Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)
2.08K subscribers
857 photos
23 videos
192 files
185 links
* Professional Tutorial service
* Book online or via phone
* Kg to university
* Flashcards
* online Tutorials
Contact
+251979795154
+251979795468

Youtube: https://www.youtube.com/@FidelTutorial


To become a tutor
join https://t.me/fideltutores
Download Telegram
Do you need help with your Degree?

We provide the best Assistants for your
-BA
-BSC
-MBA
-MSC Degree.

contact us
0979795154/0979795468.

@fideltutorial
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የሁሉም ክልል ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ለፈተናው እንዲቀመጡ የተለየ ሲሆኑ እነርሱም፦

• የመጀመሪያ ዙር ፈተናን በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት መፈተን ያልቻሉ፣

• በህግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው በነበረው መፈተኛ ሁኔታ ለመፈተን ያልቻሉ፣

• የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ፣

• በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘና ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልወሰዱ፣

• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ፣

• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው፣

• ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት ፈተና እንዲወስዱ የተወሰነላቸው።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ገፃችንን https://t.me/fideltutorial JOIN እና ሼር ያድርጉ!
በትግራይ ክልል የመማር ማስተማር ሂደትን በቀጣዮቹ አምስት ወራት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በትግራይ ክልል ላለፉት ሁለት ዓመታት ትምህርት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል።

በክልሉ የትምህርት ሥራን ለማስጀመር የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን እቅዶች መያዛቸውንና ዝግጅት መጀመሩን በሚኒስቴሩ የትምህርት መሰረተ ልማትና አገልግሎቶች ዴስክ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ለኢፕድ ተናግረዋል።

በክልሉ የሰው ሀብት የማደራጀት፣ የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን የመጠገንና ግብዓት የማሟላት እንዲሁም የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እንደሚደረግ ኃላፊው አመልክተዋል።

በትግራይ ክልል የመማር ማስተማር ሥራው ሲጀመር ከሌሎች ክልሎች በተለየ መልኩ እንደሚሆነ የጠቆሙት ኃላፊው፤ በትግራይ ክልል የተማሪዎች ምገባ ለማስጀመር አጋር አካላት እና ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
AFTER SCHOOL PROGRAM WITH FIDEL.

fidel tutorial has invited every child to participate in the following activities

-football
-basketball
-swimming
-language

with
-easy learning
-fun Activities
-new experience
-professionals

contact us
0979795154/0979795468.
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች አድማ በመምታት ትምህርት ማቋረጣቸውን ሰምተናል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዓመት ተማሪዎች ያለ አግባብ የምንመረቅበት ጊዜ በተለይም የ2013 ባች ተማሪዎች  እስከ ሁለት ሴሚስተር ያህል ማለትም ከመመረቂያ ጊዜያችን አንድ ዓመት ዘግይተን እንድንመረቅ ዩንቨርሲቲው ወስኗል በሚል ምክንያት ተቃውሟቸውን ክፍል ባለመግባት እየገለፁ እንደሆነ ከተማሪዎቹ ያግኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጉዳዩ ላይ ግልፅ ውይይት ለማድረግ ኮሚቴ አዋቅረን ጥረት ብናደርግም ዩንቨርሲቲው የኛን ጥያቄ ከመስማት ይልቅ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አካላትን በማሰማራት ማስፈራሪያ እያደረሰብን ነው ሲሉ ከሰዋል።

ቤተሰቦቻችን ከኛ ብዙ ነገር ይጠብቃሉ የሚሉት ተማሪዎቹ በሌሎች ዩንቨርሲቲዎች ከሚገኙ ጓደኞቻችን እኩል መመረቅ ባለብን ካላንደር መሰረት ተመርቀን ተወዳዳሪ እንሁን ማለታችን እንደ ስህተት ተወስዶ አግባብነት ያለው ጥያቄያችን በጉልበት ሊታፈን አይገባም ብለዋል።
ለቀጣይ ዙር የ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች;
።።።፡።።።።:::::
ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ እየተቃረበ መሆኑን አውቃችሁ በተዘጋጃችሁት ልክ ተረጋግታችሁ ለመስራት ጥረት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በተለይ በግጭት አካባቢ የነበራችሁ ተማሪዎች በብዙ ችግር ውስጥ ሁናችሁ ስትዘጋጁ እንደቆያችሁ ይታወቃል። ችግራችሁን በመገንዘብም ቀጣዩ ዙር ፈተና የተዘጋጀላችሁ መሆኑን በመገንዘብ ዕድላችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት ምክራችንን እንለግሳለን።

በአንደኛው ዙር ፈተና (በተለይ በማህበራዊ ሳይንስ ፈተና) ወቅት የተከሰቱት ችግሮች  እናንተንም እንዳይገጥሟችሁ ማስታወስ ተገቢ ነው ብዬ ስላሰብሁ የሚከተሉትን ላጋራችሁ ወደድሁ:

