ዓርብ
የፍጥረት መካተቻ ሰው ነው። እግዚአብሔር ሰውን የፍጥረታት ዘውድ አድርጎ ሲፈጥረው ደስ ተሰኘ። ሰማይና ምድርን ፈጥሮ ደስ አላለውም፣ አንበሳና ነብር ፈጥሮ ደስ አላለውም። ደስ ያለው ሰውን ሲፈጥር ደስ አለው።
የእግዚአብሔር ልብ ያረፈው በሰው መፈጠር ነው። እግዚአብሔር ደስ የተሰኘው መልኩን ሲፈጥር ሲያይ ነው። "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው" ዘፍ.1:27
እባብ፣ ፈረስ፣ ጅብ ተፈጥሯል ይኽ ሀሉ ለሐሳቡ ማካተቻ ለሆነ ሰው መጠቀሚያ ነው። ሰው ሲፈጠር ፍጥረት ይካተታል። ሰው ሲፈጠር የእግዚአብሔር ምክር ይካተታል። እግዚአብሔር ሰውን ሲያገኝ ልቡ አረፈ። ከእሁድ እስከ ሐሙስ በፈጠረው መልካም ቢሆኑም ልቡ አላረፈም። እግዚአብሔር ሰው በሆነ ሰው ያርፋል።
ዛሬ ሰው ግማሹ እባብ፣ ዘንዶ፣ ቀብር፣ ጅብ፣እባብ፣ ምስጥ ሆነናል። ሰው ከሆንን የእግዚአብሔር ልብ ያርፋል። እግዚአብሔር ሰው ይፈልጋል። እረፍቱ ሰው ነው።
ሰው ሲናቅ፣ ብረት ሲወደድ እግዚአብሔር ያዝናል። መሬት ከሰው ይልቅ ተወደደ። እግዚአብሔር ለመላእክት ለእንስሳ አልሞተም እግዚአብሔር የሞተው ለሰው ነው። ሰው ስንሆን ሀገር ያርፋል። እግዚአብሔር ዓለምን ለመቀደስ አንድ ሰው ይበቃዋል።
ሰው የፍጥረት ዘውድ ነው። የሰማና ምድር ዘውድ ሰው ነው። የእግዚአብሔር የልቡ ማደሪያ ነን። ሳንቲም ጭቃ ውስጥ ቢወድቅ አይጣልም፣ ምንም ብንቆሽሽ አይጥለንም። ለእግዚአብሔር የማይገዛ ሕዝብ ገዥዎች ጨካኞች ይሆኑበታል። መንፈሳዊ ሰው እሳትን ያለ ውሐ፣ ጦርነትን ያለመሳሪያ ያሸንፋል፣ ባሕርን ያለ መርከብ ይሻገራል፣ መርዝን ያለመሻሪያ ያጠፋል እሾኽን ያለ ጫማ ያደቃል። ያለ ጋሻ ይመክታል፣ ያለ ጦር ያሸንፋል ያለ ሠራዊት ይነግሳል።
ዓርብ የፍጥረት መካተቻ ነው።
በእግዚአብሔር ፊት መጣል ነው ክፉ። እግዚአብሔር ከጣለ የሚያነሳ የለም። ሰው ሲጥል እግዚአብሔር ያነሳል።
ዓርብ ማለት የመና መካተቻ ነው። እስራኤላውያን የአርባ ቀን ጉዞ አርባ ዓመት ተጓዙ። በበደላቸው ምክንያት ረዘመ። ዛሬ ኃጢአታችን በዝቶ መከራችን ከብዷል። በዚኽ ግዜ ዛርም ሰው ለበዓል ይዘፍናል።
እስራኤላውያን ፊንቆን ሲደርሱ ይመግባቸው የነበረ መና ቆመ። ተካተተ። ከነአን ሲደርሱ እሸቱ ሲቀምሱ መና ቆመ። በልተውት የማያድነው ሞትን ያላጠፋ ምግብ ቀረ። የዘለአለም እንጀራ ጀመረ ማለት ነው። ለመስዋዕት ፍየል ማረድ፣ በሬ፣ርግብ ማረድ ቀርቶ ክርስቶስ የታረደበት ሆነ። የረሃብ መካተቻ የምግብ መጀመሪያን ቀን ነው። የነፍስ ምግብ የተጀመረበት ነው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ የተባለበት ነው።
ጥም ይብቃ ብሎ ደሙን ያጠጣበት ረሃብ ይብቃ ብሎ ስጋውን የመገበበት ቀን ዓርብ ነው። ረሃባችን ያለቀው ዓርብ ነው። ዓርብ የፍዳ መካተቻ ነው። በለስ በመብላታችን የእሳት የበረዶ እዳ ተፈርዶብን ነበር ዛሬ እዳችን ተከፍሎ ያለቀበት ነው። ቁስላችን ቆስሎ ውድቀታችን ወድቆ እዳችን ከፍሎ ጨረሰልን። "በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው" ኢሳ.53:4
