ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media
995 subscribers
8.92K photos
102 videos
110 files
1.38K links
ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።

#የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል
#FTM
Download Telegram
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳት #እናቶቻችን #አትናስያ_እና_ኢዮዸራቅስያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ #ቅድስት_አትናስያ ✞✞✞

=>የዚህች ቅድስት ሕይወት በብዛት የእግዚአብሔርን ቸርነትና የንስሃን ፍጹምነት የሚያሳይ ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ቅድስት አትናስያ ግብፃዊት ስትሆን የነበረችውም #መኑፍ በሚባል አውራጃ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ይህ ዘመን "ዘመነ ከዋክብት" ይባል ነበር:: ከቁጥር የበዙ ቅዱሳንም በዘመኑ ነበሩ::

+ቅድስት አትናስያም ከክርስቲያን ወላጆች ተወልዳ: እንደሚገባ አድጋ: ገና በወጣትነቷ ሁለቱም ወላጆቿ ሞቱባት:: ነገር ግን ብዙ ሃብት ትተውላታልና ምን እንደምታደርገው ሃሳብ ሆናት:: #መንፈስ_ቅዱስ ግን መልካሙን ሕሊና አደላትና አብርሃማዊ ሥራን ለመሥራት ቆረጠች::

+መጀመሪያ አገልጋዮችን አዘጋጀች:: እንደየ ወገኑ ለእንግዶችና ለነዳያን ቤትን ሠራች:: በጐውን እድል መርጣለችና ለብዙ ዓመታት ለነዳያን በማድላት: እንግዶችን በመቀበል ተጠመደች:: በዚህ ሥራዋም እግዚአብሔርንም ሰውንም ደስ አሰኘች::

+ግብሯ እንዲህ ነው:: በሌሊት ጸሎት: በመዓልት ግን እንግዶችን መቀበል: እግር ማጠብ: ማስትናገድ: ማስተኛት: ስንቅ አሰንቆ መስደድ ነው:: በዚህ ግብሯ ከምንም በላይ የወቅቱን ጻድቃን አስደስታለች::

+በዚያው ልክ ግን ዲያብሎስ ተቆጥቶ ይከተላት ጀመር:: በብዙ ጐዳና አልሳካልህ ቢለውም በክፉ ጐረቤቶቿ አማካኝነት ግን ተሳካለት:: የአካባቢዋ ሰወች ወደ እርሷ ተሰብስበው በብዙ ማታለል ከቅድስና ሕይወቷ ፈቀቅ እንድትል አደረጉ::

+እነርሱ መልካም ሥራዋን ያስተዋት በመልክ ቆንጆ ነበረችና ይህንን ተጠቅመው ነው:: "ውበትና ሀብትሽን አታባክኚ" ብለው ከጐዳና አስወጧት:: መጽሐፍ ክፉ ባልንጀርነትን የሚቃወመው ለዛ ነው:: መልካም #ክርስቲያን ማለት ባልንጀራውን የሚመርጥ ነው::

+የሚገርመው ያን ያህል እንግዳ ተቀብላበት ያላለቀ ገንዘብ አሁን ግን ተመናመነ:: ክፉዎቹ ምክራቸውን ቀጠሉ:: አካሏን እንድትሸጥ አሳምነው ሴተኛ አዳሪ አደረጉዋት:: ባንዴ ከዚያ የቅድስና ከፍታ ወርዳ አካሏን ለዝሙት የምትሸጥ ሆነች::

+ነገሩን የሰሙ ገዳማውያን ሁሉ አዘኑ: አለቀሱላት:: ይልቁኑ ለእነሱ የእናት ያህል ደግ ነበረችና ከዲያብሎስ ሴራ ሊታደጉዋት ቆረጡ:: ከመካከላቸውም #ቅዱስ_ዮሐንስ_ሐጺርን ለዚህ ተግባር መረጡ:: እርሱ በአጋንንት ላይ ስልጣን ያለው ሰው ነውና::

+እነርሱ ሱባ዗ ይዘውላት አባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ መኑፍ ከተማ ሔደ: ወደ ቤቷም ደረሰ:: ጠባቂዋን አስፈቅዶ ሲገባ ለረከሰው ድርጊት የመጣ ሰው መስሏት ተዘጋጅታ ነበር:: አባ ዮሐንስ ሐጺር ግን አጋንንትን ያርቅ ዘንድ እየዘመረ ገባ::
"እመኒ ሖርኩ ማዕከለ ጽላሎተ ሞት . . . በሞት ጥላ ሥር እንኩዋ ብሔድ አንተ ከኔ ጋር ነሕና ክፉን አልፈራም" እያለ ቀረባት:: (መዝ. 22)

+ፈጠን ብሎ ከጐኗ ተቀምጦ ቅዱሱ ምርር ብሎ አለቀሰ:: አትናስያ ደንግጣ "ምነው?" አለችው:: "የአጋንንት ሠራዊት በራስሽ ላይ ሆነው እየጨፈሩኮ ነው" አላት:: አስከትሎም አጋንንቱን በጸሎቱ ቢያርቅላት በአንዴ ወደ ልቧ ተመለሰች::

+ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው የሠራችውን ሁሉ ማመን አቃታት:: ተስፋም ቆረጠች:: ቅዱስ ዮሐንስ ግን "ግዴለሽም: ንስሃ ግቢ:: ፈጣሪ ይምርሻል" ብሎ አሳመናት:: "እሺ አባቴ" ብላ ከቀደመው ዘመን ሥርዓት ያለውን አንዱን ቀሚስ ለብሳ: ጫማ ሳትጫማ: ሌላ ልብስ ሳትደርብ: ምንም ነገር ሳትይዝ ከቤት ወጣች::

