Forwarded from ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር
ቤተክርስተያኑ በእሳት አደጋ ለሊት ሙሉ በሙሉ ወደመ
የወይራ ሠፈር ኆኅተ ገነት ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ቀጠሎ ወደመ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኮሎፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የወይራ ሠፈር ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና መንበረ ብርሃን እጨጌ አቡነ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ሌሊት በእሳት አደጋ ምክንያት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የቃጠሎው መነሻ የኤሌክትሪክ መስመር ችግር እንደሆነም የተገለጸ ሲሆን ከታቦቱ በስተቀር ሌሎች ንዋየተ ቅድሳት ሙሉ በሙሉ በአደጋው ምክንያት መውደማቸው ነው የተገለጸው ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ዘግበዋል።

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
#ጾመ_ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡
ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹#ጾመ_ነቢያት (#የነቢያት_ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹#ጾመ_አዳም (#የአዳም_ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹#ጾመ_ስብከት (#የስብከት_ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹#ጾመ_ልደት (#የልደት_ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹#ጾመ_ፊልጶስ (#የፊልጶስ_ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹#ጾመ_ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡
ምንጭ፡-
ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

Forwarded from ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር ወደ ግሸን ላሊበላ ቁልቢ ገብርኤል እና ሌሎች ገዳማት ጉዞ እናዘጋጃለን (Endale Seyoum)
እንኳን አደረሳችሁ ወደ ተናፋቂዋ እና ተቦተ ጽዮን መገኛ ወደ ሆነችው አክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ ምዝገባ ጀምረናል ፈጥነው ይመዝገቡ ባለን ውሱን ቦታ ብቻ እንመዘግባለን የጥንት የጠዋቱ ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር
Forwarded from Endale Seyoum
"እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል። እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።"
ኦሪ ዘዳ 28 : 1—7
" ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል።
እኔን ስለ ተውኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስክትጠፋ ፈጥነህም እስክታልቅ ድረስ በምትሠራው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር መርገምን፥ ሽሽትን፥ ተግሣጽን ይሰድድብሃል።
እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፥ በሰባት መንገድ ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ ለምድርም መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።
ሬሳህ ለሰማይ ወፎች ሁሉ ለምድርም አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።"
ኦሪ ዘዳ 28 : 15—26።
እነዚህ ጠንከር ያሉ የአምላካችን ማስጠንቀቂያዎች የተሰጡት እስራኤል መላ ዘመናቸውን ለትውልደ ትውልድ እንዲጠብቁት ነበር፣ ግን ይህን ስለዘነጉ በጠላት ፊት እንዲመቱ አድርጓቸዋል፣ ይህም የሚያሳየው የእነርሱን ድክመት እንጂ ታቦቱ ኃይል ስለሌለው እንዳልሆነ ማስተዋል ይገባል።
ልበ አምላክ ዳዊትም "እመሰ ዐመፃ ይሬኢ ውስተ ልብየ ኢይሰምአኒ እግዚአብሔር" (እግዚአብሔር በልቤ ውስጥ ተንኮል ቢያይ ኖሮ አይሰማኝም ነበር፣ መዝ 66:18) እንዳለ የእኛን የውስጥ ችግር ባለማየት ታቦት እንዴት ይማረካል በሚል ጥያቄ ናላን ማዞር የተሳሳተ አመለካከት ነው፣
☞☞☞ታቦቲቱ ተማርካ ሳይሆን በእስራኤል ተገፍታ መሆኗን ልብ እንበል! መባረር እና መማረክ ይለያያሉና።
3. ለተአምራት:— ታቦተ ጽዮን ከተማረከች በኋላ በሀገረ ፍልስጥኤም ብዙ ተአምራትን በማድረግ በተለይም ዳጎንን በመቀጥቀጥ ኢአማንያንን አስደምማለች።
"በነጋውም ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር፤ የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር።" እንዲል
ሳሙ ቀዳ 5 : 4።
በዚህም ምክንያት " የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ይሂድ በማለት" በማለት በሠረገላ አድርገው በሁለት ላሞች እያስጎተቱ በክብር ሸኝተዋታል። ይህም ታቦትና ጣዖት ምንና ምን እንደሆኑ እግዚአብሔር ራሱ የገለጠበት ተግባራዊ ሂደት ነው።
ቅዱስ ጳውሎስም ከዚህ በመነሳት "መኑ ዘደመሮ ለታቦት ምስለ ጣዖት" በማለት የታቦትንና የጣዖትን ልዩነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል። 2 ቆሮ 6:18።
ታቦቱን ከመንበሩ
እነ የኔታን ከወንበሩ አይለይብን!!!
ጽዮን የተባለች የእናታችን የእመቤታችን በረከትና አማላጅነት አይለየን!!!
አሜን!
መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው