ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)
188 subscribers
226 photos
8 videos
19 files
37 links
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :-

፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን።

፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን።


፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን።

ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።
Download Telegram
ከዐሠርቱ ትእዛዛት ውስጥ የሚገርመኝ እውነታ ሁሉም ትእዛዝ የተነገሩት በነጠላ ለአንድ ሰው መሆኑ ነው፡፡ 'አድርግ አድርግ ፣ አታድርግ አታድርግ'! ሙሴ ዓሠርቱን ትእዛዛት ይዞ የወረደው በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩት ለእስራኤላውያን ቢሆንም ትእዛዛቱ ግን አታምልኩ ፣ አትስረቁ ፣ በሐሰት አትማሉ ወዘተ የሚል አልነበረም፡፡ ዐሥሩም በነጠላ አድርግና አታድርግ በሚሉ ትእዛዝና ሕግ የተሞሉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለው ሃሳብ እንዲህ ነው፡፡

መስረቅ ሲያምርህ 'ሀገሩ ሁሉ እየሰረቀ ነው እኔ ብቻዬን ምን ለውጥ አመጣለሁ? ጊዜው የሌብነት ነው!' ብለህ አትጽናና፡፡ እግዚአብሔር 'አትስረቅ' እንጂ አትስረቁ አላለም፡፡ ሀገሩ ሁሉ ይስረቅ አንተ ግን 'አትስረቅ' የታዘዝከው ለብቻህ ነው ፤ የሚጠይቅህም ለብቻህ ነው፡፡ ማመንዘር በእኔ አልተጀመረ የማያመነዝር ማን አለ? ብለህ ለኃጢአትህ ማኅበርተኞች አታፈላልግ፡፡ 'አታመንዝር' ያለው ለአንተ ለብቻህ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር ያለውም ላንተ ነው፡፡ 'የሥራው ጸባይ ነው፡፡ ሥራዬ መዋሸት ይጠይቃል' ብለህ ሐሰትህን የኑሮ መግፊያ ስልት አታድርገው፡፡ ብዙዎች በሐሰት ቢመሰክሩ አንተ ግን አትመስክር፡፡ ሁሉም መስክሮ እኔ ብቀር ምን ለውጥ ያመጣል? ብለህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ 'ብዙ ናቸው ብለህ ከክፉዎች ጋር አትተባበር' ፈጣሪህ ያዘዘህ ለብቻህ ነው፡፡ የጋራ ኩነኔና የጋራ ጽድቅ የለም፡፡

ጌታ እንዲህ ይላል ፦

'እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ' ራእ. 22፡12

▫️@diyakonhenokhaile

https://t.me/diyakonhenokhaile
​​​​"ጌታውን ደስ ያሰኘ ታማኝና ቸር አገልጋይ ማነው?" ቅዱስ ያሬድ

          በዲያቆን ግዛው ቸኮል


                 ክፍል አንድ[፩]

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሰንበት (ሳምንት) ገብር ኄር በመባል ይታወቃል፡፡

   ገብር ኄር ማለትም "ቸር፣ ታማኝ፣ ቅን አገልጋይ" ማለት ነው፡፡ ይህንን ስያሜ ያገኘበት ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ "ገብር ኄር ወገብር ምእመን ገብር ዘአሥመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ደስ ያሰኘ ታማኝና ቸር አገልጋይ ማነው?" በማለት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ሊቃውንቱ ስለሚያመሰግኑ ነው፡፡ (ጾመ ድጓ ዘገብር ኄር)

በዚህ ዕለትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውና በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተመዘገበው የአንድ ባለ ሀብትና የሦስት አገልጋዮቹ ታሪክ ይነበባል፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀንም ያ ባለጠጋ አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዱ እንደአቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት፣ ለአንዱ ሁለት መክሊት፣ ለአንዱም አንድ መክሊት ሰጠና ወደሌላ ሀገር ሄደ፡፡

ከብዙ ዓመታት በኋላ ተመልሶ መጣ፤ አገልጋዮቹንም ትእዛዙን መፈጸም አለመፈጸማቸውን፣ መታዘዝ አለመታዘዛቸውን ለማወቅ ጠየቃቸው፡፡

በዚህን ጊዜ አምስት መክሊት የተሰጠው ወጥቶ ወርዶ ነግዶና አምስት አትርፎ ደርቦ ዐሥር ስላመጣ ለጌታው እንዲህ አለው፤ "አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ" ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡

ጌታውም፡- "መልካም፥ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሀለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡" ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡-"አቤቱ፥ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፍሁ" አለ፤ ጌታውም "ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡" አንድ መክሊት የተቀበለው መጣና እንዲህ አለ፡- "አቤቱ፥ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፥ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ፥ መክሊትህ፡፡" ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- "አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ፥ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡" ከዚያም ጌታቸው "ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን፥ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት" ብሎ አገልጋዮቹን አዘዘ፡፡
    ማቴ.፳፭፥፲፬-፴

ባለ አምስት መክሊት የነበረው አገልጋይ ፍጹም ትምህርትን ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ደቀ መዝሙር ባፈራ መምህር ይመሰላል፡፡

ባለ ሁለት መክሊት የተባለ ፍጹም ትምህርትን ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ባወጣ መምህር ይመሰላል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌሜንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳፈሩ ማለት ነው፡፡

ባለ አንድ መክሊት የተባለ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ ነው፡፡ ዕውቀት፣ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት እያለው በግዴለሽነት ኃላፊነቱን ያልተወጣ ነው፡፡

ፍጹም ትምህርት የተማረው ወጥቶ ወርዶ መክሮና አስተምሮ ራሱን አስመስሎ አወጣ፡፡ ባለአንዱ መክሊት ዐላውያን "እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ፣ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ" ብሎ ፈርቶ ሃይማኖቱን በልቡ በመያዝ ደብቆ በሚኖር ዓይነት ሰው ይመሰላል፡፡

ባለ አምስት የተባለ ነቢዩ ሙሴ ነው፤ አምስቱን ብሔረ ኦሪት ጽፏልና፡፡

ሁለት የተባሉ ብሉይና ሐዲስ ናቸው፤ ባለአንድ የተባለ ይሁዳ ነው፡፡አምላኩን ሽጦ፣ አባቱን ሰልቦ፣ እናቱን አግብቶ ንስሓ ሳይገባ ሞቷልና፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ባላአምስት የተባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው፤ ቆሞሳትን፣ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን በአንብሮተ እድ ይሾማሉ፤ ያጠምቃሉ፤ ያቈርባሉና፡፡ ባለሁለት የተባሉ ቀሳውስት ናቸው፤ እነርሱም ያጠምቃሉ ያቆርባሉና፡፡

ባለአንድ መክሊት የተባሉ ዲያቆናት ናቸው ፤ ለተልእኮ ይፋጠናሉና፡፡ በዚህ ዘመን ባለ አምስትም፣ ባለ ሁለትም፣ ባለ አንድም ቢሆኑ የተሰጣቸውን መክሊት ተጠቅመው ወጥተው ወርደው ካተረፉ "ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" የሚለውን ቃል ሰምተው በተድላ ይኖራሉ፡፡

ከዚህ ታሪክ እንደምንገነዘበው ዛሬም እያንዳንዳችን እንደአቅማችን ከአምላካችን ዘንድ የተሰጠን መክሊት እንዳለን ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ ዓለም ያመጣነው የለንምና" እንዳለ ወደዚህ ዓለም ከመጣን በኋላ መንፈሳዊ ስጦታም ይሁን ቁሳዊ ነገሮች ሁሉንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለናል፡፡

በእርግጥ አላስተዋልንም እንጂ ከእግዚአብሔር ያልተቀበልነውና የእኛ የምንለው ነገር ቢኖር ኃጢአት ብቻ ነው፡፡

የምንሰጠው የእርሱን ለእርሱ ነው እንጂ የራሳችን የሆነ ምንም ሀብት የለንም፡፡ ፩ኛ ጢሞ ፮፥፯

ታዲያ በዚህ ዘመን ያለን ምእመናን ከጌታችን በተቀበልነው ጸጋ ለእርሱ ታማኞች የሆንን ስንቶቻችን ነን? ራሳችንንስ ቢሆን ምን ያህል ተረድተናል? ቤተክርስቲያንን አገልግለናል? ምክንያቱም የተፈጠርንበት ዓላማ እንድናገለግል ነውና፡፡

አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ሁላችንም እንደየአቅማችን እንጂ ከአቅማችን በላይ ባልተሰጠን ነገር እንደማንጠየቅ ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ላይ "እግዚአብሔርም በሰጠን ጸጋ መጠን ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት የሚናገር እንደ እምነቱ መጠን ይናገር፡፡ የሚያገለግልም በማገልገሉ ይትጋ፤ የሚያስተምርም በማስተማሩ ይትጋ፤ የሚመክርም በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥም በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛም በትጋት ይግዛ፤ የሚመጸውትም በደስታ ይመጽውት"እንዳለ ሁላችን በአቅማችን መሥራት እንዳለብን ያስተምረናል፡፡

በሌላ በኩል ሐዋርያው "መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦታው ልዩ ልዩ ነው" በማለት በሁሉ አድሮ ሁሉን የሚሠራ እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ነገር ግን የሥራ ክፍል ደግሞ እንዳለው እንድንረዳ ያስተምረናል፡፡
ሮሜ ፲፪፥፮-፰፣ ፩ኛ ቆሮ. ፲፪፥፬-፲፩

በዚህ ዘመን በየትኛውም መንገድ ቢሆን ታማኝነት የጠፋበት፣ እኛ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ራሳችንን በመተብተብ ከእግዚአብሔር ኅብረት ተለይተን ማገልገልን ለተወሰኑ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ብቻ የሰጠን ሁነናል፡፡

በዚህም በቤተክርስቲያንና በአማኞቿ ላይ ብዙ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነናል፤ አሁንም ቢሆን ከተኛንበት መንቃት ያስፈልገናል፡፡

በዚህ ዘመን ለምንኖር አገልጋዮች አገልግሎታችንን የሚያዳክሙ ነገሮች ምንድን ናቸው?

፩.የመንፈሳዊ ሕይወታችን መዛል፡-

     ክፍል ሁለት ይቀጥላል....

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የማይገባው ተሸላሚ

ቄሱ ሲናዝዙ "ኩኑ ፍቱሐነ ወንጹሐነ ይረስየኒ ወይሬሲክሙ ድልዋነ ለመንግሥተ ሰማያት" "የተፈታችሁ ንጹሐን ሁኑ እኔንም እናንተንም ለመንግሥተ ሰማያት የተገባን ያደርገን ዘንድ" ብለው ጣታችንን ዐሥራ ሁለት ጊዜ በእግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ሲያስቆጥሩን ለወትሮ ያላሰብሁት ነገር ታሰበኝ::

"እኔንም እናንተንም ለመንግሥተ ሰማያት የተገባን ያደርገን ዘንድ" የሚለው ቃል!