+ቤቷን አልዘጋችም:: ዘወር ብላ ወደ ሁዋላም አልተመለከተችም:: ቅዱሱን ተከትላ ጉዞ ወደ በርሃ ሆነ:: ያ በእንክብካቤ የኖረ አካል እሾህና እንቅፋት: ብርድና ፀሐይ ጐበኘው:: ሲመሽ እጅግ ደክሟታልና "እረፊ" ብሏት ሊጸልይ ፈቀቅ አለ::

+መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ #መላእክት ከሰማይ የብርሃን ዓምድ ዘርግተው አንዲትን ነፍስ በዝማሬ ሲያሳርጉ አየ:: "የማን ነፍስ ትሆን" ብሎ ወደ #አትናስያ ሲሔድ መሬት ላይ ዘንበል ብላ ዐርፋ አገኛት:: ቅዱሱም "ጌታ ሆይ! ምነው ለንስሃ እንኩዋ ብታበቃት?" ብሎ አለቀሰ::

+ፈጣሪ ከሰማይ ተናገረ:- "ገና ከቤቷ ተጸጽታ ስትወጣ ነው ይቅር ያልኩዋትና ደስ ይበላችሁ" አለው:: ይህንን የአምላክ ቃል ሁሉም ገዳማውያን ሰምተው እጅግ ደስ አላቸው:: "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: 7 ጊዜ ይነሳል::"

+"+ #ቅድስት_ኢዮዸራቅስያ ድንግል +"+

=>ይህቺ ቅድስት እናት የ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ስትሆን ወደ ምናኔው የገባችው ገና በ6 ዓመቷ ነው:: አባቷ ገና በልጅነቷ የሞተባት ኢዮዸራቅስያ ከእናቷ ጋር ለሥራ ወደ ግብፅ ገዳማት ይሔዳሉ:: በዚያ #ደናግል ጌታችንና እመቤታችንን ሲያገለግሉ ተመልክታ ተደነቀች::

+ምክንያቱን ብትጠይቃቸው ስለ ሰማያዊ ተስፋ ነገሯት:: የሰማችው ነገር ቢመስጣት እዚያው ገዳም ውስጥ መኖርን መረጠች:: እናት ሥራቸውን ሲጨርሱ "እንሂድ" ብትላትም ያቺ የ6 ዓመት ብላቴና "እኔ ከእንግዲህ የክርስቶስና የድንግል እናቱ ንብረት ነኝና የትም አልሔድም" አለቻት::

+እናት የሕጻን ልጇን ነገር ሰምታ "ልጄ! አንቺ ያልፈለግሺው ዓለም ለእኔስ ምን ይሰራልኛል?" ብላ እርሷም እንደ ልጇ ገዳሙ ውስጥ ቀረች:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላም እናት ታማ ዐረፈች:: ቅድስት ኢዮዸራቅስያም ንጹሕ ተጋድሎዋን ቀጠለች::

+ትዕግስት: ትሕትና: ፍቅር: ደግነትና ታዛዥነት በእርሷ ሕይወት ላይ በዝተው መገለጥ ያዙ:: እህል የምትቀምሰው በ7 ቀን አንዴ ብቻ ሆነ:: ለጸሎት ስትቆምም እስከ 40 ቀናት በተመስጦ ትቆይ ነበር:: ያቺ ብላቴና ሰይጣንን ከነ ሠራዊቱ አሳፍራዋለችና ታገላት::

+በዱላና በመጥረቢያ ሳይቀር ይመታት ነበር:: እርሷ ግን ታገሰችው:: እጅግ ብዙ ድውያንን ከመፈወስ ደርሳ ድንቅ ተአምራትን ሠራች:: በዚህች ቀንም ዐርፋ ለክብረ መንግስቱ በቃች:: ድንግል #ኢዮዸራቅስያ ለገዳሙ ሞገስ ነበረችና በዕረፍቷ ታላቅ ሐዘን ተደረገ::

=>የቅዱሳት አንስት አምላክ ከንጽሕናቸው: ትጋታቸውና ማስተዋላቸው በረከትን ይክፈለን::

=>ነሐሴ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አትናስያ ቡርክት
2.ቅድስት ኢዮዸራቅስያ ድንግል
3.ቅዱስ ዴሚና ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ:: +"+ (1ጢሞ. 1:15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/felegetbebmazkenat
††† እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን #አባ_አብርሃም: #ቅዱስ_ዮሐንስ እና #አባ_ፊልዾስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† #አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ †††

=>ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::

+ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::

+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ:: በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::

+አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::

+ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው:: ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::

+ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ ውጪም ጣሉት::

+እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::

+ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::

+የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም ለመኑት::

+ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም #በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ (#ስብሐት_ብጡል) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::

+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::

+ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ:: በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ:: ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::

+በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::

+ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት:: ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::

+በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ ኑሯል::

+በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

††† #ቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅ †††

=>ይህ ቅዱስ የነበረው በዘመነ ሰማዕታት ቢሆንም እንደ ሰማዕታት ስቃይ አልደረሰበትም:: ክርስቲያኖችን እንዲገድሉና አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያቃጥሉ ከተመደቡ ወታደሮች አንዱ ነበረ:: ታዲያ እንዲገድላቸው የሚሰጡትን ክርስቲያኖች እየወሰደ ይደብቃቸው ነበር::

+የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ድረስም ይንከባከባቸው ነበር:: ሌሎች ወታደሮች እንዳይነቁበት ሁሌም "ክርስቲያኖችን በጣም እጠላለሁ" እያለ ያወራ ነበር:: እርሱ በሌሊት ሁሌም ለጸሎት ይተጋ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ኑሮም በዚህች ቀን በሰላም ዐርፏል::