ጌታ ዓርብ ሁሉም ተፈጸመ አለ። የሞት ሥልጣን ያበቃበት፣ የሞት ግዛቱ ያበቃበ፣ ትንቢተ ነቢያት የተፈጸመበት ነው፣ የዲያብሎስ ሰንሰለቱ ተበጠሰ፣ መንጋጋው ወለቀ፣ መራቆት አለቀ፣ የነጻነት ቀናችን ዓርብ ነው።
ንዋይ ካሳሁን

❤14🙏5👌1
ችግሩ እዚኽ ላይ ነው!!
የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ የሲኖዶስ አጀንዳ ኾኖ ባይፈልጉትም አንድ ቀን ሙሉ ተነጋግረዋል። በአጭሩ ምርር ያለችውን እውነት ልንገራችሁ።
የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በዝርዝር አቅርበዋል። ሌሎችም ጳጳሳት ተጨማሪ ሐሳብ ሰጥተዋል።
የመጀመሪያው ያንን ኹሉ አጀንዳ ሲነሳ ሲወድቅ ፓትርያርኩ ትንፍሽ አይሉም። "ያኔ የኔ ሕዝብ ሲያልቅ እናንተ መች ተናገራችሁ ዛሬ የእናንተ ሲኾን ነው ወይ" ብለው ዝም ጭጭ።
ሌላው ሳዊሮስና ዲዮስቆሮስ ጉዳዩ ጠበቅ ብሎ እንዲኼድ አይፈልጉም። ምክንያቱም ከማንም ከምንም ጋር እንዲነካኩ አይፈልጉም የሚል ነው።
ጠቅላይ ምኒስትሩን እናነጋግር ሲባል "እኛ እናገኛቸዋለን" ነው ያሉት እነ ሳዊሮስ። ሌሎቹ እናንተ እንዳገኛችኋቸው እኛም እናግኛቸው አሉ። ግን ማንም የተስማማ የለም።
መጨረሻ ኦርቶዶክሳውያኑ ምን ይሉናል እንዳይባሉ ነው ወደ ሰላም ምኒስቴር የሄዱት። ኮሚቴ ተዋቅሮ ገንዘብ ይሰብሰብ የተባባሉት።
ዋናው የገዳይ ሽፋን ሰጪ ፓትርያርኩ እና ሳዊሮስ ዲዮስቆሮስ ናቸው። ይኽ ተመዝግቦ ይቀመጥ።

❤17🤔5👍1👌1
ዓርብ
የክርስቶስን መስቀልና ለሰው የፈጸመውን የድኅነት ሥራ ማሰብ። በክርስትና ሕይወትና እምነት ዓርብ ተራ የሳምንቱ ቀን ብቻ አይደለም። በተለይም የዓርብ ዕለት የጌታችንን መከራ፣ ስቅለት፣ ሞትና ለሰው ልጅ የፈጸመውን የድኅነት ሥራ የምናስብበት ቅዱስ ዕለት ነው። ይኽንን በታላላቅ የነገረ መለኮት አባቶች አስተምህሮ መሠረት እንመልከት።
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ፦
ሞትን በሞቱ ድል አደረገ። በመጽሐፉ On the Incarnation የሚያብራራው፣ ሰው በኃጢአት ምክንያት ለሞትና ለጥፋት ተገዥ ሆነ። የእግዚአብሔር ቃል ግን ሰው ሆኖ ሞትን በራሱ ሞት ድል አደረገ። የዓርብ ምሥጢር እዚኽ ነው፦ ሞትን የፈጠረው አይደለም፤ ሞትን የሚያሸንፈው ክርስቶስ ለእኛ ሞትን ተቀበለ። መስቀሉ የሽንፈት ምልክት ሳይሆን የሞት ድል መግለጫ ነው።
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ፦
የሥጋ ለባሹ ቃል መከራን ተቀበለ። እርሱ በክርስቶስ ተዋሕዶነት ላይ በጥልቀት ያስተማረ ታላቅ ሊቅ ነው። እንደ ቄርሎስ አስተምህሮ፣ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ሌላ ሰው ሳይሆን ለእኛ ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው። አምላክነቱ አልተለወጠም፤ በሥጋው ግን መከራንና ሞትን ተቀበለ። የዓርብ መስቀል የእግዚአብሔር ለሰው ያለውን ፍቅር በግልጽ የገለጠበት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦
መስቀል የዲያብሎስ ድል ነው። በስብከቶቹ ውስጥ መስቀሉ የዲያብሎስን ኃይል የሰበረበት የድል ምልክት መሆኑን ያስረዳል። ዲያብሎስ በሞት አማካኝነት ሰውን በፍርሃት ይገዛ ነበር። ክርስቶስ ግን በራሱ ሞት የሞትን ኃይል ሰበረ። “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ዕብ. 2፥14-15 ይህንን ያስረዳል። የዓርብ ኀዘን ከተስፋ የተለየ አይደለም፤ የትንሣኤ ድል መጀመሪያ ነው።
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘናዚያንዙ፦
የክርስቶስ ሞት የሰውን ባሕርይ ፈወሰ። በነገረ መለኮት የሰው መዳን ከክርስቶስ ሰው መሆንና ሙሉ የሰውን ባሕርይ መውሰድ ጋር የተያያዘ መሆኑን አስተምሯል።
ከታዋቂ አስተምህሮዎቹ አንዱ፦ “ያልተወሰደው አልተፈወሰም።” ይኽ ማለት ክርስቶስ የሰውን ባሕርይ ሙሉ በሙሉ በመውሰዱ፣ የሰውን ሕይወት በሙሉ ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን መጣ ማለት ነው። ክርስቶስ ለእኛ ብቻ አልሞተም፤ የወደቀውን የሰው ባሕርይ ለማደስም መጣ።
ቅዱስ ማክሲሞስ ዘኮንፈሰር፦
መስቀል የፍቅር ፍጹም መገለጫ ነው። የክርስቶስን ሥጋዌ፣ መከራና የሰው መንፈሳዊ ለውጥ በጥልቀት ያብራራ ሊቅ ነው። በአስተምህሮው መሠረት የክርስቶስ ፍቅር እስከ መስቀል ድረስ የደረሰ ነው። እርሱ ለጠላቶቹም ራሱን ሰጠ። ይኽም ለክርስቲያን ሕይወት ታላቅ ምሳሌ ነው። መስቀሉን ማሰብ ማለት የክርስቶስን ፍቅር መማርና በሕይወታችን መፈጸም ማለት ነው። መስቀሉን የሚያስብ ሰው ጥላቻን መተው፣ ይቅር ማለትና ሌሎችን መውደድ አለበት።
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ፦
መስቀል የሕይወት ዛፍ ነው። በመዝሙሮቹና በመንፈሳዊ ግጥሞቹ የመስቀልን ምሥጢር በሚያምር መንገድ ገልጧል። በክርስቶስ መስቀል የአዳም ውድቀት የጀመረበት የሞት መንገድ ወደ ሕይወት መንገድ ተለወጠ። በገነት የሕይወት ዛፍ ነበር፤ በጎልጎታ ደግሞ የሕይወት ምንጭ የሆነው ክርስቶስ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ። የመስቀሉ ዕንጨት የሞት ምልክት ሳይሆን የዘላለም ሕይወት ምንጭ ሆነ።
ሊቁ አውግስጢኖስ፦
መስቀሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ማስረጃ ነው። የክርስቶስን መስቀል የእግዚአብሔር ለሰው ያለው የማይለካ ፍቅር መገለጫ አድርጎ ያብራራል። እግዚአብሔር ሰውን ከሩቅ ሆኖ ብቻ አልወደደውም። ለሰው መዳን ራሱን አሳልፎ ሰጠ። ስለዚህ መስቀሉን ስናስብ እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደን እና እኛም ለሌሎች ምን ያኽል ፍቅር ማሳየት እንዳለብን እንማራለን።

❤9
እኛ ዓርብን እንዴት ማሳለፍ አለብን?
