ፍቅሬ ፍቅርሻ
117 subscribers
1 photo
2 links
Download Telegram
Channel created
ጤናውን ይስጥልን
እንዴት ናችሁ?
እስኪ በዚህ እንጀምር ለዛሬ
የሎሬት ጸጋዬ " ሃ... ሁ በስድስት ወር "....
የልጅ ጥዱ ናደው ቃለ ተውኔት፡-
........" እኔማ የሚመስለኝ፡ እኔ የምልህ፡ እኔ የማስበው፡ በኔ አስተያየት፡ በኔ አስተሳሰብ፡ ነው ወጉማ! ነው አኪሩ፣ ድግምቱ የያዘ እንደሆን፣ ወዳጄ አስበው፡ ከራማ አድርገው፡ አኪሩ የያዘ እንደሆን፡ ወጉማ ነው እኔነት፡ ግለኝነት፣ የራስ ሃሳብ አፍላቂነት፣ ግለ ወጥነት፣ የኔ እኔነት፡ ነው!.... ነው! ወጉማ፣ ብቻ ያልተቀየጠ፣ ያልተመረጠ፣ ያልተማሰለ፣ ያልተዳቀለ፣ንጹህ ባህሪ የነጠረ ግለኝነት እኛ እኛ ቤት የለም እንጂ፡ በእድሜ ልክ 'አቤት ወዴት' በዘለዓለም ' እሺ ጌታዬ' የተኮላሸ ቅይጥ እኔነት በቀር ...." አዬ......እኔ እርሶን አላምነዎትም አባቴ ግራ ጌታ!
********
እድሌ ሆኖ የድሮ ሰው ከምትባሉ ሃቀኛ ነገሮች፡ ለመድሃኒት የተረፋችሁ ለላንቲካ እንኳ የቀራችሁ በዛሬው ጊዜ አለን ትሉ እንደሆነ ነውንጂ፡ ለኔ ከቶ አትታዩኝም፡፡ እኛ በናንተ ወጣንጂ እናንተ በኣያቶቻችሁ አልወጣችሁም፡፡ ለዚህ ነው አለቅጥ መመሳሰላችን!
በኛማ በስምንተኛው ሺ የስልጣኔ የመልመጥመጥ ጥበብ ይኸው እናንተው በለጣችሁን፡፡ ለዚህ ነው ሃቀኛ ነገሮች ነን ስትሉ ለኔ የማትታዩኝ፡፡ ያባቶቻችሁ ተረት፡- "በጎራዴ እያፈፋ በጋሻ እያለፋ" ሲል
የናንተው ደግሞ " በነገር እየጠለፉ፣ በምላስ እየገረፉ" ሆኖ ቀርቷል!......የለም! ሃቀኛ ነገሮች ነን ብትሉ ለኔ አትታዩኝም፡፡ እንደውም በዳሰሳ በእግር በፈረስ ፈልጌ አስፈልጌ፡ አልገጠማችሁኝምና ሃሳብ ወለድ ሆናችሁብኛል፡፡እንደው ለወግ ዳባ ለበስ፣ እንደው ጨዋ ጭምት፣ እንደው ነጫጭ ጭራ፡ እንደውም ነጫጭ ጢም፡ ትሆኑ እንደሁንጂ፡ ' አዋጅ አዋጅ ሃቀኛ አረጋውያን እነሆ ከሰማይ የወረድን' ብትሉኝንኳ በጆሮ ቃላችሁን፣ በሃሳብ ስራችሁን እንጂ በምግባር ሃቀኛ ባህላችሁን እዉን ጠባያችሁን አየሁ የሚለኝ የለ፡ ለኔም አልገጠማችሁኝ! ለዚህ ይሆናል የቁም አፈታሪክ የሆናችሁብኝ፡፡ መቼም ለኔ ባይነስጋ ባትታዩኝ ነውንጂ፡ እርስ በርሳችሁማ፡በቅታችሁ ነቅታችሁ በቁምም በራዕይም ትገላለጣላችሁ ይባል የለ!? አባቴ ግራ ጌታ!
*****************
እናታችን የደሩ የከበሩ ሴት አዳሪ ነበሩ፡፡ እና.. ተረተ ሲተርቱ........