††† #አባ_ፊልዾስ #ዘደብረ_ቢዘን †††

=>#ደብረ_ቢዘን በቀድሞ የኢትዮዽያ ክፍለ ሃገር (አሁን #ኤርትራ) ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ገዳም ነው:: ገዳሙ #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም በስደቷ ያረፈችበት: ጌታችን የባረከውና የመረጠው ቦታ ነው:: #አባ_ዮሐንስን: #አባ_ናርዶስንና ሌሎች ከዋክብት አበውን ያፈራ ሲሆን የአባ ፊልዾስን ያሕል ግን አልተገኘም::

+ጻድቁ በግል የተጋድሎ ሕይወታቸው: ገዳሙን በአበ ምኔትነት በመምራታቸውና በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ምስጉን ነበሩ:: እርሳቸው ቅዱስ ሆነው አልበቃቸውምና ብዙ ቅዱሳንን ወልደዋል:: ይሕች ዕለትም የዕረፍታቸው መታሰቢያ ናት::

=>አምላከ ጻድቃን ገዳማትን ከመከራ ይጠብቅልን:: ከአባቶቻችን ቅዱሳን ጸጋ በረከትንም ይክፈለን::

=>ነሐሴ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ አብርሃም ገዳማዊ
2.ቅድስት ማርያ እህቱ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ
4.አባ ፊልዾስ ዘደብረ ቢዘን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

=>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ. . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ 11:23)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/felegetbebmazkenat
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅድስት #እናታችን_ማርያም_መግደላዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ #ቅድስት_ማርያም #መግደላዊት ✞✞✞

=>ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ "መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት (ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:- በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::

+ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7 አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር:: በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::

+በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት አልዘገየችም::

+ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት::

+ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች:: እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::

ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::

+ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ #መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::

+እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን አልፈራችም:: ጌታችንም #ክእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ አደላት::

+በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን (#ሚካኤልና_ገብርኤልን) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም" አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::

+ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት:: "ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::

+#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን: #ትምሕርተ_ኅቡዓትን ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ አገልግሎት ነበራት::

+ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ ነበረች::

+እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል:: እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ ይመግባቸው ነበር::

+እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን #ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች:: ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና ግርፋትን ታግሳለች::

+በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ በቀር) ያከብሯታል::

+"+ #ቅድስት_ኢየሉጣ_ዘቂሣርያ +"+

=>በቀድሞው የግሪክ ግዛት (ቂሣርያ ውስጥ) በዘመነ ሰማዕታት አካባቢ የነበረችው #ቅድስት_ኢየሉጣ ክርስትናን የወረሰችው ከወላጆቿ ነው:: ገና ወጣት እያለች ወላጆቿ በማረፋቸው የሃብታቸው ወራሽ ሆነች::

+ነገር ግን አንድ ክፉ ሰው መጥቶ ሃብቷን ነጠቃት:: በዚህ አዝና "የዳኛ ያለህ" ልትል ወደ ፍርድ ቤት ስትሔድ የጠበቃት ግን የሚገርም ነበር:: የተገፋችው እርሷ ተከሳሽ: ገፊው ደግሞ ከሳሽ ነበር:: የክሱ ጭብጥ ደግሞ "ክርስቲያን ነሽ" የሚል ነበር::

+በወቅቱ በመኯንንቱ ፊት ክርስትናዋን ብትክድ በቀጥታ ሃብቷን ማግኘት ትችል ነበር:: እርሷ ግን ለአፍታ አሰበች:: "እንዴት ዘላለማዊ ሃብቴን (ሃይማኖቴን) በኃላፊው ንብረት እለውጣለሁ" ብላ ሁሉም እየሰሙ ጮክ ብላ "#ክርስቲያን_ነኝ" አለች::

+ወዲያውም ሞት ተፈርዶባት ተገደለች:: ታላቁ #ቅዱስ_ባስልዮስ ስለ #ሰማዕታት በጻፈው ድርሳን ላይ በስፋት አመስግኗታል:: ለሴቶችም ታላቅ ምሳሌ ናት ብሏታል::

=>ቅዱሳት እናቶቻችንን ያጸና ቸር አምላካቸው እኛንም በሃይማኖትና በምግባር ያጽናን:: ከበረከታቸውም አብዝቶ ያድለን::

=>ነሐሴ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ማርያም መግደላዊት (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት)
2.ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት (ዘቂሣርያ)
3.አባ ዊጻ (የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>+"+ #ጌታ ኢየሱስም:- "#ማርያም" አላት:: እርሷ ዘወር ብላ በእብራይስጥ:- "#ረቡኒ" አለችው:: ትርጉዋሜውም "መምሕር ሆይ!" ማለት ነው:: ጌታ ኢየሱስም:- "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ:: ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሔደሽ . . . ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው" አላት:: #መግደላዊት_ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይሕንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች:: +"+ (ዮሐ. 20:16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/felegetbebmazkenat
"፯/7 ምክሮች!"
#ቁ፩.
☞ለንስሃ ተዘጋጅ!
☞ወደ ቤተክርስቲያን ና!
☞ወገብህን/ሱሪህን ታጠቅ!
(13/09/2012)

#ቁ.፪
☞ነገርን ሁሉ በ3ቱ መሥፈርት ሳትመዝን አትቀበል፡-
#መጽሐፍ_ቅዱስ #አዋልድ_መጻሕፍት #ቅዱስ_ትውፊት

#ቁ.፫.
☞ቁጥር ለማብዛትም ሆነ፡ ምን አለበት ብለህ መቼም ቢሆን ከመናፍቃን ጋር አትተባበር፡፡
እነርሱ ካሉ እግዚአብሔር ይለይሃልና!

