Addis info
1.41K subscribers
454 photos
7 videos
181 links
Download Telegram
ካልተለወጡ አይከፍሉም
ቦርጭ ላይ ተስፋ ከቆረጡ ኑ ወደ እኛ
በሶስት ወር ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ
0912653394
0949750496
0777720496
መልዕክት ብቻ ያስቀምጡ ይደርሰናል
👍1
ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ደረጃ መዘጋጀቱ ተነገረ 
 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስትም አስገዳጅነት ወደ ሀገር ቤት በብዛት እየገቡ ለሚገኙት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የደረጃ መለኪያ መስፈር መዘጋጀቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በርካታ ባለሙያዎች ወደሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወኪል አልባ ናቸዉ ከሚለዉ ጀምሮ ካለ መለኪያ መስፈርት የሚገቡ መሆናቸውን ሲናገሩ ይደመጣል። 
 
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በምን ደረጃ ላይ መገኘት አለባቸዉ የሚለዉን የሚመዝን ደረጃ ማዘጋጀቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ሰምቷል። በተጨማሪም የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑም ተገልጿል። 
 
በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሀይል መሙያ ማዕከላት የአተገባበር መመሪያ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሀይል መሙያ ማዕከላትን መላዉ ኢትዮጵያን የሚሸፍን ለማድረግ የቅድመ አዋጭነት ጥናት መደረጉንም ገልጸዋል። 
 
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሀይል መሙያ ለመገንባት ለሚያቅዱ ባለሃብቶችም ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የፕሮጀክት እቅድ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ይፋ አድረወገዋል። በአሁኑ ወቅትም ለ 162 የኤሌክትሪክ መኪና አስመጪዎች ፈቃድ መሰጠቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። 
 
ዳጉ_ጆርናል
1👍1
የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ አረፈ 
 
የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የ 15 ዓመት የመጀመሪያ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው በድንገተኛ ህመም ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። 
 
ለአርቲስት ዘሪቱና ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን 🙏

የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/felagi
👍2
"የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማግለሉ ቅር እንዳሰኘው ሲኖዶሱ ገለፀ

የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል።
በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል።

" ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል።

ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል።

በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል።
>>>>https://t.me/+qWYNiKhZSgYwYzI8
ካልተለወጡ አይከፍሉም‼️

👉ቦርጭ ላይ ተስፋ ከቆረጡ ኑ ወደ እኛ
📍ቦሌና ፒያሳ ያሉት ጂሞቻችን ዘወትር እናንተን ለመቀበል ክፍት ናቸው።
🛑ይምጡ ይለወጡ።
🎯የሶስት ወር ጉዞ ሙሌን ይዞ
0912653394
0949750496
0777720496 ላይ መልዕክት ብቻ ያስቀምጡ ይደርሰናል
👍31
መንግስት የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የባንክ አካዉንት እንዲታገድ አደረገ 
 
ተቋሙ በምን ምንክንያት እንደሆነ በማናዉቅበት ምክንያት በአንድ ዓመት ዉስጥ ለ 3ኛ ጊዜ የባንክ አካዉንቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ መደረጉን አስታዉቋል ።  
 
ፐርፐዝ ብላክ ባለፉት ሳምንታት ተቋሙን ህልዉና ዉስጥ የሚከተዉ ችግሮች እንደገጠመው አስታዉቋል። 
 
ላለፉት ሶስት ሳምንታት የተቋሙ አካዉንት ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ከመደረጉ በተጨማሪ የዋና ስራ አስፈጻሚዉ ፍስሃ እሸቱ ( ዶ/ር) አካዉንት ጨምር ተመሳሳይ እጣ ፈንታ መድረሱ ተገልጿል። 
 
ደመወዝ መክፈል የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የቢሮ ኪራይን ጨምሮ የፕሮጀክቶች ስራዎች እንዲቆሙ መደረጉ ስራ አስፈፃሚው በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል ። 
 
ከ20 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት እና ከ 1 ሺህ በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ተቋሙ አሁን ላይ ካፒታሉ 2.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል ። 
 
ካፒታል

የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/felagi
👍1
ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ የተጫወተ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆነ 
 
ስፔናዊው ታዳጊ ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ በትንሽ እድሜው የተጫወተ ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ተሰርቷል።  
 
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 2 ስፔንና ክሮሺያ ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ። 
 
ላሚን ያማል በ16 ዓመት ከ 338 ቀናት በመጫወት በውድድሩ ታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆኖ በመሰለፍ አዲስ ታሪክ ጽፏል። 
 
ከዚህ ቀደም ክብረ ወሰኑ ተይዞ የነበረው በፖላንዳዊው ካስፐር ኮዝሎውስኪ ሲሆን የተሰለፈበት እድሜ በ17 ዓመት 246 ቀናት ነበር። በዛሬው ጨዋታ ስፔን 3 ለ 0 ክሮሺያን ረታለች።
👍4
ፖሊስ በኔቫዳ በረሃ ውስጥ ምንነቱ ያልታወቀ ግዙፍ ባዕድ ነገር ማየቱን ገለጸ 
 
