ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሚያዝያ ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ቶማስ ለተገለጠለት (ለጥንት ዳግም ትንሣኤ)፣ ለአባታችን #ለቅዱስ_አዳምና_ለእናታችን_ቅድስት_ሔዋን ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው፣ #ለቅዱስ_ኖኅና ለንጉሥ #ቅዱስ_ዳዊት ለልደታቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_በትንሣኤ_ሳምንት_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጐኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም "ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመንኩ" አለ። ጌታችንም "ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው" ብሎ መለሰለት።
❤ በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች።
❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶቹም ጸሎት በተጋዮች ጻድቃን በድል አድራጊዎች ሰማዕታትም ጸሎት ይልቁንም በእመቤታችን አምላክን በወለደች በክብርት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ይማረን ዘንድ ወደርሱ እንለምናለን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባታችን_ቅዱስ_አዳምና_እናታችን_ቅድስት_ሔዋን፦ ይህን አባታችን አዳምን ሳይፈጥረው አስቀድሞ በሰማይና በምድር ያለውን አዘጋጀለት። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ መላእክትንም ስለርሱ ፈጠረ።
❤ ከዚህም በኋላ በኤዶም ተክልን አዘጋጀለት እርሱም የፍሬው ጣዕም በየራሱ ልዩ ነው የሚያሻውን ሁሉ አከናውኖ እንሆ ከምድር መካከል ይኸውም በጎልጎታ ነው። አፈር አንሥቶ በሦስት ሰዓት እርሱን ፈጠረው። ከአራት ባሕርያት ይኸውም ውኃ፣ እሳት፣ ነፋስና መሬት ነው በአርአያውና በምሳሌው ራሱን አስመስሎ ፈጠረው በፊቱም እፍ ብሎ የሕይወት መንፈስን አሳድሮ የሚናገርና የሚያስተውል የሚያውቅ አደረገው የብርሃንንም ልብስ አልብሶ ንጉሥ፣ ነቢይ፣ ካህን፣ አስተዳዳሪ አድርጎ በፈጠረው ሁሉ ላይ ሾመው።
❤ ከዚህም በኋላ አይቶ ስማቸውን ይሰይም ዘንድ አራዊትን እንስሳትን የሰማይ ወፎችን ሁሉ ወደርሱ አመጣ። አዳምም መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረው ለሁሉም ስም አወጣላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣበትና አንቀላፋ ከጐኑም አንድ ዐጥንትን ነሣ ቦታዋንም በሥጋ መላው እግዚአብሔርም ሴት አድርጎ አሳምሮ ሠራት በአዳምም በፊቱ አኖራት። አዳምም ነቅቶ "ይቺ ከዐጥንቴ ዐጥንት ከሥጋዬ ሥጋ ናት ሴት (ሚስት) ትሁነኝ ብሎ ተናገረ ስሟንም ሔዋን" አላት።
❤ አዳምም በጎልጎታ ቁሞ የፈጣሪውን ቃል እየሰማ ሳለ እንሆ ከሚስቱ ከሔዋን ጋራ በፊት በኋላ ሁነው በየነገዳቸው አዳምን ስለ አከበረው መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደመና ተሸክማ ወሰደቻቸው በኤዶም ገነትም አኖራቸው።
❤ እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን "በገነት ካለው ተክል ሁሉ ብሉ ግን ከገነት መካከል ዕፀ በለስን አትብሉ ከእርሱ በበላችሁ ቀን ሞትን ትሞታላችሁ" አላቸው። አዳምም ገነትን እያረሰና እየቆፈረ ከፍሬዋም እየተመገበ ከመላእክት ጋራ ሲያመሰግን ኖረ።
❤ የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ግን ከማዕርጉ በወደቀ ጊዜ በአዳም ጌትነትና ክብር ቀንቶ በእባብ አድሮ ወደ ሔዋን ሔደ። ያንን ዕፀ በለስንም ትበላ ዘንድ አታለላት አምላክ የመሆንንም ተስፋ አሳደረባትና አሳታት። ያንን ዕፀ በለስንም በአየችው ጊዜ አማራት በልታ ለባልዋም አበላችው ያን ጊዜ የብርሃን ልብሳቸው ከላያቸው ተገፈፈ። እነርሱም ራቁታቸውን እንደሆኑ አውቀው በበለስ ቅጠል ኅፍረተ ሥጋቸውን ሸፈኑ።
❤ እግዚአብሔርም ስሕተታቸውን አውቆ አስቀድሞ እባብን ረገመ በእርሷና በሴቲቱ ዘር መካከል ጠላትነትን አጸና። በሔዋንም ላይ "በፃር በገዐር ውለጂ ወልደሽም መመለሻሽ ወደባልሽ ይሁን እርሱም ይግዛሽ" ብሎ ፈረደባት። አዳምንም እንዲህ አለው "ስለ አንተ ምድር የተረገመች ትሁን ጥረህ ግረህ እንጀራህን ብላ አንተ አፈር ነህና ወደ አፈርነት ትመለሳለህ" አለው።