መንግሥተ ሰማያትን መውረስ መቼም ከእኛ መካከል የማይፈልግ ሰው የለም:: ለመንግሥተ ሰማያት ግን የተገባን ነን ወይ?

እውነት አሁን ጌታ ቢመጣና ሁሉንም በደላችንን ትቶ ሁላችንንም በቀኙ

አቁሞ መንግሥቴን ውረሱ ቢለንና ወደ መንግሥቱ ብንገባስ? ለመንግሥተ ሰማያት የሚሆን ማንነት አለን ይሆን? ከእኛ መካከል ለመንግሥተ ሰማያት የተገባ ማን ነው?

ጌታ ሆይ እንኳን ለመንግሥትህ በምድር ላለችው ቤትህ የሚገባ ማንነት እንደሌለኝ ሳስብ "መንግሥትህ ትምጣ" ማለት አስፈራኝ::

"በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው" በተባለላት ቤትህ እንኩዋን እንደሚገባኝ መመላለስ ላልቻልሁት ለእኔ መንግሥትህን እንዴት ልመኝ? 1 ጢሞ. 3:15

" አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?” ብሎ ዳዊት ቢጠይቅ የመለህለት ውስጥ ራሴን አጣሁት:: መዝ. 15:1 ስለዚህ ለመንግሥትህ የሚሆን ማንነት ማጣቴ አሳፈረኝ::

የሰርግ ልብስ ሳልለብስ ወደ ሰርግ ቤትህ የገባሁ ብሆንስ? በመላእክት ማኅበር መካከል ዕርቃኔን ብቆምስ? እውነት የኔን ጠባይ ወደ መንግሥትህ ይዤው ልገባ ይቻል ይሆን? በመንግሥትህ ለእኔ ዓይነቱ ሰው የሚሆን ቦታ አለህ ይሆን? እርግጥ ነው በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ብለሃል:: ለእኔ ዓይነቱ ቁስለኛ የሚሆን ቤትስ ይኖርህ ይሆን? ግዴለም ከደጁም ቢሆን አስገባኝ::

ያስተማሩ የሐዋርያት ማኅበር ፣ ድል የነሡ ሰማዕታት ማኅበር ፣ ቡሩካን የሆኑ የጻድቃን ማኅበር በዚያ እንዳለ አውቃለሁ:: ወደ መንግሥትህ ብገባ የእኔ ምድብ ወዴት ይሆን? ይቅር የተባሉ ሰዎች ማኅበር የለህ ይሆን? ምሕረትህ የበዛላቸው ሰዎች ማኅበር ፣ እንደ ቸርነትህ ብዛት የተማሩ ፣ እንደ ይቅርታህ ብዛት መተላለፋቸው የተደመሰሰላቸው ሰዎች ማኅበር የለህ ይሆን? ክርስቲያን ተብዬ ልጠራ ያልተገባኝ እኔን በቸርነትህ ለመንግሥትህ ዜግነት የተገባሁ አድርገኝ::

#share

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 2016 ዓ.ም.

@diyakonhenokhaile
"ትሑትን ቢሹ የትሑታን ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
የዋሃንን ቢሹ የየዋሃን አብነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ደጉን ቢመኙ የበጎ ምንጭ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ወዳጅ ቢሹ የማይከዳ ባልንጀራ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
መጋቢ ቢሉ የማያልቅበት ባለፀጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ማረፍ ቢሹ በክንዱ የሚያቅፍ በጀርባው የሚሽከም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
መድኃኒት ቢሹ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡"
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ!

ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡

ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

"ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
ገፅ 86
Forwarded from መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 (😎 Abreham🤠)
++ምናለ ብታስተምረኝ++
🔖🔖🔖🔖🔖🔖🔖

በክብር በሞገስ በመወደስ ፈንታ
መቀመጥ እንድችል ከመዋረድ ተርታ
ስድብን እየሰማሁ ያለ አንዳች ሁካታ
ለመቆም እንድችል ልቤ ሳይረታ
ምናል ብታስተምረኝ ብታስችለኝ ጌታ!?
ለእኔም አስተምረኝ ባላጠፉት ጥፋት
በጸጋ መቀበል የአይሁድን ትፋት
እንዴት እንደሚቻል ሳያጉረመርሙ
ንገረኝ ጌታዬ ይረዳኝ ትርጉሙ!
የመናቅን ጥበብ የውርደትን ዘዴ
እባክህ አስረዳኝ አስተምረኝ አንዴ
ብዔል ዜቡል ተብለህ ያልተበሳጨኸው
የኃጢአተኞች ወዳጅ መባል ያልጠላኸው
ጋኔን ይዞታልን የሰማህ በጸጋ
ለእኔም አስተምረኝ በቂም አልወጋ!
አልወጋ እባክህ በመራርነት ጦር
በቁጣ ጥላቻ ነፍሴ አትሰበር
እንዴት ነበር ያኔ የይሁዳን እግር