1. በ2013 ተፈትነው ነገር ግን በድጋሚ  በመደበኛው ኘሮግራም ለመፈተን እድል የነበራቸው የተወሰኑ ተማሪዎች(ሁሉንም ለማለት አይደለም) ሲያጠኑ ስላልከረሙ እና የተሻለ ውጤት ማምጣት የማይችሉ መሆናቸውን በመገመት የፈተና ስርዓቱን ለማወክ ባደረጉት ሙከራ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው እና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተስፋ የነበራቸው ተማሪዎቻችን ከፈተና ተስተጓጉለውብናል። ይህ ድድርጊት እጅግ በጣም ስሜታችንን ጎድቶት አልፏል። በመሆኑም በቀጣይ እንዳይደገም ትምህርት መውሰድ ተገቢ ነው።

2. አንዳንድ ተማሪዎች ፈታኞችን ያልተገባ ንግግር በመናገር እና በማበሳጨት እንዲሁም የክፍል ፈተና ስርዓቱ እንዲረበሽ በማድረግ ፈታኞች ፈተናውን በችግር እንዲመዘግቡት የማድረግ ያልተገባ ግፊትም ተስተውሏል።

ይህ ድርጊት ምንጩ አስከአሁን ግልፅ ባይሆንም በተለይ ፈታኞች በሳል ሁነው ችግሩን በጥበብ ማለፍ ካልቻሉ ተፅዕኖው ቀላል እንደማይሆን ስጋት መፍጠሩ አልቀረም።

በጊዜው ሁሉም ቦታ ለመድረስ ባይቻልም መድረስ በቻልንባቸው የፈተና ጣቢያዎች ፈታኞችን ለማረጋጋት እና ድርጊቱ ውስን ቁጥር ያላቸው የተለዬ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በትዕግስት የፈተና ስርዓቱን እንዲመሩት ለማግባባት ተሞክሯል። ሌሎች ያልደረስንባቸው ጣቢያዎች ሁኔታ ምንይመስል እንደነበር ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ፈታኞች ይህን ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በትዕግስት እና በጥበብ ተወጥተውት እና ለብዙሀኑ ተማሪዎች ሲባል የአንዳንድ ተማሪዎችን ያልተገባ ስነምግባር በትዕግስት አልፈውት እንደሚሆን እንጠብቃለን።

3. በተለይ ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ላይ የተፈጠረው ያለመረጋጋት ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ የሚያስችል ሁኔታ ነበር ብሎ ለማለት ያስቸግራል።  የነበረው ሁኔታ ፈተና አቋርጠው በሄዱት ላይ  ብቻም ሳይሆን በፈተና ሂደቱ ውስጥ በነበሩት ተማሪዎች ላይም ተፅዕኖው ከባድ እንደሚሆን ይገመታል።

  በዚህም ሁከት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ውጤታማ ተማሪዎቻችን ባላሰቡት መንገድ ተስተጓጉለውብናል።

በአጠቃላይ የመጀመሪያው ዙር ፈተና እንደሀገር የመጀመሪያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ከት/ቢሮውም በኩል የነበሩ ከቅድመዝግጅት መጓደለም ጋር የተያያዙት መለስተኛ ችግሮች (በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት ማስተካከያ የተደረገባቸው ችግሮች)ተጨምረውበት በርካታ ተማሪዎቻችን ከፈተና ስርዓቱ የተስተጓጎሉበት ሁኔታ መፈጠሩ  የትምህርት ማህበረሰቡን እጅግ በጣም ያሳዘነ ክስተት ሆኗል።

የነበሩ የቅድመዝግጅት መጓደሎችን እና አጠቃላይ ሂደቱን በሚመለከት ለሚመለከተው አካል በጊዜው የግምገማ ሪፓርት ስላቀረብን እዚህ ላይ መዘርዘሩ አያስፈልግም።

በአጠቃላይ ከግምገማ ሪፓርታችንም ሆነ ከሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ውሳኔ ሰጭው አካል የሚሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ ዙር ፈተና የባለፋት ችግሮች በድጋሜ እናንተንም እንዳያጋጥሟችሁ ተገቢውን የጥንቃቄ ቅድመዝግጅት እንድታደርጉ ከወዲሁ እያሳሰብሁ መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!

የአብክመ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ
Congratulations to Argentina 🇦🇷🇦🇷🇦🇷
#QatarWorldCup
Study
-SAT
-TOEFL
-IELTS
with our professionals

BOOK
NOw !

Fidel Tutorial
0979795154/0979795468.
THE G.O.A.T
why is messi called the GOAT?

The word Goat is an abbreviation word, Greatest of all time, an internet slang initialism used to compliment athletes, musicians, Writers, or other celebrities for achieving great things in life.
Why is messi called the Goat? Leonel messi has won every Grand cups in the world competitions including the world cup holding so many records even from a young age.

10 La liga cups
4 champions league cups
1 World cup

-Top scorer in La Liga history with 474 Goals.
-Most international goals by a South American male 98.
-Most goals by a player for a single club 672.

Indeed a Goat!.......