" የዛሬ ሰው፡ ነገሩ እቅጭ እህ እቅጭ
ሚስጥሩ ውጭ አውጡ እህ አውጡ
አድማው ጠልተናል ጥሉ፡ በልተናል ብሉ
እንብላው ብሉ እህ ብሉ! አመሉ ቀልተናል ቅሉ
ጠባዩ እንገንፍል ገንፍሉ
ህመሙ ፍሉ እህ ፍሉ
እድሉ ዝም እንበል ዝም በሉ እህ ዝም በሉ
ፍቅሩ ኤጭ ኤጭ እህ ኤጭ ኤጭ ኤጭ
ከድሜው ቅጭ አንደበቱ ማር ክብሩ ግን ላጥ
እህ ላጥ" ይሉ ነበር እናታችን....የደሩ ሴት አዳሪ የነበሩ"..........*******//***********
በተስፋዬ ሳህሉ/ አባባ ተስፋዬ/ የተተወነ
የፊቱን ጊዜ ያየው ታላቁ ሎሬት!
Channel photo updated
የፌስቡክ ገጽ እስኪያገግም በዚህ በኩል ብቅ ብለናል....ኋላሳ
ወይ ቫላንታይን? እንደ ድሮው መስሎኝ!!
አልጋ ወይስ ስልክ?
ለመሆኑ ሌቦች እየፈቱ ሲገጥሙኝ፡ የእዝንም የለ?
ምን ሊረባችሁ?
የስልኬ ሰልስት ላይ ጭራሽ፡ ቫላንታይን ጅኒ ቁልቋል ትያለሽ አዳሜ!?
መቀስ ምት መዠመር አለብኝ
ስልኬ የተሰረቅሁ ቀን፡ ብታዩኝ ሳስቅ
ከባልቻ ሆስፒታል የወጣ ገመምተኛ መስዬ
እያነከስኩ መሄዴ ነው የገረመኝ
ስልኪቱን ደወልኩ:
" ሄሎ "
'' አቤት!? " ማንሳቱ ይባስ
" ቅድም ስልክ የሰረቅኸኝ ነኝ ወንድሜ "
" ሌባ እያልከኝ ነው? "
ጆሮዬ ነው ወይስ???
.....ምናባቱ ልለው ኖሯል በጀወርጊስ!
ክብሩን የጠበቀ ሌባ መጣብን
" ይቅርታ ወዳጄ......."...መች አስጨረሰኝና
" ወድቆ ነው ያገኘሁት "
" አዎ ያው ኪሴ ውስጥ ወድቆ ነው "
" ማን ጣለው አለህ? "
......ምን ያለው ቱስኪ ገጠመኝ!
" ወንድሜ...እባክ......"
" ወንድሜ ወንድሜ አትበለኝ ወዲያ! "
ሆ!
" በስሜ ጥራኝ! "
" እሺ ስምህ ማነው? "
" ስሜንም አታውቅም? የማታውቀው ሰው ጋር ለምን  ትደውላለህ?....ቀዥቃዣ! "
......ዘጋው!
ያቺ የፍየል ጭራ ደግሞ ወሬዋ ሁሉ ቫላንታይን ሁኖብኝ እጅእጅ ብሎኝ ነበር...
አንቺ ምናለብሽ ወጠ መልካም አለች የቸገራት!
አሁን የያዝኩት ስልክ ያፈሳል
ሰው ሳናግርበት፡ በራሱ ተነሳሽነት ስርዓተ ነጥብ ያስገባል.....ኋላሳ
ሸክሙ ተረፈኝ!
የቫላንታይን ዋዜማ፡
" ፍቅርሻዬ "
" ወዬ ሃን " ሮማንቲክ ሆኛለሁ ዘንድሮ
" ቅናሽ አልጋ አገኘሁኮ "
" አልጋሽ አረጀንዴ? "
" ሂድዛ! ለቫላንታይን ነውንጂ "
ጎበዝ! ፈራሁልህ
" ለቫላንታይን አልጋ ያስፈልጋል?? "
....ተናደዳችሁብኝ አይደል?...
የአልጋ በአል ነውንዴ?
በያን ሰሞን ዴግሞ የስልኬ ሰልስት ነበር
አርባዋ ታይወጣ ከአልጋ መውዴቁ ግን
አሁን የእዝን ወዲህ በሉ!
አላችሁ?
የነበሩት...ያኔ
°°°°°°°°°°°°
አንዳንድ ጊዜ 'ዘመን ውለታ ቢስ ይሆን?' እላለሁ።
ላደመቁት፣ ለሆኑለት ሁሉ ቁብም የለው? አነዚያን አጋፋሪዎቹን ለምን ይረሳል?..ውበቶቹን!
ዘፈንና ሽቶ እንዲሉ ከኛም በፊት፡ በኛም ጊዜ ዘመንና ዝና ወይ የሽውታ እውቂያ ያገነናቸው ባለሞያዎች ነበሩ። ያዋሩን፣ ያጫወቱንና ያዜሙልን። የጊዜያችን ምስጉኖች ነበሩን።
በተለይ ዜመኞቹ!
የወረት ነፋስ ሳያጠፋብን፣ በራስ ግዴለሽነት በድርሳናት ስንፍና ከትዝታ ሳይጨለፉ የጠፈፉ። ወዴት ሄዱ?.. አሉ?..አለፉ?..የትና ማን ዘከራቸው?
የሚገርማችሁ በሞት የተለዩትን'ንኳን ለይተው የሚያውቁ ጥቂቶች ናቸው። ያዩዋቸው፣ የጠየቋቸው አብዝቶ ጥቂቶች ናቸው።
ዛሬ ላንሳቸው።
በቀደመው የኢትዮጵያ የዜመኞች መድረክ፡ ብቅ ብለው ዘመነኛቸውን ካዝናኑ ጠቢባን አንዱ ደርባባው አቡኑ ነበር። ደርባባው አቡኑ በጉብልነቱ ወራት የቀዳማዊ አጼ ሃይለስላሴ አዝናኝ ወይም አጫዋች ነበር። (Mekonnen Woldearegai በአንድ ወቅት እንዳጫወተኝ )። በርግጥ ዛሬ በህይወት የለም።
ደርባባው አስቂኝ ግጥሞች ባሏቸው የአዝማሪ አጨዋወት ስልቱ ይታወሳል።
" በድብቅ ነበረ መውደዴ መውደዷ
ምስጢር ለማባከን ፍጥጥ አለ ሆዷ "
ከዚህ ሌላ " የዋርዳ ሳሙና " በሚለው ዝነኛ የመድረክ ስራውም ይታወቃል።
በኋለኛው ዘመን ከመጡ የማሲንቆ አዚያሚዎች ሌላው ከብዙ ሰዎች ህሊና የማይጠፋው፡ ቻላቸው አሸናፊ ነው። ቻሌ ( ኧረ ባሏ ባሏ ) የሚገርም መረዋ ድምጽ ባለቤት ነበር። ኧረ ባሏ ባሏ የአበበ መለሰ ስራ ነው።
" ኧረ ባሏ ባሏ  የፊተኛው ባሏ ባሏ ባሏ
   እስኪ ልጠይቅህ ባሏ ባሏ ምንድነው አመሏ
   ኧረ ተይ ድማሜ ተይ ድማሜ ተይ አታንገላቺኝ
   ተይ ድማሜ
   'ንደተበተብሽኝ ተይ ድማሜ እንዳሰርሽኝ ፍቺኝ "
ቻሌ ከባድ ገጣሚም ነበር ይባላል። ከብርቱካን ዱባለ ጋር እንደዘፈነ ይታወቃል።
" እትብቴ ከወዲያ መቃብሬ ወዲህ
በተወለድሁባት አልኖርኩም ከንግዲህ
አንዲቷ ጎረቤት ያለውን ስትቀዳው
እኛ እዝህ ሁነን ተጠማን ተጓዳው
አይ አንቺ ገራገር አይ አንቺ ሞኝ አድባር
በቁመናሽ ፈቱት ያሰርሽውን አምባር "
" ሾፌርእወዳለሁ ስትዪኝ ሰምቼ
  ሞቼልሽ ነበረ ብስኪሌት ነድቼ " በሚለው ግጥሙ የማይረሳው ወረታው ውበት ነው።