ዝቅ ብለህ ያጠብኸው ስታውቅ ሁሉን ነገር?
ለእኔም አስተምረኝ ብዙ ሳልናገር!
በችንካር ተጣብቀህ ከመስቀሉ ጋራ
የደምህ ነጠብጣብ ገና ሳያባራ
አያውቁትምና የሚያደርጉትን
ይቅርታን የለመንህ ላጠጡህ ሐሞትን
ምናል ብታስተምረኝ እንዲህ ዓይነት ሕይወትን?
አሁን ምን ቸገረህ ብትሰጠኝ ለአንድ አፍታ
የትሕትናን ቀሚስ የትዕግሥትን ኩታ
እያየህም አይደል ነፍሴ እንዲህ ተራቁታ?
የመሰደብን ዘውድ የመናቅን ካባ
ምናለ ብትኖር ይ’ች ልቤ ደርባ!?
ትዕቢት ለተሞላው ለአትንኩኝ ባይ ልቤ
ለክብሩ ለሚኖር ለኮርማው ሃሳቤ
ምናለ ብትቀባው የትሕትናን ሽቶ
እንደዚህ ከሚኖር ሸትቶ ተበላሽቶ!?
ኸረ እኔ አልቻልኩም አቅቶኛል በጣም
ስድብን መቀበል ሐሜትን ማጣጣም

ስተርከው እንጂ ስኖረው አቃተኝ
ይህን መራር ኑሮ አንተው ይዘህ ጋተኝ!
እንኳን እንደ አንተ ዝም ልል ሲረግጡኝ
ቁጣዬ ነደደ ስለገላመጡኝ
ያንን ሁሉ ታሪክ ያን ሁሉ ጥቅስ ረሳሁ
በቂምና በቀል በጥላቻ ከሳሁ
እንደ አራስ ነብር ለክብሬ ተነሣሁ!
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ /
የሌሊቱ ተማሪ ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በዮሐ. 3÷1 ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ 1÷2) በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው ኒቆዲሞስ “መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርገ የሚችል የለምና።" በማለት ተናገረ።(ዮሐ3፥2) በዚህ ጊዜ ጌታችን የገነት በር ስለሆነው ስለ ምስጢረ ጥምቀት አስፍቶና አምልቶ በምሳሌ ጭምር አስረዳው። "እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” (ዮሐ 3፥3) በማለት መንፈሳዊ እውቀት የጎደለው መሆኑን አሳይቶ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጪ እንደሚሆን አስርግጦ ነገረው።

በዚህም ታላቅ ምስጢርን ሊገልጥለት ወደደ። ይህ አነጋገር ከአይሁድ አለቆች አንዱ ለሆነው ፈሪሳዊ ሰው ከባድ ነበር። ምሥጢሩም ቢጸናበት ጊዜ ጌታን እንዲህ በማለት ጠየቀው “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንደምን ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማሕጸን ተመልሶ ሊገባ ይችላልን?“። (ዮሐ 3፥4) ጌታችንም ለኒቆዲሞስ መልሶ የአዳም ልጆች ሁሉ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ካልተወለዱ (በመንፈስ ቅዱስ መታደስን በሚያሰጥ ጥምቀት ካልተጠመቁ) መንግሥተ ሰማያትን መውረስ እንደማይችሉ ነገረው።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!!
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ድኃ በቤትኽ ደጃፍ ይጮኻልን? ተነስተህ በደስታ የቤትህን ደጅ ክፈትለት የድኃውን ልመና ቸል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔር አቤቱታውን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ ይረግምህ ዘንድ ምክንያት አትሁነው አዝኖ ከሆነ በመልካም መስተንግዶ ደስ አሰኘው፡፡ በኀዘን የከበደው ልቡ በአንተ ይረፍ፤ በሕይወት ዘመንህ ማጣት የሚያመጣቸውን ስቃዮች ታውቃቸዋለህና ችግረኛውን ከቤትህ ደጅ አትመልሰው፡፡"

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶሪያዊ
እሺ ብትሉ…

ልጆቼ! እስኪ ምላሴን ላሰናብትባችሁና እናንተም በትዕግሥት አድምጡኝ! የቤት ሠራተኛ አላችሁ እንበል፡፡ ይህቺ የቤት ሠራተኛችሁ የለበሰችውንና በወጥ፣ በአመድ እንዲሁም በሌላ ቆሻሻ እድፍ ያለ ልብሷን ትለብሱ ዘንድ ትፈቅዳላችሁን? በእርግጠኝነት አትፈቅዱም፡፡ ግን የብዙዎቻችን ሰውነት ከዚህ ልብስ በላይ መቆሸሽዋስ ታውቃላችሁን?

ልጆቼ! ንግግሬ በጣም እንደሚያሳምም አውቃለሁ፤ ግን ምን ላድርግ? የተስተካከለ ሕይወት ቢኖረን እንዲህ የምናገር ይመስላችኋልን? በፍጹም! አንድ የቆሰለ የሰውነት ክፍል ቢኖራችሁ ሐኪሙ ይህን ቁስላችሁ በጣቱ ሳይነካካ ማከም ይችላልን? አይችልም! እኔም እንዲህ ቁስላችሁን ካልነካካሁት በስተቀር ማከም አልችልም፡፡ ለነገሩ ሰው ሰውነትህን አትንካ ማለት ይቻላልን አይቻልም! ታድያ እኔና እንናተ እኮ አንድ አካል ነን፡፡ በክርስቶስ አንድ ኾነን የለምን? እንግዲያውስ ንግግሬን አትጥሉት፤ ክፉ ግብራችሁን እንጂ፡፡

ችግሩ ከማን ነው ከእኛው ወይስ ከቆሻሻው? አንድ ወደ ትዕይንት (ቲያትር) ቤት የሄደ ወጣት ገላዋን ገላልጣ የምትተውን ተዋናይትን አይቶ ዝሙትን መፈጸም የማያስብ ማን ነው? ደጋግሞ የዝሙት ዘፈንን የሚሰማ ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መቋቋም እችላለሁ የሚል ማን ነው? ቀኑን ሙሉ የዝሙት ጽሑፎችን ሲያነብ የሚውል ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መጠበቅ እችላለሁ የሚል ማን ነው?