❤ እግዚአብሔርም የቁርበትን ልብስ አዘጋጅቶ አለበሳቸው ሰባት ዓመት በተድላ ከኖሩ በኋላ በምሽት ጊዜ ከኤዶም ገነት ወጡ። አዳምም በማለዳ ፀሓይ ሲወጣ ነጭ ዕጣን ቀንዓት ሰሊሖት የሚባል ሽቱ ከሎሚ ውኃ ጋር አጠነ። አዳምም በኤዶም ገነት እንደተማረ ምድሪቱን እያረሰና እየቆፈረ ኤልዳ በሚባል ምድር ኖረ።
❤ አዳምም ሔዋንን በግብር አወቃት ቃየልን ከእኅቱ ጋራ ወለደችለት ከእርሱም በኋላ አቤልን ከእኅቱ ጋራ ወለደችው ቃየልና አቤልም አድገው አካለ መጠን አደረሱ። ወደ እግዚአብሔር መሥዋዕት በአቀረቡ ጊዜ ጌታ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ ስለዚህም ቃየን ተቆጣ በአቤልም ቀንቶ ገደለው። አዳምም በልጁ በአቤል ሞት እያዘነና እያለቀሰ አራት የዘመን ሱባዔ ኖረ። ከዚህም በኋላ ሴት ተወለደለት በእርሱም መታሰቢያው ጸና ከእርሱም በኋላ ብዙዎች ወንድንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
❤ እግዚአብሔርም ንስሓውንና ልቅሶውን አይቶ የድኅነት ተስፋ ሰጠው። "አምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ወደ ዓለም መጥቼ ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ ሕፃንም ሁኜ በሜዳህ ውስጥ እድሀለሁ በመስቀሌና በሞቴም አድንሃለሁ" አለው።
❤ አዳምም ከገነት በወጣ ጊዜ የወሰደውን ወርቅ አርቤና ዕጣን ለልጁ ለሴት ሰጠው እንዲህም አለው "በኋላ ዘመን የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ ከድንግል ይወለዳል ያን ጊዜ የጥበብ ሰዎች ይህን ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን እጅ መንሻውን ያመጡለታል" እርሱም መዝግቦ በዕቃ ቤት አኖረው። ወደ ኖኅም እስኪደርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ኖረ ከኖኅም የምሥራቅ ሰዎች ወደ ሆኑ የጥበብ ሰዎች እስኪደርስ ተላለፈ። እነርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምጥተው ለእግዚአብሔር ልጅ እጅ መንሻ አድርገው አቀረቡለት እመቤታችንም ከእጃቸው ተቀብላ በኋላ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሰጠችው ቅዱስ ጴጥሮስም ለቀሌምንጦስ ሰጠው።
❤ አዳምም የሚያርፍበትን ሰዓት በአወቀ ጊዜ ልጁ ሴትን ጠርቶ "ከመሞቴ በፊት ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ወደእኔ አቅርባቸው" አለው። የአባቱን ቃል ሰምቶ ዕንባው በጉጩ ላይ እየፈሰሰ ወጣ አዳምም አቀረባቸው። አዳምም በአያቸው ጊዜ ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አለቀሰ። እነርሱም ሲያለቅስ በአዩ ጊዜ ሁሉም በአንድነት ወደ እግዚአብሔር በግምባራቸው ተደፍተው አለቀሱ "ምድር እንዴት ትሸፈንሃለች ከዐይኖቻችንስ እንዴት ትሠወራለህ" አሉ።
❤ ከዚህም በኋላ አባታችን አዳም ሁሉን ልጆቹን ባረካቸው መረቃቸው። ልጁን ሴትን እንዲህ አለው "ይቺ ዓለም ድካምና ችግርን የተመላች ናትና በእግዚአብሔር እየታመንክ ዕውነትን ንጽሕናን ጠብቅ ሰይጣን ወደሚያሳይህ ምትሐቱና ወደ ነገሩ አታዘንብል። በሞትኩ ጊዜም ሥጋዬን ወስዳችሁ ሰሊክ ሚዓ በሚባል ሽቱ ገንዛችሁ በግምጃ ቤት አኑሩኝ የጥፍት ውሃ ይመጣ ዘንድ አለውና ፍጥረት ሁሉ ይሰጥማል ከስምንት ነፍስ በቀር የሚቀር የለም። ልጄ ሆይ ለወገኖችህ ቋሚ ሁነህ እግዚአብሔር በመፍራት ጠብቃቸው የዕውነት

👍1
መንገድንም ምራቸው ለሰይጣንም እንዳይታዘዙና እንዳያጠፋቸው አደራ አስጠብቃቸው። ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ከቃየል
ልጆች ለያቸው አንድ ይሆኑ ዘንድ ከቶ አትተዋቸው ወደ ሥራቸውና ወደ ጨዋታቸውም አይቅረቡ" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ልጁ ወደ ሴትና ወደ ሔዋን መለስ ብሎ ያንን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከእርሳቸው ጋራ አኑረው ይጠብቁት ዘንድ አደራ አላቸው። እንዲህም አላቸው "የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ሥጋዬን ከወርቁ ከከርቤውና ከዕጣኑ ጋራ ወደ መርከብ ያስገቡ ከዚያም በኋላ በምድር መካከል ያኑሩት። ከብዙ ዘመናት በኋላም ያቺን አገር ይወርዋታል እሊህንም ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከብዙ ምርኮ ጋር ይወስዱትና አካላዊ ቃል መጥቶ ሰው እስኪሚሆን ድረስ በዚያ ይጠበቃል።ማሕያዊት ነገሥታትም ይዘው መጥተው ይገብሩለታል ወርቁ ስለ መንግሥቱ፤ ዕጣኑ ስለ ካህነቱ፤ ከርቤውም ስለሆች ሞቱ ነው" አላቸው።
