በብእሲ
142 subscribers
756 photos
139 videos
68 files
91 links
እንኳን ወደ በብእሲ የቴሌግራም ቻናል መጣችሁ። በቻናላችን

ግጥም
📕አዳዲስ መፅሀፍት
🤗የታዋቂ ሰዎች ታሪክ
😌 ስዕሎች
📖አጫጭር ወጎች
🤗ጭውውት ና ትረካዎች ወደናንተ ይደርሳሉ።
አብራችሁን ለመስራት እንዲሁም ማስታወቂያ እንድንሰራላችሁ የምትፈልጉ በራችን ክፍት ነው።
👇
@BebesiEthiopia
Download Telegram
እንኳን ለኢድ ዓል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@fikermahi
🐶 ቅብጥብጡ ውሻ

🐶የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡

🐶በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡

የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡

🐶የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡

🐶ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡

ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .

🐶ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡

ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!
   
                     ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ

  @fikermahi    
👍3
እኛ እራሳችንን እና ሌሎች እኛን ምን ያህል ያውቁናል?

አንዳንድ ግዜ ሰዎች እኔ እራሴን በደንብ አውቀዋለሁ ወይም እከሌን በደንብ አውቀዋለሁ ሲሉ ይደመጣል ነገር ግን የስነ-ባህሪ አጥኚዎች ሰው ራሱንም እንዲሁም ሌሎችን ሙሉ በሙሉ እንደማያውቅ እንደሚከተለው ያስረዱናል።

4ቱ ማንነቶቻችን፦

1. Open- ግልፅ ሆኖ የሚታየው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን እና ሌሎች እኛን የሚያውቁት ግልፅ የሆነው ማንነት ክፍል ነው።

2. Hidden- ድብቅ የሆነው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን የምናውቅው ሌሎች ግን ስለእኛ የማያውቁት ክፍል ነው።

3. Blind- ሰዎች ስለኛ የሚያውቁት እኛ ግን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።

4. Unknown- ሌሎች ሰዎችም ሆኑ እኛ ራሳችን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።

ስለዚህ ከሰዎች ጋር መልካም እና ሚዛናዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ከላይ የተዘረዘሩትን የማንነት ክፍሎች ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

ካልሆነ ግን እከሌን አውቀዋለሁ ብለው ሲያስቡ አንድ ቀን ድብቁ/ የማያውቁት ማንነት ሲገለጥ ሊጎዱ ይችላሉ። እንዲሁም ራስዎትን ራሴን በደንብ አውቀዋለሁ በማለት ሌሎች ከሚሰጥዎት ምክር ባለመማር ራስዎትን ከማሳደግ እና ከማሻሻል እንዳይገደቡ ጥንንቃቄ ያድርጉ።

በ መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@fikermahi
👍1
"ንጹህ ምንጭ"የብራና አውደርዕይ ነገ ይጠናቀቃል

በሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ስራ ድርጅት የተዘጋጀው "ንፁሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ታሪካዊ አውደርዕይ ከሚያዝያ 4 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ እና ነገ የመጨረሻ ቀናት ናቸው።

"ንጹህ ምንጭ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና የጥንታዊ የብራና ዝግጅትና ጽሑፍ በአካል የሚያዩበት፤ ጥንታውያን ሥዕላት ከእነ አሳሳላቸው የሚመለከቱበት፤ እንዲሁም በጥበባተ እድ ሥራዎች ጎብኚዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያን ንጹህ ምንጭነት በትክክል የሚመለከቱበት አውደርዕይ ነው ተብሏል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ዛሬ ሚያዚያ 12 እና ነገ ሚያዝያ 13 ከምሽት 11:00  ጀምሮ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የኪነጥበብ ምሽት ከዐውደ ርዕዩ ጋር በጥምረት ይቀርባል።

በዕለቱ የሚገኙ የክብር እንግዶች ዲስኩር ግጥምና የተለያዩ ኪናዊ ሥራዎች ለማቅረብ መጋቤሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ፣መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ፣ዲያቆን ዶክተር ቴዎድሮስ በለጠ፣ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ፣ሠርጸ ፍሬስብሐት፣አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ፣አርቲስት ይገረም ደጀኔ ፣አርቲስት ንብረት ገላው፣አርቲስት ናርዶስ አዳነ ፣ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ገጣሚ አስታውሰኸኝ ረጋሳ ፣ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን … በሥፍራው ይገኛሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

@fikermahi
#5ቱን_አስመሳይ_ሰዎች_ተጠንቀቃቸው!

