaumsu

@fivekjemaa
❤1
ኢማን ሬድዋን እንኳን ደስ አለሽ!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ4ተኛ አመት ፋርማሲ ተመሪ የሆነችው እህታችን ኢማን ሬድዋን እንደ አፍሪካ በተደረገ የጤና ስርዓት ኢንተርፕረይነሮች ውድድር ላይ በመሳተፍ አሸናፊ ሆና 2500 ዶላር ተሸላሚ ሆናለች። ይህ ስኬት የትጋቷ እና ጥረቷ ውጤት ነው። ከሷ አልፎ ለሁሉም ተማሪዎች አርአያ በመሆን ሙስሊሙ ጠንክሮ መማርና የሆነ አስተዋጽኦ ለማህበረሰቡ ማበርከት እንዳለበት መልእክት ያስተላልፋል ።

አላህ ይባርክልሽ! ከላቁ ስኬቶችም ደጋግሞ ያድርስሽ!!!! መብሩክክክክክክ!!!

@aaumsu
❤2
ወደ ዩኒቨርስቲዎች በተለይም ጂማ እና ሐረማያ ለመግባት ላሰባችሁ በዘንድሮ ኢንትራንስ ላለፋችሁ ተማሪዎች፦

ዩኒቨርስቲዎቹ ምን ይመስላሉ? ምን ምን አይነት ዲፓርትመንቶቹ አሉ? በየትኞቹ ዘርፎችስ የተሻሉ ናቸው? ከእኛስ ምን ይጠበቃል በሚሉ እና በሌሎች ነጥቦች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘናል። ስለ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ጠቅለል ያለ መረጃ ይሰጣል።

ተጋባዥ እንግዶች፦

፨ Muhammaddin Muhidin (በጅማ ዩኒቨርስቲ የ5ተኛ አመት ሜዲስን ተማሪ እና የጀመዓው ምክትል አሚር)

፨ Faris Mustefa (የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ምክትል አሚር)

የፕሮግራሙ አስተባባሪ፦ ሚፍታህ ኢብራሒም ነው።

ፕሮግራሙ፦ ነገ ማለትም እሁድ ጷጉሜ 1 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ @MohammadamminKassaw ይሰጣል። በፕሮግራሙ ላይ መመለስ አለባቸው የምትሏቸውን ጥያቄዎች @MOHAMMADAMMINM ላኩልን። መረጃውን ለሁሉም ይደርስ ዘንድም Share አድርጉት።

@aaumsu
❤3