በአሜሪካ ኔቫዳ ግዛት ውስጥ በሚገኝ በረሃማ ቦታ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ምንነቱ ያልታወቀ አንጸባራቂ ነገር ማየቱን ፖሊስ አስታወቀ። 
 
በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ታይቷል የተባለው ይህ ረጅም ምንነቱ ያልታወቀ አካል የፖሊስ አባላት የጠፋ ሰው ፍለጋ በተሰማሩበት ወቅት ያገኙት መሆኑንም ገልጸዋል። 
 
የፖሊስ አባላቱ ረጅሙን አንጸባራቂ ነገር ጋስ ፒክ በተባለ ሃይኪንግ (የተራራ የእግር ጉዞ) በሚደረግበት ሰሜናዊ ላስ ቬጋስ አካባቢ ማግኘታቸውንም ቢቢሲ አስነብቧል።
👍3
ከ 6ቀን በኃላ የሚለቀቀው 5ሰው በመጋበዝ(invite) በማረግ 100$ ይምታገኙበት coin ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን አሁኑኑ ይመዝገቡ የቀረዉ 6ቀን ብቻ ነው ፍጠኑ
>>https://t.me/pixelversexyzbot?start=164706397 Let's fight for rewards together! Take your welcome bonus: 💸 2,000 Coins + 2X multiplier for the first 24 hours 🔥 10,000 Coins + 3X multiplier if you have Telegram Premium
👍1
ክልያን ምባፔ ለሁለት ተከታታይ አመታት የአመቱ ትልቁን ክፍያ ያገኘ ስፖርተኛ ሆኗል! 
 
  ክልያን ምባፔ ለሁለት ተከታታይ አመት  በአመት ብዙ  ክፍያ የተከፈለው ስፖርተኛ ሆኗል። የክልያን የአመት ገቢ 110 ሚሊየን ዶላር ነው። 
 
ገና ባልተዘጋው የክረምት የተጫዋቾች የ፣ውውር መስኮት ወደ ሪያል ማድሪድ ያመራው ክልያን ምባፔ በአመት የተከፈለው ክፍያ ከሁሉም የላቀ ሲሆን በአለም ላይ በየትኛውም ዘርፍ ብዙ ክፍያ ከሚከፈላቸው ሰዎ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል 
 
ፎርብስ ከአንድ እስከ አምስት ብዙ ተከጋዮች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል እርሊንግ ብራውንት ሃላንድ  በሁለተኛነት ተቀምጧል  
 
ዛሬ 24ኛ  አመት የልደት በአሉን እያከበረ የሚገኘው ሃላንድ ባለፈው የጨዋታ ወቅት 61 ሚሊየን ዶላር ተከፍሎታል 
 
ከአንድ እስከ አምስት በወጣው ደረጃ ከምባፔና ከሃላንድ በስተቀር ሶስቱ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ናቸው።  
 
የNBA ኮከቦቹ ሉካ ዶኒች በ55.1 ሚሊየን ዶላር ሶስተኛ ፣ ትሬ ያንግ በ47.3 ሚሊየን አራተኛ ፣ ዚዮን ዊሊያምሶን በ46,1 ሚሊየን ዶላር አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።አራዳ
#የተፈጥሮ_አበባ_በ6ብር_ባሉበት_እናስረክባለን{እናከፋፍላለን}
             #ኖብ_የተፈጥሮ_አበባዎች_ነን
    1➯ አበባ በብዛት ለምትፈልጉ እናስረክባለን።
       2➯የአበባ አሰራር ሥልጠና እንሰጣለን።
          3➯ የስጦታ ፓኬጃችን ከዴሊቨሪ አገልግሎት ጋር።

እነዚህን እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች እንሰጣለን።
    ⭐️  ለሆቴሎች
    ⭐️  ለድርጅታችሁ{ለቢሮአችሁ}
    ⭐️  ለወላድ{አራስ} ወዳጅዎ
    ⭐️  ለፍቅረኛዎ ቢፈልጉ ከዴሊቨሪ አገልግሎት ጋር የምንሰጥ ይሆናል።
               ☎️ 09 16-55 80 80
   ✍️አድራሻችን:➯ጀሞ መስታወት ፋብሪካ ጎን ዳኮርድ አፓርታማ ጀርባ።
    NOB FLOWERS ARRANGEMENT
👍1
❣️ አርቲስት ያሬድ ነጉ ደግ ልቡን ይዞ ጎፋ ደርሷል 
 
አርቲስት ያሬድ ነጉ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክኒያት የደረሰውን አደጋ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎፋ ደርሷል። 
 
🛑 ያሬድ ጓደኞቹን በማስተባበርም የተለያዪ ለድጋፍ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እና ለምግብነት የሚውሉ ግብአቶችን በአይሱዙ አስጭኖ የአደጋው ስፍራ ድረስ በመገኘት በአስክሬን ፍለጋ ስራ ላይም እንደተሰማራ በስፍራው የተገኙ ምንጮች ገልጸውልናል። 
ደራሽ ለወገኔ 🙏❤️ 
 
በጎፋ ዞን ለደረሰው ጉዳት ከዛሬ ጀምሮ ብሄራዊ የዘን ቀን መታወጁ ይታወሳል።ጠ/ሚንስትር አብይ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በቦታው ተገኝተው ህዝቡን የማፅናናት ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል።
1😢1