#ቁ.፬
☞ምንም ነገርን ከመቀበልህ፡ ከመንቀፍህና ከመደገፍህ በፊት፡-
እንደ #ክርስቲያን ለፈጣሪህ ንገር!
እንደ #ሰው አገላብጠህ መርምር!
ቁ.፭
☞ከእግዚአብሔር እና የርሱ ከሆኑት በቀር ፈጽመህ ምስጢርህን አትግለጽ!
ኋላ ተወግተህ የምትሞተው ባወጣኸው ምስጢር፡ አመንኩትም ባልከው ሰው ነውና!

ቁ.፮
#የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ትጠብቅ/ታስጠብቅም ዘንድ ቸል አትበል!
አጥሩ ከፈረሰ ቤቱም መፍረሱ፡ መዘረፉም አይቀርምና!

ቁ.፯
☞በሰማይ ካለው እግዚአብሔርና ወዳጆቹ በቀር በሥጋ ለባሽ አትታመን! አትከተለው!
አታድንቀው!
አታምልከው!

@Re (14/09/2012)
DnYordanos Abebe

Re post13/09/2014
እንኳን ለጾመ ሐዋርያት አደረሳችሁ አደረሰን።

ጦምን ለመሻር ጥቅስ አያስፈልግም

☞አንዳንድ ሰዎች ሕግን ለመጣስ: ጦምን ለመሻር: ሥርዓቱንም ለማፍረስ ሲፈልጉ "ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ አያረክስም . . ." ዓይነት ያልተረዱትን ጥቅስ ይጠቅሳሉ:: ወይም ደግሞ ለጾም "የሽማግሌ": "የቄስ": "የመነኮስ": "የሕጻን" . . . የሚል ስምን ይለጥፋሉ::

+ግንኮ! . . . ሕግን ለመጣስ ከሕግ መጽሐፍ ባልተገባ መንገድ መጥቀስ አያስፈልግም:: ጦመንም ለመሻር የማታለያ ምክንያቶችን መደርደር ግብዝ (አላዋቂ) ቢያሰኝ እንጂ ሌላ ትርፍ አይኖረውም::

ለምሳሌ:-

☞አንድ ሰው ሒሳብ (Mathematics) ትምሕርት "ይከብደኛል: አልችለውም . . ." ከፈለገም "አልማርም" ሊል መብቱ አለው:: "የሒሳብ ትምሕርት አያስፈልግም: አይጠቅምም" ሊል ግን ፍጹም አይችልም:: (ቢልም አላዋቂነቱን ይገልጣል)

+እንደዚሁም ሁሉ አንድ ሰው "መጾም ይከብደኛል: አልችልም . . ." ከፈለገም "አልጾምም" ሊል ይችላል:: (እንዲህ ብሎ ክርስቲያን መሆን ባይችልም)

+ምክንያቱም እንኩዋን ምግባራት አምልኮም ቢሆን በፈቃድ (በነጻነት) የሚፈጸም ጉዳይ ነውና:: #እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነውና ማንንም አያስገድድም::

+ነገር ግን . . . ያ ሰው "ጾም ይከብደኛል: አልጾምም . . ." ለማለት መብቱ ቢኖረውም "ጾም አያስፈልግም" ሊል ግን መብቱ ሊኖረው አይችልም:: (ቢልም የሰይጣን የግብር ልጅ ከመሆን ሌላ ትርፍ አይኖረውም)

+ሰው (በተለይም #ክርስቲያን) ለድኅነት: ለበጐነትና #ለቅድስና ይጠቅሳል: ምክንያትንም ይፈጥራል እንጂ #ቅዱስ_ቃሉን እያጣመመ የጥፋትን መንገድ አይጠርግም::

+እኛ ግን:-
¤#ነቢያትን (ዘጸ. 24:18, ዘዳ. 9:9, 1ነገ. 19:8, ዳን. 10:2, መዝ. 108, 109:24)
¤#ሐዋርያትን (ሐዋ. 13:2)
¤#ጻድቃን_ሰማዕታትን: #ደናግል_መነኮሳትን (#ገድላተ_ቅዱሳን) . . . አብነት አድርገን ለድኅነት እንጦማለን::

+ይልቁኑ ግን ከክብር ባለቤት #ከመድኃኒታችን_ክርስቶስ አብነትን ነስተን (ማቴ. 4:1): ትምሕርቱን ሰምተን: ለሕይወት እንጦማለን:: "ስትጦሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ" እንዳ ለጌታችን:: (ማቴ. 6:16)

=>#ቸር_አምላከ_ቅዱሳን መዋዕለ ጦሙን #የበረከትና_የአኮቴት ያድርግልን::

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

☞ትድረስ ለሰሜናውያን ክርስቲያኖች!

❖ከየኔታ (መምህር) ገብረ መድኅን እንየው

"በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።" (ኤፌ 4፥3)

አክሱም ጽዮን መሳለም እና ክርስቲያን ወገኖቸን ማየት ናፍቆኛል።በሕይወት ያሉት መጠየቅ ለረፉት ማልቀስ ይገባኛል።
ደብረ ዳሞም ናፍቆኛል በገመዱ ተንጨዋልየ ወጥቸ የማገኘው በረከት ናፍቆኛል ።ሁሉም የበረከት እና የታሪክ ቦታዎች ገዳማት ናፍቀውኛል።እናንተስ??ግሸን፣ ላሊበላ..መጥታችሁ አብረን ታቦቱን ስናከብር ባንዲት ቅዳሴ አሜን ስንል ትዝ አይላችሁም??
የማውቃቸውም በስም የማላውቃቸውም ኦርቶዶክሳውያን ናፍቀውኛል። በቃ የሆነውን ሳስበው ልቤን ያርደኛል።ይህንን ስጽፍ እያለቀስሁ ነው።
ሰሜናውያን ወንድሞቸ እህቶቸ ያረፋችሁ ነፍሳችሁን ይማር ፦ በሕይወት ያላችሁ እደምን አላችሁ???
ከአሁን በፊት በሥሁት ፖለቲካ ሊሆን የማይገባው ሁኗል።
ይሁንም እንጂ እስከ አሁን ከሆነው ወደፊት የሚሆነው ይበልጣል። አሁንም በሥሁት ፖለቲካ መጋደል ነው የሚሻለው???
መፍትሄው ግን ከራሳችን ነው።
ምን አልባትም መረዳት ካልቻልን ከሁለት አሥርታት ዓመታት በኋላ በምሥራቅ አፍሪክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ላይኖር ይችላል።የላይ ፈሪ የታች ፈሪ እያላችሁ ማዶ እና ማዶ ሁናችሁ ክርስትና እንዳይኖር ነው የምትፈልጉት???
ዋዜማው የሚሸተው እና የሚያሳየው እንደዚያ ነው።
ለዚህ ደግሞ ብዙ መማር አይጠይቅም የምናየው እና የምንሰማው ብቻ ሊሆን የታሰበውን ይነግረናል።
በተለይም ሰሜኑ ክፍል የትናንት መሠረት የታሪክ እንብርት እንደመሆኑ መጠን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ አይፈለግም።መከራው የጠናበትም አንዱ ለዚህ ነው።