ልጆቼ! ትዕይንቱን እያየነው፣ ዘፈኑን እየዘፈንነው፣ መጽሐፉንም እያነበብነው ኾኖም ግን መፍትሔ ካላገኘንበት ችግሩ እየባሰ የሚሄድ አይደለምን? እኛ ፈቃደኞች ከኾንን ግን መፍትሔው በሥጋችን ላይ ካለው ደዌ በላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም የሥጋችን ቁስል ሐኪም፣ መድኃኒት፣ ጊዜ ያስፈልጓል፡፡ የነፍሳችንን ቁስል ግን ፈቃድ በቂ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ከእኛ በላይ በንጽሕና ሲኖሩ ሳይ በጣም አፍራለሁ፡፡ እንግዲያውስ ልጆቼ እንመለስ፡፡ ያቆሸሹንን ነገሮች እንጣላቸው፤ እንቁረጣቸው፤ እናስወግዳቸው፡፡ ሰነፎች አንሁን፡፡

ውሳኔው የእኛው ነው፡፡ መጽሐፍ ሲናገር “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል” ይላል /ኢሳ.1፡19-20/፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእኛ እሺታና እምቢታ የተወሰነ ነው ማለት ነው፡፡ የምንኮነነውም የምንመሰገነውም በዚሁ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ መድኃኒዓለም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር በቸርነቱ ይደምረን አሜን፡፡

ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀሲስ በላይ ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ አስታወቀች‼️
ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርትያኗ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን ዶቸቬለ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግለሰቡ በቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኛት ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቃለች፡፡

መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች ማለታቸውን  ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከዜና ምንጩ ዘገባ ለመመልከት ችሏል።

ኃላፊው “እስካሁን በተደረገው ክትትል “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው” ብለዋል።

መምህር ዶ/ር አካለወልድ አክለውም በቀጣይ ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለው ወይ? የሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡
እኔስ ኦርቶዶክሳዊ በመሆኔ እኮራለሁ፦

ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ቅዱሳንን እንደፀጋቸው
ያከብራሉ፡ ማክበራቸውንም በአፍ ብቻ ሳይሆን በግብር ያሳያሉ፤ ቅዱሳንንም ከሚንቁ ጋር በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው፡ በቅዱሳን ፍቅር
እየነደዱ የቅዱሳንን ክብር ይመሰክራሉ፡፡
ስለቅዱሳንም ዘብ ይቆማሉ፡፡ ይሄውም ስለቅድስና ዘብ መቆም ነው፡ ይሄውም ቅዱስ ስለሆነው አንዱ አምላካችን እግዚአብሄር ዘብ መቆም ነው፡ ቅዱሳንን የሚያናንቁት ራሳቸውን ቅዱስ ሲይደርጉ ኦርቶዶክሳውያን ግን “እኔስ በኃጢአት የወደቅኹ ከንቱ ሰው ነኝ” በማለት በትህትና ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ እኔንም ከኒህ ወገን መሆኔ ያኮራኛል፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያከብራሉ፡ “ወላዲተ አምላክ” እያሉ “ የእግዚአብሔር እናት አንቺ ነሽ” እያሉ የአምላካችን የክርስቶስን እናት ያከብራሉ፡፡

እመቤታችንን ለሚያናንቋት፡ ክብሯንም ዝቅ
ለማድረግ ከሚሮጡ መናፍቃን ጋርም ክብሯን እየገለፁ ስለእመቤታችን ዘብ ለመቆም የመጀመሪያወቹ ናቸው፡፡ “የድኅነት ምክንያታችን አንቺ ነሽ” እያሉ፤ አምላካችን ክርስቶስ የተዋሐደው ትስብእት ካንቺ የነሳውን ነው። ስለዚህም ካንቺ የተገኘውን ክርስቶስን በላነው ጠጣነው ህይወትም ሆነልን በማለት እመቤታችንን ያከብሯታል፡፡

ወዲያውም ይህ ምስጢር ላልገባቸውና ለሚጠራጠሩ ደግሞም ለሚንቁ እመቤታችንን መናቅ ክርስቶስን መናቅ ነው በማለት ዘብ ይቆማሉ፡፡ ስለክርስቶስ ሰው መሆን ዘብ ይቆማሉ፡፡ እኔንም ከእነኚህ ወገን መሆኔ ያኮራኛል፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ አምላክ ወልደ አምላክ፣ የሁሉ ፈጣሪ፣ የሁሉ አስገኝ፣ ሁሉን የሚዳኝ እግዚአብሔር ነው በማለት ያምናሉ፡፡

ሙስሊሞች ነቢይ ነው ባሉ ጊዜ እንዴት ይሆናል? በማለት ስለአምላክነቱ ይከራከራሉ፤ አርዮስና ጆሆቫ ዊትነስ ክርስቶስን ፍጡር ነው በማለት ባውካኩ ጊዜ አይደለም ክርስቶስ ስጋን የተዋሐደ የስጋ ፈጣሪ አምላክ ነው። ክብሩ ከአብ ጋር የሚስተካከል፡ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በስልጣን እኩሉ የሆነ አምላክ እንጂ ፍጡር አይደለም በማለት ሽንጣቸውን ገትረው ስለክርስቶስ ባላቸው ፍቅር ለመመስከር ችላ
አይሉም፡፡ ዳግመኛም ክርስቶስን እንደሙሴ
የሚቆጥሩ፡ ዳግመኛም ክርስቶስ የፈፀመውን ድኅነት እንዳልተፈፀመ የሚቆጥሩ፡ ዳግመኛም በሁሉ ላይ የሚፈርድ ንጉስ ሲሆን ይለምናል የሚሉ ፕሮቴስታንቶች በመጡ ጊዜ “አይ ክርስቶስማ አምላካችን ነው፤ አምላካችንም አንድ ነው፤ እንግዲህ ወደማን ይለምናል? እርሱ እግዚአብሔር ነው።” በማለት ክርስቶስን ከሁሉ በላይ በማድረግ አሁንም ስለክርስቶስ ይመሰክራሉ።

