Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)
2.04K subscribers
855 photos
23 videos
192 files
183 links
* Professional Tutorial service
* Book online or via phone
* Kg to university
* Flashcards
* online Tutorials
Contact
+251979795154
+251979795468

Youtube: https://www.youtube.com/@FidelTutorial


To become a tutor
join https://t.me/fideltutores
Download Telegram
#Ethiopis #Fidel #Fideltutorial ኑ አባከስን ከእኛ ጋር ይማሩ እና የሂሳብ ችሎታዎን ያሳድጉ።ኑ
ይመዝገባ።
አዲስ አበባ
በ ይደውሉልን
0979795154
0979795468 ይደውሉልን
#ብሔራዊ_ፈተና

" እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።

ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
👍1
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል።እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኝ ተማሪዎች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አገልግሎቱ ማሳሰቡ ተሰምቷል። በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችንም አገልግሎቱ ከነገ በኋላ የማያስተናግድ መሆኑን አሳስቧል።

@YeneTube
Fidel Magazine May Edition.pdf
13.4 MB
ሰላም የፊደል ቤተሰቦች!
ወቅቷን ጠብቃ በየወሩ ወደ እናንተ የምትደርሰውን የፊደል መፅሔት እነሆ ብለናል።
በውስጧ የተለያዩ ሐሳቦችን፣ መልዕክቶችና መረጃዎችን ይዛ መጥታለች።

ተጋበዙልን!
መልካም ንባብ!
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚሰጥባቸውን ቀናት ይፋ አደርጓል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ዲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በ2015 ዓ.ም 75,100 የ8ኛ እንዲሁም 75,078 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን ይወስዳሉ።

@tikvahethiopia