#አንድ
አስመሳይ ሰዎችን ከሕይወቴ ቆርጬ ማስወጣቴ ክፉ ስለሆንኩ አይደለም፤ ራሴን ስለማከብር እንጅ!

#ሁለት
አስመሳይ ሰዎች ጥላህን ይመስላሉ። ጥላህ ለአንተ እጅግ ቅርብ ቢሆንም በሕይወትህ የምትፈልገውን ከለላ ግን አይሰጥህም።

#ሶስት
አስመሳይ ጓደኞች አሪፍ ነህ ብለው ሲያስቡ ብቻ ከጎንህ ይገኛሉ። እውነተኛ ጓደኞች ግን ሞኝ በሆንክ ጊዜ እንኳ አይርቁህም።

#አራት
እጅግ አሳዛኙ ቀን ጓደኞቼ ብለህ ያሰብካቸው፣ ጓደኞችህ አለመሆናቸውን ያወቅክበት ቀን ነው!

#አምስት
ምርጥ ጓደኛዬ የምትለው ሰው፣ አስመሳይ ሲሆንና ከጀርባህ ሲወጋህ ከሚሰማህ የሕመም ስሜት በላይ የሚያሳምም ምንም ነገር የለም።

©Ethiopian_Psychology

@fikermahi
እርግጡን ልንገርሽ "አፈቅርሻለሁኝ" ❤️

ህልሜን እንዳዋይሽ ህልምሽን ንገሪኝ
ህልም እንደ ፈቺው ነው እባክሽ አትፍሪኝ
ብዬ ባልኩሽ ጊዜ ህልምሽን ብትነግሪኝ
እንደዚህ ፈታሁት እ'ህ" ብለሽ ስሚኝ ።
፡
ህልምሽን ስፈታው ትርጉሙ ይኸው ነው
መጣላት ለሚለው በፍቅር መውደቅ ነው
ዕንባ ማለት ደግሞ ደስታና ፌሽታ ነው
ፈልገሽ ማጣትሽ እኔን ማግኘትሽ ነው ።
፡
ህልምሽን ነግረሽኝ እኔም ፈታሁልሽ
ህልሜን ደግሞ ስሚኝ እታለም ልንገርሽ ?!
፡
በነጭ ፈረስ ላይ አንቺ ተቀምጠሽ
እኔ ስከተልሽ እርቀሽኝ ሳለሽ
ብጣራ አትሰሚኝ ሰግረሽ ትሄጃለሽ
ምንድነው ትርጉሙ ንገሪኝ አስልተሽ ።
፡
እሷ..
ህልምህን ስፈታው እንዲህ ነው የሆነው
ካንተ እቅፍ ውጪ ሌላው ወዳቂ ነው
በፈረስ መስገሩም እድሜና ጽድቅ ነው
እውነቱን ልንገርህ ሁሉም የፍቅር ነው ።
፡
እኔ...
ህልምሽን ነገርሽኝ ህልሜንም ነገርኩሽ
ህልም እንደ ፈቺው ነው እውን ይሁን አልኩሽ
ግን .......
ግን ግን - እታለሜ .....?
ህልም ተተርጉሞ ህይወት እንዲዘራ
ነይና ልቀፍሽ አዝመራው ይዘራ
እሸት ሳለሽ ልብላሽ
እሸት ሳለው ብይኝ
እርግጡን ልንገርሽ - አፈቅርሻለሁኝ ።


©noahbookdelivery

@fikermahi
❤1
ፈጣሪ ያጎደለብኝ ምን አለ?

ሰፈራችንን የሚጠብቁ አንድ ሰውዬ አሉ፣ አንድ እይታ ይበቃል እሳቸውን ለማስተዋል ብዙም ያልተቸገረ የሚመስለው ፈገግታቸው ከሩቅ ይጣራል፣ ሁሌም እናቴ ስላሉበት ሁኔታ ስጠይቃቸው ፈጣሪ ያጎደለብኝ ምን አለ ሲሉ ነው የምሰማቸው፣ እግር ጣለኝና ትናንት በወሬያቸው መሀል ገባሁ፡ በምን እንደተነሳ ባላውቀውም፡

የሶስት ልጆች አባት እንደሆኑ እናም ብዙ ብዙ ውስጠ ሚስጥራቸውን ለእናቴ አጫወቷት፣ በንግግራቸው መሀል መሀል ላይ ጣል የሚያደርጓት ፈገግታቸው ግን ሀሴት ይሰጣል፣ በመኖር ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ልጆቼን እና ባለቤቴን ብቻ ነው፡ ቀሪ ሀብት ንብረት የለኝም ለመኖር ስል ማብቂያ የሌለው ገንዘብ ሳባርር፣ በህይወት ላይ ማቆሚያ የሌለው ሰልፍ ስጠብቅ ማብቂያው ምን እንደሆነ ሳላውቅም ስሮጥ ኖሪያለሁ፣ ብቻ ሳላውቀው እየሮጥኩኝ የሆነ ነገር ብቻ ለመያዝ እያሳደድኩ እንዳልሞት እፈራለሁ፣ ለዚ ነው ፈጣሪ ያጎደለብኝ አንዳች ነገር እንደሌለ እያወራሁ በፈገግታ እና በምስጋና ህይወቴን ምገፋው አሏት፥

የህይወት ትግል የማያልቅ እና ማብቂያ የሌለው ነው…ያለትርጉም ያለፋይዳ ማብቂያ የሌለው ሩጫ...ድንገት ተራ ሲደርስ ደግሞ ባኖደውም ማረፍ…አለቀ!!

ግን ደግሞ በዚህ ስክንሳር በሞላበት አለም ላይ ፈገግታ ካለን ጠላት አይኖረንም፡ ፈገግታ የሀሴት መርጫ ሲሪንጅ ነው፡ ዛሬን በሀዘን አትግደሉ አለም ላይ የሌለን ነገር ሁሉ ቢደመር እና ቀመር ቢሰራ ያለንን ግማሽ አያክልምና!!

@fikermahi
እንኳን አደረሳችሁ!
#በብእሲ
@fikermahi
ክርስቶስ ተንስአ ሙታን በአብይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አገአዞ ለአዳም ሰላም እምእዜሰ ኮነ ፍስሀ ወሰላም!!!
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!

#በብእሲ
@fikermahi
"ፍቅር እራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም ፤ ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም ምንም አይቀበልም ። ፍቅር ለፍቅር በቂ ነውና...ፍቅር ምንም ንብረት የለውም የማንም ንብረትም አይሆንም... ።

ስታፈቅሩ፣ "እግዚአብሔር በልቤ ውስጥ ነው" ማለት የለባችሁም ። " እኔ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ነኝ " በሉ እንጂ…

ደግሞም የፍቅርን መንገድ አቅጣጫ መምራት እምትችሉ አይምሰላችሁ ። ዋጋ ያላችሁ ብቁ ሆናችሁ ካገኛችሁ ፍቅር እራሱ የመንገዳችሁን አቅጣጫ ይመራችኋል እንጂ…

ፍቅር የራሱን ቃል ከመጠበቅ ውጪ ሌላ ምኞት ፣ ፍላጎት የለውም ። ይሁንና ካፈቀራችሁና ምኞቶች ሊኖሯችሁ የግድ ካስፈለጋችሁ ምኞቶቻችሁ እነዚህ ይሁኑ ፦