❤ ለአባታችን አዳምም ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሲሆን መላልኤልም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ሲሆነው በተፈጠረባት ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት ዐረፈ። ያረፈባትም ሰዓት ከገነት የወጣባት ናት በዚያን ጊዜም የመላእክት ሠራዊት ከልጆቹ ጋራ ተሰበሰቡ። መልካም አገናነዝም ገነዙት በብዙ ሽቱዎችም መዓዛውን አጣፈጡ። ይህም በገነትና በደብር ቅዱስ ያለ ነው። ሥጋውንም በፀሐይ መውጫ በኵል በዋሻ ውስጥ አኖሩ የሚያበራ መብራትም አኖሩ ከእርሱም ጋር ወርቁን፣ ከርቤውንና ዕጣኑን አስቀመጡ ዋሻውንም በአዳምና በሔዋን በሴት ቁልፍ ቆልፈው አተሙት። የጥፍት ውኃም እስከ መጣ ድረስ ሴትና ልጆቹ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግሉ ኖሩ።
❤ ከዚህ በኋላም ኖኅ በአምላክ ትዕዛዝ ደብረ አራራት እስከሚደርሰው ከእርሱ ጋራ የአባታችን የአዳምን ሥጋ በመርከብ ወሰደው። ከዚያም ሴምና መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራቸው ይዘውት ሔዱ ከቀራንዮ ቦታ ደርሰው በዚያ ቀበሩት መልከ ጼዴቅም በዕጣን በቊርባን ሲያገለግል ኖረ። የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ ከድንግል ልጁ በተወለደ ጊዜ መድኃኒት በሆነች ሞቱ አድኖ ወደ ቀደመው ርስቱ መለሰው እርሱ ለከበሩ ደጋጎች ነቢያት ለተጋዳዮች ሰማይታትና ጻድቃን አባት ነውና ስለእርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ዓለም መጥቶ ሰው ሁኗልና።
❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችን የአዳም የእናታችን የሔዋን የቀደሙ የሁሉም አባቶች በረከት በላያችን ለዘላለሙ ይደር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ 6 ስንክሳር።

❤ እንኳን #ለሰሞነ_ሕማማት_ለመጀመርያ_ቀን #ለአንጾሖተ_ቤተ_መቅደስ (ለቤተ መቅደስ መንጻት) እና መርገመ በለስ በሰላም አደረሰን።
❤ #ዕለተ_ሰኑይ_ሰኞ።
❤ ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ የቤተ መቅደስ መንጻት እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9፡፡
❤ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ "ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ ...፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም"። ሉቃ13፥6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡
❤ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡
❤ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡
❤ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡
❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበ ሰላም አሜን።
❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾምና የስግደት ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ እንኳን #ለሰሞነ_ሕማማት_ሦስተኛ_ቀን_ለምክር፣ #ለመልካም_መዓዛ_ላለውና_ለዕንባ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
❤ #ዕለተ_ረቡዕ።
