ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)
181 subscribers
229 photos
8 videos
19 files
38 links
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :-

፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን።

፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን።


፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን።

ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።
Download Telegram
#EOTC

ዛሬ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ " በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች " ብለዋል።

ቤተክርስቲያን ፈተናዋን እንዴት ማለፍ እንዳለባት በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቀዋለን ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው የተለያዩ አባቶች በተለያየ መንገድ ተናገሯቸው ስለተባሉት ጉዳዮች ተነስቶ መንግስት ቀየሜታውን ገልጾ ቤተክርስቲያን መልስ እንድትሠጥበት አሳስቧል " ያሉት ብፁዕነታቸው " ቤተክርስቲያንም በስፋት፣ በትኩረት ተወያይታበታለች (ቅዱስ ቋሚ ሲኖዶስ) ይሁን እንጂ የብፁዓን ሊቃነጳጳሳት ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳይ ነው የሚሆነው ፣ ምክንያቱም አንድ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ፤ ቀርቦ ተጠይቆ አውንታዊ መልስ ሰጥቶ ስህተት ነው ? እውነት ነው ? ብሎ የሚወሰን እንጂ ብግድ ተብሎ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በሌላ የተለያየ መልኩ እንዲህ ነው እንዲያነው ብሎ መናገር ህገ ቤተክርስቲያናችን አፈቅድም " ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን ሰላምን መፈለግ ፣ መሻት ፣ መልካም ነገር ማድረግ ነው ከዚህ ውጭ ሌላ አቋም የላትም " ያሉት ብፁዕነታቸው ፤ " እንደ ህግ እና ስርዓታችን በአባቶች ደረጃ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነውን ይወስናል። ይህ ቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚለውን እንዲል አልፎታል " ሲሉ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " አሁን ግራ የሚያጋባው ትላንት ለበዓለ ጥምቀቱ የተሰየመው አብይ ኮሚቴ ከከተማ አስተዳደሩ፣  ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ፣ከታላላቅ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ ይህ ከባድ ፈተና እየተነሳ እንዳለና አሁንም በዓለ ጥምቀቱን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ አይነቱን ለይታ እንድታወግዝ ፣ የራሷን መልዕክት እንድታስተላልፍ በመንግሥት አቋም ተይዞ ለአብይ ኮሚቴው ተነግሯል " ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን ያራሷ ነፃነት አላት ፣ የራሷ ክብር አላት ፣ የራሷ ነፃ መድረክ ፈላጊ ናት ሁሉም እየተነሳ ያም ይሄን አድርጊ፣ ይሄም ይሄን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን አታስተናግድም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ክፉውን ክፉ፣ በጎውን በጎ፣ መልካሙን መልካም ፤ መልካም ያልሆነውን መልካም አይደለም ብላ ለማስተላለፍ የራሷ ህግ ስርዓት አላት " ብለዋል።

" የፈለገ የሚያዛት ፣ የፈለገ የሚያሽከረክራት ፣ ያልወደደ እንደ ወደደ ፍላጎቱን ምኞቱን እንድትፈፅምለት የሚጎትታት ቤተክርስቲያንን ኖራም አታውቅም ወደፊትም ልትኖር አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ቤተክርስቲያን በራሷ ነፃ መድረክ ቆማ ችግሩን ችግር ነው ብላ መናገር አለባት እያደረገችም ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይሄ በፍፅሙ አይመጥነኝም። እንዲህ አይነቱ የኔ ቃል አይደለም ብላ #ታውጃለች ግን በግልፅ መጠየቅ ያለባትን ጠይቃ መናገር ያለበትን እንዲናገር ፈቅዳ ሁሉን ነገር በአግባቡ ታደርጋለች እንጂ በኩርፊያ በአላስፈላጊ ብሂል ይሄን ካላደረግሽ በዓል ለማክበር አልችልም ፣ ከናተ ጋር ግንኙነት የለንም እስከሚባል ድረስ የሚኖረው ነገር ከማንም ከምንም በፍፁም አይጠበቅም " ሲሉ አሳውቀዋል።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #EOTC

" የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው

ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።
 
የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?

ቅዱስነታቸው ፥ " ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም  " ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናው ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ እንደሚከባትም አመልክተዋል።

" የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ " ያሉ ሲሆን " የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል።

የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑ አሳውቀዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩ ፦
° ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤
° መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣
° ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን #ተሰሚነትና #ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው " ብለዋል።

" እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጥ ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል " ሲሉም አሳውቀዋል።

ቅዱስነታቸው፤ " በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም " ያሉ ሲሆን " ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም " ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት አስከፊ የሆነ በደል መፈጸሙን የገለጹት ቅዱስነታቸው " አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል " ሲሉም አስገንዝበዋል።

ጉባኤውም በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia