ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media
993 subscribers
8.92K photos
102 videos
110 files
1.38K links
ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።

#የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል
#FTM
Download Telegram
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።»
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሰናይ አዳር
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
ሲጠበቅ የነበረው ከሀምሌ 17-19 በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተጀመረ።
ጉባኤው በ18 እና በ19 የሚቀጥል ሲሆን የመላዕኩ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረበዓል አርብ ጠዋት ላይ በደብሩ የሚከናወን ይሆናል።
ፈጣሪያችን ለክብረበዓሉ ያብቃን
መልካም ምሽት
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
የፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት በትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ የህፃናት ሰንበት ተማሪዎች ወላጆች ጋር ውይይት አደረገ።
በውይይቱ መርሀግብር ስለህፃናቱ  ስነምግባር ፣ስለህፃናት የአገልግሎት ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዬች ውይይት በማድረግ እና የወላጆች ኮሚቴ በማዋቀር መርሀግብሩን በፀሎት የዘጋ ሲሆን እንደዚህ አይነት መርሀግብር ለሰንበት ት/ቤቱ ጠቃሚ ነው እና ይበል ይቀጥል ብለን እናሳስባለን።

መልካም ቀን

ሀምሌ 21/2016 ዓ.ም
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
በፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤ የ2016 ዓ.ም የ2ኛ መንፈቀአመት ማጠቃለያ ጠቅላላ ጉባኤ ተደረገ።
በመርሀግብሩ ላይም የደብሩ ስብከተ ወንጌል ምክትል ሰብሳቢ የቢሾፍቱ እና አካባቢው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ፣በቢሾፍቱ ወረዳ ማዕከል ማህበረ ቅዱሳን ፀሀፊ እና ሌሎች የሰንበት ት/ቤት አባላት መርሀግብሩን የታደሙ ሲሆን በመርሀግብሩላይም የ2016 ዓ.ም የሂሳብ ሪፓርት፣የ2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ፣የ2017 ዓ.ም እቅድ፣ በስራ እና በተለያዩ ምክንያቶች ከስራ አመራርነት ለተነሱ አባላት በእነሱ ምትክ የሆኑ አባላት በጠቅላላ ጉባኤላይ የመምረጥ እና የተጠባባቂ አካላትን በማዘጋጀት መርሀግብሮች የተከናወኑ ሲሆን በመጨረሻም የሰንበት ት/ቤት ህብረት ሰብሳቢ እና የወረዳ ማዕከል ፀሀፊ መልዕክት እና ብራኬ በመስጠት መርሀግብሩ በፀሎት ተዘግትዋል።

እኛም እንደዚህ አይነት የአንድነት መርሀግብሮች በየጊዜያቱ ይበል ይቀጥል እያልን ምልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
#ጠቅላላ_ጉባኤ
ነሀሴ 6/2016 ዓ.ም
በቢሾፍቱ ከተማ በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ለ3ቀን  የተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት 2ኛ ቀን ጉባኤ የተከናወነ ሲሆን በነገው ዕለት በሚኖረው የማታ ጉባኤ ላይ ታላላቅ አባቶች  መምህራን የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪያን በተገኙበት መርሀግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ጉባኤው ከቀኑ 10 :00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ይሆናል።

በነገው ዕለት ጉባኤውን ለመታደም ስንመጣ 1ችቦ ይዘን መገኘታችን እንዳይረሳ።

#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም

በጉባኤው ላይ የተነሱ ፎቶግራፎችን ከስር ባለው የቴሌግራም ቻናል ላይ ያገኙታል።👇👇👇👇
https://t.me/felegetibebimage
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!!
የ2017 ዓ/ ም አዳዲስ አባላት ለመቀበል ፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት በዝግጅት ላይ ይገኛል ስለሆነም እርስዎ የዚህ እድል ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ፤መርሃ ግብሩ እድሜ ጾታ ሳይለይ ሁሉም ክርስትያን ስለ ቤተ-ክርስትያንና ስለራሱ
በደንብ አዉቆ እራሱንም ቤተ-ክርስትያንንም እንዲጠብቅና የእግዚአብሔር መንግስትን እንዲወርስ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስትያን ትምህርቶችን ኑ ተማሩ ትላለች የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት።


የፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት አባላት ክትትል እና ግንኙነት ክፍል
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!!
የ2017 ዓ/ ም አዳዲስ አባላት ለመቀበል ፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት በዝግጅት ላይ ይገኛል ስለሆነም እርስዎ የዚህ እድል ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ፤መርሃ ግብሩ እድሜ ጾታ ሳይለይ ሁሉም ክርስትያን ስለ ቤተ-ክርስትያንና ስለራሱ
በደንብ አዉቆ እራሱንም ቤተ-ክርስትያንንም እንዲጠብቅና የእግዚአብሔር መንግስትን እንዲወርስ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስትያን ትምህርቶችን ኑ ተማሩ ትላለች የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት።


የፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት አባላት ክትትል እና ግንኙነት ክፍል
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
ኑ ጥበብን እንማር
በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት የአዳዲስ አባላትን ምዝገባ ጀመረ ለመመዝገብ የሚያስፈልገው ዋነኛው ነገር ስለ ሀይማኖቱ ጠልቆ መማር ማወቅ የሚፈልግ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ብቻ መሆን ነው።

በመሆኑም በደብረዘይት/ቢሾፍቱ እና አካባቢው ላይ የምትገኙ ህዝበ ክርስቲያኖች በሙሉ ተመዝግባችሁ የህይወታችንን ስንቅ እንይዝ ዘንድ ጋብዘኖታል።

በአካል ተገኝታችሁ ለማትችሉ ኦርቶዶክሳዊያን እግዚአብሔር ከፈቀደ በቅርብ ባላችሁበት ሆናችሁ የምትማሩበትን መንገድ የምንገልፅላችሁ ይሆናል ።

የምዝገባ አድራሻ
ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት ሱቅ ።
በፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት ፅህፈት ቤት ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከምሽቱ 11:30 -1:30
በአካል ተገኝታችሁ መመዝገብ ለማትችሉ በቴሌግራም ላይ @felegetbeb12  ላይ ያናግሩን።

ለበለጠ መረጃ
0910755655
0976656045 ይደውሉ

መልካም የአገልግሎት ዘመን

#ፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሸዋ ሀገረስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በ6 ወረዳ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ላይ የ4ኛ እና 8ኛ ክፍል የእርከን መሸጋገርያ /ሚኒስትሪ/ ፈተና ዛሬ እሁድ 19/12/16 ዓ.ም ሰጠ።
የዚሁ ፈተና አካል የሆነው መርሐግብር በቢሾፍቱ እና አከባቢው ቤተክህነት ከ15 አጥቢያ ለመጡ 744 ለሚሆኑ 4ኛ ክፍል ተማራዎች  ይህንኑ ፈተና የሀገረስብከቱ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀላፊ መ/ሀ ቆሞስ አባ  ኃ/ገብርኤል የቢሾፍቱ እና አከባቢው ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ክቡር መ/ብስራት ቀሲስ ሲሳይ ደምሴ የቢሾፍቱ እና አከባቢው ቤተክህነት ዋና ፀሀፊ መጋቢ ጥበብ መ/ር እዉነቱ የደ/ዘ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መ/ሰ ቆሞስ አባ ወ/ሩፋኤል በላይ በፀሎት እና በቃለ ምዕዳን መርሐግብሩን ባርከው አስጀምረዋል።
የሀገረስብከቱ አንድነት እንደገለፀው ከሆነ ከየ አጥቢያው ብልጫ ላመጡ ተማሪዎች ጳጉሜ 02/2016 ዓ.ም የሽልማት እና ካርድ የመስጠት መርሐግብር በሀገረስብከቱ አዳራሽ የምስራቅ ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት እንደሚከናወን የገለፀ ሲሆን የቢሾፍቱ እና አከባቢው ቤተክህነት ክቡር ስራ አስኪያጅ ክቡር ፀሀፊ ለአንድነቱ ለሰ/ት/ቤት እየሰጡት ላለው ድጋፍ እና ክትትል ምስጋና አቅርበዋል።
#FTM
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ላስተማራቸው ሚኒስትሪ ተፈታኞች የምርቃትና የሽልማት መርሓ ግብር ብፁዕ አቡነ
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ላስተማራቸው የሚኒስትሪ ተፈታኞች የምርቃትና የሽልማት መርሓ ግብር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ፡ ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች ፡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፡ አበው ካህናት ፡ የአንድነቱ ከፍተኛ አመራሮች ፡ ከልዩ ልዩ ወረዳዎችና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ የደረጃ ተማሪዎችና አመራሮች  በተገኙበት በአዳማ ደብረ ታቦር  ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ  መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡

መርሐግብሩ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መሪነት በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የዝማሬ አገልግሎት በአዳማ ናዝሬት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን የቀረበ ሲሆን በዲ/ን ፍስሐ ታደሰ  የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ም/ሰብሳቢና የትምህርት ክፍል ኃላፊ በአዲስ መልክ እየተተገበረ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያና ስለ አፈጻጸሙ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም የአንድነቱ ተቀዳሚ ም/ሰብሳቢ መምህር ኢንጅነር ዓለም አንተ አበጀ የሰንበት ት/ቤት መዋቅር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ሰንበት ት/ቤት አወቃቀር የሰንበት ት/ቤት ተልዕኮ የሰንበት ት/ቤት አስፈላጊነት ምን እንደሚመስልና የሰንበት ት/ቤት መዋቅር በቤተ ክርስቲያን ላይ መዘርጋቱ ያለው ፋይዳ ምን እንደሚመስል ዘርዘር ያሉ ገለጻዎችን  አቅርቧል፡፡

በመቀጠልም ታላቁ የበረከት አባት ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ  በወጣት ከተማ የአንድነቱ ፀሐፊ  አቅራቢነት ለደረጃ ተማሪዎች የካርድና ሽልማት የሰጡ ሲሆን ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ  የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

የመርሀግርብሩን ሙሉ ፎቶ ያግኙ👇👇👇
https://t.me/felegetibebimage

#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
ጳጉሜ 2016 ዓ.ም
በደብረዘይት ደብረመዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የመልአኩ የቅዱስ ራጉኤል ክብረ በዓል እና የአዲስ ዓመት ክብረበዓልን ተከበረ።

መስከረም 01/2017 ዓ.ም
#FTM
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
በ2016 ዓ.ም በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ህፃናት ክፍል እና ትምህርት እና ስልጠና ክፍል ለተከታታይ 3ወራት ለ2017 ዓ.ም በአለማዊ የትምህርት ዙሪያ ተማሪዎችን ብቁ እና ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለማድረግ ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ መርሀግብሩን ያደረገ ሲሆን በመርሀግብሩላይም ላስተማሩ መምህራን የምስጋና ሰርተፍኬት እና ከየክፍሉ ከ1እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ይህ የጥናት እና የትምህርት መርሀግብር ከመንፈሳዊ ትምህርት ጎን ለጎን ከህፃናት ወላጆች ጋር በመወያየት በበጋ ወቅትም ለማስቀጠል ስራ ላይ እንደሚገኝ ክፍሉ አሳውቅዋል።

በዚህ መርሀግብር ላይ ሲሳተፍ የነበሩ ተማሪዎች ከ4ኛ እስከ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውን ክፍሉ የገለፀ ሲሆን እንደዚህ ያሉ መርሀግብሮች ይበሉ ይቀጥሉ በማለት አስተያየታችንን እንገልፃለን ።

መልካም የትምህርት ዘመን
መስከረም 12/2017 ዓ.ም
ደብረዘይት /ቢሾፍቱ

#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ የፈለገ ጥበብ የዲጂታል ሚዲያን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ🙏🙏🙏

👉ዩቲዩብ (Youtube)