#ካህሊል ጅብራን

@fikermahi
❤1
ፍቅር እና ቁጥር

ስንግባባ  ሰሞን እኔ መላመድን ለማምለጥ የምባትል ባተሌ ነበርኩ። የተጣመርኩት ባይኖርም ራሴን ብቻዬን እወደዋለሁ።

የማልደራደርበት ማንነት ነበረኝ። ሌሎችን የማደንቅበትና የማከብርበት የማንነት መለኪያያዎችም ነበሩኝ።

እሱ ---- አላውቅም የሱን ፍላጎት........ ብቻ አላጣደፈኝም። የተለየ ፍላጎት እንዳለውም ሊያሳየኝ አልተፍጨረጨረም። የሰው ፍላጎት እና ሀሳብ ሲጫንብኝ እንደማልወድ ገብቶታል።

ማባበሉ አጥንቶ የቀመረበት ነበር። ጆሮዬ ከአንዴም ሁለቴ ከድቶኛል እና በተቆለጳጰሰ የፍቅር ዓረፍተ ነገር የሚደነግጥ ልብ እንደሌለኝ አውቋል። ቀስ በቀስ ለፍፅምና የተጠጋ እሱነቱን ነው የጋተኝ።

በገንዘብ ተተምነው ውድ የሆኑ ስጦታዎች እየገዛ አይደለም ያቀበጠኝ፤ በአንድ አንጎል የምናስብ እስኪመስለኝ ድረስ የሚያስፈልገኝን እና ለልቤ የቀረቡ ስጦታዎችን ነበር የሰጠኝ። ውደጂኝ አላለኝም። እንድወደው ምንም አስተዋፅኦ እንዳላደረገ ዓይነት፣ .....የቀን ተቀን እሱነቱን እየኖረ እንደሆነ ዓይነት

፣....... እኔን ለመማረክ የጨመረው ምናምኒት ትጋት እንደሌለ ፣.......... ለሃጬ እስኪዝረበረብ በሱሱ ለመተብተቤ ያበረከተው ምንም እንደሌለ ሁላ ......ከደሙ ነፃ ነኝ...... እኔ የእለት ተእለት እኔነቴን ነው የኖርኩት ዓይነት እጁን ተለቀለቀ።

የሰው ልጅ አዘቦታዊ ማንነት እንዴት እንዲህ እንከን አልባ ይሆናል ብዬ አልጠየቅኩም። በየእለቱ እየገለጠ ያስነበበኝን የማንነቱን ምሰሶዎች ሰብስቤ እሱ ነው ያልኩትን እሱን በልቤ ገነባሁ ፣ በአዕምሮዬ ሳልኩ። ለዚህ ማንነት እጅ ሰጠሁ።

እዚህ ጊዜ ላይ
ፍቅሩን ፣ ጊዜውን ፣ ጆሮውን ፣ ልቡን ፣ ገላውን ፣ትኩረቱን  ያልሰጠኝ የለም። 100% እሱነቱን ያለስስት ነበር የሰጠኝ። እስክበስል ማገዶ እንደምፈጅ ገብቶታል። አልተጣደፈም። ከሞከኩኝ ኋላ እስክበሰብስ እንደምታሽ ገብቶታል።

ሱሴ የሆነ ጊዜ ላይ ....... ያለእርሱ ትንፋሽ እንደሚያጥረኝ የገባው ሰዓት ላይ .......
የሂሳብ ቀመሩን ይጫወት ጀመረ። ቀስ በቀስ ከመቶ እሱነቱ ይገምሰው ገባ። ፍቅሩንም ጊዜውንም ጆሮውኑም ልቡንም ገላውንም ትኩረቱንም በግማሽ ቦደሰው። 50% !! ልቤ የምትደገፈው ምርኩዝ ስታስስ የነጠቀኝን ትንሽ ይጨምርበታል። 75%!! ........ ጨዋታው ይሄ ነው። 100 እንደነበር ይጠፋኛል።