አሁንም ስለክርስቶስ ዘብ ከቆሙ ከእኒህ ወገን መሆኔ ያኮራኛል፡፡ እኛ ቅዱሳንን አናመልክም! የምናመልከው አስቀድሞ የነበረ፣ ሁሉን አሳልፎ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ የሆነውን ቅድሱን
እግዚአብሔር ነው። ከሳሽ ቢከስም በግድ አምልኳቸው ከሆነ የምናመልከውን እናውቃለንና አናመልክም ነው መልሳችን።

ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን የድህነት
ምክንያት አንቺ ነሽ ስንላት በፍጹም እምነትና ኩራት ነው። ሄዋን ሞት ወደ ዓለም እንዲመጣ ምክንያት ስትሆን ድንግል ማርያም ግን የዓለሙ መድኅን ሕይወት የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር እንዲመጣ ዙፋን ሆና ተገኝታለችና፣ በኖኅ ዘመን ምድር በውኃ ስትጠፋ ኖኅና ቤተሰቡ ይድኑ ዘንድ መርከቧ ምክንያት እንደሆነች የጠፋውን ዓለም ይፈልግ ዘንድ እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር ይመጣ ዘንድ ምክንያት ሆናለችና የድኅነት ምክንያታችን እንላታለን።

ቅዱስ ጳውሎስ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል
እናንተም እኔን ምሰሉ።" ማለቱ የክርስቶስን ክብር መቀናቀኑ ይሆን? እርሱ ክርስቶስን እንደመሰለ እኛ እርሱን ብንመስል ክርስቶስን መሰልን ማለት ነው። እርሱ በህይወቱ ክርስቶስን መስሎ የተመላለሰ እስከ ሶስተኛው ሰማይ ተነጥቆ ሚስጥራትን የተመለከተ ስለ ቀደሙ አባቶቹ ትጋት የጻፈ እነሱ በየትኛው ቅድስናቸው ነው ቅዱሳንን ይንቁ ዘንድ ድፍረት የሆናቸው? እኔስ የትህትና አባት ክርስቶስ ዝቅ ብሎ እግራቸውን እንዳጠበ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ "እኔ ጭንጋፍ ነኝ።" 2ኛ ቆሮ 15፥8 በማለት ትህትናን ከሰበኩት ቅዱሳን፣ ስለ ትህትና ስለ
ፍቅር አብዝታ ከምትሰብከው ከተዋሕዶ ህብረት ነኝና እኮራለሁ!!!
አዎ የኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ልጅ በመሆኔ እኮራለው!

(orthodox and bible page)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
የማይገባው ተሸላሚ

ቄሱ ሲናዝዙ "ኩኑ ፍቱሐነ ወንጹሐነ ይረስየኒ ወይሬሲክሙ ድልዋነ ለመንግሥተ ሰማያት" "የተፈታችሁ ንጹሐን ሁኑ እኔንም እናንተንም ለመንግሥተ ሰማያት የተገባን ያደርገን ዘንድ" ብለው ጣታችንን ዐሥራ ሁለት ጊዜ በእግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ሲያስቆጥሩን ለወትሮ ያላሰብሁት ነገር ታሰበኝ::

"እኔንም እናንተንም ለመንግሥተ ሰማያት የተገባን ያደርገን ዘንድ" የሚለው ቃል!

መንግሥተ ሰማያትን መውረስ መቼም ከእኛ መካከል የማይፈልግ ሰው የለም:: ለመንግሥተ ሰማያት ግን የተገባን ነን ወይ?

እውነት አሁን ጌታ ቢመጣና ሁሉንም በደላችንን ትቶ ሁላችንንም በቀኙ

አቁሞ መንግሥቴን ውረሱ ቢለንና ወደ መንግሥቱ ብንገባስ? ለመንግሥተ ሰማያት የሚሆን ማንነት አለን ይሆን? ከእኛ መካከል ለመንግሥተ ሰማያት የተገባ ማን ነው?

ጌታ ሆይ እንኳን ለመንግሥትህ በምድር ላለችው ቤትህ የሚገባ ማንነት እንደሌለኝ ሳስብ "መንግሥትህ ትምጣ" ማለት አስፈራኝ::

"በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው" በተባለላት ቤትህ እንኩዋን እንደሚገባኝ መመላለስ ላልቻልሁት ለእኔ መንግሥትህን እንዴት ልመኝ? 1 ጢሞ. 3:15

" አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?” ብሎ ዳዊት ቢጠይቅ የመለህለት ውስጥ ራሴን አጣሁት:: መዝ. 15:1 ስለዚህ ለመንግሥትህ የሚሆን ማንነት ማጣቴ አሳፈረኝ::