❤ ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፡፡ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሓፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑ ብዙውን ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጥር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ ማቴ. 26፤1-5፣ ማር. 14፤1-2 የሐዲስ ኪዳን ካህናት ምእመናን በዚህ ዕለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ከእህልና ውኃ ተለይተው፣ መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው፣ የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ስለዚህ ታሪክ የሚያወሳውንም በማንበብ እስከ ኮከብ መውጫ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ ይሁዳ ማለት ታማኝ ማለት ቢሆንም እንደ ስሙ ግብሩ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ስምና ግብሩ አልተባበረለትም፡፡ እኛ እንደ ስማችን ይሆን ግብራችን?
❤ መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል፡፡ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት ከእንግዲህ በኃጢአት ተጎድቶ የኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚሁ መልካም ሽቶ ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስላቀረበች ነው፡፡
❤ የእንባ ቀንም ይባላል፡፡ ይህም ይህችው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፡፡ ማቴ. 26፤6-13፣ ማር. 14፤3-9፣ ዮሐ. 12፤1 ከዚህም እያንዳንዳችን ልንማር የሚገባን ነገር አለ፡፡ ይኸውም የራሱን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡
❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበ ሰላም።
❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለብርሃነ_ትንሣኤው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሉ ሉያ "#ይትፌሣሕ_ሰማይ_ወትትሐሠይ_ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ኅምዝ ወይወውዑ አድባር ወአውግር ወኵሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሓ በሰማያት #ወምድርኒ_ትገብር_ፋሲካ_ተሐጺባ_በደመ_ክርስቶስ። ትርጉም፦ ምድርና ሰማይ ይደሰቱ፣ ቀርነ መለከትም ይነፋ፤ ተራሮችና ኮረብቶችም የዱር ተክሎችም ይደሰቱ፤ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ፣ #ምድርም_በክርስቶስ_ደም_ታጥባለችና_ፋሲካ (ደስታን) ታደርግ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
❤ #ትንሣኤ።
❤ ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀል ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና።
❤ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን ሙታንና ሕያውን ደስ አላቸው በዚች በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ቅዱስ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸው ነውና። ለእርሱም ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 29 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ 77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ 24፥1-13።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ 117፥24-25 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥20-41፣ 1ጴጥ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 2፥22-37። የሚነበው ወንጌል ዮሐ 20፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃነ ትንሣኤ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

🔴🔴🔴
"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም" ሉቃ፦24፥5
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሕያው ከሙታን መካከል ይኖር ዘንድ ይቻለዋልን?