@fideltutorial
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የአባልነት ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል። 

የኦንላይን ምዝገባ ለማድረግ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ፦

1. በ www.abrehot.org.et/register/ በመግባት የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ።

2. ፎርሙን እንደጨረሱ ክፍያ ገፅ ይፈጽሙ፤ ዓመታዊ የአባልነት ክፍያ በቴሌብር ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል መክፈል ይችላሉ።

3. ቅድመ ተከተሉን እንደጨረሱ አባልነትዎ ይረጋገጣል።

በ15 ቀን ውስጥ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ በኢሜይል ይደርስዎታል።
For all Junior Programmers

We have put a link step by step guides and paths to learn different tools and technologies.The intent of this guide is to give you an idea about the development landscape and to help guide your learning.

Flutter Developer
https://roadmap.sh/flutter

Android Developer
https://roadmap.sh/android

GraphQL Developer
https://roadmap.sh/graphql

Node.js Developer
https://roadmap.sh/nodejs

@fideltutorial
0979795154/0979795468.
ተከፋይ Intern መሆን ይፈልጋሉ?

#ደረጃ_ዶት_ኮም መረጃ የሚሰበስቡ ተከፋይ ተለማማጅ ሰራተኞች/Interns እየፈለገ መሆኑን አሳውቋል።

አመልካቾች ከሚከተሉት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአንዱ ተመራቂ ተማሪዎች የሆኑናና በዚያው አካባቢ የሚኖሩ መሆን አለባቸው።

➤ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ

➤ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ

➤ ቀብሪ ዳር ዩኒቨርሲቲ

➤ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ

➤ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

➤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

➤ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

➤ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው

ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScCC2eEOQ8c8BkxkBGPXy2pKUpgofa1gR1EdzlHtovDDSc9qg/viewform
Fidel Educational Consultancy

-Fidel guides students to be innovative and opens up an opportunity to explore and try different Educational sectors.

-Ethical Children that are well mannered, decent, considerate and respectful.

-Confident children that communicate well and promote a healthy companionship with others.

call us.
0979795154
0979795468.
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝነት"

ራስ ገዝ ሆነው የሚደራጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም አቀፍ ውድድር አዲስ ፕሬዝዳንቶችን እንደሚመርጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህ አሰራር በአገር ውስጥ ውድድር ተወስኖ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ቅጥር ሂደት በማስፋት የውጭ ዜጎችም ጭምር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪነት እንዲወዳደሩ ዕድል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ ዕቅድ ይዟል። በዚህ እቅድ ከተካተቱት ውስጥ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው በጀት ዓመት የራስ ገዝ አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ይጠበቃል።

መንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶቻቸውን ከሀገር ውስጥ ካሉ ምሁራን አወዳድረው ሲቀጥሩ ቢቆዩም፤ በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች (በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በመቐለ ዩኒቨርሲቲዎች) ለተወሰኑ ዓመታት የውጪ ዜጎችም በፕሬዚዳንትነት ተመርጠው አገልግለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆናቸው የአስተዳደር፣ የአካዳሚ፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

በተለያዩ አገራት በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ እና በአመራርነት የሚሰሩ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን ቢመሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል። 

ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ሊኖራቸው የሚጠበቀው የትምህርት ደረጃ “ዶክትሬት ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የሚወክል ትምህርት እና ልምድ” መሆን እንዳለበት በመመሪያው ሰፍሯል። ሆኖም የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች “በልዩ ሁኔታ” ሊመረጡ እንደሚችሉ በመመሪያው ተቀምጧል። 

እስካሁን በነበረው አሰራር በትምህርት ሚኒስቴር ሹመት የሚያገኙ ፕሬዝዳንቶች የሥራ ዘመናቸው ስድስት ዓመት ሲሆን ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ ሊመረጡ ይችላሉ። ምክትል ፕሬዝዳንቶች በአንጻሩ ሹመታቸው የሚጸድቀው በዩኒቨርስቲዎች ቦርድ ሲሆን አራት ዓመት የስራ ዘመን ይኖራቸዋል።

ራስ ገዝ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ዩኒቨርስቲዎች፤ ፕሬዝዳንቶቻቸውን የሚመርጡበትን መስፈርት፣ የአገልግሎት ዘመን እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚወስኑ ዝርዝር ድንጋጌዎች እንደሚኖራቸው ዋና ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ያለ ትምህርት ሚኒስቴር ጣልቃ ገብነት ፕሬዝዳንቶቻቸውን በቦርድ ማጽደቅ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ኢትዮጵያኢንሳይደር
Aastu.Final.Exam.Collection.pdf
4.9 MB
📚Aastu University ‼️
📚All Final Exams
📚  ፈተና  በቀጣይ  ፉይናል ያለባቹ ሞክሩት

❗️የ ዘንድሮ ነው(2014) ፎቶ በእንደዚህ መልኩ አንስታችሁ ላኩልን። ለናንተም ውጤታችሁን ፎቶ ማንሳት በኋላ ውጤታችሁ ችግር ቢያጋጥመው መፍትሔ ይሆናል።
 
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተመረጡ የጤና መስክ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ የተቀመጡ መስፈርቶችን ያሟላችሁ አመልካቾች ታህሳስ 17 18 2015 ዓ.ም በአካል በመቅረብ ምዝገባ እንድታከናውን ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አድርጓል።

@tikvahuniversty