የሰርግ ልብስ ሳልለብስ ወደ ሰርግ ቤትህ የገባሁ ብሆንስ? በመላእክት ማኅበር መካከል ዕርቃኔን ብቆምስ? እውነት የኔን ጠባይ ወደ መንግሥትህ ይዤው ልገባ ይቻል ይሆን? በመንግሥትህ ለእኔ ዓይነቱ ሰው የሚሆን ቦታ አለህ ይሆን? እርግጥ ነው በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ብለሃል:: ለእኔ ዓይነቱ ቁስለኛ የሚሆን ቤትስ ይኖርህ ይሆን? ግዴለም ከደጁም ቢሆን አስገባኝ::

ያስተማሩ የሐዋርያት ማኅበር ፣ ድል የነሡ ሰማዕታት ማኅበር ፣ ቡሩካን የሆኑ የጻድቃን ማኅበር በዚያ እንዳለ አውቃለሁ:: ወደ መንግሥትህ ብገባ የእኔ ምድብ ወዴት ይሆን? ይቅር የተባሉ ሰዎች ማኅበር የለህ ይሆን? ምሕረትህ የበዛላቸው ሰዎች ማኅበር ፣ እንደ ቸርነትህ ብዛት የተማሩ ፣ እንደ ይቅርታህ ብዛት መተላለፋቸው የተደመሰሰላቸው ሰዎች ማኅበር የለህ ይሆን? ክርስቲያን ተብዬ ልጠራ ያልተገባኝ እኔን በቸርነትህ ለመንግሥትህ ዜግነት የተገባሁ አድርገኝ::

#share

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 2016 ዓ.ም.

@diyakonhenokhaile
የሰውን ልጅ በሩህሩህነት አሸንፈው። ቀናተኛውን በመልካምነትህ እንዲደነቅ አድርገው፤ ሁሉንም ሰው ውደድ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ርቀትህን ጠብቀህ ኑር።

አባ እንጦንስ
Forwarded from መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 (²¹ዬሐንስ²¹....💜)
#መስማት_የተሳናት_እንቁራሪት!

በአንድ ወቅት የእንቁራሪቶች ውድድር እንደ ነበር ይነገራል፡፡ ውድድሩ አንድን አነስተኛ ተራራ ፈጥኖ የመውጣት ውድድር ነበር፡፡ ይህንን ውድድር ለመመልከት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ እንቁራሪቶች ተሰብስበው ምርጫቸው ለሆኑ እንቁራሪት ተወዳዳሪዎች መጮህና ማጨብጨብ ጀምረዋል፡፡

ሩጫው (ዝላዩ) ተጀመረ! ቲፎዞው ሁኔታውን ገና ሲያየው የትኛውም እንቁራሪት ተራራው ጫፍ ላይ እንደማይደርስ ስለገመተ፣ ሁሉም አሉታዊ ነገርን ማሰማት ጀምሯል፡፡ “አይ፣ ገና ከመጀመራቸው እዚያው ነው የሚዘሉት . . . ይህንን ዳገት #አይችሉትም . . .  #አይሳካላቸውም . . .” ጩኸቱ ቀጥሏል፡፡

ይህንን የብዙዎች ጩኸት እየሰሙ እነዚህ ትንንሽ እንቁራሪቶች በግራና በቀኝ እየተዘረሩ ማለክለክ ጀምረዋል፡፡ ሩጫው ቀጥሎ፣ የቲፎዞው ተስፋ አስቆራጭ ድምጽ አይሎ፣ ሁሉም እንቁራሪቶች ዝለው ሳለ #አንዲት እንቁራሪት ግን ፍጥነቷን ሳትቀንስ በመገስገስ ጫፉ ደርሳ #አሸናፊ ሆነች፡፡

ጋዜጠኞችና ዘጋቢዎች በፍጥነት ደርሰው ጥያቄን መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ሁሉም ያቃተውን ይህንን ተራራ የመውጣት ምስጢር ምን እንደሆነ ሲጠይቋት በዝምታ ተዋጠች፡፡ ደጋግመው ጥያቄያቸውን አቀረቡ፡፡ እሷ ግን መልስን አልሰጠችም፡፡ ለካ እንቁራሪቷ መስማት የተሳናት ነበረች፡፡ ምስጢሩ ያለው ያንን ሁሉ አሉታዊና ተስፋ አስቆራጭ ጩኸት #አለመስማቷ እንደ ሆነ የደረሱበት ያን ጊዜ ነው፡፡

👉🏾 አንዳንድ ጊዜ ከገጠመን የችግር ተራራ ይልቅ የበለጠ የሚያዝለንና ተስፋ የሚያስቆርጠን የምንሰማው አሉታዊ መልእክት እንደሆነ ጥሩ ማስታወሻ!

#እጠነቀቃለሁ፣ ለፍርሃት ግን ጆሮ የለኝም፡፡ ቆም ብዬ መንገዴን እንደገና እቃኛለሁ፣ ለተስፋ መቁረጥ ግን ጆሮ የለኝም፡፡ የሰዎችን ምክር እሰማለሁ፣ “አትችልም” ለሚል ድምጽ ግን ጆሮ የለኝም፡፡ ከብዙ አይነት ሰዎች የተለያዩ ሃሳቦችን ከመስማት ነጻ እንደማልሆን አውቀዋለሁ፣ ለአሉታዊዎችና ለአሸባሪዎች ግን ጆሮ የለኝም፡፡ እነዚህና መሰል መልእክቶችን አስመልክቶ እኔም ብሆን #መስማት_የተሳነኝ ነኝ፡፡

#ስብእና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሰው ስብእና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በልጅነቱ በትክክል የሚቀርጸው ካላገኘ #ተንሻፎና_ተዛብቶ_ያድጋል
ዕድሜው ከገፋ በኃላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ
አዳግቶ ሀገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሠራቱ ... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ
የሆነ ክፉ እውቀቱ... ነው።

ሼር!         ሼር!             ሼር!
     