ቅዱስ ጳውሎስ "ብንኖር ለጌታ ነው ብንሞትም ለጌታ ነው" እንዳለ በክርስቶስ ያለን እኛ ሕያው እንሆን ዘንድ ተጠርተናል።
🔴
ውድ የፍኖተ ብርሃን ልጆች በአገልግሎታችን የሚገጥሙንን ችግሮች ከኛ ፍላጎት ይልቅ የክርስቶስን ዓላማና ፍላጎት በማስቀደም። እንዲሁም ክርስቶስን ከልብ በመውደድ፤ ጥላቻንና መናናቅን አርቀን አገልግሎታችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ዕለት ተዕለት ልንተጋ ይገባል።
ውድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሰው በየቀኑ
የሚወለድ በየቀኑ ደግሞ በስራው የሚሞነገር ግን ሕያው ይሆን ዘንድ የተፈጠረ ነው።
እናም ሕያውነታችንን ለማስጠበቅ በአገልግሎታችን ተግተን ፈጣሪ ከላይ ሊሰጠን ካቀደው ፀጋና በረከት እንዳንጎድል በቅንነት እናገልግል ዘንድ ለማስታወስ እንወዳለን።
።
።
።
የትንሳኤው በረከት አይለየን። አሜን🙏
የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ፅ/ ቤት

🍂 ሰኞ ✨ #ማዕዶት ✨
ዐደወ = ተሻገረ
ማዕዶት = መሻገር
✨ዛሬ ሰኞ የፋሲካ ማግስት ማዕዶት የሚል ስያሜ በቤተ-ክርስቲያን ተሰጥቶታል ትርጓሜውም መሻገር ማለት ነው። እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን ቀን ነው ፋሲካ ብለው የሚያከብሩት እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ባሕረ ኤርትራን ከፍለው እስራኤላውያን ተሻግረው ፈርኦንን ከነሰራዊቱ አስጥመው ወደ ዘለአለማዊ እረፍት ምድር ከነዓን ገብተዋል ይኽ ምሳሌ ነው ሙሴ የክርስቶስ በትር የመስቀል ባሕረ ኤርትራ የሲኦል ፈርኦን እና ሰራዊቱ የዲያብሎስ እስራኤላውያን የምዕመናን ምሳሌ ናቸው ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሲኦልን ከፍቶ አዳምን እና ልጆቹን አሻግሮ ዲያቢሎስን በሲኦል አስጥሞ ምዕመናንንበተድላ ገነት በምስጋናና በእልልታ አኑሯቸዋል። በዚያምጊዜ የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘምረዋል እንዲህም ብለው ተናግረዋል ።
#በክብር_ከፍ_ከፍ_ብሎአልና_ለእግዚአብሔር_እዘምራለው ፤
#ፈረሱንና_ፈረሰኛውን_በባሕር_ጣለ ።
.
.
.
✨የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው።
( ዘጸ 15 ፥ 1 , 4 )
👉 በመንገድም ይጠብቃቸውም ዘንድ መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ይራዳቸው ነበር። ( ዘጸ 23 ፥ 19 )
🍀 ይህንንም በዓል የፋሲካ ( የመሻገር ) በዓል ብለው በየአመቱ ያከብሩ ነበር እሥራኤላውያን።
✨ ከግብጽ ነጻ ቢወጡ ፤
ፈርኦን ከሠራዊቱ በባሕር በሲጥም ፣
የኤርትራን ባሕር ተሻግረው ከነዓን ቢገቡም፤
#ዘላለማዊ_ዕረፍትን_ግን_አላገኙም ።
የሲኦልን ባሕር አልተሻገሩም ፤
ከዲያብሎስም አገዛዝ ነጻ አልወጡም።
🍂 + + + + + 🍂
ዘመኑ ሲደርስ በመጀመሪያው ፋሲካ በምሳሌ የተገለጸው
#አማናዊው_ፋሲካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ
+ እውነተኛውን መሻገር አሻገረን።
+ ከሞት ወደ ሕይወት ፣
+ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ፣
+ ከጨለማ ወደ ብርሃን መለሰን ።
✨ ከግብጽ ከመሻገራቸው አስቀድሞ ስለ ታረደው ስለ ፋሲካው በግ አማናዊው ፋሲካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ታርዶ ከሲኦል አንደ ተሻገርን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲል አለ።
" #ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዷልና"
( 1ኛ ቆሮ 5 ፥ 7 )
🙏 ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል
ድል መንሣትን
ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን 🙏
( 1ኛ ቆሮ 15 ፥ 55 - 57 )

🥀ማክሰኞ #ቶማስ
🥀ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ #ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ #ጌታችን_ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የ #ጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።
