Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)
2.92K subscribers
982 photos
23 videos
192 files
245 links
* Professional Tutorial service
* Book online or via phone
* Kg to university
* Flashcards
* online Tutorials
Contact
+251979795154
+251979795468

Youtube: https://www.youtube.com/@FidelTutorial


To become a tutor
join https://t.me/fideltutores
Download Telegram
We are truly grateful to conclude our incredible two-day journey at Techarena 2026 in Stockholm — Scandinavia’s largest innovation, business, and entrepreneurship event.

Over the past two days, we connected with brilliant founders, forward-thinking investors, and inspiring business leaders from around the world. For us at Fidel Tutorial, working in education and edtech, the experience was eye-opening and deeply valuable opening doors to global networking, fresh perspectives, and meaningful conversations that will help shape the future of learning.

A heartfelt thank you to Reach for Change Ethiopia for providing us with this incredible global opportunity, and to the Embassy of Sweden in Addis Abeba for their support.
We are also grateful to the entire TECHARENA team for creating such a powerful platform that brings innovators together and fosters real change.
We are honored to have been part of this experience.
Grateful for the journey and excited to turn these connections into meaningful, lasting impact.
9👏1
ስላም ወላጆች

የልጆች አስተዳደግ እና ትምህርታቸው በሚል ሀሳብ የቴሌግራም private group ከፍተናል።

ከፊደል እና ከሌሎች ውላጆች በጋራ በመሆን እድንወያይ ስንል በአክብሮት ተጋብዘዋል ወደ ግሩፕ ለመግባት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
https://t.me/+XHl2bxMDrWdkMDE0
ፊደል ቱቶሪያል ከኢቲቪ የልጆች አለም ጋር በመተባበር ዘዉትር ከምሽቱ 12፡00 እስከ 1፡00 እያቀረበላችሁ ያለዉን የጥናት ጊዜ ስንቶቻችሁ እየተከታተላችሁ ነው?

👉 ያመለጣችሁን የጥናት Episode በዩቲዩብ ቻናላችን ስለምንለቅ https://youtu.be/iAj3qpavUVk ሰብስክራብ አድርገው ይከታተሉን።

📍አስተያየትዎን በኮመንት ላይ ይፃፉ!
🔎 ይቀላቀሉን፡ https://t.me/fideltutorial
4👍1
ከ5 - 8ተኛ ክፍል ያሉ ልጆች ወላጆቻቸው እንዲረዷቸው ከሚፈልጉት ነገሮች

1. የጉርምስና ዕድሜ የሚጀምርበት ወቅት ነው እና በቀላሉ ሊበሳጩ፣በቀላሉ ሊያለቅሱ እንዲሁም ብቻቸውን መሆን ሊፈልጉ ይችላሉ። ብዙ የሆርሞን ለውጥ ስለሚኖር ታገሷቸው

2. መደመጥ ይፈልጋሉ።ሀሳቦቻቸው እንዲከበር ይፈልጋሉ።ራሳቸውን እንደትልቅ ሰው ስለሚያዩ  እንደህፃን ልጅ መታየት ያበሳጫቸዋል።

3. ውድድር አይፈልጉም። ከሌሎች ልጆች ጋር፤ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር መወዳደር በቂ እንዳልሆኑ፣ እንዳልተወደዱ እንዲሰማቸው ያደርጋል


4. በዚህ ጊዜያቸው ስለራሳቸው፤ ስለጓደኛ፤ ስለቤተሰብ፤ ስለማህበራዊ ጉዳዮች የሚያሰላስሉበት ጊዜ ነው እና በጨዋታ የታጀቡ የውይይት ጊዜያት ይፈልጋሉ

🎯 የገጠማቹን ነገር ለነሱ በሚመጥን መልኩ አጋሯቸው ሀሳቦቻቸው ጠይቋቸው

🔎 ይቀላቀሉን፡ https://t.me/fideltutorial
6
ወላጆች ስለ ልጆቻችሁ እና የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ጉዳቶች ማወቅ ያሉባችሁ ነገሮች

1. የዶፓሚን ሆርሞን ቶሎ ቶሎ መለቀቅ
ዶፓሚን ጥሩ ስሜት ሲሰማን የሚለቀቅ ሆርሞን ሲሆን ከአንድ አስቂኝ ፖስት ወደ ሌላ ሲሸጋገሩ ዶፓሚን እንዲለቀቅ አዕምሯቸው ሲያደርግ ይህ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንዲሁም ጥናትን አዕምሯቸው እንደአሰልቺ ነገር ይቆጥረዋል።

2. ትኩረት የማድረግ አቅማቸው ይቀንሳል። በተለይ ከ5 - 8ኛ ክፍል ያሉ ልጆች ትኩረት እና ውሳኔ የሚሰጠው የአዕምሯቸው ክፍል (prefrontal cortex) ገና እየዳበረ ያለ በመሆኑ በአጭር video ረዘም ያለ ጊዜ ማሳለፋቸው ትምህርት እና ጥናት ላይ ረዘም ያለ ሰአት በትኩረት ማሳለፍ ያቅታቸዋል