#መፍትሄ አንድ፦
#ክርስቲያን መሆን፦ መምሰል ሳይሆን መሆን መሆን መሆን፦ኦርቶዶክስ ስንሆን፦የአንድ ግንድ ቅርንጫፎች እንሆናለን፣አንድ አካል ህዋሳት እንሆናለን፣የአንድ መስቀል ተሸካሚዎች እንሆናለን፣የአንድ ማህፀነ ዮርዳኖስ ልጆች እንሆናለን፣አንድ ሰርግ ቤት ተጠርተን እንዴት እንባላለን? እንኳን ለምድራዊ መሬት ገና በሰማይ ተስፋ አለን ብለን እንጠብቅ የለምን??

#መፍትሄ ሁለት፦
የሥሁት ፖለቲካ መርዝን መትፋት። ኋላ ቀር የዘር ፖለቲካ የለከፈው አእምሮ ክርስቲያናዊ ሀሳብ ማሰብ አይችልምና።ይሄ መርዘኛ ተንኮል አሳነሰን እነጂ አላበዛንም። አዋረደን እንጂ አላከበረንም ።አስኮነነን እንጂ አላጸደቀንም።በታተነነን እንጂ አላዋሐደንም።በኦርቶዶክሳዊት ልብ መግባባት፦በዐይን ጥቅሻ በከንፈር ንክሻ መናበብ ይጠበቅብናል፡፡

#በየግላችን የሰማነውን፣የተባለውን፣የተማርነውን ሥሁት ሀሳብ አውልቀን መጣል እና በኦርቶዶክሳዊነት መሙላት።
በእግዚአብሔር አምሳል መሳል ሁነን መሥራት።
የሚሠራ ሰው ከአንድ የግል ፍላጎት ሰይጣን ጋር ይዋጋል።
የማይሠራ ሰው ግን ከሺህ የፍትወት ሰይጣናት ጋራ ይዋጋል።

#መፍትሄ ሦስት፦
ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ህዝባዊ መፍትሄ መፈለግ፦በዓላማ ያጋደሉን ፍጹም ዕርቅ አያመጡልንም።
በትርክት ጅራፍ እየተጋረፍን መፍትሄ አይመጣም ኦርቶዶክሳዊነት ግን እውነት እና ሕይወት መፍትሄም ነው።

#መፍትሄ አራት፦
ገዳማዊ እና ሊቃውንታዊ መፍትሄን መጠቀም፦
ከሥሁት ፖለቲካ የተላቀቁ በገዳም ያሉ አባትች እና ሰላማውያን የቤተ ክርስቲያን መምህራን በፊት ቢቀድሙልን የተሻለ ነው።
የተሰበረ የእውነት ልብን ማግኘት አለብን እና ሁነው እንድንሆን የሚያደርጉን፣በጸሎት የሚያጸድቁ በትምህርታቸው የሚያስታርቁን ከፊት ይቅደሙን።

#መፍትሄ አምስት፦
ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በተለይም በሰሜኑ ያለን፣በሀገር ውስጥ እና በሀገር ውጭ ያለን የሚድያ አንድነት መፍጠር፦ መንፈሳዊነታችንን መንፈስ ማድረግ ይጠበቅብናል።
አብዛኛውን የጥላላቻው መርዝ የሚረጨው በሚድያ ስለሆነ አንቲ ባይረስ ሁነን ማስቀረት ይቻላል።

#መፍትሄ ስድስት፦
በሆነው ልክ ለመፍትሄ መሆን፦
መፍትሄው በተዘረጋው ልክ መዘርጋት። በረዘመው ልክ መርዘም።በሥሩ ልክ ሥር መስደድ።
ይበለጠው ግን፦ትንሽ መናገር ።ብዙ መሥራት ነው።
የነፋስ መንፈስ፣የውኀ መፍሰስ፣የብርሃን መመላለስ...የማይከለክለው ኦርቶዶክሳዊ ተግባር።

#መፍትሄ ሰባት፦
እያንዳንዳችን የቤተ ክርስቲያን ችግር ከመሆን መዳን።
የችግራችን ይበልጡን ችግሮች እኛው ነን ። ሌላው በክርስቲያናዊ አንድነታችን ላይ በሴራ ቢሠራ ለዓላማው ነው ። እኛው ግን የምንታረድበትን ቢላዋ እየላስን ነው ችግር የሆነው።
ከሥሁታን መነጠል እና ለመፍትሄ ራሳችንን መስጠት
ችግር ለመፈታፍታት ብለው ራሳቸዉ ችግር የሆኑ ብዙዎች አሉና።
ከአእላፋት ቅዱሳን ኅብረት ጋር እየኖሩ ባዶነት ጽኑ ደዌ ነው።

#መፍትሄ ስምንት
በገባን እና ሊሆን በሚገባው ልክ አሁን ጀምረን መሥራት
ከኦርቶዶክሳውያን ኅብረት መከራ ይልቅ የአልጋ ቁራኛ የደዌ ዳኛ መሆን ይቀላል፡፡
በጽኑ ቆስለናል ።፦ቁስሉም ፈውስ ይፈልጋል ፡፡ ፈውሱም ከአምላካችን እና ከእኛ ብቻ ነው ያለው፡፡
ቁጭ ብሎ ከማንጋጠጥ ለፈውስ መላላጥ ይሻላል፡፡
ችጥሩ አቆሰለን እኛ ግን በዚያው ቆስለን መቅረት የለብንም ፡፡
ቁስላችንንን ለመድኃኒት፦
ምታችንን ለትንሣኤ ፦
መገፋፋታችንን ለእረፍት፦እናድርገው።
ግድ ችግሬን አርቁልኝ አይባልም እንዲርቅ ሠርቶ መገኘት።
መሆን ያለብንን ሳንሆን መሆን ያለበት እንዲሆንልን የምንፈልገው አንድነት አይሆንምና፡፡

#መፍትሄ ዘጠኝ፦
በዚህ ውስጥ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ፦
1.አንድ ሃይማኖት ያለው መሆን አለበት
2.ለአንዲት ሃይማኖቱ ዕውቀት ያለው መሆን አለበት
3.ለኦርቶዶክሳዊት ዕውቀቱ መረዳት ያለው መሆን አለበት
4.በክርስቲያናዊ መረዳቱ ላይ እምነት ያለው መሆን አለበት
5. በኦርቶዶክሳዊ እምነቱ ላይ ተግባር ያለው መሆን አለበት
6.በኦርቶዶክሳዊት ቅዱስ ተግባሩ ላይ ኅብረት ያለው መሆን አለበት
7.በኦርቶዶክሳዊት አሀቲ ኅብረቱ ላይ ለትውልድ የሚተርፍ ዓለማ ያለው መሆን አለበት
8.በኦርቶዶክሳዊት ዓላማው ላይ የመንግሥተ ሰማይ ተስፋ ያለው መሆን አለበት
9.በሰማያዊት ተስፋው ላይ የጸጋ ውሕደት ያለው መሆን አለበት
10.በጸጋ ውሕደቱ አንድ አድራጊ የሁሉም ህሊና መዳረሻ ተዋሕዶተ መንፈስ ቅዱስን የሚናፍቅ መሆን አለበት።
ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ድርሻን ለመወጣት በቅድሚያ በዓላማው አካል መሆን ይጠይቃል።
ለሌላው መትረፍ የሚቻለው መሆን ባለብን መጠን ስንከዎን ነው።
ነው።

#መፍትሄ አሥር፦
ዋናው የሁሉም መፍቻ የማይረሳው።፦ኦርቶዶክሳዊ ኅብረት፦
የኦርቶዶክሳዊነት መገለጫው መንፈሳዊ ህብረት ነው። ኅብረቱም ረቂቅ ኅብረት ነው። አካሉ አንድ ህዋሱ ብዙ የሆነለት
የግዘፍ ህብረት ቢሆን ኑሮ ነፋስ በየት በነፈሰ ውኀ በየት በፈሰሰ ነበር። ክርስቶስ የገነባው ይሄን ኅብረት ነው።
አንድ መንፈስን ተዋህደን ነው ማኅበር የሆነው።ግለኝነት የካፒታሊዝም ሥርዓት ነው።የህብረት ማሳያው መለያው ፍቅር ነው።ዓለምን በክርስትና የሠራት ያ ህብረት ነው፡፡መንፈሳዊ ኅብረት የመንፈስ ስበት ነው፡፡በኅብረት ቢጸልዩ ጸሎቱ እግዚአብሔርን ይቀሰቅሳል፡፡በኅብረት ቢሠሩ ለውጥ ይመጣል፡፡
እንኳን ለጾመ ሐዋርያት አደረሳችሁ አደረሰን።

ጦምን ለመሻር ጥቅስ አያስፈልግም

☞አንዳንድ ሰዎች ሕግን ለመጣስ: ጦምን ለመሻር: ሥርዓቱንም ለማፍረስ ሲፈልጉ "ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ አያረክስም . . ." ዓይነት ያልተረዱትን ጥቅስ ይጠቅሳሉ:: ወይም ደግሞ ለጾም "የሽማግሌ": "የቄስ": "የመነኮስ": "የሕጻን" . . . የሚል ስምን ይለጥፋሉ::

+ግንኮ! . . . ሕግን ለመጣስ ከሕግ መጽሐፍ ባልተገባ መንገድ መጥቀስ አያስፈልግም:: ጦመንም ለመሻር የማታለያ ምክንያቶችን መደርደር ግብዝ (አላዋቂ) ቢያሰኝ እንጂ ሌላ ትርፍ አይኖረውም::

ለምሳሌ:-

☞አንድ ሰው ሒሳብ (Mathematics) ትምሕርት "ይከብደኛል: አልችለውም . . ." ከፈለገም "አልማርም" ሊል መብቱ አለው:: "የሒሳብ ትምሕርት አያስፈልግም: አይጠቅምም" ሊል ግን ፍጹም አይችልም:: (ቢልም አላዋቂነቱን ይገልጣል)

+እንደዚሁም ሁሉ አንድ ሰው "መጾም ይከብደኛል: አልችልም . . ." ከፈለገም "አልጾምም" ሊል ይችላል:: (እንዲህ ብሎ ክርስቲያን መሆን ባይችልም)

+ምክንያቱም እንኩዋን ምግባራት አምልኮም ቢሆን በፈቃድ (በነጻነት) የሚፈጸም ጉዳይ ነውና:: #እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነውና ማንንም አያስገድድም::