🥀ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡
🥀ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች። በየዓመቱ በ #እመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያርፋል።

❤ #ሚያዝያ ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን #በእስክንድርያ_ለተሾሙ ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ አምስተኛ ለሆነ ለከበረ አባት #ለአባ_መክሲሞስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_መክሲሞስ፦ ይህም አባት መንፈሳዊና በሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው። እርሱም ከእስክንድርያ ሰዎች ወገን ነው ወላጆቹም ሃይማኖታቸው የቀና ነበር የዮናውያንንም ጽሕፈትና መጽሐፋቸውን ጥበባቸውንም ሁሉ ተምሮ ፍጹም አዋቂና አስተዋይ ሆነ በዮናኒ ቋንቋ። ከዚህም በኋላ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ልዑል እግዚአብሔር የሠራውን ሕግና ሥርዓት ተማረ። አባት ያሮክላም ዲቁና በእስክንድርያ ሾመው ከዚያም በኋላ ዲዮናስዮስ ቅስና ሾመው በተሾመባት ሁሉ ላይ ተጠምዶ የሚያገለግልና የሚጋደል ሆነ። አባ ዲዮናስዮስም በዐረፈ ጊዜ አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳትና ካህናት ማኅበሩም ሁሉ መረጡት በእግዚአብሔርም በፈቃድ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት።
❤ ዲዮናስዮስም ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ ከተማ የተጀመረው የኤጲስቆጶሳት ማኅበር ጉባኤ ተጀምሮ ሳይፈጸም ዐረፈ። ይህም አባት መክሲሞስ በተሾመበት ወንበር በተቀመጠ ጊዜ በማኅበሩ ጉባኤ ስለ ተወሰነውና ከሀዲው ጳውሎስ ሳምሳጢን እንደአወገዙት በጉባኤው ሹማምንት መልክቶች ወደርሱ ደረሱ። በትምርቱ ያመኑትንም መልክቶቹንም ካህናቱ በአንድነት በተሰበሰቡበት አነበበው። ከዚያም በኋላ ዳግመኛ ከራሱ መልእክቶችን ጽፎ የጳውሎስ ሳምሳጢን ስሕተት ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልዩና እንዲማልዱ እያዘዘ ወደ ግብጽ አገሮች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ኖባ አገር ላካቸው። የክብር ባለቤት ጌታችን ልመናቸውን ተቀበለ ይህም ከሀዲ ከጥቂት ቀኖች በቀር አልኖረም በፍጥነት አጠፋው እንጂ የረከሰች ሃይማኖትንም ከዓለም አስወገደ አራቀ።
❤ በዚህም አባት ዘመን ከምሥራቅ አገር ማኒ የሚባል ራሱን የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስን ያደረገና ክፉ ስሕተትን የሳተ ሰው ተገለጠ። ወደ ሶርያ ምድርም ደረሰ አርኬላዎስ የሚባል ኤጲስቆጶስም ከእርሱ ጋራ ተከራከረ ስሕተቱንም ገላልጦበት አሳፍሮ ከአገሩ አሳደደው። ከዚያም ተመልሶ ወደ ፋርስ ሔደ ራሱንም ነቢይ አደረገ የፋርስ ንጉሥ ብህራምም ይዞ ከሁለት ሠነጠቀው። ተከታዮቹ የሆኑ ሁለት መቶ ሰዎችን ዘቅዝቆ እስከ ወገባቸው በምድር ውስጥ ተከላቸው እነሆ ከሰው አትክልትን ተከልሁ አለ።
❤ ይህም አባት መንጋውን በመጠበቅ ሲጋደልና በቀናች ሃይማኖትም ሲያጸናቸው ኖረ ከመናፍቃንና ከከሀዲያን ችግር እስከ አረፈባት ቀን ድረስ በድርሳናትና በተግሣጻት ጠብቆ አዳናቸው። በቅዱስ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ስድስት ዓመት ኑሮ ሚያዝያ14 ቀን በሰላም ዐረፈ። የአባ መክሲሞስ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ14 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ሰላም_ለመክሲሞስ_ልዑል። በመንበረ #ማርቆስ_ሰባኬ_ወንጌል። ዕሩቅ ትስብእት እምተዋሕዶ ቃል። በትምህርተ ካህድ ለብእሲ ዘይብል። መጽሐፈ ግዘት አንበረ በኵ ደውል"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሚያዝያ_14።

❤ እንኳን #ለትንሣኤ_አራተኛ_ቀን_ለቅዱስ_አልዓዛር መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ጽፍት፦ "ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታነ
ተንሥአ ወፈወሶሙ ለሙቁሐን
ተንሥአ ወፈወሶሙ ለሙቁሐን።
አዝ...............
