Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)
2.06K subscribers
857 photos
23 videos
192 files
185 links
* Professional Tutorial service
* Book online or via phone
* Kg to university
* Flashcards
* online Tutorials
Contact
+251979795154
+251979795468

Youtube: https://www.youtube.com/@FidelTutorial


To become a tutor
join https://t.me/fideltutores
Download Telegram
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ

በትምህርት ሚኒስቴር ፀድቆ ለትግበራ የተላከውን የመውጫ ፈተና መመሪያ
በቴሌግራም ቻናላችን አስቀምጠንላችኋል።

@Fideltutorial ላይ ያገኙናል።
ፊደል አካዳሚ
ከ13 አመቱ ባለተሰጥኦ ፕሮግራመር የአብጸጋ ጎይቶም ጋር ያደረግነውን ድንቅ ቆይታ በYoutube ቻናላችን ይጠብቁን።

https://www.youtube.com/@FidelTutorial ላይ ያገኙናል።
መማር ለምትፈልጉ በሙሉ ከፊደል ቲቶሪያል ለእናንተ

ከ50 በላይ ለተለያዩ ትምህርቶች የሚሆኑ ዌብሳይቶችን ይዘንላችሁ መጥተናል።

@fideltutorial ላይ ያገኙናል።
1. http://Noexcuselist.com

2. https://coursebuffet.com

3. https://edureka.co/all-courses

4. http://ureddit.com

5. https://opencourser.com

6. https://khanacademy.org/test-prep

7. https://oneword.com

8. https://medium.com

9. https://stackexchange.com/sites

10. https://oyc.yale.edu

11. http://openculture.com/freeonlinecourses

12. https://ocw.mit.edu/index.htm

13. https://apple.com/education/itunes-u/

14. http://videolectures.net

15. https://kutztown.edu/about-ku/administrative-offices/small-business-development-center/resources/free-online-learning-programs.htm

16. https://scu.edu/mobi/

17. https://open.edu/openlearn/about-openlearn/welcome-openlearn-free-learning-the-open-university

18. http://freecomputerbooks.com

19. https://open2study.com

20. https://oedb.org/open/

21. https://uopeople.edu

22. https://khanacademy.org

23. https://udacity.com

24. https://hackr.io

25. https://sololearn.com

26. https://w3schools.com

27. https://coursera.org

28. https://academy.vertabelo.com

29. http://upskillcourses.com

30. https://edx.org

31. https://hackerrank.com

32. https://youtube.com/user/thenewboston

33. https://skillshare.com

34. https://futurelearn.com/courses

35. https://degreed.com

36. https://bolc.co.uk/free-online-courses-with-certificate

37. http://entrepreneurship.org

38. https://see.stanford.edu

39. http://oli.cmu.edu/learn-with-oli/see-all-oli-courses/

40. https://udemy.com

41. http://ocw.jhsph.edu

42. https://open.umich.edu

43. https://extension.harvard.edu/academics/online-campus-courses

44. https://saylor.org

45. https://universityoffashion.com

46. https://alison.com/courses

47. http://ecoursem.com/new-free-courses/

48. https://tutsplus.com

49. https://tutsgalaxy.com

50. https://memrise.com
#MoE

• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

• 200, 000  ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ  እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ " ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ  በመሆኑ ነው " ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)
Fidel December Edition Magazine.pdf
2.6 MB
እነሆ በውስጧ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን የያዘችው ወርሃዊዋ የፊደል መፅሄት ቀኗን ጠብቃ ወደ እናንተ መጥታለች።

በውስጧ

-ትምህርት
-ቤተሰብ
-ልዩ ፍላጎት
-ሳይንስና ቴክኖሎጂ
-ፊደል ሜዲካል
-ፋሽን
-ምን አዲስ በኢትዮጵያ?
-ፊደል እንግዳ
-ፊደል በዚህ ወር
-ፊደል የመፅሀፍት ጥቆማ
-ፊደል የፊልም ጥቆማ

እነዚህንና ብዙ ጉዳዮችን አካታለች።
ተጋበዙልን!
የመውጫ ፈተናን በተመለከት ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሄደ።
**

በዚህ አመት ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው ሀገር አቀፍ የመው
ጫ ፈተናን በተመለከት ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም የስነ-ልቡና ግንባታ ስልጠና እና የውይይት መድረክ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስነ-ልቡና ምሁራን የሆኑ መምህራን እና የኮሌጅ ዲኖች በተገኙበት ለሁለት ቀናት ተካሂዷል።

በመድረኩ መክፈቻ ስለመውጫ ፈተናው ሰፋ ያለ ማብራሪያ በማቅረብ ስልጠና የሰጡት የስነ-ልቦና ሙህር የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ የመውጫ ፈተና የሚሰጥበትን ምክንያት እንዲሁም የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማንሳት ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ለተማሪዎች አስረድተዋል። ከነዚህ ጥቅሞች ውስጥ የትምህርት ጥራትን ማሳደግ፣ ተወዳዳሪ የሆነ ዜጋ ማፍራት እና እራስን ለመፈተሽ እንደሚያግዝ እንዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞችን በመጥቀስ አስረድተዋል። አክለውም ተማሪዎች ፍራታቸውን አስወግደው ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመቀጠልም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የህግ ትምህርት ክፍል ዲኖች እስከ አሁን ለጤና እና ለህግ ተማሪዎች ይሰጥ በነበረው የመውጫ ፈተና ያላቸውን ልምድ ለተማሪዎች አካፍለዋል። ዲኖቹ አያይዘውም በሁለቱም ኮሌጆች እየተሰጠ ባለው የመውጫ ፈተና ተሞክሮው እንደሚያሳየው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተከታታይ ዓመታት ባስመዘገቡት ክፍተኛ ውጤት ዩኒቨሲቲው በደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ሲካተት የቆየ መሆኑን አስታውሰው የነሱን አርአያ በመከተል ይህንን ልምድ ማስቀጠል እንደሚገባ እንዲሁም ከዘንድሮ ተመራቂዎችም ትልቅ ውጤት እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ዲን መምህር ቃኘው ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ትምህርት ቤት የመውጫ ፈተና ሲጀመር የነበራቸውን ትዝታ ለተማሪዎቹ ያስታወሱ ሲሆን ተማሪዎች ስጋታቸውን አስወግደው ዝግጅቱ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ በማሳሰብ አሁንም ለመዘጋጀት በቂ ጊዜ እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

በመድረኩ የተገኝተው ተማሪዎቹን ያወያዩት የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብቴ ዱላ እና የአካዳሚክ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ካሳሁን አቤ ስለመውጫ ፈተና ከተማሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ሀብቴ በበኩላቸው ተማሪዎች ለፈተናው ያላቸውን አሉታዊ አመለካከት በመቀየር ሰፋ ያለውን አውንታዊ አንድምታ መገንዘብ እንደሚያሻ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለፈተናው ዝግጅት በቻለው አቅም ሁሉ እንደሚያግዛቸው እና ከጎናቸው በመሆን እንደሚረዳቸው ቃል ገብተዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ተማሪዎች ከራሳቸው የሚጠበቀውን ብቻ ካደረጉ የሚያስጨንቅ አንዳች ነገር እንደሌለ እንዲሁም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመውጫ ፈተናዎች ላይ የነበረውን ውጤታማነት የዚህ አመት ተመራቂ ተማሪዎችም እንደሚያስቀጥሉ ባለሙሉ ተስፋ እንደሆኑ ገልፀዋል።

“ፈተናው ግቢ ላይ ከምትፈተኑት የተለየ ፈተና አይደለም” ሲሉ የገለፁት ረዳት ፕሮፈሰር ካሳሁን አቤ ፈተናው ጠቅላላ እውቀትን ያማከለ መሆኑን ገልፀው “አንድ ምግብ አብሳይ የሚያበስለውን ምግብ ለማዘጋጀት ምን እንደሚያስፈልገው በመጠየቅ ያንን ምግብ ለማብሰል ያለውን እውቀት እንደመገምገም ነው” ማለት በምሳሌ አስረድተዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ሚካኤል ያቦነሽ ፈተናው ከመሰጠቱ በፊት ማንኛውም ተማሪ በዩኒቨርሲቲው እና በህብረቱ የሚዘጋጁ የድጋፍ ትምህርቶችን በመከታተል፣ እርስ በእርስ በመተጋገዝ እንዲሁም በተናጠል በማንበብ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።


ዘገባው የወ/ዩ/ተ/ህብረት የመረጃ እና የህዝብ ግንኙነት ነው።
How was your 1st semester grade?

which subjects can we help you with?
-Math
-Physics
-General Science
-Chemistry
-Or which Subject?

Call us
fidel Tutorial
0979795154/0979795468
Fidel tutorial
we can help you with math!

from KG to University
Contact Us
0979795154/0979795468.

@fideltutorial
ይመዝገቡ!

አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በሚቀጥለው ሳምንት አርብ 7:30 የአባልነት ምዝገባ ይጀምራል።

ይህም ለተጠቃሚዎች የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

መጻሕፍትን በነጻ መዋስ እንዲሁም ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ጆርናሎች እና ፅሁፎችን በኦንላይን ማግኘት አባል በመሆንዎ ከሚያገኟቸው ጥቅሞች መካከል ይጠቀሳሉ።

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሙሉ ወጪ በመሸፈን የሚሰጥ መሆኑንም የቤተ-መጻሕፍቱ አስተዳዳሪ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።
FIDEL TUTORIAL CENTER

Math,
physics, Science,
and English Tutoring.
Maximize your learning with
our personalized sessions!

Call us
0979795154
0979795468

@fideltutorial
ነፃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መማሪያ ገፅ

የትምህርት ሚኒስቴር  ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ነፃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ያለምንም ክፍያ  አቅርቦሎታል።

ልጆችዎ ይማራሉ  - እርስዎም የእንግሊዝኛ ቋንቋዎን ያሻሽሉበታል።

የትም ሆነው ይማሩ  የቋንቋ ክህሎትዎን ያዳብሩ!

አገልግሎቱን ለማግኘት ከታች የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ

👇👇👇
https://learn-english.moe.gov.et
ዕድሜያቸው ከ 17-21 ለሆኑ ተማሪዎች የተዘጋጀ ልዩ ሃካቶን (Hackaton)

በዚህ ውድድር መሳተፍ የሚፈልግ ተማሪ ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ መመዝገብ ይችላል።

ምዝገባው በነፃ ሲሆን ከህዳር 30 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ይቆያል።

ከእንድ እስከ ሦሥት ለሚወጡ ተማሪዎች ልዩ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ለመመዝገብ 👉     hackathon.kibur.net

ለበለጠ መረጃ፦      0113698558