+ነገር ግን . . . ያ ሰው "ጾም ይከብደኛል: አልጾምም . . ." ለማለት መብቱ ቢኖረውም "ጾም አያስፈልግም" ሊል ግን መብቱ ሊኖረው አይችልም:: (ቢልም የሰይጣን የግብር ልጅ ከመሆን ሌላ ትርፍ አይኖረውም)

+ሰው (በተለይም #ክርስቲያን) ለድኅነት: ለበጐነትና #ለቅድስና ይጠቅሳል: ምክንያትንም ይፈጥራል እንጂ #ቅዱስ_ቃሉን እያጣመመ የጥፋትን መንገድ አይጠርግም::

+እኛ ግን:-
¤#ነቢያትን (ዘጸ. 24:18, ዘዳ. 9:9, 1ነገ. 19:8, ዳን. 10:2, መዝ. 108, 109:24)
¤#ሐዋርያትን (ሐዋ. 13:2)
¤#ጻድቃን_ሰማዕታትን: #ደናግል_መነኮሳትን (#ገድላተ_ቅዱሳን) . . . አብነት አድርገን ለድኅነት እንጦማለን::

+ይልቁኑ ግን ከክብር ባለቤት #ከመድኃኒታችን_ክርስቶስ አብነትን ነስተን (ማቴ. 4:1): ትምሕርቱን ሰምተን: ለሕይወት እንጦማለን:: "ስትጦሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ" እንዳ ለጌታችን:: (ማቴ. 6:16)

=>#ቸር_አምላከ_ቅዱሳን መዋዕለ ጦሙን #የበረከትና_የአኮቴት ያድርግልን::

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳት #እናቶቻችን #አትናስያ_እና_ኢዮዸራቅስያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ #ቅድስት_አትናስያ ✞✞✞

=>የዚህች ቅድስት ሕይወት በብዛት የእግዚአብሔርን ቸርነትና የንስሃን ፍጹምነት የሚያሳይ ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ቅድስት አትናስያ ግብፃዊት ስትሆን የነበረችውም #መኑፍ በሚባል አውራጃ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ይህ ዘመን "ዘመነ ከዋክብት" ይባል ነበር:: ከቁጥር የበዙ ቅዱሳንም በዘመኑ ነበሩ::

+ቅድስት አትናስያም ከክርስቲያን ወላጆች ተወልዳ: እንደሚገባ አድጋ: ገና በወጣትነቷ ሁለቱም ወላጆቿ ሞቱባት:: ነገር ግን ብዙ ሃብት ትተውላታልና ምን እንደምታደርገው ሃሳብ ሆናት:: #መንፈስ_ቅዱስ ግን መልካሙን ሕሊና አደላትና አብርሃማዊ ሥራን ለመሥራት ቆረጠች::

+መጀመሪያ አገልጋዮችን አዘጋጀች:: እንደየ ወገኑ ለእንግዶችና ለነዳያን ቤትን ሠራች:: በጐውን እድል መርጣለችና ለብዙ ዓመታት ለነዳያን በማድላት: እንግዶችን በመቀበል ተጠመደች:: በዚህ ሥራዋም እግዚአብሔርንም ሰውንም ደስ አሰኘች::

+ግብሯ እንዲህ ነው:: በሌሊት ጸሎት: በመዓልት ግን እንግዶችን መቀበል: እግር ማጠብ: ማስትናገድ: ማስተኛት: ስንቅ አሰንቆ መስደድ ነው:: በዚህ ግብሯ ከምንም በላይ የወቅቱን ጻድቃን አስደስታለች::

+በዚያው ልክ ግን ዲያብሎስ ተቆጥቶ ይከተላት ጀመር:: በብዙ ጐዳና አልሳካልህ ቢለውም በክፉ ጐረቤቶቿ አማካኝነት ግን ተሳካለት:: የአካባቢዋ ሰወች ወደ እርሷ ተሰብስበው በብዙ ማታለል ከቅድስና ሕይወቷ ፈቀቅ እንድትል አደረጉ::

+እነርሱ መልካም ሥራዋን ያስተዋት በመልክ ቆንጆ ነበረችና ይህንን ተጠቅመው ነው:: "ውበትና ሀብትሽን አታባክኚ" ብለው ከጐዳና አስወጧት:: መጽሐፍ ክፉ ባልንጀርነትን የሚቃወመው ለዛ ነው:: መልካም #ክርስቲያን ማለት ባልንጀራውን የሚመርጥ ነው::

+የሚገርመው ያን ያህል እንግዳ ተቀብላበት ያላለቀ ገንዘብ አሁን ግን ተመናመነ:: ክፉዎቹ ምክራቸውን ቀጠሉ:: አካሏን እንድትሸጥ አሳምነው ሴተኛ አዳሪ አደረጉዋት:: ባንዴ ከዚያ የቅድስና ከፍታ ወርዳ አካሏን ለዝሙት የምትሸጥ ሆነች::

+ነገሩን የሰሙ ገዳማውያን ሁሉ አዘኑ: አለቀሱላት:: ይልቁኑ ለእነሱ የእናት ያህል ደግ ነበረችና ከዲያብሎስ ሴራ ሊታደጉዋት ቆረጡ:: ከመካከላቸውም #ቅዱስ_ዮሐንስ_ሐጺርን ለዚህ ተግባር መረጡ:: እርሱ በአጋንንት ላይ ስልጣን ያለው ሰው ነውና::