ካጣሁት ግማሽ ይልቅ የተጨመረልኝ እሩብ ያስቦርቀኛል። ልቤ መልሳ እሱን ማምለኳን ትቀጥላለች። መልሶ ከ75% ወደ 25% ሲወርድብኝ የአየር ቧንቧዬ የጠበበ ያህል ደረቴን ያፍነኛል። መልሶ 25% እሱን ይጨምርልኛል። ግማሽ እሱነቱን እንደነሳኝ አላላዝንም። የጨመረልኝ ያስደንሰኛል።

አንድ ቀን ገላውን ለሌላ ሴት አዋሰብኝ። እዚህ ጊዜ ላይ ከሙሉ እሱነቱ 5% ፐርሰንቱን እንኳን አልሰጠኝም።

በብዙ ትዕግስት እና ጥበብ ውስጤ የገነባው እሱነቱ ግን አሁንም አልተገመሰም። ወይም በቀላሉ እንዳይፈርስ አድርጎ ከዓለት ገንብቶታል። ወይም ማመን አልፈልግም። ፍንክች አይልም።

አልካደኝም። በእንባ ታጅቦ ይቅርታ ጠየቀኝ። ይቅርታውን በአግቢኝ ጥያቄ እና ቀለበት አጀበው። የምለው ገባችሁ? ከአምስት 25% ነዳው አይደል? ያደረገውን ሳይሆን ያደረገልኝን እያሰብኩ ተፍለቀለቅኩ። ስለሚወደኝ አይደል አዳራሽ ሙሉ ህዝብ ጠርቶ ፕሮፖዝ ያደረገኝ?

ሶስት ቀን የት እንዳለ እንኳን ሳይነግረኝ ዘግቶኝ ይከርምና በአራተኛው ቀን ለእናቴ ከክርስታል የተሰራ የአበባ ማስቀመጫ ገዝቶ ከች ይላል። ሶስቱን ቀን ረስቼ ለእናቴ ላሳያት ፍቅር እሸነፋለሁ።

እሱ ከሚያሳየኝ የዘቀጠ ማንነት ይልቅ በልቤ ያነገስኩት ማነነት ላይ ሙጭጭ አልኩ። በሂሳብ ቀመሩ ተወናበድኩ።

የእሱን ስዕል ከልቤ ከማፍረሴ ብዙ ቀን ቀድሞ እኔ ፈረስኩ። የእሱን እውነተኛ ማንነት አምኜ ከመቀበሌ ከብዙ ቀናት ቀድሞ የራሴ ማንነት ጠፋኝ።

መላመድን ላመልጠው የምሸመጥጥ አትሌት አልነበርኩ? እሱ ከልቤም ከህይወቴም ሲወጣ ለመሮጥም ለማምለጥም ለማሰብም የተረፈ አቅም አልነበረኝም። 


ሜሪ ፈለቀ


@fikermahi
እወዳታለሁ ❤

መውደዴ ሰላማዊ ነው።  ጥርጣሬ የሚፈጥር ጨዋታ አታመጣም ። ከሰዎች ጋ ያላት ጨዋታ ሁኔታ፣ ትውውቅ ጨዋነት የተሞላበት ስለሆነ አይረብሸኝም ።

እወዳታለሁ ፦

እንከኔን ስታይ እንዴት እንደምታስተካክለው እያሰበች  ነው  አሁን ማክሰኞ ለ'ት ወረቀት  ኪሴ ውስጥ   ሲዝረከረክ ተመልክታ  ሌዘር ቆንጆ ዋሌት አመጣችልኝ ።

የተበሳጨሁበትን ነገር ደግማ  አታደርግብኝም ። እማትወደውን ነገር "ማርዬ እንዲ አታድርግ" ትለኛለች ለስለስ ያለ ሁኔታ ውስጥ  ግግር አቋሟን አየዋለሁ ። 

