Addis info
1.41K subscribers
454 photos
7 videos
181 links
Download Telegram
በሁለት ሲዝን ዋና አሰልጣኝነት ሶስት ጊዜ ወደ ዌምብሌይ ፍጻሜ ጨዋታዎች አምርተዋል። ከሶስቱ ሁለቱን አንስተዋል። ኤሪክ ቴን ሃግ።
ማንቸስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ሲዝን በዩሮፓ ሊግ እንዲጫወት አድርገውታል። ግን ኤሪክ አስር ሃግ አሁንም ኃላፊ ሆነው ይቀጥላሉ?
አስተያየታችሁን ጻፉበት።
ሰላም ቤተሰቦች በሞባይ ባንኪንግ ስለሚደረግ ዘረፋ በጓደኛዬ ላይ የደረሰውን ላሰውቃችሁ 
 
ምን አልባት ብዙዎች እየገጠማቸው ሊሆን ይችላል ጓደኛየ የሚኖረው አዋሣ ከተማ ነው ሥራው ንግድ ላይ ነው ከአንድ ወር በፊት አንደ ሰው ወደሱቁ መጥቶ ዕቃ ይገዛው እና በሞባይል ባንኪንግ 40,000 ብር አስተላልፎለት ሰውየውም ደረሰኝ ይሰጠውና ይለያያሉ። 
 
ሰሞኑን የንግድ ባንክ አካውንቱ ብሎክ ተደርጎበት ችግሩን ለማጣራት ባንክ ቤት ስንሄድ በፍርድ ቤት ትዛዝ ነው የተዘጋብህ ይሉታል። 
 
እሱም ምን አጥፍቼ ተዘጋብኝ ሲላቸው ካዘጋበት ሰውየ ጋር አገናኙት ሰውየው የፖሊስ መጥርያና ፖሊስ ይዞ ነበረና ወደ ፖልስ ጣቢያ ያስገቡታል። 
 
ከወር በፊት 4ዐ,ዐዐዐ ብር ዕቃ የገዛኝ ሰውየ በተሰረቀ ስልክ ነበር ገንዘብን የላከለት ስልኩን የተሰረቀው ሰውየ ደግሞ password ቁጥሩን ስልኩ ላይ መዝግቦት ነበር ስልኩን የሰረቀው ሰው በቀላሉ pasword አገኜ እና ለማጭበርበር ተጠቀመበት። 
 
በዚህ ምክንያት አሁን ሻሸመኔ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል እኛም በሽምግልና 4ዐ,ዐዐዐ መልሱና ታረቁ እያሉው ጎደኛዬ ንግድ ፍቃድ ያለው ህጋዊ ነጋዴ ነው። 
 
ይህ አይነት የአዘራረፍ ዘዴ እየተበራከተ ስለሆነ በውስጥ መሥመር የተላከልንን አስተማሪ ጽሁፍ የየኔታ ቲዩብ ቤተሰቦች እና መላ ኢትዮጵያውያን ትጠነቀቁ ዘንድ መልዕክቱን ልናጋራችሁ ወደድን። 
 
Source : Yeneta
👍2
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀች  
 
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች። ፋስት መረጃ የእግቱን መልዕክት እንደተመለከተው ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች። 
 
ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች። 
 
ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች።  
 
Fast Mereja

የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/felagi
👍21
ዘማሪ ዲያቆን ይገረም ጸጋዬ አረፈ

ዘማሪ ዲያቆን ይገረም ጸጋዬ ለአገልግሎት በተጠራበት ቦታ ሁሉ ገጠር ከተማ ሳይለይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራትም ጭምር ቤተክርስቲያንና ምዕመናንን ሲያገለግል ሲታዘዝ የነበረ መልካም አገልጋይ እንደነበር በቅርብ ወዳጆቹ ተነግሯል።

ነፍስ ይማር ‼️
FastMereja
👍21🙏1
ይህ ራሺያዊ ኬኒያዊቷን አፍቅሮ ራሺያዊት ሚስቱን ፈቶ ጎረቤታችን ኬኒያዊቷን አግብቶ መኖር ይጀምራል።

ከዛም ሀብት ንብረታቸውን ሽጠው ወደ ኬኒያ ኑሯቸውን በመቀየር በሰፊው ኢንቨስት እያደረጉ ሀብታቸውን ያሳድጋሉ።

ከዛም ኬኒያዊቷም ማን እንደ ሀገሬ ልጅ ብላ ሌላ አፍቅራ ሁሉም ድርጅትና ኢንቨስትመንት በሷ ስም ስለነበር አሱን እንደተበላ ዕቁብ አሽቀንጥራ ጣለችው።

አሁን እዛው ኬኒያ ውስጥ ጎዳና ተዳዳሪ ሆኖ የቀን ስራ እየሰራ ህይወቱን እየገፋ ይገኛል።

Via:- WAKENYA
👍5
ተረጋገጠ ⬜️⬛️ 
 
የአውሮፓ ሻምፒዮኖቹ ኪሊያን ምፓፔን በነፃ ለማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።  
 
በነፃ የተገኘ ወርቅ🔥
1
ማቲያስ ደርብ የ2016 የደሞ አዲስ ኮከብ ተወዳዳሪ በመሆን የ1 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ሆነ

ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) የደሞ አዲስ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን 1 ሚሊዮን ብር አሸንፋለች

በደሞ አዲስ የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር፤ የ2 ሚሊዮን ብር ፍልሚያ እግቱ እና ማትያስ ደርብ አሸነፊ ሆነዋል።

በአጓጊው የደሞ አዲስ የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር ያሬ ነጉ እና አብርሃም ኸይሩ፣ የሺ እና ዮሐንስ ወርቁ እንዲሁም ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) እና ማትያስ ደርብ ለ2 ሚሊዮን ብር አሸናፊነት ያደረጉት ፍልሚያ መቋጫውን አግኝቷል።

በዚህም መሰረት እግቱ እና ማትያስ ደርብ የ#ደሞ_አዲስ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ሆነው ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ያሬ ነጉ እና አብርሃም ኸይሩ በሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የሺ እና ዮሐንስ ወርቁ ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

ከደሞ አዲስ ተወዳዳሪዎች መካከል የነበረው አብርሃም ሸዋንቅጣው የደሞ አዲስ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የ50ሺሕ ብር ተሸላሚ ሆኗል።
👍2
ካልተለወጡ አይከፍሉም
ቦርጭ ላይ ተስፋ ከቆረጡ ኑ ወደ እኛ
በሶስት ወር ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ
0912653394
0949750496
0777720496
መልዕክት ብቻ ያስቀምጡ ይደርሰናል
👍1
ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ደረጃ መዘጋጀቱ ተነገረ 
 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስትም አስገዳጅነት ወደ ሀገር ቤት በብዛት እየገቡ ለሚገኙት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የደረጃ መለኪያ መስፈር መዘጋጀቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በርካታ ባለሙያዎች ወደሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወኪል አልባ ናቸዉ ከሚለዉ ጀምሮ ካለ መለኪያ መስፈርት የሚገቡ መሆናቸውን ሲናገሩ ይደመጣል። 
 
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በምን ደረጃ ላይ መገኘት አለባቸዉ የሚለዉን የሚመዝን ደረጃ ማዘጋጀቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ሰምቷል። በተጨማሪም የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑም ተገልጿል። 
 
በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሀይል መሙያ ማዕከላት የአተገባበር መመሪያ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሀይል መሙያ ማዕከላትን መላዉ ኢትዮጵያን የሚሸፍን ለማድረግ የቅድመ አዋጭነት ጥናት መደረጉንም ገልጸዋል። 
 
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሀይል መሙያ ለመገንባት ለሚያቅዱ ባለሃብቶችም ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የፕሮጀክት እቅድ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ይፋ አድረወገዋል። በአሁኑ ወቅትም ለ 162 የኤሌክትሪክ መኪና አስመጪዎች ፈቃድ መሰጠቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። 
 
ዳጉ_ጆርናል
1👍1
የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ አረፈ 
 
የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የ 15 ዓመት የመጀመሪያ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው በድንገተኛ ህመም ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። 
 
ለአርቲስት ዘሪቱና ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን 🙏

የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/felagi
👍2
"የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማግለሉ ቅር እንዳሰኘው ሲኖዶሱ ገለፀ

የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል።
በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል።

" ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል።

ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል።

በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል።
>>>>https://t.me/+qWYNiKhZSgYwYzI8
ካልተለወጡ አይከፍሉም‼️

👉ቦርጭ ላይ ተስፋ ከቆረጡ ኑ ወደ እኛ
📍ቦሌና ፒያሳ ያሉት ጂሞቻችን ዘወትር እናንተን ለመቀበል ክፍት ናቸው።
🛑ይምጡ ይለወጡ።
🎯የሶስት ወር ጉዞ ሙሌን ይዞ
0912653394
0949750496
0777720496 ላይ መልዕክት ብቻ ያስቀምጡ ይደርሰናል
👍31
መንግስት የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የባንክ አካዉንት እንዲታገድ አደረገ 
 
ተቋሙ በምን ምንክንያት እንደሆነ በማናዉቅበት ምክንያት በአንድ ዓመት ዉስጥ ለ 3ኛ ጊዜ የባንክ አካዉንቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ መደረጉን አስታዉቋል ።  
 
ፐርፐዝ ብላክ ባለፉት ሳምንታት ተቋሙን ህልዉና ዉስጥ የሚከተዉ ችግሮች እንደገጠመው አስታዉቋል። 
 
ላለፉት ሶስት ሳምንታት የተቋሙ አካዉንት ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ከመደረጉ በተጨማሪ የዋና ስራ አስፈጻሚዉ ፍስሃ እሸቱ ( ዶ/ር) አካዉንት ጨምር ተመሳሳይ እጣ ፈንታ መድረሱ ተገልጿል። 
 
ደመወዝ መክፈል የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የቢሮ ኪራይን ጨምሮ የፕሮጀክቶች ስራዎች እንዲቆሙ መደረጉ ስራ አስፈፃሚው በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል ። 
 
ከ20 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት እና ከ 1 ሺህ በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ተቋሙ አሁን ላይ ካፒታሉ 2.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል ። 
 
ካፒታል

የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/felagi
👍1