👉ቲክቶክ (Tiktok)

👉ኢኒስታግራም (Instagram)

👉ፌስቡክ (Facebook)

👉ቴሌግራም (Telegram)
በ2017 ዓ.ም የአዳዲስ አባላት ቅበላ ተደረገ። በመርሀግብሩላይም የትምህርተወንጌል ፣መዝሙር፣የኪነ ጥበብ ፣የፀበል ፃዲቅ መርሀግብር የተካሄደ ሲሆን በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ምክትል ሰብሳቢ ወጣት ተሾመ ዳባ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና የሰንበት ት/ቤቱ ህገ ደንብ በጥቂቱ የአንድ አባል መብትና ግዴታን በተመለከተ አጭር መክዕክት ያስተላለፈ ሲሆን በመጨረሻም የሰንበት ት/ቤቱ አባላት ክትትል እና ግንኙነት ክፍል ሰብሳቢ በሆነው አቶ ተሸመ ደስታ በቀጣይ የገብትን አባላት በመመዝገብ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ በጥቂቱ በመግለፅ መርሀግብሩ በፀሎት ተዘግትዋል።

በተያያዘ በ2017 ዓ.ም የአዳዲስ አባላትም ይሆን የነባር አባላት የትምህርት በመስከረም 19 በሰንበት ትምህርት ቤቱ በሁሉም መርሀግብሮች ( በህፃናት እና ወጣቶች) የሚጀምር ሲሆን
የህፃናት (ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል አዳዲስ አባላትን ጨምሮ) እሁድ ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:00 ትምህርታቸው የሚሰጥ ሲሆን

የወጣቶች (ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዳዲስ አባላትን ጨምሮ) ከ ቀኑ 7:00 - 10:00 ሰዓት የሚሰጥ ይሆናል።

አዳዲስ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ የተቀላቀላችሁ አባላት እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን በዛሬው መርሀግብር ላይ ያልተሳተፋችሁ ነገር ግን መማር የምትፈልጉ ምዕመናል መስከረም 19 ለመማር በመምጣት በዚያውም ምዝገባውን ማካሄድ አደንደምትችሉ በደስታ እንገልፃለን።


መስከረም 12/2017 ዓ.ም

#ፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ የፈለገ ጥበብ የዲጂታል ሚዲያን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ🙏🙏🙏

👉ዩቲዩብ (Youtube)

👉ቲክቶክ (Tiktok)

👉ኢኒስታግራም (Instagram)

👉ፌስቡክ (Facebook)

👉ቴሌግራም (Telegram)
በ2016 ዓ.ም የደብረዘይት ደብረመዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ከደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ለ3ወራ ሲያስተምሯቸው የነበሩትን የክረምት ኮርስ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ ጉባኤ ላይ ያስመረቀ ሲሆን በመርሀግብሩላይም ታላላቅ ሰባኪያነ ወንጌል ፤ መዘምራን እና አባቶች የተካፈሉ ሲሆን በኮርሱ ላይም ለተሳተፍ ተማሪዎች የሰርተፍኬን መስጠት መርሀግብር እና በ3ቱም ዙሮች ላይ ከ1 እስከ 3 ለወጡ ተማሪዎች የስጦታ መርሀግብር የነበረ ሲሆን ላስተማሩ መምህራንም ከተማሪዎች ስጦታ በማበርጀት በአበርክተዋል።

እንደዚህ አይነት መርሀግብሮች ይበሉ ይቀጥሉ በማለት የፈለገ ጥበብ የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ህንኙነት ክፍል በማለት ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

መልካም የአገልግሎት ጊዜ

መስከረም 12/2016 ዓ.ም
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ የፈለገ ጥበብ የዲጂታል ሚዲያን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ🙏🙏🙏

👉ዩቲዩብ (Youtube)

👉ቲክቶክ (Tiktok)

👉ኢኒስታግራም (Instagram)

👉ፌስቡክ (Facebook)

👉ቴሌግራም (Telegram)

👉የፎቶ ማህደር ቴሌግራም ቻናል