በተጣላንበት በተጨቃጨቅንበት ጉዳይ በሌላ ቀን አንስተን አንንዘባዘብም ። ፍቅራችንን እና ፀባችንንም እወቁልን ስሙልን አንልም ።

እሷን የሚያሳጣኝ ሁኔታ ውስጥ አልሳተፍም ። እንደምወዳት ነግርያታለሁ  እንደምወዳት  አሳይቻታለሁ  ። እንደምቶደኝ ነግራኛለች  እንደምቶደኝ አይቻለሁ  ።

መዋደድ  ደስስ ይላል   ❤


©እንማር

@fikermahi
“ዛሬ እጥበቱ ካለፈኝ እሞታለሁ"

ጠና ያሉ ሰውዬ ናቸው - በግምት 54 አመት ገደማ

"ልጄ እባክህን እርዳኝ: የኩላሊት እጥበት አለብኝ" አሉኝ

ስልክ ላይ ነበርኩኝ: አንገቴን ጎንበስ አድርጌ "ፈጣሪ ይርዳዎች" ብዬ ወደ ስልኬ ተመለስኩኝ

"እባክህን ልጄ ዛሬ እጥበቱ ካለፈኝ እሞታለሁ" ሲሉኝ የማወራው ስልኬን ዘጋሁኝ

👇🏾

ሰውዬው በተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ውስጥ ለ17 አመታቶች በተለያዩ ሀላፊነቶች ሰርተዋል - ከ7 አመት በፊት ግን የስኳር ህመም ተጠቂ ሆኑ: ኩላሊቶቻቸው ስራ መስራት አቆሙ: የመተንፈሻ ችግር ገጠማቸው

ቤታቸውን እስከ መሸጥ ድረስ ገንዘባቸውን አንጠፍጥፈው ተጠቀሙት

ኩላሊቶቻቸው በየሳምንቱ ይታጠባሉ

በስኳር ህመም የተነሳ የሚበሉት ውስን ምግቦችን ነው

የመተንፈሻ መሳርያ ይጠቀማሉ

👇🏾

ኩላሊቶቼ በየሳምንቱ የማይታጠብ: ያገኘሁትን ምግብ ሳላማርጥ የምበላ: አየሩን እንደፈለግኩኝ የምምግ እኔም አማርራሉሁኝ

ኩላሊትህ በየሳምንቱ የማይታጠብ: እንደፈለግክ እየበላህ: አየር ያለምንም ከልካይ እየሳብክ ታማርራለህ

👇🏾

በነጻ የተሰጠን ይበልጣል !!❤️🙌🏼


©Enmare1988

@fikermahi
መፍትሄ ለማይሰጥህ ሰው ችግርህን አታጋራ

ችግርህን ላገኘኸው ሰው ሁሉ የመንገር ልማድናጥማት  ካለብህ ያንን ጥማት ለጊዜው ከማርካት ውጪ ከሁኔታው ምን ጥቅም እንደምታገኝና እንዲያውም ሊጎዳህ እንደሚችል ላስታውስህ፡፡ ችግርህን ምንም መፍትሄ ለማይሰጥህ ሰው የመናገር ጥማቱ ግን ረክቶ ስለማይረካ እንደገና ችግርህን የምታወራበት መስክ ፍለጋ መዞርህና መጦዝህ አይቀርም፡፡

ችግርህን ባገኘህበት ስፍራ የመናገር ሌላው መዘዝ ለሰሚዎቹ የግል አመለካከት ራስህን የማጋለጥና የሰዎች ፍልስፍና ማራገፊያ የመሆን ችግር ነው - አንዳንዴ ደግሞ የወሬኛ ሰው ሰለባ ትሆናለህ፡፡

ለሰዎች ችግርህን ስትነግር እነዚያ ሰዎች ከሁለቱ አቅም ቢያንስ አንዱ ሊኖራቸው ይገባል፡ 1ኛ) ችግርህን ከሰሙ በኋላ ያንን ችግር የማቃለልና መፍትሄ የመስጠት አቅም፤ 2ኛ) ችግርህን ከሰሙ በኋላ ምንም እንኳን የማቃለል አቅም ባይኖቸውም አንተን ከነሸክምህና ከነሚስጥርህ የመሸከም አቅም ሊኖራቸው ያስፈልጋል፡፡