ወረታው ተስረቅራቂ ድምጽ የነበረው፡ ለየት ባለ የግጥም አገላለጹ የሚታወቅ ነበር።
" ከደን የወጣች አርጩሜ 'ምትመስል
  ጀግና እንደ ተስቦ የምታሰለስል " የምትለው ግጥም ያለችባት ዘፈን በጣም ደስ ትለኛለች። ስለወረታው አሁን አሁን ብዙም አልሰማም።
ሌላው በኋላ ከመጡ ዜመኞች የሆነው ደግሞ ተስፋዬ ወርቅነህ ነው።
ተስፋዬ ወርቅነህ ( ከሚላ ነይ ከረሜላ ) በሚል ዘፈኑ በ1992 አካባቢ ብቅ ያለ የተለየ ድምጽ የነበረው ድምጻዊ ነበር።
" አበጀሁ ወደድኩሽ እኔስ እንኳን እንኳን
ፍቅርሽ አይደለምወይ የጣለብኝ ድንኳን "
በወጣትነቱ በሞት ተለየ። ሞቱ ብዙዎቹን የሙያ ጓዶቹን ያጎደለ ከባድ ሃዘንም ላይ የጣለ ነበር።
አስናቀ ገብረየስን የሚረሳ ይኖር ይሆን?
አስናቀ ( ነይ ሰናድሬ ) በቅርቡ ሚዲያ ላይ አይቼው ነበር።
ኮልፌ ይመስለኛል ሰፈሩ። ከተሳሳትኩ አርሙኝ። በህይወት የሌለው ታናሽ ወንድሙ ይመስለኛል ለኋለኞቹ የሚታወቀን።
" አላሳዝንም ወይ '' በሚለው ነጠላ ዜማው የሚታወቀው።
አስናቀ በርካታ ዜማዎች አሉት፡
" እምዬ ወዴት ነሽ እማማ ወዴት ነሽ
  ልጆችሽን በትነሽ ጎጇችን ዘሞ እያየሽ
  ኢትዮጵያ ወዴት ነሽ.." የሚለው ዘፈኑ ይለያል።
ለእናቱም አዚሟል፦
" በፈረሰው ጎጆ በሚያፈሰው ቤቴ
  አንድ ቀን እንደሰው ሳይደላት እናቴ
  እህ እንዳለች ቀረች ወይ ምስኪኗ እናቴ
  ወይ ድሃዋ እናቴ
  ያላንድ ደጋፊ እምይ ለብቻዋ
  አጣችም አገኘች ክፉ ደጉን ቻይዋ
  ያፈር ቀለብ ሆነች..ዋ!..በመጦሪያዋ..."
ሌላው ብቅ ብሎ የጠፋ ላስታውሳችሁ፡
ዘውዱ ወርቅነህ ( አታላይ ነች )
" ይጨንቀኛል ወዳጄ ይጠበኛል
  ሰው ጠፍቶብኝ ፍለጋ ታክቶኛል "
በውነቱ ይኸ ሰው ያለ መረጃ ያለ አድናቂውቹ እውቂያ የት እንደገባ ምን እንዳጋጠመውንኳን ሳይታወቅ የቀረ ነው። የምታውቁ ንገሩን እባካችሁ።
እሱ ብቻም አይደል፦
ወንድሙ አማረ
ሙሉቀን አለነ
ስዩም ዘውዴ
ስፈልግ አያሌው
ሰርጎለም ተገኝ
ጌታቸው ስሑል ( አውቶቡሰይ )
አበበ አበሹ ( ታርታሌ ቢሻን ሃሮ )
የምታውቁትን የምታስታውሱትን።
🔹የእትዬ ፍትፍቴ ታፋ!🔹
👇
" ፍቅርሻ "
" ኧ "
" ታፋ ታያለሽ? "
" የማንን "
" የእትዬ ፍትፍቴን ነዋ "
" ማን አሳየሽ? "
" ያፌትን [ ልጃቸው ] ን ልጠራ ስሄድ በረንዳቸው ላይ እንሶስላ ሲሞቁ አየሁ!....ያው በቃ ታፋቸውን አየሁ "
ጓጓሁና መጓዝ ጀመርሁ!
ያፌትን ፍለጋ እግረመንገዴን ታፋንም ለማየት!

