" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር ሳይጋጭ እንደሚከናወን አሳውቋል።
በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ፣ ከመውጫና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲከናወን የሚረዳ ዕቅድ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ አስታውሰዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ዶ/ር ኤባ ፤ በዘንድሮው ዓመት 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸው ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡
የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱን አመላክተዋል።
ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በማዕከል ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና ሥርዓት ለመሞከር እንደ አገር ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቀው፤ በዚህም ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከልና ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።
ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደራጀ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ለመውጫ ፈተናው የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ጄኔሬተሮች ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tikvahethiopia

Fidel june Magazine.pdf
10.1 MB
ሰላም የፊደል ቤተሰቦች!
ወቅቷን ጠብቃ በየወሩ ወደ እናንተ የምትደርሰውን የፊደል መፅሔት እነሆ ብለናል።
በውስጧ የተለያዩ ሐሳቦችን፣ መልዕክቶችና መረጃዎችን ይዛ መጥታለች።
ተጋበዙልን!
መልካም ንባብ!

👍5
Come join us at fegegta event at torhailoch
ሰበር ዜና!
የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ትምህርት ቢሮ) ከ28 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ የተሰጠው ከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በዛሬው እለት ይፋ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰተዋል፡፡
ኃላፊው በመግለጫቸው ዘንድሮ ፈተናውን 73,667 ተማሪዎች መውሰዳቸውን ጠቁመው 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ 7ኛ ክፍል እንዲዘዋወሩ መወሰኑን በመጥቀስ የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 80.2% ያህሉ 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን ዶክተር ዘላለም ገልጸው 67,939 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 56,842 የሚሆኑት ማለትም 83.6 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን መዘዋወራቸውን አስረድተዋል፡፡
ቢሮው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ6ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ዶክተር ዘላለም ገልጸው በዋናነትም አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት ያደረገ የማጠናከሪያ ትምህርት እና የሞዴል ፈተናን በመስጠት ፤የተሻለ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት፤ እንዲሁም መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ተማሪዎችን ብቁ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መደረጉ ተማሪዎቹ አበረታች ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማስቻሉን አስታውቀዋል፡፡

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa6.ministry.et/#/result ወይም በ @G6MinistryResultQMTBot " መመልከት ይችላሉ " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።
ከ28 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ የተሰጠው ከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።
ዘንድሮ ፈተናውን 73,667 ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ 7ኛ ክፍል እንዲዘዋወሩ ተወስኗል።
የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 80.2% ያህሉ 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸው ተነግሯል።
67,939 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 56,842 የሚሆኑት ማለትም 83.6 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።
ከ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሀገሪቱን ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ የማያደርጉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች(international school) የሚማሩ ተማሪዎች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያን ጨምሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን እንደማይችሉ ቢሮው አሳውቋል።
ወላጆች ከወዲሁ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ በመወሰን ልጆቻቸውን ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት ተለልፏል።
ተማሪዎች ውጤታቸውን ተከታቹ ሊንኮቹን በመጫን መመልከት ይችላሉ።
https://aa6.ministry.et/#/result
Telegram bot: @G6MinistryResultQMTBot

👍1