Addis info
1.41K subscribers
454 photos
7 videos
181 links
Download Telegram
በአሜሪካ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የ2.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ጥበበ እሸቱ ሀይሌ ይባላል ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከእዚህ በፊት በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ሲለግስ ቆይቷል።

በሠሜኑ ጦርነት ጊዜም የተፈናቀሉ ወገኖችን ከመደገፍም ባሻገር 140 ለሚደርሱ የጋሸና አካባቢ ነዋሪዎች ቤት ሰርቶ አስረክቧል ።

በቅርቡም በትግራይና በአማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግሯል።

ይህ ቅን ሰው በዛሬው ዕለት ለመቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከል ከ2.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ እና ለአረጋውያኖቹ የምሳ ማብላት ፕሮግራም አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊታደስ ነው

ለረዥም አመታት እድሳት ሳይደረግለት የቆየዉ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአዲስ መልክ ሊገነባ መሆኑ ተነገረ

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት እና የከተማ አስተዳደሩ በጋራ በመሆን ከ 40 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለዉን እና ብቸኛዉን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ሊጀመር እንደሚችል ተጠቁሟል።

የንግድ ምክርቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ለካፒታል እንደተናገሩት የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎች የተወሰዱ መሆኑን በማንሳት የኤግዚቢሽን ማዕከሉን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የማልማት እቅድ መያዙንና በቀጣይ ዓመት ሊጀመር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል ።

ከ4 አስርት አመታት በላይ ያስቆጠረዉ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሀገር ዉስጥና ዓለምአቀፍ የንግድ ትርኢቶችን አሁን ላይ እያዘጋጀ ቢሆንም ማዕከሉ ያረጀና አገልግሎት መስጫዎቹም በሙሉ የደከሙ መሆናቸው ይነገራል ።

(ካፒታል ጋዜጣ)
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቦሌ አየር መንገዱ ይቅርታ ጠየቀ  
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ዛሬ ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ የታየ ቢሆንም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገዶኞቻችንን ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወርደዋል። በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ውድ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡
በውስጥ ይነበሩት ተሳፋሪዎች በሰአቱ የነበራቸው ሁኔታ በቪዲዬ !!!
👍2
ቦርሲያ ዶርቱመንድ በዌምብሌይ በሚከናወነው የ 2023/2024 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል 
 
ፓሪሰንት ዠርመ 0-1 ቦርሲያ ዶርቱመንድ (0-2) 
                                 ሁመልስ 50'

Join: @felagi
👍1
ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል 

ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዓለም ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ በቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ብቻ መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

በመሆኑም ከግንቦት 1 ቀን 2016 ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የአይሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

በዚህም መሰረት:-
ቤንዚን ……………………………………… ብር 78.67 በሊትር
ነጭ ናፍጣ………………………………… ብር 79.75 በሊትር
ኬሮሲን …………………………………... ብር 79.75 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ………………... ብር 70.83 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………… ብር 62.36 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 61.16 በሊትር ሆኗል።
👍1
ሪያል ማድሪድ ባየርን ሙኒክን 2-1 በማሸነፍ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አልፈዋል። በፍፃሜው ቦሩሲያ ዶርትሙንድን የሚገጥሙ ይሆናል።
የሰዋሰው መተግበሪያ ጉዳይ . . .🤔

መተግበሪያው ወደ ስራ ሲገባ ያስፈረማቸው ድምፃዊያን ብዛት፣ የድምፃዊያኖቹ ተነሳሽነት፣ ፕሮሞሽኑ . . . ብቻ ብዙ ነገሮቹ ሙዚቃችንን ያነቃቃ ነበር።

አልበም ሲያወጡ ከተማውን የሚቆጣጠሩት አብነት አጎናፍር፣ ግርማ ተፈራ እና አስቴር አወቀ አልበማቸው በሚገባው ልክ ተደራሽ ሳይሆን አለፈ፤ ብዙ የቪዲዮ ክሊፕ እንደተሰራ ብንሰማም ከአንድ የበለጠ ቪዲዮ ከአልበማቸው አለየንም። ብዙ ድምፃዊያን ከሰዋሰው ጋር የገቡትን ውል ለማቋረጥ መወሰናቸው አግባብም ነው።

ዓርብ አልበሟን ለመስማት የምንጓጓላት ለምለም ሀ/ሚካኤል ሰዋሰው የተመረቀ ጊዜ ስምምነት ካደረጉ ድምፃዊያኖች ውስጥ አንዷ ነበረች።(Tsion T)
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊውን የሚለይ የተባለለት ተጠባቂ ጨዋታ ምሽቱን ይካሄዳል
⚽️❤️ https://ethaistoothi.com/4/7483071 ⚽️❤️
04:00 ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ
የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል
ቶተናም ለጎረቤቱ መድረስ አልቻለም፤ ሲቲ ትልቁን የቤት ስራ በድለ አጠናቆ የሊጉን መሪነት ተረከበ  
 
ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል።  
 
የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።  
 
የሚያስገርመው ማንችስተር ሲቲ በአዲሱ የቶተንሀም ስታዲየም የፕርሚየር ሊግ ጎል ሲያስቆጥር ይህ የመጀመሪያው ነው። 
 
ፔፕ ዋንጫ አይቶ🙊
👍1
አዋሽ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡ ተገለፀ። 
 
ግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ለ31ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው መሠረት ከ36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከተመረጡ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ አንዱ ሆኗል። 
 
የምርጥ ባንኮች ልየታ የተደረገው በተለያዩ መስፈርቶች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የባንኮቹ ትርፋማነት፣ የሀብት ዕድገት፣ተደራሽነት እና የመሳሰሉት ከመስፈርቶቹ መካከል የተካተቱ ናቸው። 
 
በዚህ መሠረት አዋሽ ባንክ ከ36 አገራት ከተመረጡ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን እና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛው ባንክ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጸዋል። 
 
በዚህኛው አመት በተካሄደው ምርጫ ከ1መቶ50 በላይ አገራት የሚሰሩ ባንኮች የተካተቱበት መሆኑም ነው የተገለጸው። 
 
አዋሽ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ9መቶ38 በላይ ቅርንጫፎች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ከ12.1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችንም ማፍራቱ ተነግሯል። 
 
የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ2መቶ15 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱም ተገልጿል። 
 
ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠንም ከብር 1መቶ78 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። 
 
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት ለባንኩ የሚሰጠው ዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት የአለም ገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በዋሽንግተን ዲሲ በኦክቶበር 2024 በሚያደርጉት ጉባኤ ወቅት እንደሚከናወን አስታውቀዋል።(ethiofm)
👍21
የ12ኛ ክፍል የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ‼️
የትምህርት ሚኒስቴር በብሔራዊ ደረጃ በወረቀትና በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና፣ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ ተማሪዎች እንዲዘጋጁ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ላፕቶፕም ሆነ ሌሎች ግብዓቶችን አዘጋጅተው በፈተና ወቅት ኢንተርኔት ከተጠለፈ ወይም ከተቋረጠ እነሱም ሆኑ ሚኒስቴሩ ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚወድቁ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል ያሉት፣ የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር ተወካይ ወ/ሮ ሐረገወይን ገረሱ ናቸው፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች እንዲህ ዓይነት መሠረተ ልማት ያሟላሉ ወይ የሚለውን ራሱ ሚኒስቴሩ መፈተሽ እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ ሐረገወይን፣ በአገር ደረጃ በትምህርት ቤቶች የኢንተርኔት አቅርቦት ተደራሽ ሆኖ ሲስተሙ በምንም ዓይነት ምክንያት ሳይቋረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ተሞክሮ ስለሌለ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
👍2