+እነርሱ ሱባ዗ ይዘውላት አባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ መኑፍ ከተማ ሔደ: ወደ ቤቷም ደረሰ:: ጠባቂዋን አስፈቅዶ ሲገባ ለረከሰው ድርጊት የመጣ ሰው መስሏት ተዘጋጅታ ነበር:: አባ ዮሐንስ ሐጺር ግን አጋንንትን ያርቅ ዘንድ እየዘመረ ገባ::
"እመኒ ሖርኩ ማዕከለ ጽላሎተ ሞት . . . በሞት ጥላ ሥር እንኩዋ ብሔድ አንተ ከኔ ጋር ነሕና ክፉን አልፈራም" እያለ ቀረባት:: (መዝ. 22)

+ፈጠን ብሎ ከጐኗ ተቀምጦ ቅዱሱ ምርር ብሎ አለቀሰ:: አትናስያ ደንግጣ "ምነው?" አለችው:: "የአጋንንት ሠራዊት በራስሽ ላይ ሆነው እየጨፈሩኮ ነው" አላት:: አስከትሎም አጋንንቱን በጸሎቱ ቢያርቅላት በአንዴ ወደ ልቧ ተመለሰች::

+ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው የሠራችውን ሁሉ ማመን አቃታት:: ተስፋም ቆረጠች:: ቅዱስ ዮሐንስ ግን "ግዴለሽም: ንስሃ ግቢ:: ፈጣሪ ይምርሻል" ብሎ አሳመናት:: "እሺ አባቴ" ብላ ከቀደመው ዘመን ሥርዓት ያለውን አንዱን ቀሚስ ለብሳ: ጫማ ሳትጫማ: ሌላ ልብስ ሳትደርብ: ምንም ነገር ሳትይዝ ከቤት ወጣች::

+ቤቷን አልዘጋችም:: ዘወር ብላ ወደ ሁዋላም አልተመለከተችም:: ቅዱሱን ተከትላ ጉዞ ወደ በርሃ ሆነ:: ያ በእንክብካቤ የኖረ አካል እሾህና እንቅፋት: ብርድና ፀሐይ ጐበኘው:: ሲመሽ እጅግ ደክሟታልና "እረፊ" ብሏት ሊጸልይ ፈቀቅ አለ::

+መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ #መላእክት ከሰማይ የብርሃን ዓምድ ዘርግተው አንዲትን ነፍስ በዝማሬ ሲያሳርጉ አየ:: "የማን ነፍስ ትሆን" ብሎ ወደ #አትናስያ ሲሔድ መሬት ላይ ዘንበል ብላ ዐርፋ አገኛት:: ቅዱሱም "ጌታ ሆይ! ምነው ለንስሃ እንኩዋ ብታበቃት?" ብሎ አለቀሰ::

+ፈጣሪ ከሰማይ ተናገረ:- "ገና ከቤቷ ተጸጽታ ስትወጣ ነው ይቅር ያልኩዋትና ደስ ይበላችሁ" አለው:: ይህንን የአምላክ ቃል ሁሉም ገዳማውያን ሰምተው እጅግ ደስ አላቸው:: "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: 7 ጊዜ ይነሳል::"

+"+ #ቅድስት_ኢዮዸራቅስያ ድንግል +"+

=>ይህቺ ቅድስት እናት የ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ስትሆን ወደ ምናኔው የገባችው ገና በ6 ዓመቷ ነው:: አባቷ ገና በልጅነቷ የሞተባት ኢዮዸራቅስያ ከእናቷ ጋር ለሥራ ወደ ግብፅ ገዳማት ይሔዳሉ:: በዚያ #ደናግል ጌታችንና እመቤታችንን ሲያገለግሉ ተመልክታ ተደነቀች::

+ምክንያቱን ብትጠይቃቸው ስለ ሰማያዊ ተስፋ ነገሯት:: የሰማችው ነገር ቢመስጣት እዚያው ገዳም ውስጥ መኖርን መረጠች:: እናት ሥራቸውን ሲጨርሱ "እንሂድ" ብትላትም ያቺ የ6 ዓመት ብላቴና "እኔ ከእንግዲህ የክርስቶስና የድንግል እናቱ ንብረት ነኝና የትም አልሔድም" አለቻት::

+እናት የሕጻን ልጇን ነገር ሰምታ "ልጄ! አንቺ ያልፈለግሺው ዓለም ለእኔስ ምን ይሰራልኛል?" ብላ እርሷም እንደ ልጇ ገዳሙ ውስጥ ቀረች:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላም እናት ታማ ዐረፈች:: ቅድስት ኢዮዸራቅስያም ንጹሕ ተጋድሎዋን ቀጠለች::

+ትዕግስት: ትሕትና: ፍቅር: ደግነትና ታዛዥነት በእርሷ ሕይወት ላይ በዝተው መገለጥ ያዙ:: እህል የምትቀምሰው በ7 ቀን አንዴ ብቻ ሆነ:: ለጸሎት ስትቆምም እስከ 40 ቀናት በተመስጦ ትቆይ ነበር:: ያቺ ብላቴና ሰይጣንን ከነ ሠራዊቱ አሳፍራዋለችና ታገላት::

+በዱላና በመጥረቢያ ሳይቀር ይመታት ነበር:: እርሷ ግን ታገሰችው:: እጅግ ብዙ ድውያንን ከመፈወስ ደርሳ ድንቅ ተአምራትን ሠራች:: በዚህች ቀንም ዐርፋ ለክብረ መንግስቱ በቃች:: ድንግል #ኢዮዸራቅስያ ለገዳሙ ሞገስ ነበረችና በዕረፍቷ ታላቅ ሐዘን ተደረገ::

=>የቅዱሳት አንስት አምላክ ከንጽሕናቸው: ትጋታቸውና ማስተዋላቸው በረከትን ይክፈለን::

=>ነሐሴ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አትናስያ ቡርክት
2.ቅድስት ኢዮዸራቅስያ ድንግል
3.ቅዱስ ዴሚና ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ:: +"+ (1ጢሞ. 1:15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/felegetibebmedia