ከእነዚህ የአበው አስተምህሮዎች በመነሳት የዓርብን ቀን በስድስት መንገዶች ማሰብ ይቻላል።
* በንስሐ፦ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን የተቀበለውን መከራ በማሰብ ከኃጢአት መመለስ።
* በጸሎት፦ የጌታን ሕማማት በማሰብ ልባችንን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ።
* በጾም፦ ሥጋዊ ፍላጎታችንን በመግዛት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ማጠናከር።
* በይቅርታ፦ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ ጠላቶቹ የጸለየውን በማሰብ እኛም የበደሉንን ይቅር ማለት። (ሉቃስ 23፥34)
* በምጽዋትና በርኅራኄ፦ ክርስቶስ ራሱን ለሰው እንደሰጠ እኛም ለተቸገሩት መስጠት።
* በቅዱስ ቁርባን፦ በቤተ ክርስቲያን ትምህርትና በሥርዓተ ቅዳሴ የክርስቶስን የድኅነት ሥራ ማሰብና በተገቢው ዝግጅት ቁርባን መቀበል።

❤14
ዓርብን ማሰብ
ሰማዕታቱን ያስጨከረችው ዓርብ ናት። ጊዮርጊስ መንከራኩር ገብቶ ሲፈጭ ያስጨከነው ዓርብን ማሰብ ነው። አንገቱ ሲሰየፍ ተመቻችቶ አንገቱን የሰጠው ዓርብን እያሰበ ነው።
ቅድስት አርሴማን አንገቷን ለቆራጮች ልብሳን ገልጣ የሰጠችው ዓርብን እያሰበች ነው።
ቅዱስ ጳውሎስን ቅዱስ ጴጥሮስን ለስቅላት ለሰይፍ ያስቻላቸው ዓርብን ማሰብ ነው።
የዓርብ ቀን ጾም ከጌታ ሕማም መሳተፊያ ነው።
ዓርብን ማሰብ ያልቻለ ሰው በምንም መከራ መጽናት አይችልም።ፕ ሰማዕትነትም አይገባውም። መከራ ሲሰማ ይሰቀሳል። ዓርብን ካላሰብክ ስለ አርሲ ሰማዕታት ማሰብ አትችልም። የክርስትና እንብርቱ ዓርብን ማሰብ ነው።

❤21🙏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እመለሰታለኹ
ይኽንን አራምባና ቆቦ ንግግር!!
ይኽንን አራምባና ቆቦ ንግግር!!