እትዬ ፍትፍቴ ሞላ ያሉ ደመ ግቡ ናቸው...ሞንደልደል ያሉ መልከኛና ቁመተ ዝግባ!

መምህራኖቻችን ይወዷቸዋል!

ያፌት ብብቱን ከፎከተ ከተያዘ፣ ወይ ቧንቧው ላይ አፉን ሲደቅን ከተያዘ፣ አደናቅፎት ሲወድቅ ሁላ ወላጅ ያስመጡት ነበር።

ወላጅ ደግሞ እትዬ ፍትፍቴ ናቸው!

አቤት ሲያምሩ!..መምህራኑ ያኔ ደስ ይላቸዋል።

ያፌት ባለጌ ነው። ትምህርት እንዲገባን ግንባራችንን  እየፋቀና የደረት ጸጉር ታበቅላላችሁ ብሎ ፋንድያ የሚቀባንና ለዚህም ሃምሳ ሳንቲም የሚቀበል ነበር !፤

መስታወት ይዞ ቀሚስ ያደረጉ ሴት ተማሪዎች እግር መሃል ጣል አድርጎ ያማል!

" ማሜ ፓንት የላትም " ብሎን ልጅቷን እንደ ጥላ ወጊ ከኋላ ከኋላ ስንከተላት ውለናል ሁላ!

ሲያዝ ወላጅ አምጣ ይባላል፤ ያው ውቢቷን እናቱን ፍትፍቴን ይዞ ከች!
የመምህራኑ ይባስ

" ልጅዎ ጨዋ ነው ግን ከአንዳንድ ነቀዞች ጋር ይውላል። እንዳያበላሹት ብለን ነው! "
..እንዴ?....ጭራሽ?

የሆነው ሆኖ ዛሬ እንሶስላ ይሞቃሉና ታፋ ማየት አለብኛ ቂቂቂቂቂቂ

ስደርስ አሉ እንሶስላቸውን እየሞቁ!...አቤት ታፋ!
ፉርኖ መስሎ!

'' ልዥ ፍቅሬ ደህና ነህ?...ምነው ዛሬ ተገኘህ!?..ግቢውን ታውቀዋለህ?..ከውጪ ማፏጨት ብቻ ነበር ዛሬ ገባህ!...ያፌትዬ ጋር ነህ? "

" አ...አ ዎ " አልኩ አይኔን ከፉርኖ ማለቴ ከታፋቸው ሳልነቅል! "
መቼም የሃሜት ትኒሽ የለውም አይደል?
ዮናስ መጣ፣ ያሬዶ፣ መቅድም፣ ሱሬ፣ ጌቱ፣ ጋሹ፣ ታሬ ተከታትለው ገቡ!

ውሪዎች!....ለቡሄ ተፈልገው ያልተገኙ ማቲዎች!

እትዬ ፍትፍቴ ደንገርገር አላቸው!

" ያፌት!...አንተ ያፌት!..ና!..ተሰብስበውልሃል! "

ከኋላ በሩን የከፈቱት አዛውንት አባቱ ጋሽ ነውጤ ነበሩ!

" ፍትፍቴ ኧረ ባልቦላሽን! " .....ፍትፍቴ ገባቸው!
እናም ባልቦላው ጠፋ!
........ፉርኖውም ተሸፈነ!...በቃ!.....አቤት ሃዘናችን!