Forwarded from መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 (²¹ዬሐንስ²¹....💜)
#መስማት_የተሳናት_እንቁራሪት!

በአንድ ወቅት የእንቁራሪቶች ውድድር እንደ ነበር ይነገራል፡፡ ውድድሩ አንድን አነስተኛ ተራራ ፈጥኖ የመውጣት ውድድር ነበር፡፡ ይህንን ውድድር ለመመልከት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ እንቁራሪቶች ተሰብስበው ምርጫቸው ለሆኑ እንቁራሪት ተወዳዳሪዎች መጮህና ማጨብጨብ ጀምረዋል፡፡

ሩጫው (ዝላዩ) ተጀመረ! ቲፎዞው ሁኔታውን ገና ሲያየው የትኛውም እንቁራሪት ተራራው ጫፍ ላይ እንደማይደርስ ስለገመተ፣ ሁሉም አሉታዊ ነገርን ማሰማት ጀምሯል፡፡ “አይ፣ ገና ከመጀመራቸው እዚያው ነው የሚዘሉት . . . ይህንን ዳገት #አይችሉትም . . .  #አይሳካላቸውም . . .” ጩኸቱ ቀጥሏል፡፡

ይህንን የብዙዎች ጩኸት እየሰሙ እነዚህ ትንንሽ እንቁራሪቶች በግራና በቀኝ እየተዘረሩ ማለክለክ ጀምረዋል፡፡ ሩጫው ቀጥሎ፣ የቲፎዞው ተስፋ አስቆራጭ ድምጽ አይሎ፣ ሁሉም እንቁራሪቶች ዝለው ሳለ #አንዲት እንቁራሪት ግን ፍጥነቷን ሳትቀንስ በመገስገስ ጫፉ ደርሳ #አሸናፊ ሆነች፡፡

ጋዜጠኞችና ዘጋቢዎች በፍጥነት ደርሰው ጥያቄን መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ሁሉም ያቃተውን ይህንን ተራራ የመውጣት ምስጢር ምን እንደሆነ ሲጠይቋት በዝምታ ተዋጠች፡፡ ደጋግመው ጥያቄያቸውን አቀረቡ፡፡ እሷ ግን መልስን አልሰጠችም፡፡ ለካ እንቁራሪቷ መስማት የተሳናት ነበረች፡፡ ምስጢሩ ያለው ያንን ሁሉ አሉታዊና ተስፋ አስቆራጭ ጩኸት #አለመስማቷ እንደ ሆነ የደረሱበት ያን ጊዜ ነው፡፡

👉🏾 አንዳንድ ጊዜ ከገጠመን የችግር ተራራ ይልቅ የበለጠ የሚያዝለንና ተስፋ የሚያስቆርጠን የምንሰማው አሉታዊ መልእክት እንደሆነ ጥሩ ማስታወሻ!

#እጠነቀቃለሁ፣ ለፍርሃት ግን ጆሮ የለኝም፡፡ ቆም ብዬ መንገዴን እንደገና እቃኛለሁ፣ ለተስፋ መቁረጥ ግን ጆሮ የለኝም፡፡ የሰዎችን ምክር እሰማለሁ፣ “አትችልም” ለሚል ድምጽ ግን ጆሮ የለኝም፡፡ ከብዙ አይነት ሰዎች የተለያዩ ሃሳቦችን ከመስማት ነጻ እንደማልሆን አውቀዋለሁ፣ ለአሉታዊዎችና ለአሸባሪዎች ግን ጆሮ የለኝም፡፡ እነዚህና መሰል መልእክቶችን አስመልክቶ እኔም ብሆን #መስማት_የተሳነኝ ነኝ፡፡

#ስብእና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሰው ስብእና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በልጅነቱ በትክክል የሚቀርጸው ካላገኘ #ተንሻፎና_ተዛብቶ_ያድጋል
ዕድሜው ከገፋ በኃላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ
አዳግቶ ሀገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሠራቱ ... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ
የሆነ ክፉ እውቀቱ... ነው።

ሼር!         ሼር!             ሼር!
     
"ጌታ ሆይ አንተን ምን ብሎ መጥራት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ጌታ ሆይ እናትህን ድንግል ብለን እንጥራትን? እንዲያ ብለን እንዳንጠራት የአንተ እናት መሆኑዋ ምስክር ይሆንብናል፤ ጌታ ሆይ እናት እንበላትን? እንዲህ እንዳንል ወንድ የማታውቅ ድንግል ናት፤ የእናትህ ነገር ለመረዳት የረቀቀ ከሆነ አንተን ሊረዳ የሚችል ሰው ማን ነው?"

ቅዱስ ኤፍሬም
#ሆሳዕና
(የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት)

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራ ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡

በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተዋቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡

#ለምን_ዘንባባ_ያዙ_ቢባል፡-
ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡

#የተምር_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡-
ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው
ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡-
ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡

#ልብሳቸውንም_ማንጠፋቸው፡-
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡

#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡…..
ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።

#መልዕክታት
ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡  (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ግብረ_ሐዋርያት
የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷   (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ምስባክ
"ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3
ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
ወይም
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2
ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡

#ወንጌል
ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡
#ንጉሥ_በአህያ_ላይ
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)

"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።

ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ። 

ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?

ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።

እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው  በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