የመጨረሻ መንፈሳዊ ግንዛቤ
የዓርብ ታላቅ ምሥጢር ይኽ ነው፦
* በመስቀሉ የኃጢአት ኃይል ተሰበረ።
* በሞቱ ሞት ተሸነፈ።
* በደሙ የሰው ልጅ መቤዠት ተፈጸመ።
* በፍቅሩ የሰው ልጅ ወደ አምላኩ የሚመለስበት መንገድ ተከፈተ።
አንድ አስፈላጊ ነጥብ፦
የክርስቶስን መስቀል ማሰብ ማለት የ2000 ዓመት ታሪክን ብቻ ማስታወስ አይደለም። የድኅነቱ ፍሬ በዛሬው ሕይወታችን እንዲገለጥ መኖር ማለት ነው። እንዲኽም በየዓርቡ ይኽንን ማሰብ የክርስቶስን መሥዋዕትነት እንደገና መፈጸም ሳይሆን አንድ ጊዜ ለዘላለም የተፈጸመውን የድኅነት ሥራ በእምነት መዘከር ነው።
ስለዚህ ዓርብ የምናስበው ክርስቶስ ምን ያኽል መከራ እንደተቀበለ ብቻ ሳይሆን፣ እኛ በዚያ ታላቅ ፍቅር ምን ዓይነት ሰው መኾን እንዳለብንም ጭምር ነው።

❤12🙏1
ዓርብ ላይ ኾኜ ዓርብን ሳስብ
ዛሬ በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን መገደል መጨፍጨፍ ቆጭቷችኹ፣ መፍጠን አለብን ጊዜ የለም እያላችኹ በፍጥነት ወገኖቻችኾን ለመታደግ በገንዘብ በምክር ድጋፍ ያደረጋችኹ የዓርብን መከራ ተሳትፋችዃል።
ምንም እንኳ ብዙ ቢቀረን በጥቂት ወራት ግን እግዚአብሔር የሠራውን ነገር ለማሰብ ይደንቀኛል። ብዙ ቢከፋኝም ጭላንጭል ብርሃን ሳይ በጣም ደስ ይለኛል።
ከዚኽ በኋላ በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ ብታዩ ብትሰሙ በእኛ ስንፍና እንጂ በገዳዮች ጉብዝና አይደለም።
ሕዝቡ ቆመን አንሞትም ብሎ ቆርጧል። ምን ብዬ ልጻፍ.... ግን ባካችኹ አግዙን እያለን ነው።
የእኛ ቸልታ ብቻ ነው እንዲሞቱ የሚያደርገው። አንድ ሰው ሙሉ ቤተሰቡን አካባቢውን እንዲጠብቅ ለማድረግ $1500 ዶላር ያስፈልጋል። በብር እስከ 300 ሺኽ ሰው ማለት ነው። የምትችለትን አድርጉ። እየሠራን ያለነው ይኽንን ነው። እናንት ትጉኀን ያገዛችኹ ዋጋችኹን ከሰማዕታቱ በረከት ያሳትፋችኹ።

❤12👍2
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ኦርትዶክሳውያን ተማሪዎች ዛሬ ይዘው የወጡት መፈክሮች
፩ . የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሞት ሞታችን ነው፣ሀዘናቸው ሀዘናችን ነው።
፪. የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን የሚገደሉት፣የሚታረዱት፣በእሳት የሚቃጠሉት አንገታቸው ላይ ባሰሩት ማዕተብ ነው!
፫. በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብ በኦርቶዶክሳያውን ላይ የሚደረገው ፍጅት ይቁም!
፭. ዝምታችን እንደ ፍርሃት አይቆጠር!
፮ . ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል አይደለም
፯. አርሲ ውስጥ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚደረገው ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ይቁም!
፰. የክርስቲያኖች ሕመም የማይሰማው እርሱ ክርስቲያን አይደለም!
፱. መንግስት በክርስቲያኖች ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ያስቁም!
፲. ከዚኽ በኋላ በሃይማኖታችን አንደራደርም!
፲፩. እየሞትን አንበዛም!
፲፪. አርሲ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!
፲፫. ኦርቶዶክሳውያን በጅምላ ሲጨፈጨፉ እና ሲሰደዱ የማይገዳው እረኛ እረኛችን ሊሆን አይችልም!!
፲፬. አባቶች ሆይ! በድሆች ገንዘብ እየኖሩ ድሆች በጅምላ ሲታረዱ ዝም ማለት አረመኔነት ነው።
፲፭. ሕንጻ ሥላሴ እየፈረሰ ስለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ማውራት ይቁም
፲፮ . አትግደሉን አታፈናቅሉን ቤተ ክርስቲያን አትቃጠል ማለት ፖለቲካ አይደለም!!
@የድምጽ አልባዎች ድምጽ

❤38👌4👍1🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውነቷን ቆፍጠን ብለኽ ስማ!! ከዚኽ ውጭ የሚያተርፍኽ ኀሳብ የለም። ግራኝን ያስቆመው መሸነፉ ነው።
💯20👍2