እነዚህን ሁለት መመዘኛዎች ያለመጠቀም ምርጫ ከተከተልክ በየስፍራው ችግርህን ከማዝረክርክ ልማድህ የሚመጣውንም ሌላ ችግር ለመቀበል ዝግጁ መሆን የግድ ነው፡፡

ትምህርቶቼን በ YouTube የመከታተል ምርጫ አላችሁ::
Subscribe፡-

https://m.youtube.com/user/naeleyob623


@fikermahi
የፈጣሪ እዝነት ግሩም ነው!!
.
ይህን ለመፃፍ እጄን ሳነሳ አይኔ በእንባ ተሞላ፣ግን ከተማርኩት እና ብርታት ካገኘሁት የህይወት ክፍል ትንሽ ላካፍላችሁ፣ባለማወቅ ውስጥ ሁነን ከምንጠፋ ትንሽም ቢሆን ድክመታችንን አውቀን ወደ ጥንካሬ እንቀይረው፥
.
.
የሰው ልግስና ሁኔታን አስልቶ ነውና ይቋረጣል።የፈጣሪ ግሩምነት ግን በሁኔታ፣ ጊዜ እና ጥቅም የተመረኮዘ አይደለም።"በጠየቅነው ልክ የማይመለስ፣ በመለስነው ልክ ያልተጠየቅነው ነገር ብዙ ነው" ስንቱን ሰርቼ፣ ስንቱን አጥፍቼ ይቅር ብሎኝ ይሆን፥
.
አንዳንዴ እጄን ዘርግቼ መጠየቅ አፍራለሁ፥ ብዙ የማይገቡኝ ነገሮችን በመስጠት ውስጥ ያኖረኝ ፈጣሪን፡ለድክመቴ ብቻ መሸሸጊያ ሳደርገው፣ ዳግም ቀና ብዬ መራመድ ስጀምር ፡መሸሼን ሳስብ ያመኛል፥
.
ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው...ብዙ ሰው መሆን አይጠበቅባችሁም ፈጣሪ ዘንድ ዋጋ እንዲኖራችሁ፣ የፈለጋችሁትን ጠይቃችሁ ለማግኘት፣ ወድቃችሁ መሸሸጊያ ለመፈለግ፣ ከምንም በላይ ደግሞ አጥፍታችሁ ምህረት ለማግኘት፥
.
ለመልካም ነገር እንኳን በቂ ላልሆነ እድሜ ክፉ አንስራበት...እስከዛሬ ስንት ቀን ተጨምሮልን ይሆን? ቀን ዕድሜ ነውና ስንኖር የማይገፋን ፈጣሪን ላለማስቆጣት እንኑር!!!

@fikermahi
ጥያቄ፡-

ዶ/ር ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር ከ2 አመት በኻላ በድጋሚ ማውራት ጀምረናል፡፡ እናም ይቅርታ ተደራርገን አብረን እንድንሆን ጠየቀኝ እኔ ግን በፊት ካደረገው ነገር አንፃር ከልቡ መሆኑን ስለ ተጠራጠርኩኝ ጊዜ እንዲሰጠኝ ጠይቄዋለው እሱም የፈለኩትን ጊዜ ወስጄ እንድወስን ተስማምቷል። እኔ ግን እንዴት ብዬ እና ምን ተጠቅሜ ከልቡ እንደተፀፀተ እና በድጋሚ ታማኝነቱን እንደማያጓድል ማረጋገጥ እንዳለብኝ አላውቅም። ወይስ ግንኙነቱን ማደሱ ስህተት ነው?