3. ራሳቸውን ከሚያዩት ነገር  ጋር ስለሚያወዳድሩ በራስ መተማመናቸው ሊወርድ ይችላል።እንዲሁም ራሳቸው በሚያገኙት ላይክ እና  ቪው መለካት እንዲሁም ለራሳቸው ዝቅተኛ አመለከካት እንዲኖራቸው ያደርጋል

4. የእንቅልፍ ሰአት መዛበት እና ውጤታማ የትምህርት ቀን ማሳለፍ አለመቻል

🔎 ይቀላቀሉን፡ https://t.me/fideltutorial
👍65
TECHARENA 2026 | Connecting Ethiopia’s EdTech to the Global Stage

At TechArena 2026 in Stockholm, global leaders, founders, and investors gathered under the theme New Era, Next Mindset to explore the technologies, partnerships, and leadership shaping the future. From the keynote by former UK Prime Minister Boris Johnson emphasizing girls’ education to discussions on AI driven business models, one message stood out: innovation must expand opportunity.

In collaboration with the Embassy of Sweden in Addis Abeba, Reach for Change Ethiopia facilitated international market linkages for our Fellows, positioning Ethiopia’s EdTech entrepreneurs within the global ecosystem.

We proudly stood alongside GlobeDock Academy, Fidel Tutorial, AIT Technology, and Kuraztech as they stepped onto the global stage.
5
📚ለተማሪዎች (ለተማሪ ወላጆች) ከዚህ በፊት ከሰኞ እስከ እሁድ ከ 12፡00 - 1:00 በኢቲቪ የልጆች አለም ሲተላለፍ የነበረዉን የጥናት ፕሮግራማችን እንደቀጠሉ ናቸው እናንተም በእነዚህ ሰዓት እየገባችሁ መከታተል ትችላላችሁ🔎 ይቀላቀሉን፡ https://t.me/fideltutorial
4
ልጆች በትምህርታቸው ስኬታማ መሆን እየፈልጉ በገንዘብ ማነስ ምክያት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ማጣት አለባቸውን? 📚

ፊደል ቱቶርያል ከግለሰቦች እና ከድርጅቶች ጋር በመተባበር ለ 3 ወር የሚቆይ የጥናት መረሃግብርን በጥናት መዕከላችን ለመስጠት ዝግጅታችንን የጨረስን በመሆኑ እርሶም ከአንድ ልጅ ጀምሮ የጥናት ወጪአቸውን በመቻል የበኩሎን ድርሻ ይወጡ።

የልጆችን በሕይወት እኩል የመወዳደር መድረክ በጋራ እንድናመቻች ስንል በተማሪዎች፣ በተማሪ ወላጆች እንዲሁም በድርጅታችን ስም በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

☎️ ለበለጠ መረጃ 0979795154/0979795468
🔎 https://t.me/fideltutorial
👍4
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሰዎ! ⚔️🛡

ፊደል ቱቶርያል | Fidel Tutorial
https://t.me/fideltutorial
7👍4
ተማሪዎች በራስ መተማመናችሁን እንዴት ልታሳድጉት ትችላላችሁ?

1. ለራሳችሁ ለማድረግ/ላለማድረግ የገባችሁትን ቃል ተግብሩት ለምሳሌ ጠዋት ተነስቼ ስፖርት ሰራለሁ ካላችሁ ጠዋት ለመነሳት ቢደብራቹም ያላችሁትን አድርጉት። ይህ በጊዜ ሂደት ለራሳችሁ የምትሉት የምትተገብሩ ናችሁ እና በራስ መተማመናችሁን ያሳድጋል

2. ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ሁልጊዜ እሺ ብቻ የምትሉ ሳይሆን  አይሆንም የምትሏቸው ነገሮችን በግልፅ አስቀምጡ። በሁሉም ግንኙነቶቻችሁ ውስጥ መስመር ማስመር አትዘንጉ

3. ለጊዜያችሁ ከፍተኛ ዋጋ ስጡ። ጊዜያችሁ በእጃቹ ያለ ሀብት ከመሆኑም በላይ ዛሬ የምታደርጉት ነገር ነጋችሁን ስለሚሰራ በጥንቃቄ ጊዜያችሁን ተጠቀሙ

4. ዲስፒሊን ይኑራችሁ አንድ ነገር ስታደርጉ ስሜቱ ደስ አላችሁም አላላችሁም መደረግ ያለበት ከሆነ አድርጉት። ዲስፕሊን  አሰልቺ እና ውጤቱ ቶሎ የማይታይ ቢሆንም  ከሞቲቬሽን ጋር ሲነፃፀር በራስ የመተማመን ስሜታችሁ ላይ ለውጥ አለው

#Discipline #Plan 📝
#Confidence #Action

ፊደል ቱቶርያል | Fidel Tutorial
https://t.me/fideltutorial

ከKG - ዩንቨርስቲ ለጥናት አግልግሎት ☎️
0979795154/0979795468 ይደዉሉልን
6👍1