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
ወአግዓዘ ነፍሰ ጻድቃን።
አዝ…………………
ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ
ወእውርኒ ዘፈወሶ በቃሉ።
አዝ……………………
ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት በሣልስት ዕለት"። ትርጉም፡- ሙታንን ሁሉ ያስነሳ የታሠሩትንም የፈወሳቸው በታላቅ ሥልጣን ተነሣ የጻድቃን ነፍሳትን አጋዘ አልዓዛን ተነሥ ያለው ዕውሩንም የፈወሰው ትንሣኤውን በሰንበት አደረገ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_መዝሙር፦ "ዛቲ ፋሲካ ዕለተ በርህ ወዋካ ዛቲ ፋሲካ(፪)"። ትርጉም፦ ይህቺ ፋሲካ የብርሃን ቀን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ።
❤ #ዕለተ_ረቡዕ።
✝ ✝ ✝
❤ #ረቡዕ_አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

❤ #ሚያዝያ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን #ለወንጌላዊው-ቅዱስ-ዮሐንስ ረድኡ (አገልጋዩ) ለሆነ ለበአርማ አገር ኤጲስቆጶስ #ለቅዱስ-አንቲቦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕት-ሳባ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_አንቲቦስ፦ እርሱም የመለኮትን ነገር ለሚናገርና ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ረድኡ ነው። እርሱም ከአይሁድ ወገን በግዛቱ ውስጥ አንድ ሰው የሚታይ እስከ አልሆነ ድረስ አይሁድን ያጠፋቸውና ኢየሩሳሌምንም በአፈረሳት በአስባስያኖስ ልጅ በግማትያኖስ ዘመን ነበር። ከእስራኤል መንግሥት ትውልድ ያላቸውንም ብዙዎችን ገደላቸው ለመንግሥቱና ለራሱ ስለ ፈራ ነው። የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካቸውና ንጉሣቸው ድል አድራጊና እርሱም ወገኖቹ እንደሆኑ ክርስቲያኖች ይናገራሉና ስለዚህ ከአማንያን ብዙዎችን ገደለ።
❤ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሱ ሸሸ የዮሴፍ ልጅ በሮሜ ከተማ ታሥሮ ሳለ ወደ ኢየሩሳሌም ጭፍራ ልኮ የይሁዳን ተወላጆች ወደርሱ አስመጣቸው የክብር ባለቤት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት በጠየቃቸው ጊዜ ክርስቶስ ሰማያዊ ንጉሥና በሰማያት የሚኖር እንደሆነ በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ለሁሉም እንደየሥራው ሊከፍለው ዳግመኛ ይመጣ ዘንድ እንዳለው አስረዱት። ይህንንም ሰምቶ እጅግ ፈራ ክርስቲያኖችንም ማሠቃየቱን ተዋቸው።
❤ ቅዱስ አንቲቦስ ግን የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን ሊአስክደው ሽቶ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው እርሱም በሥቃዩ ውስጥ በመታመን ጸና። ከዚህም በኋላ ከናስ በተሠራ በላም ፈጅ ጋን ውስጥ አድርገው ከበታቹ እሳትን አነደዱ እርሱም በውስጧ ሁኖ ስለከበረ ስሙ ምስክር ሊሆን ያደውን እግዚአብሔርን ፈጽሞ ያከብርና ያመሰግን ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ስሙን ለሚጠሩና መታሰቢያውን ለሚያደርጉ ከነፍስ ከሥጋ ደዌ ሁሉንም ይፈውሳቸው ዘንድ እግዚአብሔር ፈለገ። ከዚህም በኋላ ከነሐስ በተሠራው በላም ፈጅ ውስጥ የምስክርነቱን ተጋድሎ ፈጽሞ ሚያዝያ 16 ቀን ነፍሱን ሰጠ። በድኑንም ሲጥሉት ምዕመናን አንሥተው በታላቅ ክብር ፈጽሞ እያመሰግኑ ወስደው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት።
❤ እርሱም አስቀድሞ በግዞት ቤት ሳለ ከወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ የሚያጽናናውና የሚያአረጋጋው "ቸር ጠባቂ እረኛና ታማኝ አገልጋይ ካህን" የሚለው መልእክት ወደርሱ መጣ። እንዲህም ብሎ ሁለተኛ ነገረው "በሰማዕትነት እንደሚሞት አንተ በከበሩ ሐዋርያትና ከሰማዕነት ጋራ ተቆጥረሃል"።
❤ ደግሞ ከሥጋው ጣፋጭ የሽቱ ቅባት እንደሚፈስ ስለርሱ ተነገረ እርሱም መዓዛው እጅግ ጣፍጭ የሆነ በእምነት ለሚሻው ሁሉ እስከ ዛሬ ጠቃሚ የሆነ ነው። የቅዱስ አንቲቦስ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።