መልስ፡-

አንድ የፍቅር ግንኑነት ከተበላሸ በኋላ እንደገና ለመመለስ የመፈለግ ሁኔታ የተለመደ ሲሆን ውሳኔውም ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ውሳኔውን በማመዛዘን ሂደት ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ ነገሮችን በሚገባ ማመዛዘን አስፈላጊ ነው፡፡

1. እንደገና ወደፍቅር ግንኙነቱ ለመመለስ ያለሽ ፈቃደኝነት፡- በሁኔታዎች ተገድደሽ ሳይሆን ግንኙነቱን ከልብሽ የመፈለግሽ ሁኔታ፡፡

2. ለመለያየት ያበቃችሁ የስህተት አይነት፡- ስህተቶቹ ቀላል አለመግባባቶች የመሆናቸውና በተቃራኒው ለመለወጥ ጊዜ የሚፈጁ ጥልቅ የባህሪ ችግሮች የመሆናቸውን ሁኔታ የመለየቱ ጉዳይ፡፡

3. ወደቀደመው ግንኙነት ለመመለስ ጥያቄውን ያቀረበው ሰው ማን መሆኑና ለምን መመለስ እንደፈለገ፡- አንቺ ካቀረብሽው ለምን? እሱ ካቀረበውስ ለምን?

4. ስህተታችሁ መታረሙ የመመዘኑ ጉዳይ፡- አንቺም ሆንሽ እሱ ለመለያየት ያበቃችሁን ስህተቶች ማረማችሁ የሚረጋገጥበት መመዘኛዎች የማስቀመጣችሁ ጉዳይለ፡

5. ለዚህ ሂደት በቂ ጊዜ በመስጠት በሚገባ የመግባባታችሁ ጉዳይ፡፡

በመጀመሪያ እነዚህን ሂደቶች ለጠቅላላ እውቀትና በጉዳዩ ለመብሰል መጠቀምሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡ ከዚም በኋላ ስህተቱ መታረሙን የምታረጋግጪባቸውን ነጥቦች አስቀምጪ፡፡ ያንን ለማስቀመጥ ቀላሉ መንገድ ስህተቱ መሰራቱን ያመለከቱሽን ንግግሮች ወይም ተግባሮ ደግመው አለመሰራታቸውንና ያንን ለማረጋገጥ የሚኖርን ግልጽነት መመልከት ነው፡፡

ፍቅረኞች በእውነተኛ ይቅር መባባል ካደረጉትና ትክክለኛውን ሂደት ከተከተሉ ሁል ጊዜ ግንኙነትን ማደስ የሚመከር ነው፡፡ 

https://m.youtube.com/user/naeleyob623


@fikermahi
አንድ ቪዲዮ እያየሁኝ ነበረ

👇🏾

እዚህ ቪዲዮ ላይ ቃለ መጠይቅ የሚቀርብለት ሰው ከተወሰኑ አመታቶች በፊት ከትልቅ ድልድል ላይ በመውደቅ ራሱን ለማጥፋት ሲሞክር በሰዎች ርብርብ የተረፈ ሰው ነው

"ራስህን ለማጥፋት ስትሄድ ምን እያሰብክ ነበር ከቤትህ የወጣኸው?"

ሰውዬው ይመልሳል

👇🏾

“በወቅቱ እጅክ ከፍቶኝ ነበር: ከጎኔ ሰው አልነበረም: ኑሮም ከብዶኝ ነበር:: ከዚያም ከቤት ወጥቼ ራሴን እስከማጠፋበት ድረስ ባለው መንገድ ላይ ሰላም የሚለኝ ሰው: ፊቱ ላይ ፈገግታ የሚያሳየኝ ሰው: እንዴት ነህ የሚለኝ አንድ ሰው ካገኘሁኝ ራሴን አላጠፋም ብዬ ነበር"

"እና ምን ሆነ ታዲያ?"

"አንድም ሰላም የሚለኝ ሰው አልነበረም: አንድም ጥሩ ፊት ያሳየኝ ሰው አልነበረም"

👇🏾

ሰላም በሉ!

ፈገግታን ስጡ

ሰው ምን ውስጥ እያለፈ እንደሆነ አናውቅምና !🙌🏼❤️


@እንማር

@fikermahi
👍7